• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

News
ዜና

አስፋልቱ “አብስትራክት” የሆነው የደምቢዶሎ ኤርፖርት

June 27, 2016 10:04 am by Editor 2 Comments

አስፋልቱ “አብስትራክት” የሆነው የደምቢዶሎ ኤርፖርት

ህወሃት በግፍ በሚመራት ኢትዮጵያ የማይጠፋ ነገር የለም፡፡ ምናልባት መብራት ብቻ ነው የሚጠፋው ብሎ የሚያስብ የቅርቡን ክስትት ያልተከታተለ ብቻ ሊሆን ይችላል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ መብራት፣ ውሃ፣ የስልክ ኔትወርክ፣ ወርቅ፣ … ብቻ ሳይሆን ጋዜጠኞች፣ ፖለቲከኞች፣ የሥርዓቱ ተቃዋሚዎች … በሚጠፉባት አገር ከሰማኒያ በላይ ኮንዶሚኒየም ይጠፋል፤ ሰሞኑን ደግሞ በኢትዮጵያ የህወሃት ተጠሪ ኃይለማርያም በነቀምቴ ከተማ  አውሮፕላን ማረፊያ ያስቀመጡት የመሠረት ድንጋይ ጠፍቷል ተብሎ የማኅበራዊ ሚዲያውን ሰፈር አድምቆታል፡፡ የነቀምቴው ሳያንስ ደምቢዶሎ ደግሞ ተመረቀ የተባለው የአፈር አየር ማረፊያ ህወሃትን ለከፍተኛ ስላቅና ፌዝ አጋልጦታል፡፡ የሥርዓቱ ደጋፊ የሆኑት ሳይቀሩ "ገንዘቡ ተበልቷል" ያሉበት የዚህ አውሮፕላን ማረፊያ የማኮብኮቢያና የማረፊያ መንገድ ከአፈር መሆኑ ብቻ … [Read more...] about አስፋልቱ “አብስትራክት” የሆነው የደምቢዶሎ ኤርፖርት

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”

June 25, 2016 06:27 am by Editor 4 Comments

“ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”

የኢትዮጵያን ሕዝብ በነጻ አውጪ ስም እስካሁን በግፍ እየገዛ ያለው የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ሥልጣን በኃይል ከመያዙ በፊት ሲፈጽም የነበረውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ፤ ሥልጣን ከያዘም በኋላ ላለፉት 25 ዓመታት ቀጥሎበታል፡፡ ህወሃት ሥልጣን ከያዘ ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ግፍ ያልተፈጸመበት አካባቢ የለም የሚለው አባባል የተጋነነ አይደለም፡፡ “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት” በሚል ርዕስ ጋዜጠኛ ግራሃም ፔብልስ በኦጋዴን የሚካሄደውን የሚዘገንን ግፍ ሰኔ 15፤ 2008ዓም (June 22, 2016) ዩትዩብ ላይ ለቋል፡፡ (ዘጋቢ ፊልሙ እዚህ ላይ ይገኛል) “በዛፍ ላይ ለተወሰኑ ደቂቃዎች ሰቅለውኝ ነበር፤ በርካታ ደቂቃዎች ካለፉ በኋላ አወረዱኝ፤ … ከዚያም ካሁን በኋላ የምንልሽን ታደርጊያለሽ አለበለዚያ እንገድልሻለን አሉኝ” የግፍ ዶፍ የወረደባት አናብ … [Read more...] about “ኦጋዴን፤ የኢትዮጵያ [የህወሃት] ድብቅ ኃፍረት”

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

ህወሃት “አምባሳደሮችን” በታማኞቹ ሊተካ ነው!

June 22, 2016 08:43 am by Editor 2 Comments

ህወሃት “አምባሳደሮችን” በታማኞቹ ሊተካ ነው!

በተለያዩ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በወሳኝ የህወሃት ሰዎች ሊተኩ እንደሆነ ተነገረ፡፡ በህወሃት ውስጥ ያለው ፍርሃቻና አለመረጋጋት ለሁኔታው አስገዳጅነት ምክንያት ሆኖ ቀርቧል፡፡ ህወሃት ለዓመታት ያገለገሉትን ሎሌዎች የማያምናቸው ከሆነ እነርሱም “አለመታመናቸውን” ማሳየት ይገባቸዋል፡፡ በአሜሪካ፤ በአውሮጳ፤ በአውስትራሊያና በኢትዮጵያ አጎራባች በሆኑ አገራት የሚገኙ አምባሳደሮች በቅርቡ ወሳኝ በሆኑ የህወሃት ሰዎች ሊተኩ መታሰቡን ማንነታቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የጎልጉል መረጃ አቀባይ አስታውቀዋል፡፡ ለመረጃው ቅርብ እንደሆኑና የአገራቱም ዝርዝር እንዳላቸው የተናገሩት መረጃ አቀባይ የሹምሽሩ ምክንያት ይህ ነው ተብሎ በውል ባይታወቅም ህወሃት ከውስጥና ጫና ተጠቃሽ እንደሆነ ይጠቁማሉ፡፡ በኢህአዴግ ተለጣፊና ድቃይ ድርጅቶች ታቅፈው የሥርዓቱ ሎሌ የሆኑት አምባሳደሮች በመጪዎቹ … [Read more...] about ህወሃት “አምባሳደሮችን” በታማኞቹ ሊተካ ነው!

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

“‘ጭካኔ የተሞላበት አፈና’ – የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ”

June 16, 2016 08:03 am by Editor 3 Comments

“‘ጭካኔ የተሞላበት አፈና’ – የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ”

ከሰብዓዊ መብቶች ጋር በምንም ዓይነት መልኩ የማይተዋወቀው፤ መተዋወቅና መግባባትም የማይችለው ህወሃት ሰሞኑን “የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን” ብሎ ባቋቋመው ጽ/ቤቱ አማካኝነት “በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር” በማለት ዘገባ ካወጣ ጥቂት ቀናት በኋላ ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት ማምሻውን የህወሃትን ቅጥፈት ርቃኑን የሚያወጣ ዳጎስ ያለ ዘገባ ይፋ አድርጓል፡፡ ከዘገባው ጋር በማያያዝ የተወጣው መግለጫ ከዚህ በታች ይገኛል፡፡ (ናይሮቢ፤ ሰኔ 9 ቀን 2008 ዓ.ም) – ከህዳር ወር 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በኦሮሚያ ክልል በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች የኢትዮጵያ መንግስት የጸጥታ ሀይሎች ከ400 በላይ የሚሆኑ ሰልፈኞችን የገደሉ ሲሆን ከአስር ሺህ በላይ የሚቆጠሩትን ደግሞ ማሰራቸውን ሂዩማን ራይት ወች ዛሬ ይፋ … [Read more...] about “‘ጭካኔ የተሞላበት አፈና’ – የግድያ እና የእስራት ምላሽ፤ ለኢትዮጵያ የኦሮሞ ተቃውሞ”

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

ከ300 በላይ ዜጋ መገደሉ “አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነው” የህወሃት ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

June 13, 2016 08:31 pm by Editor Leave a Comment

ከ300 በላይ ዜጋ መገደሉ “አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነው” የህወሃት ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

በኦሮምያ ክልል የተቃውሞ እንቅስቃሴ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች የተወሰደው እርምጃ አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነበር ሲል የኢትዮጵያ (ህወሃት/ኢህአዴግ) ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ ዓለም በሙሉ በሚያውቀው በየትኛውም ሚዛን እርምጃው ተመጣጣኝም፣ አስፈላጊም አልነበረም ሲሉ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም “የኢትዮጵያ መንግሥት እንኳን ያላለውን ኮሚሽኑ ደፍሮ ‘ተመጣጣኝ ነው’ ማለቱ አስቂኝም አስገራሚም ነው”ብለዋል። ከቅማንት የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ ለተፈጠረው ግጭት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሕዝቡን ይቅርታ መጠየቅ እንዳለበት ሪፖርቱ ሃሣብ ያቀረበ ሲሆን የክልሉ መስተዳድር ቀደም ብሎ ይቅርታ መጠየቁን አስታውቋል፡፡ ዝርዝሩን ከዚህ በታች ይገኛል ተጭነው ያድምጡ:: (ምንጭ: የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ - VOA) … [Read more...] about ከ300 በላይ ዜጋ መገደሉ “አስፈላጊና ተመጣጣኝ ነው” የህወሃት ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን

Filed Under: News Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

ህወሃት ጉሮሮውን ሳይታነቅ የበላውን በ30 ቀን “እተፋለሁ” አለ

June 11, 2016 05:09 am by Editor 4 Comments

ህወሃት ጉሮሮውን ሳይታነቅ የበላውን በ30 ቀን “እተፋለሁ” አለ

ህወሃት በቦንድ ስም ህግ ጥሶ ሲሰበስብ የነበረውን ገንዘብ ክስ ተመስርቶበት ጉሮሮው ሳይታነቅ ወዶ ለመትፋት መስማማቱ ታወቀ። ድርጊቱ ኢትዮጵያን መሳቂያ፣  የምትተዳደረው በህገ አራዊት መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑንና የህወሃትን የወሮበላነት ባህሪ እርቃን ያወጣ ነው ተባለ። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው እንደሚሉት ከውጭ ምንዛሬ  ገበያ ጋር በተያያዘ ተጨማሪ ምርመራ ሊካሄድ የሚችልባቸው በርካታ አግባቦች እንደሚኖሩ ነው። ራሱን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ” የሚለው አገዛዝ ከቦንድ ሽያጭ ጋር በተያያዘ ሰሞኑንን ይፋ የሆነበት ዜና “ነጻ አውጪው ሃይል” አሁንም ከጫካ አስተሳሰብ አለመላቀቁን የሚያመለክት እንደሆነ ተጠቆመ። በፍርድቤት ተከስሶ እና ጉሮሮውን ታንቆ ከውርደት ጋር በርካታ የገንዘብ ክፍያ ውስጥ ከመግባቱ በፊት “ጥፋተኛ ነኝ፤ ፍርድቤት አትውሰዱኝ፤ ያላችሁኝን አደርጋለሁ” በማለት … [Read more...] about ህወሃት ጉሮሮውን ሳይታነቅ የበላውን በ30 ቀን “እተፋለሁ” አለ

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

የመለስ “ሌጋሲ” የመጨረሻው ዙር የመጀመሪያ ክፍል?

May 26, 2016 10:09 am by Editor 2 Comments

የመለስ “ሌጋሲ” የመጨረሻው ዙር የመጀመሪያ ክፍል?

ሰሞኑን የተሰማው ዜና በህወሃት መንደር የሥርዓት መናጋትና የፖለቲካው ችግር ነጸብራቅ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። “ይህ ችግር እንደ ተስቦ ይዛመታል፤ ሲዛመት መቆሚያ አይኖረውም” የሚሉም አሉ። ሲያክሉም “ተስቦው ወደ መበላላት ሊያመራ ይችላል። ይህ ሊሆን ግድ ካለ ደግሞ እሽቅድድም ይጀመራል። እሽቅድድም ሲኖር ላለመቀደም የፈሪ ዱላ አይነት ጨዋታ ይነሳል። የፈሪ ዱላ ክፉ ነው” በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉንም ወገኖች አስተሳሰብ የሚያጣጥሉ አልታጡም። ይህ አስተያየት የተሰጠው ከሁለት ሳምንት በፊት አብረዋቸው ከሚሰሩት ባለቤታቸው ጋር ከሃላፊነታቸው ተነሱ የተባሉት የመረጃና የደህንነት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ኢሳያስ ወልደጊዮርጊስ ዜና ተከትሎ ነው። አቶ ኢሳያስ የደህንነቱ “መለስ” በሚል ስያሜ ይጠሩ ስለነበር ዜናው በህወሃትም ሆነ ህወሃት “መንግስት” የመሆን አጋጣሚ ሲመቻችለት ባቋቋመው … [Read more...] about የመለስ “ሌጋሲ” የመጨረሻው ዙር የመጀመሪያ ክፍል?

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛን ቅድመ መስፈርት ያደረገ የስራ ማስታወቂያ አወጣ

May 14, 2016 02:45 am by Editor 3 Comments

የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛን ቅድመ መስፈርት ያደረገ የስራ ማስታወቂያ አወጣ

ተቀማጭነቱ አዲስ አበባ የሆነው የጀርመን ኤምባሲ የትግርኛ ቋንቋን ቁልፍ ቅድመ መስፍርት የሚያደርግ ክፍት የስራ ማስታወቂያ አዲስ አበባ ለሚገኘው ጽህፈት ቤቱ አወጣ። ትግርኛ ዋና መስፈርት የሆነበት ምክንያት ይፋ አለመደረጉ ጥያቄ አስነስቷል። ጉዳዩን የሚከታተሉ ወገኖች የኤምባሲው ተግባር የኢትዮጵያውያንን እኩልነትን ከህወሃት በላይ ያንቋሸሸ ነው ብለውታል፡፡ ኤምባሲው ማብራሪያ እንዲሰጥ ይጠበቃል። ኢምባሲው በድረገጹ ሜይ 4 ቀን 2016 ያወጣው  ማስታወቂያ የሚፈልገው ባለሙያ የቪዛ ማመልከቻ ስራን የሚያመቻች፣ የሚያረጋግጥ፣ ቪዛ ነክ ጉዳዮችን አስመልክቶ የቃልና የጸሁፍ መረጃዎችን የሚሰጥ፣ የቪዛ ክፍያን የሚፈጽምና የመዝግብ አያያዝ ስራን የሚያከናውን እንደሆነ ያረጋግጣል። የስራው ቦታ ከአዲስ አበባ ውጪ ስለመሆኑ የሚለው ነገር የለም። ማስታወቂያውን የተመለከቱ ወገኖችን ያነጋገረውም … [Read more...] about የጀርመን ኤምባሲ ትግርኛን ቅድመ መስፈርት ያደረገ የስራ ማስታወቂያ አወጣ

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

ኦባንግ አባ “ቃኘው” የደቡብ ኮሪያ ዳግም ዘማች!

May 4, 2016 08:14 am by Editor 4 Comments

ኦባንግ አባ “ቃኘው” የደቡብ ኮሪያ ዳግም ዘማች!

የመን ትነድዳለች ኢትዮጵያውያን ግን ወደዚያው ያቀናሉ። ሶማሊያ ዋስትና ቢርቃትም ወገኖች ሊረማመዱባት አሁን ድረስ ምርጫቸው ናት። በሲና በረሃ ሰው በቁሙ ይበለታል። ለእኛ ኢትዮጵያውያኖች ግን አሁንም አማራጭ መንገድ ነው። ሲኦል መሆኑ እየታወቀ እህትና ወንድሞች ወደ አረብ አገር ይተምማሉ። ኬንያን፣ ታንዛኒያን፣ ዛምቢያን፣ … አቆራርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚጓዙ ቁጥራቸው ሲቀንስ አይታይም። በደቡብ አፍሪካ ወገኖች በእሳት ሲቃጠሉና በገጀራ ሲጨፈጨፉ ማየት ወደዚያ የሚደረገውን ጉዞ አልቀነሰውም። ለምን? በቀይ ባህርና በሜዲትራንያን የሰመጡ ወገኖች መርዶ ሳያሰልስ ሌሎች መሰመጥ የመጨረሻ አማራጭ መሆኑን እያወቁ ይገቡበታል። ሊቢያ የታረዱትን ወገኖች እያዩ ሌሎች ወደ ሊቢያ ለማቅናት አያቀማሙም። ለምን? በኩባ ቪዛ ተነስተው መከራቸውን ለወራት በበረሃ የሚያሳልፉ ወገኖች ቁጥር ... ስንቱ … [Read more...] about ኦባንግ አባ “ቃኘው” የደቡብ ኮሪያ ዳግም ዘማች!

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

ጋምቤላ ከውስጥም ከውጭም የምትለበለብ ለም ምድር!!

April 22, 2016 07:21 am by Editor 3 Comments

ጋምቤላ ከውስጥም ከውጭም የምትለበለብ ለም ምድር!!

ጋምቤላ ውብ ምድር፣ ጋምቤላ የተፈጥሮ ባለጸጋ፣ ጋምቤላ ድንግል መሬት፤ ጋምቤላ  ያላትን የማትበላ፣ የተረገሙ የሚመሯት፣ የደም መሬት፣ የዕንባ ምድር፤ ጋምቤላ የምትዘረፍ ምድር፣ ግፍ የተትረፈረፈባት የግዞት መሬት፣ የደም አውድ፣ ከውስጥም ከውጭም የምትለበለብ “አካላችን”፤ ጋምቤላ ያላቸውን የማይበሉ ህዝቦች፣ ባላቸው ሃብት የተነሳ የግፍ መከራ የሚጋቱ ምስኪን ወገኖች የሰፈሩባት ገነተ ሲኦል፤ ተቆርቋሪ አልባ “ኢትዮጵያኖች” ፍትህን ስትናፍቁ  ከሁልጊዜውም በላይ በከፋ ሃዘን ተመታችሁ!! አዎ፣ የጎልጉል ዝግጅት ክፍልን ጨምሮ ዜጎችን ያቃጠለው ዜና ባልተለመደ መልኩ የተበሰረው በህወሃት ንብረት ራዲዮ ፋና አማካይነት ነው። ባለፈው አርብ የተሰማው ክፉ ዜና እነዚያ ለቱሪዝም ማስታወቂያነት ብቻ የሚፈለጉት ወገኖቻችን በድንገት ስለመጨፍጨፋቸው ነው። ከ240 በላይ እናቶችና ህጻናት በጅምላ … [Read more...] about ጋምቤላ ከውስጥም ከውጭም የምትለበለብ ለም ምድር!!

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

  • « Previous Page
  • Page 1
  • …
  • Page 27
  • Page 28
  • Page 29
  • Page 30
  • Page 31
  • …
  • Page 74
  • Next Page »

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule