(ይህ ጽሁፍ "የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉት የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ የቅሱፋን?" በሚል ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው ለጻፉት የተሰጠ ምላሽ ነው) መቼም ታሪክሽ መያዣ መጨበጫ ያጣ ይመስላል፡፡ ሁሉም ተነስቶ የሚጽፈው አይነት ሆኖልሻል፡፡ አንዳች እውነት ውስጡ ለማግኘት በደንብ መበርበር የሚፈልግ፤ አንደኛው የሚጽፈውን ሌላኛው በእርግጥም ድብን አድርጎ አሳማኝ በሆነ ሁኔታ የሚሽርበት አይነት ነው፡፡ ሀገሬ ግን በመሀከል ቤት ቁጭ ብለሽ ታሪክ አልባ እየሆንሽ ያለሽ መሰለኝ፡፡ በ‹‹አዋቂነት እርሾ›› ሰበብ ሁሉም እየተነሳ የሚጽፍብሽ አይነት ሆነሽ፤ ቀራጺውም፤ ሰዓሊውም፤ የታሪክ ምሩቁም፤ ፖለቲከኛውም፤ ለቀስተኛውም፤ አላቃሹም፤ ታሪክ ጸሐፊ ሆኖብሽ የተቸገርሽ መሰለኝ ሀገሬ፡፡ ሀገሬ ምናባቴ ላርግሽ? ምን ይሻልሽ ይሆን? እኔም ታዲያ ልጠይቅሻ፡፡ እንደእናት አንድ … [Read more...] about ዝምታሽ አልበዛም ኢትዮጵያዬ?
Opinions
የኔ ሃሳብ
የኛና የነሱ ኢትዮጵያ
እኛ የምናውቃት ኢትዮጵያ ከግማሽ በላይ ህዝቧ በመብራትና በውሃ እጦት የሚሰቃይባት ፣ በስልክና በኔትወርክ ችግር የሚማረርባት ፣ በመልካም አስተዳደር እጦት አሳሩን የሚበላባት ፣ አብዛኛው ህዝቧ የዛሬን እንጂ የነገን ማቀድ የማይችልባት፣ የተለያዩ ተንታኞችና አለማቀፍ ድርጅቶች “ችግር አለ” ብለው የሚያስጠነቅቋት ፣ ለዲሞክራሲ ፈር ቀዳጅ መሆን የሚገባው የፖለቲካ ስርዓት የሚያስፈራና ደም ደም የሚሸትባት ፣ ብዙ ዜናና ትንታኔ ስለ አንዲት የመንግስት ፕሮጀክት ለአመታት የሚነገርባት ፣ ከአንዲት ፕሮጀክት ብዙ ሚሊዮን ብር በሙስና ተዘርፎ ጥቂቶች የሚከብሩባት ፣ መንግስት ተብየው ሃገርና ህዝብ ከማስተዳደር ይልቅ ስልጣኑን ለማደላደል ተግቶ የሚሰራባት ፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎቿን በየአመቱ በስደት የምታጣ ፣ ለቁጥር በሚታክቱ አሰቃቂ የመኪና አደጋዎች በየቀኑ ዜጎቿ የሚረግፉባት ፣ በመቶ … [Read more...] about የኛና የነሱ ኢትዮጵያ
Ethiopia’s Strategic Importance in Africa: Will Its Influence Be Used for Good or for Ill?
Good evening! I want to thank Women's National Democratic Club for inviting me to this very important discussion today. It is an honor to be here at this very historic meeting place, established only two years after the women of America were given the right to vote in 1920 with the passage of the 19th Amendment. At the time, Eleanor Roosevelt affirmed the God-given right for women to choose who they wanted to represent them in their government. Since that time, the seeds she, the founder’s of … [Read more...] about Ethiopia’s Strategic Importance in Africa: Will Its Influence Be Used for Good or for Ill?
ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ!
የአዲስ አበባን መኪናዎች በተለይም በጫት የሚሽከረከሩት ታክሲዎችን በማንኛውም መስቀልኛ መንገድ ላይ ለአምስት ደቂቃ ቆሞ የተመለከተ ሰው በቀላሉ እንደሚረዳው "እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም!" በሚል መመሪያ መኪናዎቹ ተቆላልፈው እንዲቆሙ ማድረግ ነው፤ እንደሚመስለኝ የአባቶቻችንን ዕዳ እየከፈልን ነው፤ ዱሮ በደጉ ዘመን ሁለት ኢትዮጵያውያን መስቀልኛ መንገድ ላይ ሲገናኙ አንተ-እለፍ አንተ-እለፍ እየተባባሉ የሰማዕታቱንና የቅዱሳኑን ስም እየጠሩ ይገባበዙ ነበር! ይህ ባህል በጠንካራ የሥልጣኔ ላጲስ ተደምስሶ ጠፍቶ በምትኩ እኔ ካላለፍሁ ማንም አያልፍም መንገዱን ሁሉ መቆላለፍ አዲስ የመጠላለፍ ባህል እየተተከለ ነው፤ የመጠላለፍ ባህል የሚታየው በባቡር መንገዶች ላይ ብቻ አይደለም፤ በብዙ ነገር መጠላለፍ ባህል እየሆነ ነው! የዚህ ዝንባሌ መጨረሻው አሸናፊ የሌለበት ሙሉ ጥፋት … [Read more...] about ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ!
ሕይወትና የሚፈለጉት ቁም፥ነገሮች (ግብ)
ባንገቴዙሪያበጸጉሬሰንሰለት፣ ተሰቅላሰዓትለምልክት ለኔአበቃጊዜናጉዞውየከዋክብት፤ ጸሃይየለች፣ጥላዋየለእንደድሮ እ-በሬላይአይጮህ፣አይጣራአውራዶሮ ሰዓት፣ከንግዲህአይሰማአይናገርታውሮ! ሁሉምተፈጥሮ፣ ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ … [Read more...] about ሕይወትና የሚፈለጉት ቁም፥ነገሮች (ግብ)
የአሉላ፣ የዮሐንስ፣ የጎበና እና የምኒሊክ ትውልድ!
የዚህ ጽሑፍ ግብ በመንግስት ስልጣን ሽሚያ የተነሳ በአንድ ወገን በዮሐንስ እና በአሉላ ትውልድ በሌላ ወገን በምኒልክ እና በጎበና ትውልድ መካከል የነበረውን የፖለቲካ ባላንጣነት፣ ለስልጣን ሲሉ የተደራረጉትን እና የፈጸሙትን ስህተት መተረክ አይደለም። በመካከላቸው የነበረው ጸብ ዙፋኑ ለእኔ ይገባ ነበር የሚል ጸብ ነበር፡፡ የስልጣን ጸብ ነበር። በእርስ በርስ ጦርነት የሚፈጸመው ስርዓት አልባው የመንግስት ሽግግር ባህላችን የፈጠረው ጸብ ነበር። ይህ የቀድሞ አባቶቻችን የፖለቲካ ባህል ችግር ዛሬም አብሮን አለ። ያን ችግር ለማስወገድ ሰላማዊ ትግል ጀምረናል። የኢትዮጵያን ህዝብ የመንግስት ስልጣን ባለቤት ለማድረግ ጉዞ ላይ ነን። ወደ ዴሞክራሲ ለመሸጋጋር በቁርጠኛነት ተነስተናል። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የአሉላ፣ የዮሐንስ፣ የጎበና እና የምኒሊክ ትውልድ!
መናገርና መፃፍ ወንጀል የሆነባት ሃገራችን
ከአመታት በፊት በአዲስ አበባችን ውቧ ቅዳሜን በውቧ አዲስ ነገር ጋዜጣ በምናጣጥመበት ግዜ አንድ በጣም የማከብረው አምደኛ በኢትዮጲያ ስላለው የጋዜጠኝነትና የመፃፍ ነፃነት ያለው ቃል በቃል ባይሆንም በጥቅሉ ይህ ነበር፣ “ . . . በኢትዮጲያ የጋዜጠኝነት ሞያ በአግባቡ የተተገብረው እንዲሁም በነፃነት መፃፍና መተንተን የሚቻለው ስለ አውሮፓ እግር ኳስ በተለይም ስለ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቡድኖች ነው። ይህም የሆነበት ምክንያት ነዳጅ ጨመረ ፖለቲካ ነው ፣ ነዳጅ ቀነሰም ፖለቲካ ነው ፣ ኑሮ ተወደደ ፖለቲካ ነው ፣ ታክሲ ጠፋ ፖለቲካ ነው ፣ ምርጫ ደረሰ ፖለቲካ ነው ፣ ሁሉ ነገር ፖለቲካ ነው። ታዲያ በጋዜጠኝነት የተመረቁ ፣ በፅሁፍና በትንተና የተካኑ ስለምን ይፃፉ ሰው መቼም ቋንቋ እያለው ሳያወራ ፣ ሳይፅፍ አይኖር . . . “ ይህ ፀሃፊ ያለው እውነቱን ነው አብዛኛው የሃገራችን … [Read more...] about መናገርና መፃፍ ወንጀል የሆነባት ሃገራችን
የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከጭቁን የአማራ ህዝብ ጋር ሳይሆን ከገዢው መደብና ከቀድሞው ሥርዓት ነፋቂዎች ጋራ ነው።
በአርዕስቱ ለመጥቀስ እንደሞከርኩኝ የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከትውልድ ለትውልድ ሲተላለፍ የመጣው ከገዥዎችና ከረዳቶቻቸው የውጪ ኃይላት ጋር ነው። ይህ ህዝብ በነፍጥ አንጋቾች ቅኝ (አቅኝዎች) ሥር ከቀደቀበት ጊዜ አንስቶ አስከ ዛሬ ድረስ ትግሉን ያቁዋረጣበት ጊዜ የለም። ይህም የሆነበት ወቅት ብናስብ ሴሜቲኮች (ሓበሾች) ወደ ምስራቅ አፍሪካ ከመጡበት ጊዜ አንስቶ ነው። እነዚህ ህዝብ ወደ ምስራቅ አፍሪካ የመጡት በተለያየ ጊዜ ሲሆን፣ ሰበባቸውም የተላያየ ነው። ከመጡም በኃላ በኩሾች ንጉሥ (አባ ገዳ) “ኩሳ” በተባለ የሥልጣን ወይም የንግሥና ስም ስር በመተዳደር ነው። ቀስበቀ እየበረከቱ ሲሄዱ በተንኮልና በኃይል የነበረውን የኩሽ ህዝቦችን መስተዳድር ደምስሳው ሥልጣኑን ተቆጣጠሩ። የዛጉዌዎች ሥርወመንግስት መሃል ገብ እንጂ እስካሁን በሥልጣኑ ሲፈራረቁበት ቆዩ። እስኪ አቶ አምሳሉ ገ/ኪዳን … [Read more...] about የኦሮሞ ህዝብ ትግል ከጭቁን የአማራ ህዝብ ጋር ሳይሆን ከገዢው መደብና ከቀድሞው ሥርዓት ነፋቂዎች ጋራ ነው።
ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ ለማፋጀት የገነባውን “የመርዝ ብልቃጥ”
ኢትዮጵያን እየመራ የሚገኘው ኢህአዲግ/ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከቀን ወደ ቀን እርስ በርሱ እንዳይተማመን፣ እንዲነቃቀፍ፣ እንዲጠራጠር ከእዚህ ባለፈ ደግሞ ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ 22 ዓመታትን ዘለቀ። ህዝቡ እለት ከእለት በገዢው መንግስት የሚወጠኑለትን የእርስ በርስ ማጋጫ ተንኮሎች እየተመለከተ ልቦናው በእጅጉ እየደማ ነው። አንድ ወራሪ የውጭ ጠላት ሊሰራ የሚችለውን ያህል ህዝብን ከሕዝብ ጋር የማጋጨት ሥራ ኢህአዲግ/ወያኔ በትክክል ሰርቶበታል። የሃገሪቱን ፌድራል አስተዳደር በየትኛውም ዓለም ያልታየ ቋንቋን መሰረት ያደረገ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ደገሰላት። ፌድራላዊ አስተዳደር በዘመናዊው ዓለም አንዱ እና አማራጭ የአስተዳደር ዘይቤ ይሁን እንጂ በየትኛውም ሀገር መሰረት የሚያደርገው የመልክዓ ምድርን አቀማመጥ እና ታሪካዊ አሰፋፈርን ነው። እርግጥ ነው ጣልያን ሀገራችንን በወረረ … [Read more...] about ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ ለማፋጀት የገነባውን “የመርዝ ብልቃጥ”
ወፈ ግዝት!
መግቢያ ወያኔ የማትሞክረው የለም። አንዳንዴ አቅሟን አታውቅም ልበል? በዚያን ሰሞን፣ ቺፍ ሳጂን ዘመድኩን የተባለ የወያኔ ጉደኛ የፖሊስ ባለጊዜ፣ የቮኤውን ጋዘጠኛ፣ ሰሎሞን ክፍሌን በስልክ ሲያስፈራራ፣ “ዋሺንግተን አይደለም፣ ሰማይ ቤት ብትሆን መጥቼ እወስድሀለሁ” ነበር ያለው[1]። የወያኔ ካድሬ ጉዶች፣ በለስ አንዴ ከቀናቸው፣ ሁሌ የሚቀናቸው ይመስላቸዋል። ከኢትዮጵያው ውጪም፣ የኢትጵያውያንን ሕልውና ለመቆጣጠር ያምራቸዋል። ሲያምራቸው ይቅር። ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጽሙት ግፍ አንሶአቸው፣ ባህር ማዶም የቁጥጥራቸውን መረብ አሻግረው ለመዘርጋት የኢትዮጵያን ገንዘብ እንደ ጉድ ይረጩታል። ኬኒያና ጂቡቲ ቀንቶአቸው ይሆናል። እንግሊዝ ግን፣ ኬኒያም፣ ጂቡቲም አይደለችም። ሆድ-አደሮችን ወያኔ ትቆጣጠራቸው እንደሆን እንጂ ሌሎቻችን ዕምነታችንንም ሆነ መብታችንን አናስነካም። … [Read more...] about ወፈ ግዝት!







