መገናኛ ብዙሃንን መቼ እና እንዴት መጠቀም እንዳለበት ጠንቅቆ ያውቃል። የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ከፈጸመ በኋላ ግን እንደ በረሃ ተኩላ እያደፈጠ ይናከሳል። ሲናከስ ደግሞ ማንንም አይምርም። ውለታ የሚባል ነገር አያውቅም። ይሉኝታ አይነካካውም። እፍረትም በእርሱ ዘንድ የለችም። ከቶውን መቀበል እንጂ መስጠትን አያውቅም። አስር ተቀብሎ በዜሮ የሚሸኝ ጀግና ነው። በዚህ ተግባሩ አድናቂው ነኝ። “እኔ-ነኝ” ያለ የዲሲ ፖለቲከኛን ሳይቀር ከአንዴም ሁለቴ እንደማስቲካ እያኘከ መትፋቱን እንመሰክራለን። የጡት አባቱ የሆነው ኦነግንም ቢሆን "A Critical Assessment of the Oromo Liberation Front” በሚለው መጣጥፉ እንዳይሆን እንዳይሆን አድርጎ የጠረበ ፍጡር ነው። ይህ ሰው እንደገና ተመልሶ የ”ነፍጠኛውን ሚድያ” ለመጠቀም የማይሞክርበት ምክንያትም የለም። ጃዋር … [Read more...] about የጃዋር መሃመድ ቅኝቶች
Opinions
የኔ ሃሳብ
ያገር ያለህ!!! የዳኛ ያለህ!!!
1/ መግቢያ በድሮ ጊዜ ሰው በሰው ሲበደልና ፍትሕ ሲጓደል ‘ያገር ያለህ’ ወይም ‘የዳኛ ያለህ’ በማለት ይጮህ ነበር፤ ይህ ዓይነቱ የተበዳይ ጮኸትም ለትውልድ መርገም እንዳይሆን ተብሎ በአካባቢው በሚኖሩ እድሜና ልምድ ጠገብ ሺማግሌዎች ገላጋይነት/ዳኝነት የበደለ እንዲክስ የተበደለ ደግሞ እንዲካስ በማድረግ ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ይደረግ ነበር፤ እኔም ዛሬ በዲሞክራሲ ስም በምድራችን ውስጥ እየሆነ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ /በተለይ ባለውለታ በሆነችው በኦርቶዶክስ ቤ/ክ ውስጥ/ ቀረብ ብየ ስመለከት ይህ እውነተኛ የፍትህ ፈላጊዎች ያገር ያለህ ጩኸት ትዝ ብሎኝ ለኢትዮጵያውን በሙሉ ለውይይትና ለመፍትሄው ፍለጋ ጭምር የሽማግሌ ዳኞች ያለህ በማለት ጮኸቴን ላቀርብ ተገደድኩ። መቸም ለተወሰኑ ዓመታት ከአገሩ ራቅ ብሎ ለኖረ ኢትዮጵያዊ የአዲስ አባባ ገጽታ ቀየር እንደምትልበት ይታመናል፤ … [Read more...] about ያገር ያለህ!!! የዳኛ ያለህ!!!
ከድጡ ወደ ማጡ፣ አሰብ በአረቦች እጅ ገባች
የአገራችን አንድነትና ብሎም ሕልውና በቋፍ ባለችበት በዚህ ቀውጢ ወቅት ውይይቱ ሁሉ ማተኮር ያለበት ለሥጋቶቹ ምንጭና ምክንያት ስለሆኑት ስለ ዴሞክራሲ ደብዛ መጥፋት፣ ስለፍትህ መቅጨጭ. በብሔረሰቦች መካከል ስለሚታዩት ጥላቻና ግጭቶች እነዚህን የወለደው ሥርዓት ስለመለወጥ ብቻ መሆን አለበት ሌላው ሁሉ ገብስ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፡፡ ከእነዚህ ውጭ በሆኑ ጉዳዮች መነጋገር ሥርዓቱን ለውጦ ዴሞክራሲና ፍትህ ለማስፈን በሚደረገው ትግል ላይ ቀዝቃዛ ውሃ እንደመቸለስ አድርገው ይቆጥሩታል፡፡ ሆኖም ዘላቂ የአገር ጥቅሞችን መዘንጋት የኋላ ኋላ ሕልውናን ወደ መፈታተን ደረጃ ሊደርሱ ይችላሉ አገር ከሌለ ዴሞክራሲ ምን ሊፈይድ ፍትህስ ምን ሊረባ? ምናልባት የአገር ሕልውናን እስከመፈታተን ሊደርሱ ከሚችሉ ከዋነኛ የአገር እሴቶች አንዱ የባህር በር አለመኖር ነው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ሁኔታ በማይጨው … [Read more...] about ከድጡ ወደ ማጡ፣ አሰብ በአረቦች እጅ ገባች
የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
መጽሔቱን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ መጽሔት
ጊዜ በማያደበዘዝው የአድዋ ድል ማግስት…
የዓለም ህዝብ ሁሉ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን ድል ያደረገውን የጥቁር ጦር መሪ አጤ ምኒልክን ለማወቅ እጅግ ጓጓ፡፡ ምስላቸውን ለማየት ተቁነጠነጠ፡፡ ሙሉ ታሪካቸውን ለመስማት ተንሰፈሰፈ፡፡ ይህንኑ ተከትሎም፤ "እንኳንም ደስ አለዎት" ለማለት ከቁጥር የበዙ ደብዳቤዎች ይጎርፉላቸው ነበር፡፡ ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ በፖስታ ቤት በኩል የኢትዮጵያ ቴምብር የተለጠፈበት መልስ እንዲላክላቸው ይጠይቁ ነበር፡፡ ለምን… ? ቴምብሩ ላይ ያለውን የምኒልክን መልክ ለማየት፡፡ ባለ ብዙ ዝናና ክብር ባለቤት የሆኑትን የምኒልክን ጥቁር ፊት ለማየት፡፡ የሰው ሀገር ሰው ሁሉ፤ "ዝናውን እንደሰማሁ መቼ ሄጄ ባየሁት"፣ "በጀግንነቱ እንደ ተማረኩ መች ተጉዤ ባገኘሁት"፣ "ካሁን ካሁን ፈቅዶልኝ ወታደር ሆኜ ባገለገልኩት" ያለላቸው አጤ ምኒልክ የኛ ናቸው፡፡ በዓለም ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነጭን ያንበረከከ … [Read more...] about ጊዜ በማያደበዘዝው የአድዋ ድል ማግስት…
ፍቅር እና የትብብር መንፈስ የታየበት ጉባኤ
በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካና ማህበራዊ ቀውስ አስመልክቶ እሁድ ፌብሩዋሪ 14 ቀን፣ 2016 ከቀኑ 2:00pm 7:30 pm በሳን ሆዜ ከተማ ማሶኒክ ሴንተር፤ የተጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ አራት ተናጋሪ እንግዳወች፣ የእምነት አባቶች፣ እንዲሁም ከተለያዩ የሰሜን ካሊፎርኒያ ከተሞች የመጡ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት ሲሆን ከፍተኛ የሐገር ፍቅር ስሜት እና የትብብር መንፈስ በታየበት ሁኔታ ተጠናቋል። አዘጋጅ ኮሚቴውን ወክለው ስብሰባውን የመሩት ዶ/ር አበበ ገላጋይ፤ የውይይቱ ትኩረት ለሱዳን ስለተሰጠው የሀገራችን ለም መሬት፣ በወገናችን ላይ ስለደረሰው የድርቅና የረሀብ አደጋ፣ ስለሰብአዊ መብቶች መጣስ፡ የህዝብ መፈናቀል እና የኢትዮጵያ ህዝብ የአብሮነት ትስስሮች ላይ መሆኑን ገልጸው፤ አላማውም በተለያዩ ምክንያቶች የተራራቀውን ማህበረሰባችን በማቀራረብ የጋራ ችግሮቹን በጋራ ተወያይቶ … [Read more...] about ፍቅር እና የትብብር መንፈስ የታየበት ጉባኤ
በሪሞት ኮንትሮል ትግል መምራት አለመቻልና ሕብረት በዲያስፖራ
የአዲስ ድምጽ ሬዲዎ ጃንዋሪ 17.2016 3 ሰዎችን፤- 1ኛ. ዶ/ር አረጋዊ በረሄን የትግራዮች ለደሞክራሲያዊ ትብብር ሊቀ መንበር፤ 2ኛ. ዶ/ር በያን አሶቦን ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር 3ኛ/ አቶ ተክሌ የሻውን ከሞረሽ ወገኔ የአማራ ድርጅት አቅርቦ በኢትዮጵያ ጊዜያዊ ሁኔታ ላይ አወያይቷቸው ነበር። በቅድሚያ አቶ አበበ የተዋንያኑ አመራረጥ የተዋጣለት ስለ መሆኑ ያለኝን አድናቆት ልገልጽለት እወዳለሁ፤ እነሱም ለዚህ መልካም ተግባር ዝግጁ ሆነው መገኘታቸው የሚያስመሰግን ነው። እኔ ታዲያ ያንን ሰፊ ውይይት ለመተቸት የተነሳሁ አይደለሁም፤ ሀሳብ ልሰጥበት በርዕሰ ስላስቀመጥኩት ጉዳይ መዳረሻ የሚሆነኝን ያህል ብቻ ቀንጨብ አድርጌ ለመያዝ ነው። አስተናጋጁ ለሁሉም ያቀረበው የጋራ ጥያቄ፤ "ባሁኑ ሰዓት ብዙዎቻችንን እያበሳጨ ያለው በጣም በየጊዜው የተደረገ ነገር ነው፤ አዲስ ነገር … [Read more...] about በሪሞት ኮንትሮል ትግል መምራት አለመቻልና ሕብረት በዲያስፖራ
ኢትዮጵያ ሀገራችን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ልጇን አጣች
በሰብአዊ መብት ተሟጋችነታቸው፣ ለሰላምና ለዲሞክራሲ መስፈን ታጋይነታቸው የሚታወቁት ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ዶ/ር ማይገነት ሽፈራው ስለ ሰላም የሰበኩ ያስተማሩና የጻፉ ቀንዲል ኢትዮጵያዊ ነበሩ። ድህነትና በሽታ፣ ርሐብና ስደት፣ አምባገነንትና ጦርነት እያለ የኢትዮጵያ ሴቶች መብት መከበር፣ የሰብአዊ መብት መረጋገጥ፣ ዲሞክራሲና ሰላምን ማስፈን አይቻልም በሚል እምነታቸው በጽናት ታግለው ያታገሉ የዘመናችን ጣይቱ ነበሩ። የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፣ የመናገር የመጻፍ የመሰብሰብ የመደራጀትና በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞን የማሰማት መሠረታዊ መብቶች እውን እንዲሆኑ እንዲሁም ለኢትዮጵያ ሕዝብ ሰብአዊ መብት መከበር፣ ለሃገራችን ሰላም፣ የሃገራችን የፖለቲካ ችግር በዲሞክራሲ፣ በመቻቻልና በሰከነ ውይይት እንዲፈታ፣ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ እድሜያቸውን ሙሉ ታግለው ያታገሉ … [Read more...] about ኢትዮጵያ ሀገራችን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ልጇን አጣች
የጥቁር ሕዝብ ኩራት!
መጪውን የአድዋ ቀን ስናስብ “እምዬ ምኒልክ ምን ዓይነት ውርስ ትተውልን ሄዱ?” ብለን እንድንጠይቅ የሚያደርገን ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ጦርነት ለመግባት ሳይፈልጉ “በግድ” ወደሄዱበት የጣሊያን ጦርነት መለስ ብለን የሆነውን እንድናስብ ወደድን፡፡ ክተት፡- “እግዚአብሔር በቸርነቱ እስካሁን ጠላትን አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ፡፡ እኔም እስካሁን በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛሁ፡፡ እንግዲህ ብሞትም ሞት ለሁሉ ነውና ስለ እኔ ሞት አላዝንም፤ ደግሞ እግዚአብሔር አሳፍሮኝ አያውቅም፤ እንግዲህም ያሳፍረኛል ብዬ አልጠራጠርም፡፡ አሁንም አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ ጠላት እግዚአብሔር የወሰነልንን የባሕር በር አልፎ መጥቷልና እኔም ያገሬ ከብት ማለቁንና የሰዉን መድከም አይቼ እስካሁን ዝም ብለው ደግሞ እያለፈ እንደ ፍልፈል መሬት ይቆፍር ጀመር፡፡ አሁን ግን በእግዚአብሔር ረዳትነት … [Read more...] about የጥቁር ሕዝብ ኩራት!
ተሰማ ናደው
ለዛሬ የማስታውሳቸው በዚህ ምስል ላይ የሚታዩት የአደዋ ጀግና የአጤ ምንሊክ ታማኝ የጦር አዝማች አቤቶ ልጅ እያሱ ባውሮጳ አቆጣጠር1913 ዘውድ ሲጭኑ እንደራሴ ወይም የቅርብ አማካሪ በመሆን ያገለገሉት ራስ ተሰማ ናደው ናቸው ። በተጨማሪ ራስ ተሰማ እቴጌ ጣይቱ ከምንሊክ ቤተ መንግስት ለቀው እንጦጦ ጋራ ላይ ካለው ዕልፍኝ ውስጥ ከቅጥር ግቢው እናዳይወጡ ታግደው እንዲቀመጡ ካዘዙት መኳንንቶች አንዱ ናቸው። ይህ ድርጊት በእቴጌ ጣይቱ ላይ የተፈጸመው እቴጌ ብልህ ስለነበሩ ከሌሎች ሃይሎች ጋር ተባብረው ልጅ እያሱን ከጥልጣን ያወርዳሉ በሚል ፍራቻ ነበር። ራስ ተሰማ በ1916 ዓም ላይ በራስ ተፈሪ እና ልጅ እያሱ መካከል በተደረገው የሰገሌው የዘውድ ሽኩቻ ጦርነት ላይ ተሳትፈዋል። (ምንጭ: Eduardo Byrono ፌስቡክ ገጽ) … [Read more...] about ተሰማ ናደው










