ይህ ጽሁፍ በኢትዮጵያ እየተደረገ ያለዉን ዲሞክራሲን ለመመስረት በመደረግ ላይ ያሉትን የትግል ስልቶች መርምሮ ፤ የሁለቱን የትግል ስልቶች ተደጋጋፊነት እና ተቀናባሪነትን አቅርቦ ለዉጥ ለማምጣት አብሮ መስራት አስፈላጊነቱን ያቀርባል። በኢትዮጵያ ያለውን ዘረኛ መንግስት ለማስወገድ የሚደረገው ትግል የተለያዩ ድርጅቶች የተለያዩ የትግል ስልቶች መምረጣቸዉ ይታወቃል። የሁሉም ድርጅቶች አላማ ያለዉን ዘረኛ መንግስት ማዉረድ ቢሆንም፤ የመረጡት የተለያዩ የትግል ስልቶች በድርጅቶቹ መካከል ትብብር እንዳይጎለብት ማድረጉ ግልጽ ነዉ። ዋናዉ የዚህ ጽሁፍ አላማ፤ እነዚህ የትግል ስልቶች ተደጋጋፊ መሆናቸው እና ተቀነባበረዉ የተሻለ የትግል ዉጤት ማምጣት የሚችሉ መሆናቸውን መገንዘብ ያስፈልጋል የሚል ነዉ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” … [Read more...] about በኢትዮዽያ ዲሞክራሲ ለመመስረት የሚደረጉ የትግል ስልቶች ተደጋጋፊነት እና አሰፈላጊነት
Opinions
የኔ ሃሳብ
ከዝምታው በስተጀርባ
አንዳንድ ወገኖች የወያኔ አገዛዝ መቶ በመቶ አሸነፍኩ ያለበት ደረጃ መድረሱ እያበገናቸው፣ በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚደርሰው ጥፋት እያስቆጫቸው የሕዝቡን ዝምታ በፍርሀት ሲገልጹት ይሰማል፡፡ አንዳንዶች እንደውም ገፋ አድርገው በቅርብ ግዜ የታየውን የአረብ አብዮት እየናሱና ተኒዚያና ግብጽን እየጠቀሱ ኢትጵያዊ በምን ያንሳል በማለት በምሬት ይናገራሉ ይጽፋሉ፡፡ የአረብ አብዮት አይነት ሰላማዊ የሕዝብ ተቃውሞና አምቢተኝነት ወያኔ አጥብቆ የሚፈራው፣ ተቀዋሚው ቢሆን የሚሻው፣ የኢትዮጵ ሕዝብ ሊያደርገው የማይችለው ነው፡፡ ሁሉም የየራሳቸው ምክንያት አላቸው፡፡ ወያኔ በሕዝብ አለመወደዱን ማወቁ፣ ለሥልጣኑ መስጋቱና ፍርሀቱ ሲሆን ፤ተቀዋሚው ለውጥ መሻቱ፣ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን መናፈቁ ነው፡፡ ሕዝቡ የማያደርገው ደግሞ ከጥንት እስከ ዛሬ የኖረበት ወግ ልማዱ ስላልሆነ፣ ትናንት ንጉሶች በቅርቡ ደግሞ … [Read more...] about ከዝምታው በስተጀርባ
የኤርትራ ጉዳይ
ለብዙ ኢትዮጵያዊያን፤ የኤርትራ ከኢትዮጵያ መገንጠልና የአገነጣጠሏ ሁኔታ፤ የውስጥ አካላችንን ያኔም፣ አሁንም እያንጠረጠረው ነው። በርግጥ በየኪሳችን ያለ የየግል ንብረት ስለተነጠቀብን አይደለም። በኤርትራ መገንጠል የቀረብን የግል ጥቅም ስለነበረም አይደለም። የሀገር ጉዳይ፤ ከንብረት፣ ከአባትና እናት፣ ከኑሮ የበለጠ ክብር የምንሠጠው ነው። በወቅቱ የቅርብ ጓደኛዬ የነበረ ኤርትራዊ፤ በኤርትራ መገንጠል ፍንደቃው ጊዜ አልሠጥህ ብሎት፤ መኖሬንም ረስቶ፤ ለሳምንታት ከወገኖቹ ጋር ሲጨፍር ከረመ። በመጨረሻም ቀን ቀንን እየወለደ፤ ሳንገናኝ ብዙ ጊዜ አለፈ። መራራቅ መራራቅን ነውና የሚያስከትለው፤ በየጎጣችን ተሸጉጠን፤ በመካከላችን የነበረው ጓደኝነት፤ ጊዜን መቀራረብ አላድሰው አለና ጠፋ። በርግጥ እኔም መላዕክ አልነበርኩም። ልክ ያለሁበት ቤት እንደተቃጠለ፤ በግል ሰው እንደበደለኝ፤ ብሽቀት … [Read more...] about የኤርትራ ጉዳይ
Saluting the greatest Ethiopian “Masinko” man and dissident artist Shambel Belayneh
“Enlighten the people generally, and tyranny and oppressions of body and mind will vanish like evil spirits at the dawn of the day.” -TJ Behold, he is daring, he is a rebel and the fearsome black lion is roaring. “Endyaw zerafewa endeyaw zerafewa, Ye Gondern meret ye humeran meda, Tedanegbet enji mech dagnebet bada. Wede temari bet temeleshi kine, Wendoch kewalubet ewelalhu ene.” Millions of his fans often say Shambel Belayneh is the undisputed successor to the late legendary … [Read more...] about Saluting the greatest Ethiopian “Masinko” man and dissident artist Shambel Belayneh
የኢሳያስ (የሻዕቢያ) ስታራተጂ፤ ኢትዮጵያን ለመታደግ ወይስ እንደገና ለመግደል?
የተለያዩ ድርጅቶች የወያኔ/ ኢህአዴግን መንግስት በትጥቅ ሀይል ለማስወገድ በአስመራ ስልጣን ከያዘው ሻቢያ ጋር መቀራረብና ተባብሮ መስራትን መርጠዋል። ይህን በተመለከተ ባንድ በኩል የወያኔ/ኢህአዴግን የግፍ ስርአት ለማስወገድ ከማንም ጋር ቢሆን ማበር አስፈልጊ ነው የሚሉ ሲኖሩ ሌሎች ደግሞ የወያኔን የግፍ ስርአት ማስወገድ አስፈላጊ ሲሆን ሻዕቢያ ኢትዮጵያን በተመለከተ የሚከተለው ፖሊሲ በብሄራዊ ጥቅማችን ላይ እና በመጻኢው ነጻነታችን ላይ እጅግ ታላቅ አደጋን ስለሚያሰከትል ድንገት ብቅ ያለው ተቋርቋሪነት ከምን የመነጨ እንደሆነ ጠንቅቆ መረዳትና ታላቅ ስህተት ከመፈጸም መታቀብ ያሻል ይላሉ:: በዚህ ጽሁፌ የሻቢያ “ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪነት” በተግባር ሲታይ ምን ማለት እንደሆነ ለማሳየት በጥቂት ውሱን ጉዳዮች ላይ በማተኮር ያለኝን አመለካከት አካፍላለሁ። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ … [Read more...] about የኢሳያስ (የሻዕቢያ) ስታራተጂ፤ ኢትዮጵያን ለመታደግ ወይስ እንደገና ለመግደል?
Je Suis ኢትዮጵያዊ!
ከብሄር ፖለቲካ እንውጣ! የተባበረችውን ኢትዮጵያን እንገንባ! በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ስብሰባ ላይ ጠቅላይ ሚንስትር ኣቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሲናገሩ ኣገራችንን የሚበትኑ ኣጥፊ ዘሮች ያሏቸውን ሶስት ጉዳዮች ኣነሱ። ኣንደኛው ጠባብነት፣ ሁለተኛው ትምክህተኛነት፣ ሶስተኛው በሃይማኖት ሽፋን የሚራመድ ኣክራሪነት ናቸው ኣሉ። በመሰረቱ እነዚህን ጉዳዮች ኣቶ ሃይለማርያም ለመጀመሪያ ጊዜ ያነሷቸው ጉዳዮች ኣይደሉም። በ”ኢህዓዴግ” ውስጥ ብዙ ጊዜ የሚነሱ ሁሌም ሲባሉ የነበሩ ናቸው። ኣቶ ሃይለማርያም ኣዲስ ነገር ኣልተናገሩም። ለማናቸውም ግን እነዚህ ኣደገኛ ዘሮች ከየት መጡ? ኣገሪቱንስ ወዴት እየወሰዱ ነው? በርግጥ ከብሄር ፖለቲካው ኣዝማሪዎች ኣልፎ ወደ ታች ወርዶ የኔብጤው ተራው ህዝብ ኣካባቢ እነዚህ ዘሮች ጎልተው እየታዩ ነው ወይ? የሚለው ጉዳይና ኢትዮጵያ በምግብ … [Read more...] about Je Suis ኢትዮጵያዊ!
ስለ “ጽናት” የቀረበ ተጨማሪ መረጃ
ማሳሰቢያ፡- ከዚህ በፊት ኢንጂነር መሃመድ አባስ በጽናት ዙሪያ ባቀረቡት ዘገባ ከብዙ አንባቢዎቻችን ብዙ ተብለናል፡፡ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ እንደመሆኑ ሕዝብ መረጃ ከማቅረብ ጀምሮ መጦመርና ዜና መሥራት ይችላል፡፡ በዘመናዊው ጋዜጠኝነት የተለመደ አሠራር ነው፡፡ በመሆኑም ባለፈው ከቀረበው መረጃ አኳያ አሁን ደግሞ ደጋፊ የሚሆን የድምጽ መረጃ ከአጭር መግቢያ ጽሁፍ ጋር ልከውልናል፤ እንዲህ ይነበባል፡- “እራሱን ጽናት እያለ በሚጠራው ጀሌ ላይ ላቀረብኩት ጽሁፍና ማስተባበያ ለቀረበበት “ዘረፋ” ግልጽ የሆነ ማስረጃ!” ድምጻችን ይሰማን ለሁለት በመስንጠቅ የህዝበ ሙስሊሙን አንድነት ለመናድ ሀወሃት/ኢህአዴግ እንቅልፍ አጥቶ ማደር የጀመረው ዛሬ እንዳልሆነ ይታወቃል። ህወሃት/ኢህአዴግ የሃይማኖት ነጻነት ትግሉ በተጀመረ ማግስት መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን ዘብጥያ በማውረድ … [Read more...] about ስለ “ጽናት” የቀረበ ተጨማሪ መረጃ
Guddaa saalpaa fariddi guniddaan dhessa
ማስታወሻ፡- ቀጥሎ የምታነቡትን ጽሑፍ በፍቃዱ ኃይሉ በአማርኛና በኦሮምኛ ቋንቋዎች ለአንባቢያን እንዲደርስለት ለነገረ ኢትዮጵያ የላከው ነው፡፡ Dhumnii jaarraa kudha saglaffaa dhuma yeeroo Awuroopaanoonnii ardii Afrikaa hirachuuf murtteeffatan ture. Mootootnii awuuroopaa kan ga’ee isaanii yoommuu fudhatan, ga’een Xaaliyaanii naannawa Itiyoophiyaa tuuree.Weerartoonnii Awuroopha sababni weerarreef ‘’ummata Afrikaa hirriba irra damaqsiinee qaroomsuufii’’ yoo jedhan illee dhugaan yeeroo sanaa garuu kanarraan adda.Sababnii weeraraa innii guddaan … [Read more...] about Guddaa saalpaa fariddi guniddaan dhessa
የመሐል ሀገር ሰው መልዕክት ለትግራይ ሰው!
ማስታወሻ፡- ቀጥሎ የምታነቡት ጽሑፍ በፍቃዱ ኃይሉ ከቂሊንጦ እስር ቤት ለነገረ ኢትዮጵያ የላከው ነው፡፡ ጽሑፉ በአማርኛና ትግርኛ እንዲነበብለት በጠየቀው መሰረት አማርኛው ቀጥሎ ቀርቧል፤ ትግርኛውን ከዚህ በታች ማግኘት ይቻላል፡፡ ትግራይ የኢትዮጵያ ገናና ታሪክ መሬቷ ላይ የተጻፈባት ክልል ናት፡፡ ብዙዎች ‹‹የኢትዮጵያ ራስ ናት›› የሚሉት ለዚህ ነው፡፡ የኢትዮጵያን ታሪክ ወደኋላ 3000 ዓመት የሚያደርሰው የአክሱም ስልጣኔ አሻራውን ትቶ የሄደው በትግራይ ክልል፣ አክሱም ከተማ ነው፡፡ ከአረቦች ተቀድቷል የሚባለውን የንግስተ ሳባ ታሪክ ‹‹ክብረ ነገስት›› በሚባለው መጽሐፍ ተርጉመው ለዚህ ትውልድ ያኖሩልን የትግራይ ሊቃውንት ናቸው፡፡ ሌላው ቀርቶ ህብረ-ብሄራዊ ቅርስ የሆነንን የሳባ ፊደል ለመላው ኢትዮጵያዊ ያወረሱት የትግራይ ሊቃውንት ናቸው፡፡ ከኢትዮጵያዊነት ቀለሞች አንዱ … [Read more...] about የመሐል ሀገር ሰው መልዕክት ለትግራይ ሰው!
ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ
ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። አዎ! ማተቡን ላጠበቀና በአምላኩ ለሚታመን በእርግጥ ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ። ሰዉ ነኝና እንደ ፈጣሪ ቃሌ ሁሉ እዉነት ነዉ ብዬ አለተፈጥሮዬ አላብጥም። ግን ሰዉ ብሆንም ፈጣሪዬን የምፈራ ሰዉ ነኝና ለፕሮፓጋንዳ ፍጆታ ስል ልቦናዬ እያወቀዉ እንደነ ጋሼ እንደልቡ ዉሸት ደርድሬ ለአንባቢ የማቀርብበት ምንም ምክንያት የለም። ከዚህ ቀጥሎ የማስነብባችሁ እያንዳንዱ ቃል እንደ ዳያስፖራ ተረተኞች የምተርተዉ ‘ሰዉ ሰዉ’ የማይሸተት ተረት ሳይሆን ኢትዮጵያ ድንበር ላይ በየግንባሩ የተሰለፉትንና በስልጠና ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አርበኞች ስጎበኝ በአይኔ ያየሁትንና በጆሮዬ የሰማሁትን ቃል ነዉ። ቨርጂኒያ ወደሚገኘዉ “Dulles” አዉሮፕላን ማረፊያ የሄድኩት ከልጄ ጋር ነበር። ከቤቴ Dulles የግማሽ ሰዐት መንገድ ነዉ። ያቺን ግማሽ ሰዐትና አዉሮፕላን ማረፊያ ደርሼ … [Read more...] about ቃል የዕምነት ዕዳ ነዉ










