በኢትዮጵያም ሆነ በጥቁር አፍሪካ ኦሊምፒክ ታሪክ ሁለት ወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችው ደራርቱ ቱሉ ባለፈው ሳምንት ከደቡብ አፍሪካው ዌስተርን ኬፕታውን ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተቀበለች፡፡ ከኦሊምፒክ በተጨማሪ በዓለም ሻምፒዮንም ሆነ በተለያዩ አህጉርና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ቁንጮ በመሆን ታላቅነቷን ማስመስከሯ ይታወሳል፡፡ ደራርቱ ለመጀመርያ ጊዜ በባርሲሎና ኦሊምፒክ (1984 ዓ.ም.) በ10,000 ሜትር ተወዳድራ የወርቅ ሜዳልያውን ያገኘችው የቅርብ ተፎካካሪዋንና የዓለም አቀፍ ውድድሮች ልምድ የነበራትን ደቡብ አፍሪካዊቷን ኤሌና ሜየርን በረዥም ርቀት ጥላት በማሸነፍ ነበር፡፡ ፎቶግራፉ ደራርቱ የክብር ዶክትሬቷን ከተቀበለች በኋላ ከዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ሐኔኮም (በግራ) እና ከዩኒቨርሲቲው ሬክተር ፕሮፌሰር ብሪያን አ ኮኔል ጋር ሆና ያሳያል፡፡ ሁለተኛው ፎቶ በባርሴሎና ኦሊምፒክ … [Read more...] about ክብር ከደቡብ አፍሪካ ለደራርቱ ቱሉ
“ብሄድም እመለሳለሁ”
በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አራተኛ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሆኑት ዌንዲ ሸርማን ሰኔ 23፤ 2007 ዓም ከሥልጣናቸው እንደሚለቁ ከተሰማ ጥቂት ሳምንታት የተቆጠሩ ቢሆንም ተመልሰው በከፍተኛ ባለሥልጣንነት ሊመጡ እንደሚችሉ ተጠቆመ፡፡ ከጥቂት ወራት በፊት በኢትዮጵያ የሥራ ጉብኝት ያደረጉት ሸርማን በወቅቱ ከቴድሮስ አድሃኖም ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ያሰሙት ንግግር ከፍተኛ ተቃውሞ አስነስቶባቸው ነበር፡፡ ባለሥልጣኗ ፈጽሞ ባልተጠበቀ ሁኔታ ለኢህአዴግ በካድሬ ደረጃ ሙገሳ ቸረው ነበር፡፡ ኢህአዴግ በሚገዛት ኢትዮጵያ ያለውን ህዳሴ ካወደሱ በኋላ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያዊ መንገድ በተመረጠ አስተዳደር ሥር እንዳለች ተናግረው ነበር፡፡ በመቀጠልም ይህንን በዴሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠን በኃይል ለመጣል የሚንቀሳቀሱ በሙሉ ሊጠነቀቁ እንደሚገባቸው አሳሰቡ፡፡ ሲቀጥሉም ግንቦት ሰባትን በስም … [Read more...] about “ብሄድም እመለሳለሁ”
በብላቴናው ላይ የዘገየው ፍትህ!
* የእናት 9 ዓመት ሰሚ ያጣ ጩኸት የ4 ዓመት ደልዳላ እያለ ድክ ድክ እያለ ሮጦ ለቀላል ህክምና ከጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት አፍንጫ ስር በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ገባ። ብዙም ሳይቆይ ከሰመመን መንቃት አልችል አለ፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከሰመመን አልነቃም፣ በሃኪሞች ስህተት ብላቴናው መሀመድ ህይዎቱ ተሰናክሎ ላለፉት 9 ዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሆነል። ትናንትም ሆነ ከትናንት በስቲያም መሀመድና ቤተሰቦቹ ፍትህ ርትዕ ያገኙ ዘንድ ደጋግሜ ጠይቄያለሁ፣ ዛሬም እጠይቃለሁ! ላለፉት በዘጠኝ አመታት ከጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች ጀምሮ ሳይኖር "አለሁ" እስከሚለን የሴቶች ማህበር ተወካዮች ፍትህን ለመሀመድ ያስገኙ ዘንድ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦ ፍትህ ማስገኘት ገዷቸዋል፣ ተበዳዮች ፍትህ ርቋቸዋል. . .! ክልትሙ ተንከባሎ ዛሬ ላይ ሲደርስ . . . ታሪኩን ከመሀመድ እናት ቃል በቃል ስሙት፣ ከዚህ ሁሉ … [Read more...] about በብላቴናው ላይ የዘገየው ፍትህ!
የስርዓቱን ብልግና ለመድነው
አሁን አሁንማ ዜና የሚሆን ነገር ጠፍቷል፡፡ መታሰር ተለምዷል፡፡ መደብደብ ተለምዷል፡፡ የሀሰት ምስክርነት ተለምዷል፡፡ ከአሁን ቀደም ‹‹ጉድ ነው!›› ያሰኙ የነበሩ ህገ-ወጥነቶች አሁን የቀን ተቀን ተግባር ሆነው ወደ ጎን እያየን እየተውናቸው ነው፡፡ በአጠቃለይ የስርዓት ነውር፣ ብልግና፣ ስርዓት አልበኝነትን ለዜናም የሚበቁ አልሆኑም፡፡ በአንድ ወቅት ‹‹እንትና ጠያቂ ተከለከለች፣ እንትና ምግብ እንዳይገባለት ተደረገ›› ተብሎ ዜና ይሰራ ነበር፡፡ እንደ ትልቅ የስርዓቱ ብልግና እና ነውርም ተደርጎ ይታይ ነበር፡፡ እንዲያውም ይህ አይነት በደል የሚፈፀምባቸው በፀረ ሽብር ህጉ ተከሰው የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን ብቻ ነበሩ፡፡ አሁን በሰልፍና በሌሎች ሰበቦች የሚታሰሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ይህ በደል እየተደጋገመ ወደ ተራ አሰራርነት (የስርዓቱ ህግና ደንብ) ተቀይሯል፡፡ ነውር ቢሆንም እኛ ግን … [Read more...] about የስርዓቱን ብልግና ለመድነው
ምርጫ ሲባል፣
ምርጫ ሲባል የነጻነት ዓየር አለ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ተፎካካሪዎች በእኩልነትና በነጻነት የቆሙበት መድረክ አለ፤ ምርጫ ሲባል የራሱን ፍላጎት በትክክል የሚያውቅና ከፍርሃት ነጻ የሆነ መራጭ አለ፤ ምርጫ ሲባል የተፎካካሪዎቹን እኩልነትና ነጻነት፣ የመራጮቹን እኩልነትና ነጻነት የሚያከብሩና የሚያስከብሩ ዳኞች አሉ፤ ምርጫ ሲባል የመራጮቹን ፍላጎት በትክክልና ያለአድልዎ የሚያሳይ ሰነድ የሚያዘጋጁ እግዚአብሔርን የሚፈሩ፣ ሕግን የሚያከብሩ፣ ለሕዝብና ለአገር የሚቆረቆሩ ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል ይኸኛው ከዚህኛው ይሻለኛል ብለው የመወሰን ችሎታ ያላቸው ሰዎች አሉ፤ ምርጫ ሲባል መራጮቹ ተመራጮቹን ማገላበጥ አለ። ታዲያ እኛ ምርጫ የምንለው ይህንን ሁሉ የያዘ ነው? ከዚህ በላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አንዱም እንኳን ቢጎድል፣ ምርጫ አንለውም፤ ምርጫ-መሳይ ልንለው እንችል … [Read more...] about ምርጫ ሲባል፣
ለፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ምስክር
ሰሞኑን በታጋዩ ወገን ስለ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ብዙ እየተወራ ነው። ገና ብዙ እንደሚወራም አጠያያቂ አይደለም። ለምን ፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ፤ በኛ ትግል ሂደት፤ ይሄን የመሰለ ቦታ ይዘው እንደተገኙ፤ ራሱን የቻለ ጥያቄ ነው። ነገር ግን፤ ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸው ስለኢትዮጵያና ስለሚደረገው ትግል ያላቸው ሃሳብ ተዘግቧል። በአንጻሩ ደግሞ ስላሳቸው የኢትዮጵያ ጠላትነትና የትግሉ እንቅፋትነት ምስክርነት የሠጡ አሉ። በዚህ ሂሳብ፤ እስኪ እኔም በውል የማውቀውን ላቅርብ። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ለመጀመሪያ ጊዜ ተከዜን ተሻግሮ ወልቃይት በገባ ጊዜ፤ ሸረላ ላይ ጦርነት ገጥመን ክፉኛ ቆስዬ ነበር። በዚህም ምክንያት፤ የነበርኩበት የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ሠራዊት በጣም ተመናምኖ፤ ሕልውናው አስጊ በሆነበት ሰዓት፤ ለመሰባሰብ፤ የኤርትራ ነፃ አውጪ ግንባር - ጀብሃ - … [Read more...] about ለፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቅ ምስክር
የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ “ሰላይ” ነው – ዲና ሙፍቲ
* “አቶ መለስ በጣም ይናፍቁናል” አሸባሪነት በኢትዮጵያ ሊስፋፋ ያልቻለው ሕዝቡ በሙሉ ሰላይ በመሆኑን ዲና ሙፍቲ አስታወቁ፡፡ ከአገር ተሰድደው የሚውጡት አብዛኛዎቹ ገጠሬ ወጣቶች እንደሆኑና ሟቹ መለስ ዜናዊ የኢትዮጵያ ህዳሴ አባት በጣም እንደሚናፍቋቸው ተናገሩ፡፡ ቀድሞ በቃል አቀባይነት ሲሰሩ የነበሩት በአሁኑ ወቅት ደግሞ በኬኒያ ተወካይ የሆኑት አቶ ዲና ሙፍቲ ስታንዳርድ ዲጂታል ከተባለ የኬኒያ ሚዲያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎች ድርጅታቸውን በመወከል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ የአልሸባብና መሰል ታጣቂዎች የአሸባሪነት ተግባር በኢትዮጵያ ለማድረስ ያልቻሉበት ምክንያት ምንድርነው ተብለው ለተጠየቁት ሲመልሱ ሕዝቡ ሰላይ እንዲሆን የሰለጠነ መሆኑን በመጥቀስ ማንኛውንም ተጠርጣሪ ድርጊት ህዝቡ ሲያይ ሪፖርት እንደሚያደር ተናግረዋል፡፡ ሠራዊቱም እስኪበቃው ድረስ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ “ሰላይ” ነው – ዲና ሙፍቲ
Ethiopian Election Results: Behind the Numbers
The truth may not be black or white. It may be gray. And embracing this fact is good for Ethiopia. Here is my take as an independent voice. My heart is for Ethiopia to find a bridge in reconciliation and mutual understanding. The Story of White The government is joyful that it had secured 100% of the known seats yet (442). This story states that the people had given a green card to the government and thus empowers the government to continue with the status quo. The story dictates that the … [Read more...] about Ethiopian Election Results: Behind the Numbers
የኖርዌይና የስደተኞቻችን ፍልሚያ
የዛሬ አራት ዓመት በኖርዌይ ተቀስቅሶ የነበረው የ500 ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ጉዳይ በኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 127ኛ ችሎት በቅርቡ ሲታይ ሰንብቷል፡፡ ይህ ቀደም ሲል በዶ/ር ግሩም ዘለቀ የግል ተነሳሽነት በኖርዌይ ጠበቆች አማካኝነት በየደረጃው ላሉ የኖርዌይ ፍርድ ቤቶችና በኋላም ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ጉዳይ አሁን የታየው እ.አ.አ. ከሜይ 4 – 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ነው፡፡ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት መቀመጫውን ለንደን ባደረገው ”ዘ አየር ሴንተር - The AIRE Center” (Advice on Individual Rights in Europe) በተሰኘው መንግሥታዊ ባልሆነው የሕግ ባለሙያዎች ድርጅት አማካኝነት የቀረበለትን ይህን ጉዳይ፣ ከሦስት ዓመታት ተኩል በላይ ለሆነ ጊዜ ሲመለከተው መቆየቱም … [Read more...] about የኖርዌይና የስደተኞቻችን ፍልሚያ
ምርጫ ቢቀርስ?!
* “በየ5 ዓመቱ ምርጫ እያሉ ህዝብን ከማሰቃየት፣ እንደነ ሰሜን ኮርያ እና ቻይና የአንድ ፓርቲ አገዛዝ ነው ብሎ ማወጁ ይመረጣል” * “ኢህአዴግ ያሸነፈው ወደ ዘረፋ ስለገባ ነው እንጂ ተቃዋሚ ስለተዳከመ አይደለም” * ዋናዎቹ ተቃዋሚዎች የምርጫ ውጤቱን አንቀበለውም አሉ * ምርጫ ቦርድ የተቃዋሚዎች ውንጀላ መሰረተቢስ ነው ብሏል ባለፈው እሁድ በተከናወነው 5ኛው አገር አቀፍ ምርጫ የተወዳደሩ ዋና ዋናዎቹ ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣የምርጫውን ፍትሃዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ግድፈቶችና የህግ ጥሰቶች መፈጸማቸውን ጠቅሰው የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉ አስታወቁ፡፡ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በ442 የምርጫ ክልሎች ኢህአዴግ ሙሉ በሙሉ እንዳሸነፈ መግለጹን ተክትሎ መድረክ፣ ሰማያዊ፣ ኢዴፓና መኢአድ የምርጫውን ውጤት አንቀበለውም ብለዋል፡፡ ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግን ተከትሎ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው … [Read more...] about ምርጫ ቢቀርስ?!










