ከአቶ ሀብተማሪያም ሞገስና ከወ/ሮ ደስታ አየለ በ1935 ዓ.ም የተወለዱት ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም በ 71 ዓመታቸው በአዲስ አበባ ከተማ አረፉ። ደራሲ መስፍን በልጅነታቸው ባህላዊ የቤተ ክህነት ትምህርት የተማሩ ሲሆን ፣ በሞጆና በአንቦ የአንደኛና የሁለተኛ ደራጃ ትምህርታቸውን አጠናቀዋል። በወቅቱ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ዩኒቨርስቲ ተብሎ በሚጠራው የትምህርት ተቋምም በመግባት በቋንቋዎችና ሥነ-ፅሁፍ ክፍል በማዕረግ በቢኤ ዲግሪ ተመርቀዋል።በመቀጠልም ካናዳ በሚገኘው ቫንኩበር ከተማ በመሄድ ዪኒቨርስቲ ብሪቲሽ ኮሎምብያ ገብተው የፈጠራ ሥነ- ፅሁፍ የማስተር ድግሪ አግኝተዋል። ደራሲ መስፍን ሀብተማሪያም አገራቸው ከተመለሱ በኋላ በአማርኛ ቋንቋ በኢልብወለድ አጻጻፍ የትምህርት መስክ በተለያዩ ቦታዎች አስተምረዋል በአዲስ አበባ ዪኒቨርስቲም በቋንቋዎች ጥናት ተቋም የስነጽሁፍ ኮርሶችን … [Read more...] about ወግ ቀማሪው ደራሲ መስፍን ሀብተማርያም አረፉ
እኚህ ሴት ማናቸው? – ፰
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፯” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሰባት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ማራቶን ማራቶን ማራቶን ልዕልቷ አበበና ማሞ ሆኑ ባለቤቷ ማራቶን ደንግጠሽ አቤን ብትቆጪ ዕድሉ የኛው ነው የትም አታመልጪ ብለው ያወደሱ - ሜክሲኮን ኦሎምፒክ የኳስ ስም ሲነሳ - የሚታውሱ ሰርክ ግጥም ያቀበሉ - ለብዙ ዘፋኞች ዝናን ያተረፉ - በስፖርት ዓለም ሰዎች አገር የሚሸበር - ድምጻቸው ሲሰማ እኚህ ሰው ነበሩ - ስለሞን ተሰማ፡፡ ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፰” ወለላዬ የሚከተለውን … [Read more...] about እኚህ ሴት ማናቸው? – ፰
“ጎንደር ቤተ መንግስት ውስጥ ኦሮሚኛ ቋንቋ ይነገር ነበር”
በተለያዩ ድረ-ገፆች በኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በሚያንሸራሽሩት ሃሳብ ይታወቃሉ፡፡ ስለ ኢትዮጵያኒዝም፣ ስለ ፓንአፍሪካኒዝም እንቅስቃሴዎች የተለያዩ ምልከታዎችና ምክረ ሃሳቦችን በማቅረብ ተሰሚነት ካላቸው ኢትዮጵያዊያን ምሁራን አንዱ ናቸው - ፕ/ር ማሞ ሙጬ፡፡ ሰሞኑን ጐንደር ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበትን 60ኛ አመት በዓል ሲያከብር “Towards Innovative Africa: The Significance of Science, Technology, Engineering and Innovation for Sustainable Development” በሚል ርዕስ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ ፕሮፌሰሩ በአሁን ሰአት በደቡብ አፍሪካ ሊዋኔ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ቴክኖሎጂና በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በማስተማር ላይ ይገኛሉ፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ባለፈው ሳምንት በጐንደር … [Read more...] about “ጎንደር ቤተ መንግስት ውስጥ ኦሮሚኛ ቋንቋ ይነገር ነበር”
የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሂደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ!
ይሄንን ጽሑፍ ታች አምና ከጉራፈርዳና አካባቢው አማራ በመሆናቸው ምክንያት ብቻ ሕጋዊነታቸውን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ይዘው እያለ ሕጋዊ ሆነው የየክልሉ መንግሥት አውቋቸው በሥርዓቱ ግብር እየከፈሉ እየኖሩ የነበሩ ምስኪን ገበሬዎችን “ሕገ ወጥ ሰፋሪዎች” በሚል ሕገ ወጥነታቸው አግባብነት ባለው የሕግ አካል (ፍርድቤት) ክስ ተመስርቶባቸው ሳይረጋገጥባቸው በጅምላ በግፍና በሕገ ወጥ መንገድ ንብረታቸውን ሁሉ ተወርሰው እንዲወጡ በተደረገ ጊዜ ጽፌው ለጥቂት መደበኛና ኢመደበኛ (Conventional and Social Media) ልኬው ነበር እስከማውቀው ድረስ ለሕዝብ ይፋ አድርገውት ያስነበቡት ወይም ያስደመጡት አልነበሩምና ሕዝብ ሊያውቃቸው የሚገባ በርካታ ቁምነገሮች ስላሉት እንዳያመልጣቹህ በማሰብ ወደ እናንተ አድርሸዋለሁ መልካም ንባብ፡፡ የዐፄ ዮሐንስ 4ኛ መንግሥታዊ (official) ቋንቋ … [Read more...] about የዘር ማጥፋት ወንጀሎች በአማራ ሕዝብ ላይ በታሪክ ሂደት ውስጥ ከጥንት እስከ ዛሬ!
ጥላቻ በዛ፣ ቂም አበበ፣ በቀል አፈራ!! ኢህአዴግም አልረካም
“እነሱ ሁለት አገር አላቸው። ኢትዮጵያን ይዘዋታል። በስደትም እንደፈለጋቸው እየኖሩ ነው። እኛ ግን አንድም አገር የለንም። በስደት እንኳን እንዳንኖር እየተደረግን ነው። ሸሽተን በተሰደድንበት ምድር እንኳን ዋስትና የለንም። ከዚህ በላይ ምን ይምጣ?” ይህንን የዛሬ ሶስት ወር ገደማ ለጎልጉል የተናገሩት በኖርዌይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር ጸሐፊ ወ/ት የሺሃረግ በቀለ ነበሩ። የወ/ት የሺሃረግን ሃሳብ በመንተራስ ለጎልጉል አስተያየት የሰጡ እንዳሉት “አገር ውስጥም እስር፣ በስድት ምድርም ስጋትና እስር ካለ፣ የይለይለት መንፈስ መነሳቱ አይቀርም። ሰዎች የመኖር ተስፋቸው ሲመናመን የፈለገው ይምጣ ይላሉ። አሁን ኢህአዴግ ከስጋቱ ብዛት እየፈጸመ ያለው ድርጊት ሰዉን ሁሉ ወደዚሁ የሚያመራ ነው።” ሰሞኑን ኢህአዴግ የወሰደውን፣ ቀደም ሲልም በተመሳሳይ ሲከናውን የቆየውን፣ ወደፊትም በቀጣይነት … [Read more...] about ጥላቻ በዛ፣ ቂም አበበ፣ በቀል አፈራ!! ኢህአዴግም አልረካም
ዛፎች
ከዛፎች መካከል ዛፎች ሲቆረጡ ዎዮው ላሽሟጠጡ፡ ዎዮው ላላገጡ፡ የተጨፈጨፉት የተቆረጡቱ፡ ለምሣር እጄታ ተገጥመው ሲመጡ። … [Read more...] about ዛፎች
ወራቱ ረመዷን ነው! ፍቷቸው!
ወራቱ ረመዷን ነው፡፡ በዚህ ወር ሰላም፣ ማርታ፣ ይቅርታ እና ምሕረት ነው የሚለመነው፡፡ አዲስ ሰው ለመሆን ነው ጥረት የምናደርገው፡፡ ባለፉት ሶስት ዓመታት ባሳለፍኳቸው ረመዳኖች የሚሰሩት ነገሮች ግን ከዚህ ቅዱስ ወር የምናገኘውን በረከትና ጸጋ በአግባቡ እንዳንቋደስ እና ቀልባችንን ሙሉ በሙሉ ወደ ፈጣሪያችን እንዳንመልስ ጋሬጣ እየሆኑብን ተቸግረናል፡፡ ወራቱ ረመዳን ነው፡፡ ትናንት ሰዎች ታስረዋል፡፡ ማን እንደታሰረም ስለሚታወቅ መግለጹ አስፈላጊ አይደለም፡፡ ነገር ግን በየጊዜው ሰዎችን ማሰር የምንመኛት ኢትዮጵያ እንድትመጣ ለማድረግ አንዳች ጠቀሜታ የለውም፡፡ ገዥው ፓርቲ የሚያልመውን የኢትዮጵያ ራዕይን በ2020 ለማሳካትም ሆነ ሌሎች በተለየ መንገድ የሚመኟትን ለሁላችንም የምትሆነውን ኢትዮጵያን ለመፍጠር ምንም አይፈይድም፡፡ በሰከነ መንፈሰ መደማመጥና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት … [Read more...] about ወራቱ ረመዷን ነው! ፍቷቸው!
መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም!!!
የህወሓት/ኢህአዲግ አገዛዝ በኢትዮጵያ ስልጣን ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ዜጎችን በማፈንና በማሰቃየት ብሎም በመግደል የአፈና አገዛዙን ለረጅም ጊዜ ሲያራምድ መቆየቱ ዓለም የሚያውቀው ሀቅ ነው፡፡ በተለይም ባለፉት 10 ዓመታት የህዝብን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማፈን እስራትና ግድያውን ህጋዊ ለማስመሰል የተለያዩ አፋኝ አዋጆችን አውጥቷል፡፡ እነዚህን አዋጆችንም ተገን አድርጎ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችንና አባለትን፣ ጋዜጠኞችንና ጦማርያንን፣ እንዲሁም የእምነት ተቋማት መሪዎችን እና በአገዛዙ ላይ ጥያቄ የሚያነሱ ዜጎችን ማሰሩን፣ ማሰቃየቱንና ግድያውን ተያይዞታል፡፡ በህገ መንግስቱ የተካተቱ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን በሙሉ የሚጥሰውና የአምባገነንነት ስልጣኑን ለማራዘም ሲል ያፀደቀው የፀረ-ሽብር አዋጅ ከፀደቀበት እለት አንስቶ ኢህአዴግ ለስልጣኔ … [Read more...] about መንግስታዊ ሽብርተኝነትን የሚሸከም ትከሻ አይኖረንም!!!
የመከራ ደወል በጋዛ!
ባሳለፍናቸው ሳምንታት የሶስት እስራኤል ታዳጊዎች መጥፋትና ከቀናት በኋላ ተገድሎ ተገኘ። ይህም እስራኤላውያንን አስቆጥቶ በአንድ ታዳጊ ፍልስጥኤማዊ ላይ የበቀል እርምጃ አስወሰደ። ሟች እንጅ ገዳይ አይታወቅም ተባለ። ውጥረቱ ማየል መክረር ያዘ ... የፍልስጥኤም ታጣቂዎች ተፈጸመብን ያሉትን በደል ለመበቀል በአጸፋው በተወንጫፊ ሮኬት ሚሳኤል የእስራኤን መዲና ሳይቀር ማጥቃት ያዙ። ቴል አቢብን፣ እየሩሳሌምና ወደ የተለያዩ ከተሞች ዘልቆ የደረሰው ጥቃት ድንጋጤን ፈጠረ። ጠቅላይ ሚነኒስትር ናታንያሁ ተበሳጩ፣ ተሶረፉ! "እስራኤል አጸፋ ትወስዳለች!" ብለው በተናገሩ ቅጽበት የማጥቃት እርምጃውን አዘዙ! ጥቂቶችን ለማጥቀሰት በጋዛ ፍልስጥኤማውያን ላይ የመከራው ደወል ተደወለ...! የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ናታንያሁ ጋዛን መልሰው ለማጥቃት የክተት አዋጅ ጠሩ። ሰኞ አጸፋ የአየር ጥቃት … [Read more...] about የመከራ ደወል በጋዛ!
የስብሰባ ጥሪ
ሞረሽ ወገኔ የባህል ማህበር በስዊድን፤ የወያኔ ትግሬዎች ስልጣን ከያዙበት ጊዜ ጀምሮ በአማራው ህዝብ ላይ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል ተፈጽሞበታል፣ አሁንም እተፈጸመበት ነው ብሎ ያምናል። ይህ በአንድ ነገድ ላይ ያተኮረ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ወንጀል በዚህ ከቀጠለ የነገዋን ኢትዮጵያ ህልውና ይፈታተናል፣ በህዝብ መካከል ያለውንም የአንድነት ስሜት ያደበዝዛል። ስለዚህ፤ በአንዲት ኢትዮጵያ ሀገርና በህዝቧም አንድነት የምታምኑ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ በኦገስት 2 ቀን 2014 - አቶ ተክሌ የሻውን ከአሜሪካ ጋብዘን ባዘጋጀነው ስብሰባ ላይ አንድትገኙልን በአክብሮት ጋብዘናችሗል። የክብር እንግዳ - አቶ ተክሌ የሻው የስብሰባ ቦታ - ሀሉንዳ ፎልኬት ሁሰ ( HALLUNDA FOLKETS HUS ) የስብሰባ ቀን - ኦገስት 2 ; 2014 ሰዓት - ከ 13 ሰዓት እስከ 20 … [Read more...] about የስብሰባ ጥሪ










