ሥልጣንን ይዞ ሀገርንና ሕዝብን ለማሥተዳደር ሁለት የትግል አማራጮች አሉ፡፡ በሀገራችን ሁለቱም ዓይነቶች በሚገባ ይታወቃሉ ተሞክረዋልም፡፡ አንደኛው ሕዝብ በሚያደርገው ምርጫ የመንግሥትነት ሥልጣንን መያዝ መሠረቱ ያደረገው ሰላማዊ የትግል አማራጭ ሲሆን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ይህ ሰላማዊ የትግል አማራጭ ዝግ ሲሆን ወይም ሊሠራ በማይችልበት ጊዜ በሕዝብ ላይ በኃይል የተጫነን አንባገነን አገዛዝን በኃይል ለማስወገድ የሚደረግ የኃይል እንቅስቃሴዎችን መሠረቱ ያደረገ የትጥቅ ወይም የዐመፅ የትግል አማራጭ ነው፡፡ እስኪ ሰላማዊው የትግል አማራጭ በዘመነ ወያኔ ምን እንደሚመስል በአጭሩ ዕንይ፡፡ ወያኔና ምርጫ፡- በዘመነ ወያኔ ምርጫ እየተባለ ለአራት ጊዜያት ያህል በሕዝብና በሀገር ላይ ከባድ ቀልድና ሹፈት ሲቀለድና ሲሾፍ ሲፌዝ ተቆይቷል አሁን ደግሞ ለአምስተኛ ጊዜ እየተሾፈና እየተቀለደ … [Read more...] about ላልቀረልን ሀገርንና ሕዝብን የመታደግ ትግል ተነሡ!
Opinions
የኔ ሃሳብ
ባቡር
ትናንትና (እሁድ) የከተማ መለስተኛ የባቡር መጓጓዣ አገልግሎት ተጠናቆ ለአገልግሎት ተመረቀ፡፡ አሄሄሄ! ውስጡን ለቄስ! አሉ፡፡ ይሄ የባቡር ሥራ ብቻ ሳይሆን በወያኔ እጅ የሚሠራ ሥራ ሁሉ ከፍተኛ ብቻ ሳይሆን እጅግ አደገኛና አሳሳቢ የጥራት ችግር እንዳለባቸው በግልጽ የሚታይ ጉዳይ ነው፡፡ ቢሊዮኖች ዶላር (ብልፎች ዶላር) ልብ በሉ ቢሊዮን (ብልፍ) ነው ያልኩት ሚሊየን (አእላፋት) አይደለም ፈሶበት ቴሌ ላይ የተሠራውን ሥራ እና ውጤቱን ዐይተናል፣ መብራት ኃይል ላይም አሁንም እንዲሁ በቢሊዮኖች (ብልፎች) ዶላር ወቶበት ከህንድ እንዲገባ ያደረጉት ትራንስፎርመር (ማስተላለፊያ) በሙስና ምክንያት ከጥራት ደረጃ በታች እንዲሠራ የተደረገ በመሆኑ በተገጠመ ቁጥር እየተቃጠለ ምን ዓይነት ችግር ላይ እንዳለን ለቀባሪ ማርዳት ነው፡፡ በዚህ በባቡር ሥራው ላይም የጅብነታቸው ጅብነት የሸክላ ሀዲድ … [Read more...] about ባቡር
Ethiopia-visions of the final battle
We all should thank the Central Committee of Tigrai Peoples Liberation Front for making things a little clearer in our country. When election season is close the TPLF removes all pretenses and makes itself visible to the citizen of Ethiopia. The picture is not pretty. Their latest bold move to delete and erase Andenet is no matter how you look at it a most daring act worthy of the late visionary dictator. It was illegal, some would say irrational but vintage TPLF. If you really want to know … [Read more...] about Ethiopia-visions of the final battle
The Charities and Societies Proclamation and its impact on human rights and women’s rights activism in Ethiopia
Four years after a draconian law stymied the work of civil society associations in Ethiopia, it has remained imperative to search for ways and means of the public making its input towards ensuring its entitlement to human rights, needs satisfaction and human development Ethiopia passed the Charities and Societies Proclamation (CSP), (No.621/2009), in February 2009 to regulate the work of civil society organizations in the country. This Law classified Ethiopian organizations into Charities or … [Read more...] about The Charities and Societies Proclamation and its impact on human rights and women’s rights activism in Ethiopia
የፈረንሳዩ ቻርሊ ሂብዶ ጋዜጣ አሸባሪዎችና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት!
ከሰሞንኛው የዓለም አቀፍ የብዙኃን መገናኛዎች ወሬ እንዳዳመጣቹህት ሰሞኑን ፈረንሳይ ውስጥ በሚታተም ቻርሊ ሄብዶ በተባለ ጋዜጣ ጥቅማችን ተነካብን ያሉ የመካከለኛው ምሥራቅ ተወላጆች በአሸባሪነት ከተፈረጁ ቡድኖች በተደረገላቸው ድጋፍ በጋዜጣው ሠራተኞች ላይ በፈጸሙት ጥቃት ባጠቃላይ 17 የሚሆኑ ሰዎች ለሕልፈት መዳረጋቸውን ተከትሎ የምዕራቡ ዓለም መንግሥታትና ዜጎች በቁጣ በመነሣት አውግዘዋል ለጋዜጣውም ያላቸውን አጋርነት ገልጸዋል፡፡ የፈረንሳይ መንግሥትም ይሄንን ጥቃት በፈጸሙትና በደጋፊዎቻቸው ላይ እርምጃ ወስዷል እየወሰደም ነው፡፡ ይሄ ዓይነት ጥቃት ያሠጋናል የሚሉ ሀገራትም ተመሳሳይ እርምጃዎችን እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ ይሄንን ጉዳይ በተመለከተ እዚህ ሀገር ውስጥም የበሰለና ጥልቀት ያለው አይሁን እንጅ ኢ.ቴ.ቪ (ኢ.ቢ.ሲ) በልዩ ዝግጅት እና የሸገር ኤፍ.ኤም በሸገር ሸልፍ ዝግጅቱ … [Read more...] about የፈረንሳዩ ቻርሊ ሂብዶ ጋዜጣ አሸባሪዎችና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት!
ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ!
አቶ ኢሳይያስ እንዴት ነዎት ባያሌው? ሌሎቹ የሕዝባዊ ግንባር አመራሮችስ እንዴት ናቸው? ሕዝቡስ እንዴት ነው? አቤት! አቤት! አቤ……..ት! ለማንኛውም ድምፅዎን ማሰማትዎ መልካም ነው፡፡ በቅርቡ ለኢሳት የራዲዮና የቴሌቪዥን (የነጋሪተ-ወግና የምርዓየ-ኩነት) ጣቢያ የሰጡትን ቃለ መጠይቅ ጣቢያው ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያደርስልዎት ዘንድ ከኢሳት ጋዜጠኞች ጋር ቃለመጠይቁን ማድረግዎን ሰማን፡፡ እግዚአብሔር ይስጥልን! እግዚአብሔር ያክብርልን! ብለናል፡፡ ግን እንዲያው እውነት ለመናገር አቶ ኢሳይያስ ከአማርኛ ይልቅ እንግሊዝኛው ቀንቶዎት ቀርቦዎት ቀሎዎት ነው ከፊሉን ቃለ ምልልስ በእንግሊዝኛ ያደረጉት? በእርግጥ አባትዎ እንዳስጠነቀቁዎት ጠንቅቀው (perfectly) በማያውቁት ቋንቋ ያውም ቃለ መጠይቅን ያህል ነገር ማድረግ ከባድ ነው፡፡ ነገር ግን እኮ አቶ ኢሳይያስ የእርስዎ አማርኛ ደኅና እና … [Read more...] about ግልጽ ደብዳቤ ለአቶ ኢሳይያስ አፈወርቂ!
ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ
በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በዛሬው እለት ሰኞ (January 26,2015) በኖርዌ ኦስሎ በእንግሊዝ ኢንባሲ ፊት ለፊት በኖርዌይ የሚኖሩ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በህብረት ሁነው ከ14፡00-15፡00 ስዓት ታላቅ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ በደማቅ ሁኔታ አካሄዱ። የሰልፉ ዋና አላማ የግንቦት 7 የፍትህ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ዋና ፀሃፊ የነበሩትንና የሰባዊ መብት ተቆርቋሪ የሆኑትን አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በአረመኔው፣ ሰው በላ፣ ጨቋኙና በአንምባ ገነኑ የወያኔ ፋሺስታዊ ቡድን የአለም አቀፍ የሰባዊ መብትን ህግ በጣሰ መንገድ በሰኔ 2014 ታፍነው እስኳሁንም ድረስ ፍትህ ተነፍገው በእስር ቤት መታሰራቸውን ለመቃወም እንዲሁም የእንግሊዝ መንግስት አርበኛው የነጻነት ታጋዩ አንዳርጋቸው እየተፈጸመበት ያለውን ተፈጥሮአዊና … [Read more...] about ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ እንግሊዝ ኤምባሲ ፊት ለፊት በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ
የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ
በመጀመርያ ዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ደጋፊና ተደጋፊ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን በሙሉ ጠሯቸው። ሰበሰቧቸው። እንዲህም አሏቸው። "ወደ ደደቢት አብራችሁን ትሄዳላችሁ፤ እዛ እንደደረሳችሁም አመጣጣችንንና አካሄዳችንን በደንብ አድርጋችሁ ታጤናላችሁ። ከዚያ ስትመለሱ ሁሉንም ነገር ለህዝቡ ትናገራላችሁ።..." በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የሃገር መሪ ሆነው የሚሰሩት እኝህ ሰው መልዕክታቸውን በዚህ አላበቁም። አይናቸውን ፈጠጥ፤ ጉሮሯቸውንም ጠረግ-ጠረግ አደረጉና ንግግራቸውን ቀጠሉ "ስለረጅሙና መራራው ትግላችን፤ ከጅምራችን እስከ አያያዛችን የታዘባችሁትን ሁሉ ንገሩን። ጥሩውንም ይሁን መጥፎውን ነገር ሳትደብቁ ተናገሩ።..." ድምጻዊው በዝማሬ፣ ጸሃፊው በድርሰት፣ ተዋንያኑ በተውኔት ስለ ህወሃት የአርባ አመት ጉዞ እንዲመሰክሩ የተሰጠች … [Read more...] about የደደቢት ጉዞ መዘዝ፤ ከሰራዊት ፍቅሬ እስከ ታገል ሰይፉ
የሐመር አርብቶ አደሮችና የፖሊስ ግጭት ወቅታዊ መረጃ
በጥር 7/2007 ሐሙስ ዕለት በሐመር ወረዳ በ"ላላ" ቀበሌ በሐመር ብሔረሰብ አርብቶ አደሮችና ፖሊስ መካከል በተፈጠረ ግጭት የደረሰዉ ጉዳት የሚከተለዉን ይመስላል፤ ሀ/ የሞቱ-- 1. ሻምበል ለማ አሸናፊ 2/ ወ/ር ሙሴ ማቱሳላ 3/ ወ/ር ደፋሩ ጦና 4/ ወ/ር ካሬ 5/ ወ/ር በኃይሉ 6/ ስሙ ለግዜዉ ያልታወቀ የልዩ ኃይል ባልደረባ 7/ ስሙዋ ለግዜዉ ያልታወቀ ሴት ባለሙያ 8/መምህር መሳይ ነሽ መርነህ ለ/ የቆሰሉ 1/ አቶ ቹሜሬ የረር /የደቡብ ኦሞ ዞን ፍትህ ጸጥታና ደንብ ማስከበር ምክትል ሀላፊ 2/ ምክትል ሣጅን ጌታሁን ቶላ 3/ ወ/ር ተሰማ መሰረት 4/ ወ/ር ጌታቸዉ ጻንቃ 5/ ወ/ር ቱላ ኪያ 6/ ባሻ ወንድማገኝ ጨነቀ 7/ ወ/ር ሚልኪያስ ግራኝ 8/ ወ/ር ዘለቀ (አባታቸዉ ያልታወቀ) 9/ አቶ ደምሳሽ ሞላ (የዞኑ ሴቶችና ሕጻናት መምርያ … [Read more...] about የሐመር አርብቶ አደሮችና የፖሊስ ግጭት ወቅታዊ መረጃ
በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ሰራተኞች ድምጽ አልባው እሮሮ!
ንብረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደሆነ በሚነገርለት ካፍቴሪያ ውስጥ የሚፈጸመው ግፍ አይሏል ። ከዛሬ 10 ዓመት በፊት እዚህ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ውስጥ በተለያየ የሙያ ዘርፍ ሰማርተው እያገለገሉ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን አብዛኛዎቹ በወጣትነት እድሚያቸው የተቀጠሩ ናቸው። ታዲያ ለወጣትነት እድሜ ጉልበታቸው ሳይሰቱ ነገን በተስፋ በመናፈቅ ተመጣጣኝ ባልሆነ ክፍያ በቀን ከ 8 ሰዓት በላይ አውዳአመታትን ሳይቀር ያለ እረፍት በስራ በማሳለፍ ኮሚኒቲውን አገልግለዋል። ሰራተኞቹ በተሰማሩበት የስራ መስክ በሚከፈላቸው ደሞዝ እንደማንኛውም ማህበረሰብ ቤትሰብ አፍርተዋል ። እነዚህ ወገኖች እንደመነሻ በተቀጠሩበት አነስተኛ ደሞዝ ከግዜ ወደ ግዜ እየከበደ የመጣውን የስደት ዓለም ህይወት መቋቋም ተስኗቸው ገሚሱ በብስጨት በደረሰበት የጤና መታወክ ለህለፍት ሀይወት ሲዳረግ በስኳር በሽታ … [Read more...] about በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ካፍቴሪያ ሰራተኞች ድምጽ አልባው እሮሮ!










