ወቅቱ 1973 ዓ.ም ነበር፡፡ አገሪቱ ከተለያዩ የውስጥና የውጪ ኃይሎች ጋር ጦርነት ውስጥ የገባችበት ጊዜ ነው፡፡ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ልጆቻቸውን ያለ አሳዳጊ ጥለው በየጦር ሜዳው ወድቀዋል፡፡ አሳዳጊና ተንከባካቢ ያጡት ህፃናት በየጎዳናው መውደቃቸው ያሳሰበው የደርግ መንግስት፤ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በነበሩት መንግስቱ ኃይለማርያም ልዩ ትዕዛዝ የአብዮታዊት ኢትዮጵያ ህፃናት አምባ ተቋቁሞ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ በቀድሞ አጠራር በሸዋ ክፍለ ሃገር ሀይቆችና ቡታጅራ አውራጃ፣ በአላባ ቁሊቶ ወረዳ፣ አላጌ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ወላጆቻቸውን በጦርነትና በሌሎችም ሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋዎች ያጡ ህፃናትን ተቀብሎ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸውን በማሟላት፣ በትምህርትና በሥነ ምግባር ኮትኩቶ የማሳደግን ዓላማ አንግቦ የተቋቋመው አምባው፤ “ሰብለ አብዮት”፣ “መስከረም ሁለት ኦጋዴን”፣ … [Read more...] about የህፃናት አምባ ልጆች ትዝታና ቁጭት
Opinions
የኔ ሃሳብ
“የልማታዊ” እና “ሁለገብ” ጋዜጠኞች አንድም – ሁለትነትም
ጋዜጠኝነት ትልቅ ክብር የሚሰጠው፣ የራሱ የሆነ መርህና ስነ-ምግባር ያለው፣ ጠያቂነትን ብቻ ሳይሆን ተጠያቂነትንም በውስጡ የያዘ የሙያ መስክ ነው። ለዛም ነው ጋዜጠኛ የሕዝብ አንደበት፣ አይንና ጆሮ ነው የሚባለው። ሕዝብ በሚከበርበት ቦታ ሁሉ ጋዜጠኛም ይከበራል። ሕዝብ በሚዋረድበት፣ በሚታፈንበትና በሚዋከብበት ስፍራም ጋዜጠኛ ይዋረዳል፣ ይሳደዳል፣ ይታፈናል፣ ይዋከባል፣ ይታሰራል፣ ሲከፋም ይገደላል። ይህም በሕዝብ፣ በመንግሥትና በጋዜጠኛ መካከል ያለውን ቁርኝት በደንብ ያሳያል። ሕዝብና መንግሥት ልብ ለልብ ሊገናኙ የሚችሉት ጋዜጠኛ ሲኖር ነው። የሁለቱን የልብ ትርታ እያደመጠና ያንዱን ላንዱ እያስደመጠ በመካከላቸው ገደል እንዳይኖር ድልድይ ሆኖ ያገለግላል። ጋዜጠኞች ይህን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት ከሚጠበቅባችው ነገሮች ዋነኛውና መሰረታዊው ነገር የሙያውን ሥነ-ምግባርና መርሆዎች ጠንቅቆ … [Read more...] about “የልማታዊ” እና “ሁለገብ” ጋዜጠኞች አንድም – ሁለትነትም
Misplaced Opposition to the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD): Update
In our April 30 2014 commentary which appeared on several media outlets, we outlined the fallacies of the Egyptian policy towards GERD. It appears that the last few months have witnessed breath-taking diplomatic developments. For one, Egypt has returned to the African Union. It also has been reported that there were several rounds of side and formal meetings between Ministers and the Heads of States and Governments of Egypt, Ethiopia and Sudan. Egypt has also shown a renewed interest on … [Read more...] about Misplaced Opposition to the Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD): Update
ለሃጅ ጸሎት መጥቶ ሳውዲ የቀረው ገበሬ እንግልት
ወንድም ራያ ጀማ የ5 ወንድ እና የ3 ሴት ልጆች ጎልማሳ አባት ነው። ወደ ሳውዲ የመጣው ድህነት፣ የኑሮ ውድነት፣ የፖለቲካው ሙቀት አለያም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ገፍቶት አይደለም። ሳውዲ የመጣው፣ በእስልምና እምነቱ በሚያዘው መሰረት በህይወት ዘመኑ የሚጠበቅበትን ለማድረግ ከብቶቹን ሽጦ የሃጅ ጸሎት ለማድረግ ነበር . . . ዳሩ ግና የጅማው ገበሬ ራያ ጀማል እንደ ቀሩት ጓደኞቹ ጸሎቱን አድርጎ ለመመለስ አልቀናውም! ከሀጃጅ ጓደኞቹ ተለይቶ ከቤተሰብ እንደራቀ ፣ ላለፉት ሁለት አመት ከመንፈቅ ገደማ ሳውዲ በእንግልት ጊዜውን ሊገፋ ግድ ብሎታል። ምክንያቱም የሃጅ ጸሎቱን ከውኖ መካ ውስጥ መኪና አደጋ ደረሰበትና ነው! የራያ ጀማል ጉዳት. . . ራያ ጀማል በደረሰበት የመኪና ግጭት የተለያየ የአካሉ ክፍል በጠና ስለተጎዳ በከፍተኛ ህክምና መካ ውስጥ ለሁለት አመት ተኩል ገደማ በሳውዲ … [Read more...] about ለሃጅ ጸሎት መጥቶ ሳውዲ የቀረው ገበሬ እንግልት
ወያኔና ሽብርተኛነት
ወያኔነትና ሽብርተኛነት ትናንት ምን ዓይነት ግንኙነት ነበራቸው? ዛሬ ምን ዓይነት ግንኙነት አላቸው? ወደዚያ ከመሄዳችን በፊት የአሸባሪነት የተግባር መገለጫው ምንድን ነው? ብለን እንጠይቅ፤ አሸባሪነት፡- • ያለውን የሥልጣን ሥርዓት የማፍረስ ዓላማ ያለው ነው፤ • ዓላማውን ለማሳካት ጉልበቱን የሚያፈረጥመው ከሥርዓቱ ጠላቶች በሚያገኘው፡-- • የመሣሪያ እርዳታ፣ • የእውቀት ድጋፍና ገንዘብ • ዓላማውን ለማሳካት o ሰዎችን ገድላል o ያስራል፤ ያሰቃያል o ይዘርፋል፤ ይቀማል፤ • ዓላማውን ለማሳካት o ሃይማኖቶችንና ባህልን ያዳክማል፤ o የጥንት ታሪክ ማስታወሳዎችንና የቆዩ መጻሕፍትን ያጠፋሉ፤ o የፖሊቲካ እምነትን ያግዳል፤ o የመሰብሰብ ነጻነትን ይከለክላል፤ o የመደራጀት ነጻነትን ይከለክላል፤ o ሀሳብን የመግለጽ ነጻነት ይከለክላል፤ o ጉልበትን ወደሥልጣን … [Read more...] about ወያኔና ሽብርተኛነት
DCESON Press release
Press release DCESON has arranged a public meeting and fundraising event on April 18, 2015 from 15 pm to 22 pm, Come and contribute your share to the HULEGEB TIGEL for freedom and democracy. Let’s support ultimate struggle for building democratic system in Ethiopia. There was no reign or rule in the history of Ethiopia like the rule of Wayne under which Ethiopians humiliated, undignified, undermined and lost their identity. At present the fundamental trouble of Ethiopia and its citizen is not … [Read more...] about DCESON Press release
“አልሸጥም ማለትም ዕብሪት አይደለም”
ኢትዮጵያውያን በታሪካችን የታወቅነው በኩራታችንና ራሳችንን በማክበራችን ነበር፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት የስዊስ አምባሳደርን ወያኔ አስፈራራውና በኢሰመጉና በሱ መሀከል የነበረውን ልዩነት አደባባይ አወጣው፤ ስለኢሰመጉ የሆነ ያልሆነውን ለመናገር መብት ያገኘህ የመሰለህ አሥር ሺህ ዶላር ስለሰጠኸን ነው፤ ይህንን አሥር ሺህ ዶላር መኪናዬን ሸጬም ቢሆን እመልስልሃለሁ ብዬ በጋዜጣ አወጣሁ፤ ይህንን ያነበበ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ እቤቴ ድረስ መጥቶ የአሥር ሺህ ዶላር ቼክ ሰጠኝና መከናህን አትሸጥም፤ ይኸውልህ አፍንጫው ላይ ወርውርለት ብሎኝ ሄደ፤ እኔም ለስዊስ አምባሳደር የአሥር ሺህ ዶላር ቼክ ላክሁለት፤ እሱም አልተቀበለኝም፤ በመቀስ ቆርጦ መለሰልኝ፤ ልናገር የፈለግሁት ዋናው ነገር ሁለት ነው፤ አንዱ ክብራችንን በገንዘብ የማንሸጥ እንደነበርን ለማስታወስ ሲሆን ሌላው ደግሞ ደጉን ጓደኛዬን … [Read more...] about “አልሸጥም ማለትም ዕብሪት አይደለም”
የፕ/ር አስራት መታሰቢያ
በስዊድን የኢሳት እርዳታ ማስተባበሪያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ
የኢሳት መዝሙር ተበረከተ ቅዳሜ የካቲት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. (ፌብሪዋሪ 28 ቀን 2015 ዓ.ም.) በስዊድን የተደረገው የኢሳት መርጃ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለጸ። ዝግጅቱ ከቀኑ ሰባት ሰዓት (13፡ 00) የተጀመረ ሲሆን፣ የዕለቱን ዝግጅት የመሩት ወ/ሮ መቅደስ ወርቁ የስዊድን የኢሳት ድጋፍ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና አቶ በረከት ንጉሱ ነበሩ። በቦታው ላይ ዝግጅቱን ለመካፈል የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን፣ በክብር እንግድነት የተገኙት ደግሞ ታዋቂዎቹ የኢሳት ጋዤጠኞች መሳይ መኮንን እና አበበ ቶላ (አቤ ቶክቻው) እንዲሁም ኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ከተንገላቱት ስዊድናውያን ጋዜጠኞች ውስጥ ዮሀን ፐርሾን ናቸው። ዝግጅቱን በጸሎት የከፈቱ በክርስትና ኃይማኖት በኩል ቄስ ፍስሀ ተስፋዬ፣ ሙስሊሙን በመወከል ደግሞ የተናገሩት ሀጂ ሁሴን ሺፋ ሲሆኑ፤ የጸሎቱ ሥነሥርዓት … [Read more...] about በስዊድን የኢሳት እርዳታ ማስተባበሪያ ዝግጅት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቀቀ
የአድዋ ድልና እኛ
1.መቅድም ይህ የአድዋ 119ኛ አመት መታሰቢያ እኛና አድዋ በተሰኘ ርእሰ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። ድርሰቱ ስድስት ንኡሳን ክፍሎች አሉት። ሁላችንም በጦርነቱ በድሉም ወቅት ስላልነበርን የተጻፈ አንብበን ከምናውቀው አመሳክረን ነው ጽሁፉ የተዘጋጀው። የተጻፈ አንብበን ላልኩት የጳውሎስ ኞኞን ምክር ከልቤ አድርጌ ነው። ጳውሎስ ኞኞ ኢጣሊያና የኢትዮጵያ ጦርነት በሚለው መጽሃፉ እኛ ስለራሳችን ስንጽፍ እናጋንናለን ስለዚህ የውጭ አገር ምእራባውያን የመሰከሩልንን ተጠቅሜያለሁ ይላል። የጳውሎስ አንደኛውን ምክር ከልብ ማድረግ ነው። ሁለተኛ ቢያሳዝንም እውነት ስለሆነ የሰዎች ስም በክፉ ይነሳል፤ አያት ቅድመ አያት ለሰራው ባንጠየቅም የአያቶቻችን ስም ሲነሳ አለመቀየም ነው። ከተቀየማችሁም ምን ይደረጋል ከመጻፍ አይቀርም። ራስ ደስታ ዳምጠው በሁለተኛው የጣሊያን ጦርነት የደቡቡን ውጊያ የመሩ ለጣሊያን … [Read more...] about የአድዋ ድልና እኛ










