Opinions
የኔ ሃሳብ
“ታህሳስ 5 ከሰአት በኋላ ለመገደል ፈርሜአለሁ”
ታህሳስ 5 ከሰአት በኋላ ለመገደል ፈርሜአለሁ ገጽ 410 ይላል የስደተኛው ማስታወሻ፤ አቶ ተስፋዬ ገብረአብ "ጓደኛዬ" የሚለው ሆላንዳዊ ስለያዘው የሞት ቀጠሮ ሲያብራራ፤- ለሚቀጥለው … ማስታዉሻ መጽሀፉ ይረዳው ዘንድ ሆላንድ ውስጥ የሞት ቀጠሮ እንዴት እንደሚያዝ ከዚህ በታች አብራራለሁ፤ ከዚያ በፊት ግን ስለ ስደተኛው ማስታወሻ የምለው ከዚህ የሚከተለውን ነው፤ ጫልቱ ብሎ የሰየማትን ተዋናይ እዛው የቡርቃ ዝማታው ላይ ቢከታት ኖር ገጸ ባህርይዋ ከዛ ጋር ይሰምርለት ነበር፡፡ ነገር ግን ከአለቆቹ የደረሰው ትእዛዝ አማራና ኦሮሞን ማፋጀት የኢትዮጵያን ስማ ማጥፋት በመሆኑ የግድ መካተት ነበረባት፤ በጎሳ እምነት የተለከፉ ሰዎች አመለካከታቸው ወደሌላ ሰውነት እንደተሰራጨ ካንሰር ነው፤ ቢነግሩአቸው ቢያስረዷቸው አይጠሩም፤ የተስፋዬ ገብረአብ ተማሪዎች በቀደም ሳውዲ አረቢያን ተቃውሞ ሰልፍ ላይ … [Read more...] about “ታህሳስ 5 ከሰአት በኋላ ለመገደል ፈርሜአለሁ”
አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ ሁለት
አበሻ ድግስ ይወዳል፤ ድግስ የሚወደው መብላትና ማብላት ስለሚወድ ነው፤ ለመብላት የአበሻ ምክንያቱ ብዙ ነው፤ ልጅ ተወለደ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ክርስትና ተነሣ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ አገባ ብሎ መብላት ነው፤ ልጅ ሞተ ብሎ መብላት ነው፤ አበሻ ሰው ቀብሮ ሲመለስ በንፍሮ ይጀምርና ቀስ በቀስ ወደሌላው ይተላለፋል። ሃይማኖትም ቢሆን ለመብላት ካልሆነ የነፍሱ ጉዳይማ በጣም ሩቅ ነው፤ ሕያዋን ለነገሥታት፣ ሙታን ለካህናት ይገብራሉ፤ በሚለው መመሪያ መሠረት ግብር መቀበል ያለ ነው፤ ክርስቶስ ተወለደ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ተጠመቀ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ሞተና ተቀበረ መብላት ነው፤ ክርስቶስ ተነሣ መብላት ነው፤ ማርያም አረገች መብላት ነው። ማኅበርም የሚጠጣው (የሚበላው ለማለት ነው፤) ለመብላት ነው፤ አምላክ በተለያዩ ስሞቹ፣ ቅድስት ማርያም በተለያዩ ስሞችዋ፣ መላእክት፣ ቅዱሳን፣ … [Read more...] about አይ አበሻ! አበሻና ሆድ፤ ሁለት
ከሰማይ የራቀችው ምድር ከምድሪቱ የራቀው ሰማይ
ከጥቂት ጊዜያት ወዲህ ‹‹መንግሥት›› ስደትን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ባልነበረው ትኩረት ያስቆጨውና ያሳሰበው መስሎ በመታየት በሕዝብ የብዙኃን መገናኛዎች የተለያዩ ዲስኩሮችን እያደረገ ይገኛል ፡፡ ሲጀመር ገዥው ፓርቲ (ቡድን) የዜጎችን ስደት በተመለከተ ማንነቱን አሳምሮ ለሚያውቀው ሕዝብ ምንም የማለት የሞራል (የግብረ-ገብ) ብቃት ጨርሶ አልነበረውም፡፡ ራቅ ካለው ታሪኩ እስከ ቀረብ ካለው ከዚያም እስከአሁን ካለው ታሪኩ አሁን ባለበት ሁኔታም ተስፋ የሚሰጥ ምንም ነገር ባለመኖሩ ነገም ከሚኖረው ታሪኩ ስንመለከት ይሄንን ክስ የሚያስተባብል ሆኖ አናገኘውም ፡፡ ከዚህ አንጻር ትኩረቱን በጣም አጥቦ በአራቱም አቅጣጫዎች በእግር እግራቸው ወደ አመራቸው በሚሰደዱ ታዳጊ ሕፃናትና ወጣቶች ላይ ማድረጉ በቦሌ በኩል በተለያየ ጫና ፣እንግልትና ውክቢያ ሳይወዱ ሀገራቸውን ጥለው በሚሰደዱት፤ ሕዝቡ … [Read more...] about ከሰማይ የራቀችው ምድር ከምድሪቱ የራቀው ሰማይ
ለነ ድንጋይ ልቡ
ካላየህ ከልነበርክ ሕሊና ከሌለህ፣ ግድ የለም ይመችህ፤ ወሬህን አሳምር አፊዝ እሞቀህ ቤት፣ ቁስሉ የሰው ነው እንጨት ስደድበት፤ አንድ ቀን ጀንበርህ የጠለቀች ዕለት፣ እስቲገለጽልህ ያለህበት ሌሊት፤ (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ለነ ድንጋይ ልቡ
አቶ ታምራት ላይኔ እንዳደመጥኳቸው
የቀድሞው የኢትዮጵያ የሽግግር ዘመን ጠቅላይ ሚኒስትር ኋላ ላይ ደግሞ የኢፊድሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ታምራት ላይኔ ከአውስትራሊያዊው የኤስ.ቢ.ኤስ የአማርኛ ራዲዮ ባልደረባ ጋዜጠኛ ካሳሁን ሰቦቃ ጋር ያደረጉትን በሶስት የተከፈለ ሰፊ ቃለመጠይቅ በአንክሮ ተከታተልኩት:: አቶ ታምራት ብዙ ነገሩን፤ ብዙ ደበቁንም:: ከምንም በላይ አቶ ታምራት በረጋ አንደበት ከቁጣ እና ከብስጭት የጸዳ ቃለምልልሳቸውን በዚህ አጋጣሚ ሳላደንቅ አላልፍም:: እርግጥ ነው ቃለመጠይቁ ሰፊ ቢሆንም በደምሳሳው አቶ ታምራት በመለስ ዜናዊ ተታለልኩ የሚል ቃና ያለው መልዕክት እንዳስተላለፉ ነው የተረዳሁት:: ከምንም ነገር በላይ አሁን ከሚከተሉት ሃይማኖት ጋር አያይዘው ቢሆንም ኮሚኒዝም አንደርዮት አለም በፍጹም የስሕተት እና የጥፋት መንገድ አንደነበር በአደባባይ መናገራቸው ለኔ ታላቅ ቁም ነገር ሁኖ … [Read more...] about አቶ ታምራት ላይኔ እንዳደመጥኳቸው
የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ
1. መግቢያ ከደርግ የ17 አመታት የአገዛዝ ውደቀት በኋላ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ኃይሎች በስፋት ሲንጸባረቁ ከነበሩ ጥያቄዎች መካከል የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ ዋነኛው ነው:: በዚህ ወቅት ውስጥ ለብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄ በፖለቲካ ኃይሎች የቀረቡት የመፍትሔ ሃሳቦች የተለያዩ ቢሆንም የመፍትሔ ሃሳቦቹ የሚመነጩት ግን በዋናነት ከሁለት ተገዳዳሪ አስተሳሰቦች ነው:: አንደኛው አስተሳሰብ የሚያጠነጥነው የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄው የሚካትተው ከኢትዮጵያ ዘመናዊ የሃገር ግንባታ ጋር ተያይዞ የተፈፀሙ ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነትንና በደሎችን እንዲሁም በያ ትውልድ ውስጥ የተፈፀሙ መጠፋፋትን አካቶ ሁሉን-አካታች መድረክ በማዘጋጀት ያለፈውን በደሎች ዕውቅና በመስጠት በፖለቲካ ሊህቃን መካከል መግባባትን ማስፈንን ነው:: ሁለተኛው አስተሳሰብ የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄን የሚመለከተው ኢትዮጵያን እንደ ሀገር በአዲስ መሰረት … [Read more...] about የብሔራዊ ዕርቅ ጥያቄና ፈተናዎቹ በኢትዮጵያ
መንግስት – ስደት – ውርደት
ጀርመን አገር የምትታተመው ጥላ መጽሔት 8ኛ እትም ለንባብ በቅታለች። ለወቅታዊው ሁኔታም ልዩ ትኩረት ሰጥታለች። የሽፋን ስዕሉም ሙሉ ገፁን ለዚሁ ጉዳይ አውሎታል። (ሙሉውን መጽሔት ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about መንግስት – ስደት – ውርደት
የትምህርት ተቋማት የእውቀት ወይስ የፖለቲካ ሜዳ!?
ትምህርት ዜጎችን ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ በመቅረጽ ለራሳቸው፣ ለማህበረሰባቸውና ለሃገራቸው ጠቃሚ ዜጋ እንዲሆኑ የሚያግዝ የእውቀት ማሸጋገርያ ስልት ነው፡፡ ዛሬ በስልጣኔ የገሰገሱ የአለም ሀገራት የዕድገታቸው ዋነኛ መነሻ ትምህርት ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ነው። ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ የአገልግሎት ፓኬጅም ሆነ ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች በዘመናዊ አኳሃን እንዲመነደጉ ከተፈለገ በተግባር የታገዘ፣ ፈጠራና ክህሎትን የሚያዳብር ጥራት ያለው ትምህርት እጅግ ወሳኝ ነው፡፡ የትምህርት መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ መጣል ከጀመረ ከመቶ ዓመታት በላይ የተቆጠረ ሲሆን ከሁለተኛው አለም ጦርነት በፊት ትምህርት የሚሰጠው በመንግስትና በሃይማኖት ተቋማት ዙርያ ለአስተዳደራዊ ክህሎት፣ ለቀኖናና ለሃይማኖት እውቀት ሲባል እንደነበረ ጥናቶች ይገልጻሉ፡፡ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት በኋላ የአፄ ሃይለ ስላሴ ስርዓት … [Read more...] about የትምህርት ተቋማት የእውቀት ወይስ የፖለቲካ ሜዳ!?
ሞት፣ ወያኔና “እኛ”
የግፍ ጽዋው ሞልቶ፣ …… ሞልቶ፣….. ሞልቶ ፈሶ ሰው መባል በሰው፣ ስዕብናችን አሶ ከ'ጥናፍ- እስከ-አጥናፍ፣ ደማችን “'ረክሶ’’፤ ውቅያኖስ፣ ባህሩን፣ ወንዙን አደፍርሶ እዩት ይ'ጣለላል፣ አስፋልቱን አልብሶ። ግን እኮ፣ …….. እንኳ’ ደም ውኃ ፈሶ፣ አይቀርም ይዘገያል እንጂ፣ በሰፈሩት ቁና፣ መሰፈር አይቀርም:: '' ዓለም የም'ጠፋው፣ ሰይጣናዊ ምግባር በሚፈጽሙ ሳይሆን፤ ምንም ሳያደርጉ ቀጭ ብለው በሚመለከቷቸው ሰዎች ነው።" /አልበርት አነስታየን/ እናም የምድርን የሰቆቃና የሞት አይነት ሁሉ እያስከፈሉን፣ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊያንን እያጠፉ ያሉት፣ ወያኔ/ሻአቢያ፣ ሳውዲ አረቢያ/ አረቦች፣ ምእራቡ ዓለም፣ ወይም ሌላ ሳይሆን፣ እኛ እራሳችን ቁጭ ብለን የምንመለከተው ወይም ለታይታ የምንታይው፣ ኢትዮጵያዊያኖች ነን። እኛ ነን….. በሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን … [Read more...] about ሞት፣ ወያኔና “እኛ”










