የወያኔ አስተዳደር የማዕከላዊውን የመንግሥት ሥልጣን ከተቆጣጠረ በኋላ በሀገሪቱ ተግባራዊ ያደረገው የፌደራል ሥርዓት ጎሣን መሠረት ማድረጉ የሚታወቅ ነው። እንደ ወያኔ አገላለጽ ይህ የጎሣ ፌደራሊዝም በኢትዮጵያ ደም መፋሰስን ያስቀረና ሀገሪቱንም ከመበታተን አደጋ የሚታደግ ነው ይላል። ይሁን እንጂ በተግባር እየተፈፀመ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ በጥልቀት ስንፈትሽ ይህ ወያኔ-ሰራሽ የሆነው የጎሣ ፌደራሊዝም ዓላማም ሆነ እያስከተለ ያለው ውጤት ከዚህ በተቃራኒ ሆኖ እናገኘዋለን። በመጀመሪያ ምንም እንኳን በሕገ መንግሥቱ ላይ “ሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ራሳቸውን በራሳቸው የማስተዳደር መብት አላቸው” ቢልም በተግባር ግን አምስት ብሔሮች ብቻ የራሳቸው ክልል እንዲኖራቸው አድርጓል። ሌሎች ከሰባ አምስት በላይ የሚሆኑ ብሔረሰቦች ወይ ባለብዙ ብሔር ክልል በመፍጠር በዚያ እንዲታቀፉ ሲያደርግ፤ አልያም … [Read more...] about የወያኔ የጎሣ ፌደራሊዝም ሲፈተሽ
ለሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ አገልግሎት የገንዘብ እርዳታ ጥየቃ ማስታወቂያ
ለሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ ሥርጭት መጀመር የሚያግዘንን ገንዘብ በተከታታይ እርዳታ መጠየቂያ። ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ማስታወቂያና የሕዝብ ግንኙነት … [Read more...] about ለሞረሽ የዐማራ ድምፅ ሬድዮ አገልግሎት የገንዘብ እርዳታ ጥየቃ ማስታወቂያ
ኢህአዴግ ኅብረ ብሔር ፓርቲ ሲሆን ኤፈርትና ሚድሮክ ይዋሃዳሉ?
ኢህአዴግን ወደ ኅብረ ብሔር ፓርቲ የማሸጋገር ሥራ እየተሰራ መሆኑንን ሃይለማርያም ደሳለኝ የአገሪቱን “ምሁራን” ባናገሩበት ወቅት ፍንጭ ሠጥተዋል። የዛሬ ሰባት ዓመት ከመስከረም 5 እስከ 7 ቀን 2001 ዓ.ም ሃዋሳ ተካሂዶ በነበረ የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ አቶ መለስ ድርጅታቸው ወደ ብሄራዊ ፓርቲ ወይም አሃዳዊ ፓርቲ ስለመሸጋገሩ እየተጠና መሆኑንን ተናገረው በቀጣዩ ጉባኤ ሪፖርቱ እንደሚቀርብ ቃል ገብተው ነበር። ጥያቄው ዝም ብሎ የቀረበ ሳይሆን ታስቦበትና ከዚህ ቀደም የተሰጠውን መልስ በማስታወስ ነበር። ይህ የሚያሳየው አሃዳዊ ፓርቲ የመሆን ጉዳይ የዛሬ አለመሆኑን ነው። ከብአዴን እንደሆነ የጠቀሰ አንድ ጉባኤተኛ ጥያቄውን ሲያነሳ ቀደም ሲል ይህ ጉዳይ ተነሥቶ እንደነበር ጠቆመ። በማስከተልም በወቅቱ ጥያቄው ሲነሳ አጥኚ ግብረ ሃይል መሰየሙን አወሳ። አያይዞም “ጉዳዩ የት ደረሰ?” … [Read more...] about ኢህአዴግ ኅብረ ብሔር ፓርቲ ሲሆን ኤፈርትና ሚድሮክ ይዋሃዳሉ?
“ለሕዝብ ይፋ ካላደረጋችሁት የፋይናንስ ሪፖርቱን እሰጣችኋለሁ”
የሆላንድ ዜምብላ ጋዜጠኞች የኦሮሞ ጸሃፊው የሆነውን ያሶ ካባባን ይዘው ወደ ጊንጪ ያመራሉ። እግረመንገድ ላይ የሚያገኟቸው ገበሬዎችም ሲጠይቋቸው በምስሉ ይታያል። እነዚያ በቀያቸው ማረፍያ እንኳን የሌላቸው ገበሬዎች የጋዜጠኞቹን መኪና ከብበው እንዲህ ሲሉ ይደመጣሉ። "መሬታችንን ቀምተው ለነጮች ሰጡብን። እኛንም በታተኑን..." በገዛ ቀያቸው ስደተኛ የሆኑ እነዚህ ወገኖቻቸን ሰቆቃቸው የከፋ ነበር። በመጨረሻ ተሰባሰቡና መከሩ። ሰባት ሺህ የሚሆኑ የጊንጪ ተወላጆች ሆ! ብለው ወጥተው ይህንን የሁለት ሚሊዮን ዩሮ (ሃምሳ ሚልዮን ብር) ንብረት በሰኮንዶች ውስጥ አወደሙት። ምስላቸውን ለካሜራ ሳይደብቁ፣ ስሜታቸውን እና የወደፊት እቅዳቸውን ይናገራሉ። "ከአምባገነን መንግስት ጋር አብሮ ከመስራት ይልቅ የአካባቢው ነዋሪዎች ሊጠቀሙ በሚችሉበት መንገድ መስራት እንደሚችሉም" ለፈረንጆቹ ይመክራሉ። … [Read more...] about “ለሕዝብ ይፋ ካላደረጋችሁት የፋይናንስ ሪፖርቱን እሰጣችኋለሁ”
የሽብርተኛ ትርጉም
የሚማር የለም እንጂ የሚማር ቢኖር የሽብርተኛነትን ትርጉም ሰሞኑን በቤልጂክ እያየንና እየሰማን ነው፤ በኢትዮጵያ ያሉ የእውቀት ምልክቶችን በዶላር እየገዙ ስማቸው ላይ የለጠፉ ጉልበተኞች ተናገርክ(ሽ) ብለው ብቻ ሳይሆን አሰብህ(ሽ) ብለው ሰፋፊ እስር ቤቶች እያሰሩ ወጣቶችን ሲያጉሩበት ምክንያታቸው ሽብርተኛነት ነው፤ ሽብር ማለት ሰሞኑን በቤልጂክ አውሮጵላን ጣቢያና በባቡር ጣቢያ ላይ እንደታየው ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ አልታየም፤ ከታየም በአገዛዙ ኃይሎች የተፈጸመ ነው፤ ለብዙ ዓመታት ሲፈጸም የቆየ ነው፤ የኢትዮጵያ ጉልበተኞች ከቻሉ ሊያስተውሉት የሚገባ አንድ ነገር አለ፡- ሽብርም ነጻነትን ይፈልጋል፤ በቤልጂክ ሽብሩን የፈጸሙት ሁሉ ነጻነትን ፈልገው ከአገራቸው የተሰደዱና በአገራቸው ያላገኙትን ነጻነት በሰው አገር እየተሞላቀቁበት እንደሆነ የሚያመለክት ነው፤ ትርጉሙ፡- ነጻነት በሌለበት … [Read more...] about የሽብርተኛ ትርጉም
የስልጣን ተስፈኛ ፖለቲከኞች
የኢህአዴግ የቁርጥ ቀን ልጅ ልደቱ አያሌውና ፓርቲው ኢዴፓ ባዲስ ትርፍ የፓርላማ መቀመጫ ፍለጋ ሰሞኑን ከእንቅልፋቸው መንቃታቸውን ሰምቼ ትንሽ ተገረምኩ። በውል ያልተደነቅሁበት ምክንያት ኢዴፓንና ሌሎች በኢህአዴግ-ወለድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ም/ቤት ውስጥ የታጨቁ የስልጣን ተስፈኞች እንጂ ፖለቲካ የሚያውቁ ቁርጠኛ ተቃዋሚዎች ናቸው ብዬ ስለማላውቅ ነው። ደግነቱ ደግሞ ነገሩ እውነት መሆኑ ነው። እነዚህ ኢህአዴግ በልካቸው በሰራላቸው ጉረኖ ታሽገው በኢትዮጵያ ህዝብ መስዋእትነት ስልጣን ለመቀላወጥ በተስፋ የሚያደቡት ኢዴፓና አጃቢዎቹ ሰሞኑን የኢህአዴግ ዙፋን ሲነቃነቅ በፈጠረው የፖለቲካ ስንጥቅ ለመሰካት በጠቅላይ ሚንስትሩ እግር ስር ወድቀው ትራፊ ወንበር እንዲረጥቧቸው ልመና መጀመራቸውን ሰምቼ አፈርኩባቸው። የኢዴፓ ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደ አርብ መጋቢት 16 ቀን 2008 ዓም ለአሜሪካ … [Read more...] about የስልጣን ተስፈኛ ፖለቲከኞች
“የልጄን ነገር አደራ…” እናት ሎሚ
የእናትን መሪር ሐዘን ሰምቸ ሆዴ ተላውሷል፣ የእናትን ጥልቅ ጭንቀቷ፣ ያለ አባት በአሳር በመከራ ያሳደገቻት የእናትን ሎሜ መሪር ሐዘን ተረድቸ ህመም መታመሜ እውነት ሳለ በዝምታ እየቆሰልኩ ማስረጃ መረጃ ፍለጋ መዋተቴ ህመሜን አክብዶታል፡፡ ከጉያዋ ወሽቃ፣ በትንፋሿ አሙቃ፣ ስታገኝ በደስታ፣ ስታጣ ተከፍታ ድሃ አደግ ቤቷን አሟሙቃ ነገን ልጆቿን ለወግ ለማዕረግ የማድረስ ምኞት ተስፋን ሰንቃ ተስፋዋን የተነጠቀች እናት እንባ ውስጤን አድምቶ አቃጥሎታል። እናት ዛሬ ማለዳ በላኩልኝ መልዕክት እንዲህ ይላል “የልጀን ነገር አደራ እባክህ ነፍሴን አሳርፋት" … ሰው ሆዬ ሲጨንቀው እኔ መረጃን ከምንጩ ከማሰራጨት ባለፈ ሁሉን ማድረግ የሚቻለኝ አድርጎ ይስለኛል፤ እኔ ግን አቅሙ የለኝም! መረጃዎችን ለወገናቸው ጥቅም ቅድሚያ ከሚሰጡ የመንግስትና የድርጅት አባላት በሚስጥር፤ ከቀሩት ወገኖች … [Read more...] about “የልጄን ነገር አደራ…” እናት ሎሚ
ህወሃት ራሱን በራሱ ሸንጎ አስገምግሞ የእጁን ደም ሊያጸዳ ነው
ህወሃት በኦሮሚያና በአማራ ክልል በንጹሃን ዜጎች ላይ የፈጸመውን ወንጀልና ርህራሄ አልባ ግፍ ራሱ አጣርቶ፣ ራሱ አጠናክሮ፣ ራሱ በፈጠረው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አማካይነት አቅርቦ፣ በራሱ ሸንጎ በማጸደቅ እጁን ከደም ሊያጸዳ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ይፋ መሆኑንን ተከትሎ ለሪፖርቱ ማዳመቂያ የምስል ቪዲዮዎች መዘጋጀታቸው ታወቀ። በኦሮሞና በአማራ ህዝብ ላይ የተወሰደውንና እየተወሰደ ያለውን የኃይል ርምጃ አስመልከቶ ድራማ እየተሰራ ነው ሲል የጎልጉል የአዲስ አበባ ተባባሪ ሪፖርተር የኢህአዴግ ጽ/ቤት ምንጮቹን ጠቅሶ ነው ስለ ሁኔታው የዘገበው። ህወሃት በአዋጅ ያቋቋመው የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መሪ ዶ/ር አዲሱ ገብረ እግዚአብሔር ቀደም ሲል በጉዳዩ ዙሪያ ሪፖርት ያቀረቡትን የመብት ተሟጋች ድርጅቶች እንደማይታመኑ ተናግረዋል። በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግንባር መመሪያ ሰጪነት ህወሃት … [Read more...] about ህወሃት ራሱን በራሱ ሸንጎ አስገምግሞ የእጁን ደም ሊያጸዳ ነው
ለአዲስ አበባ የውሃ ድርቅ “ፈረቃ” መፍትሔ ሆኖ ተበሰረ
ራሱን “ልማታዊ” እያለ የሚጠራው ኢህአዴግ በውሃ ድርቅ ሳቢያ በአዲስ አበባ በዝርዝር ባልተገለጹ ቦታዎች ውሃ በፈረቃ ማቅረብ መፍትሔ ሆኖ ተበሰረ። በአገሪቱ በይፋ ያልተገለጸ የውሃ ችግር አለ። አዲስ አበባን በተመለከተ የከርሰ ምድር ውሃ ችግር እንደሌለ ባለሙያዎች ሃሳብ ሲሰጡ ኖረዋል። ኢህአዴግም ቢሆን ከ1997 ምርጫ በኋላ የአዲስ አበባን የውሃ ችግር ለመፍታት የከርሰ ምድር ውሃን እንደሚያጎለብት በተደጋጋሚ ሲገልጽ ነበር። የአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነትን ጠቅሶ ቪኦኤ እንደዘገበው የፈረቃው አሠራር የተጀመረው የካቲት 24 ነው። ፈረቃው መፍትሔ ሆኖ የቀረበው የድሬና የለገዳዲ ግድቦች በቂ ውሃ ባለመያዛቸው ሲሆን ፈረቃውም የሚያካትታቸውን ቦታዎች “የተወሰኑ” ከማለት ሌላ ዝርዝር አልቀረበም። በከፊል አዲስ አበባ ተብሎ በደምሳሳው ውሃ በፈረቃ እንደሚታደል ሲገለጽ … [Read more...] about ለአዲስ አበባ የውሃ ድርቅ “ፈረቃ” መፍትሔ ሆኖ ተበሰረ
በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጣዊ መግለጫዎች
ገዢው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት በየዕለቱ በሚያደርገው ፀረ-ኢትዮጵያዊ ተግባር፤ የተለያዩ የፖለቲካ ሕዝባዊ ስብስቦች መግለጫ ያወጣሉ። አዳዲስና ነባር የፖለቲካ ድርጅቶች፤ አለን በማለት ስማቸውን በአንባቢዎች ያስመዘግባሉ። ለመሆኑ ጋዜጣዊ መገለጫዎች ለምንድን ጉዳይ ነው የሚወጡት? ማነው የሚያወጣቸው? መግለጫዎችን ተከትሎ የሚተገበሩት ምንድን ናቸው? አሉስ ወይ? መግለጫ አውጪዎቹና መግለጫ ያላወጡ የፖለቲካ ሕዝባዊ አካሎች መለያቸው ምንድን ነው? መግለጫዎችና አውጪዎቻቸው፤ ሕዝባዊ ናቸው ወይንስ ጠባብ ወገንተኛ? መልዕክት አላቸው ወይንስ አደረግሁ ለማለት የተወረወሩ? አስፈላጊነታቸውስ ምን ያህል ነው? በተደጋጋሚ ጋዜጣዊ መግለጫ በተንጎደጎዱ ወቅት የደረሱኝ እጦማሮች ነበሩ። ሁሉም ወቀሳዎች ናቸው። “ለምን መግለጫ አታወጣም?” “ካሁን በፊትም ዝም ብለሃል!” የሚሉና … [Read more...] about በመቶዎች የሚቆጠሩ ጋዜጣዊ መግለጫዎች










