የአንድ አገር ችግሮች የዛሬ ሁኔታዎች የፈጠሩዋቸው ብቻ አይደሉም። እንዳውም የአብዛኞቹ ችግሮች መነሻ መሠረታቸው ዛሬ ሳይሆን፣ ትናንትና ከትናንት ወዲያ ነው። የወቅቱን ችግሮቹ አስቸጋሪና ውስብስም የሚያደርጋቸውም ይኸው ምንጫቸው ካለፉ ትውልዶች ተያይዘው መምጣታቸው ነው። የዛሬውን የአገራችን ፖለቲከኞች አብሮ ለመሥራት ቀርቶ እንደ ኢትዮጵያዊ ዜጋ ማሰብ ያቃታቸው የለውጥ አራማጅ ነኝ የሚለው ትውልድ ዘርቶት የሄደው «ኢትዮጵያ አገር አይደለችም፤ እንዳውም የብሔረሰቦች እስር ቤት ናት፤» የሚለው አስተሳሰብ ተሸካሚ በመሆኑ ነው። በመሆኑም ዛሬ ትውልዱ ለገጠመው ሁለንተናዊ ችግር መፍትሔ ለመሻት ከልቡ ካሰበና ለዚህም ቆርጦ ከተነሳ፣ ያለፉት ትውልዶች የተከተሉትን ሕዝብን በቋንቋ፣ በሃይማኖትና በማንነት የመከፋፈል አስተሳሰብና አመለካከት አውልቆ መጣልና ኢትዮጵያዊ ማንነትን መቀበል ይጠበቅበታል። … [Read more...] about ካለፉት ድርጊቶች መማር ያልቻለ ትውልድ፣ ለገጠሙት ችግሮች መፍትሔ ማግኘት አይቻለውም!
Opinions
የኔ ሃሳብ
በውጥረት ላይ ውጥረት መደራረብ ይቁም!
ሰሞኑን በኦሮሚያ እና በሰሜን ጎንደር የተከሰተው የተቃውሞ ንቅናቄ ሀገሪቱን ውጥረት ውስጥ ከትቷታል፡፡ አመጹ እየተጋጋለ መሄድ እንጂ የመቀዛቀዝ ባህሪ አላሳይ ብሏል፡፡ አሁንም በልዩ ልዩ አካባቢዎች ቀጥሏል፡፡ በአራቱም አቅጣጫዎች ውጥረት ሰፍኗል፡፡ በህይወት ዘመኔ ይህንን ያህል ዘላቂ ሆኖ የቆየ አመጽ አይቼ አላውቅም፡፡ በዚህ አመጽ ለጠፋው ህይወትና ንብረት እናዝናለን፡፡ በየትኛውም ወገን ሆኖ በትርኢቱ ውስጥ የተሳተፈው የኛው ዜጋ በመሆኑ ነፍሱና አካሉ ታሳዝነናለች፡፡ ታዲያ አመጹ የተከተሰው በመንግሥት ሚዲያ እንደሚነገረው “ኪራይ ሰብሳቢዎች፣ ግንቦት ሰባቶችና ኦነጎች በወጠኑት ሴራ ነው” የሚለው ምክንያት መሰረት የለውም፡፡ እንደዚህ ማለት “ህዝቡ አያገናዝብም፤ በማንም ይታለላል” የማለትን ያህል ነው፡፡ በኤርትራ የመሸጉት ድርጅቶችም ሆኑ “ኪራይ ሰብሳቢ” የሚባሉት የማይታወቁ ሃይሎች … [Read more...] about በውጥረት ላይ ውጥረት መደራረብ ይቁም!
የሰሞኑ “የኦሮምያ ግርግር” ግራ ገብቶኛል
በሁለት ደረጃ የሚቀርቡ ጥያቄዎች አሉኝ፤-- አንድ፡-- ግርግሩ የኦሮምያ ነው? ወይስ የኢትዮጵያ? ወይስ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ ተለይቷል? ሁለት፡-- የኢትዮጵያ የመሬት ጉዳይ ኦሮሞዎችን ብቻ የሚመለከት ነው? ወይስ የኢትዮጵያን ሕዝብ በሙሉ? አንደኛ፣ ግልጽ ከሆነው እውነት እንነሣ፤ ኦሮምያ ከኢትዮጵያ አልተለየም፤ ስለዚህም ግርግሩ የኢትዮጵያ ነው እንጂ የኦሮምያ አይደለም፤ ጥንቱኑ ለማጋጨት የተሰጠውን ስያሜ በስምነቱ ከማጽደቅ በላይ ለታቀደው ዓላማ አመቺ መሣሪያ ማድረግ ነው፤ ይህ ደግሞ በቅድሚያ መሸነፍን የሚያረጋግጥ በመሆኑ ከወያኔ በቀር ደጋፊ ያለው አይመስለኝም፤ ቁርጠኛ ትግል ቁርጠኛ ዓለማና ቁርጠኛ ስልት ያስፈልገዋል፤ ስለዚህም ቁርጠኛ መሪ ያስፈልገዋል፤ የሕመሙን መርዝ እየተጎነጩ ከሕመሙ ፈውስ ለማግኘት አይቻልም፤ ግርግሩ የኦሮሞ ከተባለ ሁለት ውጤቶች ይከተላሉ፤ አንዱ ውጤት … [Read more...] about የሰሞኑ “የኦሮምያ ግርግር” ግራ ገብቶኛል
መሬት ለአራሹ!
በኣስራ ዘጠኝ ስልሳዎቹ ኢትዮጵያ ደምቃ ነበር። የለውጥ ጥም ይዟት ትጮህ ነበር። መቼም በየሃገሩ ኣገራዊ ችግሮችን መልክ ኣስይዞ፣ መሪቃል ወይም መፈክር ኣውጥቶ ለውጡን የሚመራውና የለውጥ ሃይል የሆነው ወጣቱ ሲሆን በተለይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሁሌም ቀዳሚዎች ናቸው። ታዲያ በዚያ የለውጥ ወራት ጊዜ ከነበረው ኣንዱና ትልቁ ጥያቄ የመሬት ላራሹ ጉዳይ ነበር ኣሉ። መሬት ላራሹ! መሬት ላራሹ! መሬት ላራሹ!……… ወጣቱ ድምጹን ኣሰማ ። ኣራሹ ማን ነው? ያውጭሰኛውና መሬት የለሹ ዜጋ ነዋ። በጥቂት የመሬት ከበርቴዎች እየተጨቆነ የሚኖረው የሰፊው ድሃ ህዝብ ግፍ ይብቃ፣ ኣዲስ ዘመን መጥቷልና እናንተ የመሬት ከበርቴዎች ሆይ በቃችሁ። ኣራሹ ገበሬ እጣው በሆነችው በዚህች ኣገር ውስጥ፣ የርስቱ ገመድ በወደቀባት በዚህች ምድር ላይ መሬት ይኑረው ነው ጥያቄው። በርግጥ ይህ ጥያቄ በጥሩና ሳይንሳዊ … [Read more...] about መሬት ለአራሹ!
ለጋራ አላማ ለጋራ ትግል
በኦሮሞ ወጣቶች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም የተጀመረውና በደርዘን ለሚቆጠሩ ዜጎች ህይወት ማለፍ ምክንያት የሆነው እንቅስቃሴ አሁን ባለው አዲስ ሁኔታ በአጀንዳውም በተሳትፎውም እየሰፋ ሲሄድ እየታዘብን ነው፡፡ ለዚህ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ በወያኔ/ኢህአዴግ ግፈኛ አገዛዝ በተሰጠው የጭፍጨፋ ምላሽ የተነሳ ንቅናቄው በአጠቃላይ ቁጣን በተላበሰ መልክ ለዴሞክራሲ ወደሚለው ጥያቄ እየተቀየረ ነው፡፡ እንደዚህ በመሆኑም በአንድ በኩል በዚያው በኦሮምያ ክልል ከተማሪዎቹ ባሻገር ገበሬዎች፣ ሰራተኞች፣ ሴቶችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከትግሉ እየተቀላቀሉ ሲሄዱ በሌላ በኩል ደግሞ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከኦሮሞ ወጣቶች አንድነት ለማሳየት ብቻ ሳይሆን ፍትህና ዴሞክራሲ ለሚለው ለዚህ የጋራ የሆነ አጀንዳ የመንቀሳቀስ አዝማሚያ እያሳዩ ነው፡፡ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለጋራ አላማ ለጋራ ትግል
“ደሞዝ የከፈለ ማዘዝ ይችላል” የሚለው አባባል በፖለቲካ ይሰራል
እንደ ሰላማዊ ትግል ተማሪ ከህዳር ወር መጀመሪያ ግድም አንስቶ እስከ ታህሳስ ወር አጋማሽ 2008 ድረስ የተካሄደውን የኦሮሚያ ተማሪዎች ሰላማዊ ትግል በቅርብ ስከታተል ነበር። የሰላማዊ ትግሉ መልዕክት “የኦሮሚያን መሬት አስመልክቶ የፌደራል እና የክልል መንግስት የወጠናችሁትን እቅድ እናውቃለን ። እኛ ለእቅዳችሁ ትብብር አንሰጠውም፣ አናጸድቀውም፣ እንቃወመዋለን። እኛን እንደ ተመልካች ማየታችሁን አቁማችሁ አዳምጡን። የመሪታችን ባለቤቶች እኛ መሆናችን ተገንዝባችሁ አነጋግሩን፣ በውሳኔ መስጠቱ ሂደት አሳትፉን። የመሪታችን ተጠቃሚነት መብታችንን እወቁ።” የሚል ነበር። ካለምንም ጥርጣሬ፣ ንቀት እና እብሪት ሰልፈኞቹ የሚናገሩትን ላደመጠ እና ያነገቡዋቸውን ጽሑፎች ላነበበ ሰው የሰልፈኞቹ መልዕክት ግልጽ ነበር። ጥያቄው እጅግ በጣም ቀላል ነበር። ምንም ውስብስብነት አልነበረውም። መንግስት … [Read more...] about “ደሞዝ የከፈለ ማዘዝ ይችላል” የሚለው አባባል በፖለቲካ ይሰራል
“ፕሮፌሰር፣ ጄኔራል” ሳሞራ
ረቡዕ በተሰማው ዜና መሠረት የቻይናው ቲያንጂን የቴክኖሎጂና ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ለሳሞራ የኑስ የክብር ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡ ሚያዚያ 1999 የዖጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጪ ግምባር በክልሉ በሚገኝ የነዳጅ ፍለጋ ቦታ ላይ ባደረሰው ጥቃት ከ70 በላይ ንጹሃንን በገደለበት ወቅት ዘጠኝ ቻይናውያን ከሞቱት መካከል ነበሩ፡፡ በትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር አዛዥነት በየጊዜው በዖጋዴን ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ሲቃወም የነበረው ኦብነግ ለወሰደው ድንገተኛ እርምጃ በሟቹ መለስ የሚመራው ህወሃት በክልሉ አምስት ቦታዎች ማለትም በፊቅ፣ ቆራሄ፣ ጎዴ፣ ዋርድሄር እና ደጋሃቡር ዘግናኝ የሆነ የመልሶ ማጥቃት ጭፍጨፋ በነዋሪው ሕዝብ ላይ አድርሷል፡፡ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት (ሂውማን ራይትስ ዎች) ባወጣው ዘገባ መሠረት ኦብነግ ላደረሰው የአጸፋ መልስ እና ታጣቂዎችን ለመደምሰስ … [Read more...] about “ፕሮፌሰር፣ ጄኔራል” ሳሞራ
ሳይቃጠል በቅጠል
በአገራችን በኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ የሕዝብ ትግልና እንቅስቃሴ ሲካሄድ ቆይቷል። ከተካሄዱት ትግሎች ውስጥ የአገርን ነጻነት በማስከበሩ ከውጭ ወራሪ ሃይሎች ጋር የተደረገ የነጻነት ትግል የሚያኮራ ውጤት ሲያመጣ በውስጥ አስተዳደር ዙሪያም ለዘመናት ተንሰራፍቶ የነበረውን ባላባታዊ ስርዓት ለመለወጥ የተደረገ ትግል ሙሉ ለሙሉም ባይሆን መለስተኛ ድሎችን አስመዝግቦ አልፏል። ከአርባ ዓመት በፊት በተፈጠረለት አጋጣሚ ለአስራ ሰባት ዓመት በስልጣን ላይ በቆየው፣ በአምባገነኑ የደርግ የገዳዮች ስርዓት ላይ ያነጣጠረ ለሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ ለውጥ የተደረገው ህብረብሔራዊ እንቅስቃሴ ከሽፎ በውጭ ሃይሎች የታገዘ አገር አፍራሽ የሆነ ሃይማኖትንና ጎሳን (ብሔርን) ያማከለ ታጣቂ የጎሳ ስብስብ ስልጣኑን ቀምቶ እስከአሁን ለመቆየት ችሏል። ምንም እንኳን ሕብረብሔሩ ትግል በገጠመው ውስጣዊና ውጫዊ … [Read more...] about ሳይቃጠል በቅጠል
“ቅማንት ዐማራ፣ ዐማራም ቅማንት ነው”
ቅማንት እና ዐማራ የተባሉት ነገዶች ለዘመናት አብረው ኖረዋል። አብረው በመኖራቸው ብዛትም በረጅሙ የአገራችን የመዋሐድ እና የመቀላቀል ሂደት አንድ ሆነዋል። ስለዚህ እኒህ ሁለት ነገዶች በጊዜ ሂደት የጋራ ኃይማኖቶች ተከታዮች፤ አንድ መግባቢያ የአማርኛ ቋንቋ፣ አንድ የጋራ አገር እና መልከዐምድራዊ መለያ፣ ከዚህም በላይ አንድ የነፃነት ታሪክ ባለቤት ለመሆን በቅተዋል። በመሆኑም የወል የሆነ ማኅበራዊ ሥነልቦና መስርተዋል። በዛሬው ዘመን የነገዶቹን ተወላጆች ሁለንተናዊ ማንነትን መነሻ አድርጎ ለመለያየት መሞከር፣ ውኃ እና ወተት ከቀላቀሉ በኋላ እንደገና ለመለየት እንደመሞከር ይቆጠራል፥ ውሕድ አካል ሆነዋልና። ሆኖም የትግሬ-ወያኔ ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትን እና ዐማራን ለማጥፋት ላለው ረጅም ዕቅድ ብቸኛ ማሳኪያ መንገድ አድርጎ የወሰደው የ«ከፋፍለህ ግዛው» ሥልትን ነው። የዚህ ሥልት … [Read more...] about “ቅማንት ዐማራ፣ ዐማራም ቅማንት ነው”
ማፈናቀል እንደገንዘብ
ከ1966 ዓ.ም. በፊት መሬት አገር ነበር፤ ከዚያ በኋላ እስከ 1983 መሬት የጋራ ሀብት ሆነ፤ ከ1983 ወዲህ መሬት ገንዘብ ሆነ፤ ጡንቻ ገንዘብ ሆነ፤ መሬት ጡንቻና ገንዘብ ሆነ፤ አገር የት ደረሰ? በጡንቻ ሀብታም መሆን ይቻላል፤ በጡንቻ ገበያውን መቆጣጠር ይቻላል፤ በጡንቻ ሻጩን መቆጣጠር ይቻላል፤ በጡንቻ ገዢውን መቆጣጠር ይቻላል፤ ገበያውን፣ ገዢውንና ሻጩን መቆጣጠር ከተቻለ ዋጋውን መቆጣጠር ይቻላል፤ እዚህ ደረጃ ላይ ከተደረሰ ምሥጢሩ ግልጽ ይሆናል፤ ምሥጢሩ ምንድን ነው? ዋናው ነገር ጡንቻ ነው፤ ጡንቻ የሀብት ምንጭ ነው፡፡ ጡንቻ ካለ ተማሪ ቤት ወይም ሀኪም ቤት፣ ወይም አንድ መሥሪያ ቤት ለመሥራት በሚል ሰበብ አንድ መቶ ቤተሰቦችን ከኑሮአቸው ማፈናቀል ሕጋዊ ያሆናል፤ አንድ መቶ ቤተሰቦች ሰፍረውበት የነበረው በአማካይ በነፍስ ወከፍ 100 ሜ.ካ. መሬት ነው እንበል፤ አንድ … [Read more...] about ማፈናቀል እንደገንዘብ










