ውድ አንባብያን፣ ይህ ጽሁፍ ከዚህ ቀደም ከዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ጋር ተስፋዬ ገብረአብን አስመልክቶ አወጥተን ከነበረው ሪፖርት ጽሁፍ ተከታይ ነው። በዚህ መሰረት ከተስፋዬ ገብረአብ ጋር አብረን ስንኖር እጄ ላይ ከወደቁትን መረጃዎች መሃከል የመጀመሪያው ጽሁፍ ተከታይ ይሆናል ብዬ የመረጥኳቸውን ቃል በገባሁት መሰረት ከነማብራሪያቸው አቀርባለሁ። ለዛሬ የማቀርበው መረጃ ተስፋዬ ገብረአብ እንደ ሸፋን ከሚጠቀምበት የደራሲነት እና የጋዜጠኘነት ስራ ባሻገር ለማመን በሚያዳግት ይሰራ የነበረውን የወንጀል ድርጊት ፍንትው አድርጎ ያሳያል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ:: አለማየሁ መሰለ ከህብር ሬዲዮ ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ ለማዳመጥ እዚህ ላይ ይጫኑ) ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ በዚህ ጉዳየ ላይ ዳኛ ወልደሚካኤል መሸሻ ካወጡት ዘገባ ጋር በማያያዝ ተስፋዬ ገ/አብ እንደ … [Read more...] about ጊዜ መስታወቱ!! ተስፋዬ ገብረአብ ማነው?
Opinions
የኔ ሃሳብ
ኳሱ በማን እጅ ነው?
ከአምስት ወር በፊት የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የአዲስ ዓመት የሥራ ዘመን መጀመር አስመልክቶ በጋራ ባአካሂዱት ጉባዔ አዲሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመም ፕሬዚዳንታዊ የመክፈቻ ንግግር ማድረገቸው የሚታወቅ ነው፡፡ የፕሬዚዳንቱ የንግግር ይዘት መንግሥት በ2006 ዓ.ም. ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባሮች ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የፕሬዚዳንቱ ንግግር በሕግ መንግስቱ በተሰጣቸው ሥልጣንና ተግባር መሠረት የተደረገ ንግግር ስለመሆኑ የሚያመላክት አንዳችም ነገር አላየሁበትም፤ በመሆኑም የፕሬዚዳንቱ ንግግር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢነገር የተሻለ ይሆን ነበር ግን በሁለቱም ቢነገር ውጤቱ ዉሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ባቀረቡት የመክፈቻ ንግግር ላይ ሊካተቱ የሚገባቸው ነገር ግን ያልተካተቱ፣ እንዲሁም … [Read more...] about ኳሱ በማን እጅ ነው?
ሁሉም አይነት አክራሪ መስመሮች ይጎዱናል!!!
(ይህንን ጽሁፍ በከፊል ከሁለት ዓመት በፊት በ16-08-2011. "ሁለቱም መስመሮች ይጎዱናል" በሚል አርዕስት አውጥቼው በተለያዩ የኢንተርኔት ድኅረ ገጾች ተነቦ የነበረ ቢሆንም፣ አብዛኛው ጽንሰ ሃሳብ፣ ሰሞኑ እየተካሄደ ካለው ጽንፈኛ የጎጥ ፖለቲካ ጋር፣ ብዙ ተያያዥነት ያለው ስለሆነ፣ አንዳንድ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር የማይሄዱትን አስተካክዬ፣ ካሁኑ ሁኔታ ጋር አያይዤ ነው ያቀረብኩት፡፡ ፒዲኤፉ ብቻ ስለሆነ በእጄ የቀረውና ከፊሉን ማረም ስላልቻልኩኝ፣ ስለጥራቱ አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡) ሰሞኑን በዲያስፖራ የፓልቶክ የውይይት መድረኮች፣ የአጼ ሚኒሊክንና እና ቴዲ አፍሮን በሚደግፉና በሚቃወሙ፣ በመቶዎች በሚቆጠሩ ታዳሚዎች መሃከል ይካሄድ የነበረውን ውንጀላና፣ መከላከልን እኔም ለጥቂት ቀናት እያዳመጥኩኝ ስከታተል፣ ሁኔታው እንዳሳዘነኝ የገባት ባለቤቴ፣ ወንበሯን ስባ ተጠግታኝ፣ እሷም … [Read more...] about ሁሉም አይነት አክራሪ መስመሮች ይጎዱናል!!!
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ወጣቱ ትውልድ ራሱን ከፅንፈኞች ማራቅ ታሪካዊ ግዴታው ነው !
ከጠባቦችና የግንጠላ አራማጆቸ ጎራ እንደሚስተጋባው ከንቱ ታሪክ አገራችን ኢትዮጵያ በድንገት የዛሬ መቶ አመት የተከሰተች ሳይሆን በብዙ ዘመናት የዜጎች መስዋዕትነት የተገነባች አገር ናት። ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ለማድረግ የብዙ ሚሊዮንና የአያሌ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ህይወት ተገብሮባታል። ይነሰም ይብዛም፣ ይጉላ ይደብዝዝ፣ ሁሉም ህዝብ ለዚያች አገር ግንባታ አሰተዋፅኦ አድርጉአል። በሌሎች አገሮች ታሪክም እንደተከሰተው ሁሉ በኢትዮጵያም ታሪክ ጦርነት የሀገር ግንባታው ሂደት አካል ሆኖ ተገኝቷል። በሂደቱ ለጠፋው ህይወትና ለደረሰው በደል የዛሬው ትውልድ ከቶም ተጠያቂ ሊሆን አይችልም ብሎ ኢወክንድ ያምናል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ወጣቱ ትውልድ ራሱን ከፅንፈኞች ማራቅ ታሪካዊ ግዴታው ነው !
“Time to bring back Eritrea from the cold”
Many observers agree that recent unfortunate developments in the Middle East can easily spillover to the Greater Horn of Africa region2. There are groups that are fanning ideologies advanced by the various actors in Middle East’s sectarian conflict. In the light of the new developments in the region, it makes sense for the United States to review its relationship with Eritrea and Ethiopia and rebalance its portfolio. The interesting question for Eritrea and Ethiopia is therefore how to respond … [Read more...] about “Time to bring back Eritrea from the cold”
ዜጋዊ ጥያቄ
የካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” በሀገራችን የራሷን ዩኒቨርስቲ ልትከፍት ነው በግንባታ ላይ ይገኛል፡፡ ስለ ጉዳዩ ምን ታስባላቹህ ? ይህ ነገር ከኢትዮጵያዊነትና ከብሔራዊ ጥቅም አንጻር በረከት ነው ወይስ መርገም ? በነገራችን ላይ ዩኒቨርስቲውን በሀገራችን ለምን እንደሚከፍቱት ታውቃላቹህ ? የካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” ከመጀመሪያው ጀምሮ በሀገራችንና በሕዝቡ ላይ የነበራትንና ያላትን ጥቅምና ፍላጎት ታውቃላቹህ ? የካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” አስቀድሞ በታሪካችን ያደረገችውን ታውቃላቹህ ? የካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” አስቀድሞ ከረጅም ጊዜና ከአጭር ጊዜ ዐቅድ አንጻር ጥቅሟን የሚያሳካላት ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር ለሀገራችን ያደረገችው አንድም የመልካም ሥራ ዝጋብ (ሬከርድ) እንደሌለ ታውቃላቹህ ? የካቶሊክ “ቤተክርስቲያን” ፋሺስት ጣሊያን ሀገራችንን በወረረ ጊዜ እጇን በቀጥታ … [Read more...] about ዜጋዊ ጥያቄ
ህ.ወ.ሓ.ት. የኢ.ሕ.አ.ፓ. አመራርና ሌሎች ታጋዮች የጦር ምርከኞች በጅምላ ረሽኖ በትራክተር አፈር መልሶባቸው እንደቀበራቸው
ይህንን አሳዛኝና ዘግናኝ ዜና "ኢትዮሚዱያ" በመባል የሚታወቀው ድህረ ገጽ ላይ በጀነዋሪ 2014 ዓ.ም. ወጥቶ አንብቤአለሁ:: ህወሓት በኢ.ሕ.አ.ፓ አመራርና ላልች ታጋዮች የጦር ምርከኞችን በጅምላ ረሽኖ በትራክተር አፈር ተመልሶባቸው እንዲቀበሩ ማድረጉን ኢትዮሚዲያ አስነብቦናል:: ህወሓት ከዚህ የበለጠ ብዙ ዘግናኝና አሰቃቂ ድርጊቶችን በሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ እየፈፀመ እንንሆነ አስተርጓሚ የሚያሻው አይደለም:: (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ህ.ወ.ሓ.ት. የኢ.ሕ.አ.ፓ. አመራርና ሌሎች ታጋዮች የጦር ምርከኞች በጅምላ ረሽኖ በትራክተር አፈር መልሶባቸው እንደቀበራቸው
The Ethiopians and their past
We love to visit the past. There is no one like us that digs deeper, travel further to harvest the bounty of our rich past. To say we dwell on the past is definitely an understatement. I would not be surprised if scientists after mapping our brain find a special pocket where we store ugly little tidbits of the past to fuel our anger. To claim we live in the past is not far from the truth. Compared to others what makes our situation a little different is how we use the past to explain or … [Read more...] about The Ethiopians and their past
“ወደው አይስቁ”
የጥምቀት በዓልን ተሰባስበን በምናከብርበት አንድ ቤት ውስጥ ካለወትሮው ፓልቶክ ተከፍቷል። በዚያ የበዓል ድባብ፤ የፓልቶክ ንትርክ መከፈቱ ሳይገርመን፣ ርእሱ የሁላችንንም ቀልብ መሳቡ። በእርግጥ አንድም ቁም ነገር በንግግሩ አልሰማንም። አዲሱን ቋንቋ ልዋስና የፓልቶኩ ተናጋሪዎች ሙድ የሚያስይዙ ነበሩ። ሰዎቹ በዚህ ከቀጠሉ የእነ ክበበው ገዳን ገበያ መዝጋት እንደሚችሉ አያጠራጥርም። የድምጽ መነጋገርያውን የያዘው ሰው ጉሮሮውን ጠራርጎ ንግግሩን እንዲህ ሲል ጀመረ። "የምኒሊክ ወንጀል በጡት መቁረጥ ብቻ አያበቃም። ... የወንዶች ብልትም ተቆርጧል።..." በአኖሌ ሃውልት የምትገረሙ ነፍጠኞች ካላችሁ። በዚህ ብዙም አትደነቁ። ገና የወንድ ልጅ ሃፍረተ-ስጋ በሃውልት መልክ በአደባባይ ይቆምላችኋል። "የባሰ አታምጣ!" ነው ነገሩ። ሜንጫዎቹ ሰክረዋል። አእምሮዋቸውም ስቷል። የሚናገሩትን … [Read more...] about “ወደው አይስቁ”
ግራና ቀኝ ጠፋን!
በአለፉት ሃያ ዓመታት ውስጥ ወያኔ-ኢሕአዴግ የሚወቀስበት ሥራ በጣም ቢያመዝንም የሚመሰገንበት ሥራ የጽሑፍ ቁጥጥርን ማስቀረቱ ብቻ ነው፤ ሁልጊዜም አንድ ጥሩ ነገር የሚያስከትለው አብዛኛውን ጊዜ የማይጠበቅ ነገር ሊኖር ይችላል፤ ለምሳሌ አጠቃላይ ነጻነት ሲመጣ ወንጀለኛነት ይጨምራል፤ እንዲሁም የጽሑፍ ቁጥጥር ሲነሣ ጸሐፊዎች ይበዛሉ፤ ትምህርት በተስፋፈበትና ማንም እንደፈለገ ለመጻፍና ለማሳተም ችሎታውም ዕድሉም በማይገኝበት፣ ሳያበጥርና ሳይሰልቅ አሰር-ገሰሩን ጽፎ በአደባባይ የሚወጣውን ጥምብ-እርኩሱን አውጥተው ሁለተኛ እንዳይለምደው የሚያደርጉ የታወቁና የሰላ አእምሮና ብዕር ያላቸው አርታእያንና ሐያስያን (ገምጋሚዎች) ባሉበት ብዕሩን የሚያባልግ ጸሐፊ አይወጣም፤ ይህ ሁሉ ባልተሟላበት እንደኛ ባለ አገር ውስጥ ብዕርን ማባለግ እንደመብት ወይም እንደነጻነት እየታየ ነው፡፡ በአደባባይ … [Read more...] about ግራና ቀኝ ጠፋን!










