አርእስቴን በጥቂቱ ያልኩበት ምክንያት የተነሳሁበት ርእስ ምን ያህል ሰፊ እንደሆነ ስለማውቅ ነገር ግን ልንወያይበት እንደሚገባ በመረዳቴ ለውይይት መክፈቻ ይሆን ዘንድ እንጂ እኔ ባለኝ እውቀት ብቻ ሙሉ በሙሉ ልተነትነው እንደማልችል በማመኔ ነው። ይህም ቢሆን እንደዜግነቴ ሃገሬን ለዘመናት ለተቆራኛት የድህነት ችግር መንስኤና መፍትሄ ሊሆኑ ይችላሉ ብዬ ያሰብኳቸውን ዋና ዋና ነጥቦች በመጠኑ ለመተንተን ለመሞከር ነው። በአንድ ሃገር ወይም አካባቢ የሚኖር ማህበረሰብ ለግላዊም ሆነ ማህበራዊ ፍላጎቶቹ በበቂ ሁኔታ መሟላት አጣጥሞና አስማምቶ በእኩልነት ሊያኖረው የሚችል ህግና ስርዓት በብዙሃኑ ፍላጎትና ስምምነት ላይ ተመስርቶ መቀረፅ አለበት። የሰውን ልጅ ከእንሰሳት የሚለየውና የተሻለ ያደረገውም አንዱ ሌላውን በእኩልነት ማየቱ እንዲሁም ሰው በጉልበቱ የበላይ መሆን የማይችልበት ሁናቴ መፈጠሩ … [Read more...] about የኢትዮጵያ የድህነት አዙሪት መንስኤና መፍትሄዎች “በጥቂቱ”
Opinions
የኔ ሃሳብ
የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ የ3 ቀን ቆይታ በኖርዌ
ተወዳጁ የሰብአዊ መብት ተከራካሪና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ በ8-2-2014 በኖርዌ ኦስሎ በመገኘት ከኢትዮጵያዉያን የስደተኞች ማሕበር ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጋር በኖርዌ ስለሚገኘው ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮዽያዊ የሰብዓዊ መብት አያያዝ ሁኔታ እና ይህ ጥገኝነት ጠያቂ በኖርዌ ምን ያህል ተቀባይነት አለው በሚለው ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድርገዋል። በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ9-2-2014 በሳውድ አረቢያ የተጎዱ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ለመርዳት በተዘጋጀው የገንዘብ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ እኛ ስንሰቃይ አሜሪካ ዝም ብላ ይሆናል፣ እኛ ስንሰቃይ የአውሮፓ ሕብረት ምንም አላለ ይሆናል የኢትዮጵያ አምላክ ግን ከኛ ጋር ነው በሚል ልብ የሚንካ ነገር ተናግረዋል። በተጨማሪም አቶ ኦባንግ በ10-2-2014 በኖርዌ ጥገኝነት በጠየቁ ኢትዮዽያዊ ወገኖቻቸው ላይ … [Read more...] about የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ ኦባንግ ሜቶ የ3 ቀን ቆይታ በኖርዌ
118ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል
ተጨማሪ መረጃ እዚህ ላይ ያገኛሉ:: … [Read more...] about 118ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ክብረ በዓል
ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ
ሰሞኑን እንደአዲስ ሆኖ የሚወራው ስለጥርነፋ ነው፤ ጥርነፋ ከዲያብሎስ ፋብሪካ የወጣ የክፋትና የጭቆና መሣሪያ ነው፤ ሰዎችን በመጨቆንና በማሰቃየት፣ ምቾትና እንቅልፍ በማሳጣት፣ ፍርሃትንና ስጋትን በማሰራጨት ሕዝብን ለጥ-ጸጥ አድርጎ ለመግዛት የሚፈልጉ ጠርናፊዎች፣ አምባ-ገነኖች፣ ጨቋኞች፣ አፋኞች፣ ዘራፊዎች፣ ወሮበሎች፣ ምድራዊም ሆነ ሰማያዊ ሕግ የማይገዛቸው፣ አምላካቸው አድርገው የሚያገለግሏቸው ሎሌዎችን በሆዳቸው ገዝተው የሚያሰልፉ ናቸው፤ እንኳን የገጠር ልጆችና አኛም የአዲስ አበባዎቹ መሰንከል ምን እንደሆነ እናውቃለን፤ እንስሳትን (በቅሎዎችንና አህዮችን፣ አንዳንዴ በገግና ፍየልም) የፊት እግር ከኋላ እግር ጋር በአጭር ገመድ እያሰሩ እንደልባቸው እንዳይንቀሳቀሱ ማድረግ ነው፤ ሀብት በመሆናቸው ቢጠፉ ባለቤቶቹ ይጎዳሉ፤ ስለዚህ በየአካባቢያቸው ያለውን እየጋጡ ችለው እንዲኖሩ … [Read more...] about ልፋ ያለው በሕልሙ ዳውላ ይሸከማል! ጠርናፊና ተጠርናፊ
በጅዳ አለም የኢትዮጵያውያን አቀፍ ት/ቤት ከትምህርት ጥራት እስከ ባለሙያው ፈተና
ባሳለፍነው ሃሙስ የወላጅ መምህራን ስብሰባ ላይ ስለጅዳው አለም አቀፍ የኢትዮጵያውያን ትምህርት ቤት አስተዳደር ፍትሃዊነት የቅጥር ሂደት እና በትምህርት ጥራቱ ዙሪያ ላይ አንድ በኢኮኖሚክስ ትምህት በከፍተኛ ማዕረግ የተመረቀ ወጣት የሰላ ሂስ አቀረበ። በቀረበው የወጣቱ የዩኒቨርስቲ መምህር ስደተኛ ስራ ፈላጊ አስተያየት ድጋፍና ተቃውሞ ቤቱን በየተራ ናጠው። በትምህርት ጥራት አለመኖር የሚስማማው ወላጅ በጭብጨባ ድጋፉን ሲገልጽ የትምህርት ጥራቱን አንድ ከኢትዮጵያ ትምህርት ቤት የ12 ኛ ክፍል ተማሪ ጋር በእንግሊዝኛ ትምህርት እውቀታቸው የኤርትራ ኢምባሲ የ7ኛ ክፍል ተማሪ እንደሚልቅ በንጽጽር ማቅረቡ የተከፉ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ፖርቲ አባላትና ደጋፊዎች ውግዘት አስከተለበት። አንዲት የወላጅ መምህራን ህብረቱ አባል ለትምህርት ጥራቱ ንጽጽር "ኤርትራ" የምትባለውን ሃገር ከአፉ … [Read more...] about በጅዳ አለም የኢትዮጵያውያን አቀፍ ት/ቤት ከትምህርት ጥራት እስከ ባለሙያው ፈተና
ትምህርት ቤታችን እና ኮሚኒቲውን የከበበው አደጋ …!
የመምህራን ማስጠንቀቂያ ... ሰሞነኛው የጅዳዎች ጉዳይ የመኖሪያ ፈቃድን በማስተካከል ዙሪያ ቢሆንም ከ 3000 (ከሶስት ሽህ) በላይ ታዳጊዎችን የሚያስተናግደው የጅዳው አለም አቀፍ ት/ቤት አሁንም አደጋ ላይ መሆኑን እየሰማን ዝም ብለናል! ከሳምንታት በፊት መምህራን አመጽ አድርገው ነበር። ከቀናት በፊትም 25 መምህራን ስብሰባ ተቀምጠው፣ በአንድ አቋም ጸንተው ጠንከር ያለ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል። ላለፉት 8 ወራት በትምህርት ቤቱ ባለቤት በኮሚኒቲው ጉዳያቸው ቢያዝም እስካሁን ከወሬ ያላለፈ አርምጃ አለማየታቸውን ገልጸዋል። 25 ቱ መምህራን ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር፣ ለኮሚኒቲው፣ ለጅዳ ቆንስልና ለወላጅ መምህራን ህብረት ባስገቡት ደብዳቤ እስከ ቀጣዩ ሳምንት የሁለተኛው የትምህት አጋማሽ መጀመሪያ የመኖሪያና የስራ ፈቃዳቸው ተስተካክሎ ካልተሰጣቸው በማስተማር መደበኛ ስራቸው … [Read more...] about ትምህርት ቤታችን እና ኮሚኒቲውን የከበበው አደጋ …!
አራተኛው ሰው ጉድ አፈሉ!
ኢትዮጵያና አሜሪካ የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ከጀመሩ ዘንድሮ 111ኛ ዓመታቸውን ይዘዋል። በቀድሞው የኢትዮጵያ ንጉስ አፄ ምንሊክና በአሜሪካው አቻቸው ፕሬዚዳንት ቴዎዶር ሩዝቬልት ልዑካን መካከል ለዘጠኝ ቀናት ድርድር ከተካሄደ በሁዋላ ነበር ግንኙነቱ በይፋ የተጀመረው። ከአንድ ክፍለ-ዘመን በላይ ያስቆጠረው የአገራቱን ግንኙነት በመጠቀም ኢትዮጵያ ጠቀም ያለ እርዳታዎችን ተቀብላለች።በአሁኑ ወቅትም በየዓመቱ ከ500 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ የልማትና የወታደራዊ እርዳታ ተጠቃሚ ናት። አሜሪካም ብትሆን ፖለቲካዊ ወታደራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከአገራችን ታገኛለች።ሆኖም ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ አሜሪካ በኢትዮጵያ ባሉ የሰብዓዊና የዴሞክራሲያዊ መብቶች መከበር ዙሪያ ቅር መሰኘቷን ደጋግማ ስትገልፅ ቆይታለች። በየዓመቱ በአሜሪካ መንግስት ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በሚወጣው የአገራት የሰብዓዊ መብት … [Read more...] about አራተኛው ሰው ጉድ አፈሉ!
ወያኔ: የነፃው ፕሬስ ፀር!
ነፃ- ፕሬስ ለነፃነት፤ ለፍትህና ለእኩልነት የሚኖረውን አስተዋፅኦ የሚገነዘቡ ገዢዎች ፕሬሱ ለአንባገነንነት አገዛዛቸው የሚመች ስለማይሆን ይፈሩታል፤ ይጠሉታል፤ ያጠፉታል። ወያኔም እያደረገ ያለው ይህንኑ ነው። ነፃ ፕሬስ የሀሳብ ነፃነት መብት አልፋና ኦሜጋው ነው ብል ማጋነን አይሆንም። የነፃ ፕሬስ መኖር የሚያረጋግጠው ጋዜጠኞች ያለምንም ጭንቀትና ፍርሃት የሚያስቡትን፡ የሚሰማቸውን፡ የሚሰሙትን እንዲሁም ምርምር አድርገው የደረሱበትን ዜናዎች በነፃ ለመፃፍና ለማሰራጨት ብሎም ሕዝብ እንዲወያይበት ለማድረግ ያላቸው ያልተገደበ መብት ነው። ይህም ጤናማ ሕብረተሰብ ለመፍጠር ብቻ ሳይሆን ለእድገቶቹም ጉልህ ድርሻ አለው። ነፃ ፕሬስ የኃሳብ ነፃነት ተግባራዊ ለመሆኑ ዋስትናም መፈተኛም ነው። ኃሳብን ያለምንም ጭንቀትና ፍርሃት በነፃ ለመግለፅ መቻልና መለዋወጥ እንደ ምግብና መጠጥ፤ ሁሉ ሰብአዊ … [Read more...] about ወያኔ: የነፃው ፕሬስ ፀር!
ሌንጮ ለታ – ታሪክ ሊሰሩ ወይንስ ታሪክ ሊጽፉ…?
ኢትዮጵያዊው ቱጃር ለለውጥ ብለው በኮንትራት ታክሲ በመሄድ ላይ ናቸው። እሳቸውን የጫነው ታክሲ መስቀል አደባባይ ላይ ሲደርስ በድንገት ቀጥ ብሎ ቆመ። ሾፌሩ ተደናጋጠ። መኪናውን እንደገና ለማስንሳት ብዙ ሞከረ። ከብዙ ሙከራ በኋላ ጥረቱ ስላልተሳካለት ቱጃሩን ለትብብር ጠየቃቸው። እንዲህ ሲል። "ወጣ ብለው ይግፉ።" ቱጃሩ በመገረም ሾፌሩን አዩት። "ይግዙ" ማለትህ ነው ሲሉም መለሱለት። እኚህ ሰው መኪናውን ከመግፋት ይልቅ አዲስ መኪና መግዛት ይቀላቸዋል። የቤቶች ድራማ ላይ እከ ደከ አስር ጊዜ "እኔን ነው?" የሚለው ወዶ አይደለም። ማመን የሚቸግሩንን ነገሮች ማጣራት ስንፈልግ እንደጋግማለን። በዚያን ሰሞን በኦቦ ሌንጮ ለታ የወጣው ዜና ብዙዎችን አስገርሟል። "ሃገር ቤት ገብተን በመታገል አዲስ ታሪክ እንሰራለን።" የሚል ነበር የዜና እወጃው ርዕስ። ይህን ርዕስ እንዳየሁ አይኔን … [Read more...] about ሌንጮ ለታ – ታሪክ ሊሰሩ ወይንስ ታሪክ ሊጽፉ…?
Good Bye Dogmatic Wreath
When is the Ethiopian political class going to get rid of its dogmatic wreath? A glance at the political discussion all through the active organized political players and stakeholders would suffice to find out that this is not the case. With this in mind to give social harmony a chance I have presented a model of harmony, which I was promoting during the last decade so that a touch of serenity and sovereignty would come to the latter. Say good bye to the bewildered spirit of the youth of the … [Read more...] about Good Bye Dogmatic Wreath










