ኢትዮጵያ ወጣትነትን15-29 ዓመት ባለ የዕድሜ ክልል ከፍላ ትበይነዋለች፡፡ አገሪቱ ውስጥ ካለው የህዝብ ብዛት በአማካይ 60% የሚሆው ወጣት ተብሎ ሊጠቀስ በሚችለው የዕድሜ ክልል ይገኛል፡፡ የተሻለ የትምህርት ጥራት፣ አማራጭ የሥራ ዕድል፣ ምቹ ማህበራዊ አገልግሎት፣ የፖለቲካ ነፃነትና መሰል ወሳኝ ጉዳዮችን አጥብቀው የሚሹት የኢትዮጵያ ወጣቶች ከህወሓት/ኢህአዴግ አፓርታይዳዊ ዘረኛ የፖለቲካ አሰላለፍ ጋር በተደጋጋሚ ሲላተሙ ይስተዋላል፡፡ ለህወሓት/ኢህአዴግ አንድ አይነት ወይንም ተመሳሳይ አጀንዳ የሚያነሳ፣ በዘውጋዊ (በዘረኛ) ማንነት የማይከፋፈል፣ ለአገዛዙ የማያጎበድድ ወጣት “የሥርዓቱ አደጋ” ነው፡፡ በ1997 ታሪካዊ የምርጫ ዘመን የአገዛዙን ዘረኛ የአፓርታይድ አሰላለፍ የማይቀበሉ፣ ከአካባቢያዊ ማንነት ይልቅ የጋራ ማንነትን ያቀነቀኑ ወጣቶችን ከመንግስታዊ ፍጅቱ ጎን ለጎን “አደገኛ … [Read more...] about ኢትዮጵያ፤ ህወሓትና የትግራይ ወጣት
News
ዜና
በግብረሰዶማዊያን የተወረረችው አዲስ አበባ!
ግብረ-ሰዶማዊነትን እንደገቢ ምንጭ የሚጠቀሙበት ወንድ አዳሪዎችና (male prostitutes) ደላሎች አሉ! ግብረሰዶማዊያኑ የራሳቸው መገናኛ ቤቶችና ምሽት ክለቦች አሏቸው “ዜጋ” የሚለው ቃል የመግባቢያ ኮድ ሥማቸው ነው! ግብረሰዶማዊያኑ በድብቅ መኖሪያ ቤቶችና በምሽት ክለቦቻቸው “የጋብቻ ሥነሥርዓታቸውን” ይፈጽማሉ! ዳዊት ተሰማ (የባለ ታሪኩ ስም የተቀየረ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በድህረ ምረቃ መርሐ-ግብር የህብረተሰብ ጥናት ተመራቂ ተማሪ ነው፡፡ ተማሪው ለዲግሪ ማሟያ ጥናት ለማዘጋጀት ለአማካሪው ካቀረበው የጥናት ሀሳብ አንዱ ግብረሰዶማዊነት በአዲስ አበባ በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ፤ በተለይም ሁኔታውን ከውጪው ዓለም ተጽዕኖ አኳያ በማያያዝ ለማቅረብ ነበር፡፡ የተማሪው የጥናት ሀሳብ በአማካሪው መምህሩ ውድቅ የተደረገ በመሆኑ ሌላ ርዕስ የጥናት ሀሳብ ለመምረጥ … [Read more...] about በግብረሰዶማዊያን የተወረረችው አዲስ አበባ!
ተስፋዬ ገ/አብ “የሚዲያ ያለህ” እያለ ነው!
ለተስፋዬ ዕድል መስጠት ሬዲዮ RTLM መሆን ነው የኢትዮጵያ ስም ሲጠራ፣ ከፍ ከፍ ሲል “የዘር ወባው” የሚነሳበት ተስፋዬ ገ/አብ አሜሪካ ገብቶ የሚያናግረው ሚዲያ በማጣቱ “በሚዲያ ረሃብ” እየተሰቃየ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በክፉም ይሁን በመልካም ከሚዲያ መገለል የማይወደው ተስፋዬ “ሻዕቢያን የሚያጋልጥ መጽሐፍ ጽፌአለሁና አናግሩኝ” እያለ በዳያስፖራ ያሉትን ሚዲያ እየለመነ፣ በራቸውን እያንኳኳ መሆኑ ተነግሯል - በተለይ የተንቀሳቃሽ ምስልና (TV and YouTube) የሬዲዮን፡፡ ዛጎል እንደዘገበው ከሆነ እስካሁን ዕድሉን የሰጠው የለም፡፡ ተስፋዬ ከዚህ በፊት እየጻፈ የሚያወጣቸው መጣጥፎች እንደዱሮው ተነባቢነት ካጡ ሰነባብተዋል፡፡ የኦሮሞም ጽንፈኞችም እንደፈለጉ ሲጠቀሙበትና እሱም በተራው ሲጠቀምባቸው ቆይቶ አሁን ከእርሱ “የተሻሉ” አግኝተው ትተውታል፡፡ በርካታ እርሱን የሚተኩ … [Read more...] about ተስፋዬ ገ/አብ “የሚዲያ ያለህ” እያለ ነው!
የትግራይ ብሄርተኞች ዕብሪትና የጣናው ሞገድ ፈተና በመቀሌ!
“የትምክህት ፈረስ፣ ነፍጠኛ፣ የምኒልክ ርዝራዥ፣ አማራ አህያ፣ ገና መቶ ዓመት እንገዛሃለን፣ …” የመቀሌ ከነማ ደጋፊዎች ጭፈራ “የሌባ አይነ ደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ” የባህርዳር ከነማ ደጋፊዎች የመልስ ጭፈራ የመጨረሻው መጀመሪያ ይሆን? ያስፈራል! በኢትዮጵያ እግር ኳስ ውድድር ከፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች ቀጥሎ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች የተለየ ትኩረት ይስባሉ። የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ወደ ፕሪሚየርሊግ ለማደግ የሚደረጉ ፍልሚያዎች በመሆናቸው የተመልካቾችን ቀልብ ይስባሉ። የከፍተኛ ሊግ ጨዋታዎች ምድብ “ሀ” ላይ የተደለደሉት ክለቦች በወጣላቸው መርሐ-ግብር መሰረት ግንቦት 5 ቀን 2009 ዓም በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ጨዋታቸውን አድርገዋል። የዚህ ውድድር ተሳታፊ የሆኑት መቀሌ ከነማ እና ባህርዳር ከነማ (የጣናው ሞገድ) በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስ ግቢ (FB campus) … [Read more...] about የትግራይ ብሄርተኞች ዕብሪትና የጣናው ሞገድ ፈተና በመቀሌ!
የኮሌራው ምሥጢር! የቴድሮስ “የጥቅምት ዱብ ዕዳ”?
በህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ የገንዘብ ድጎማና ድጋፍ ለዓለም የጤና ጥበቃ ድርጅት ዳይሬክተርነት የሚወዳደረው ቴድሮስ አድሃኖም የመመረጡ ጉዳይ አደጋ ገጥሞታል፡፡ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በነበረበት ወቅት ሦስት የኮሌራ ወረርሽኞች በምሥጢር እንዲያዙ ማድረጉ ለዳይሬክተርነት እንዳይበቃ ያደርገዋል ተብሏል፡፡ እንደ አሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ይህ ጉዳይ የቴድሮስ “የጥቅምት ዱብ ዕዳ” ሊሆን እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ሜይ 13፤2017 ዓም “የዓለም ጤና ጥበቃ ድርጅትን ለመምራት የሚወዳደረው እጩ ወረርሽኝ በመደበቅ ተከሰሰ” በሚል ርዕስ ባስነበበው ዜና የቴድሮስን የመመረጥ ተስፋ ስለሚያጨልመው የኮሌራ ወረርሽኝ ምሥጢር በዝርዝር አትቷል፡፡ በያዝነው የግንቦት ወር (ከሜይ 22፣ 2017) ጀምሮ በጄኔቫ በሚካሄደው የአንድ ሳምንት ስብሰባ ድርጅቱን ለመምራት ከሚወዳደሩት ሦስት … [Read more...] about የኮሌራው ምሥጢር! የቴድሮስ “የጥቅምት ዱብ ዕዳ”?
እንባ ካለ አሁን እናልቅስ!! ሊታመን ባይችልም አማኑኤል ሆስፒታል እንዲህ እየሆነ ነው!
“ቅባትና ደረቅ” በአማኑኤል የአዕምሮ ህክምና ሆስፒታል ታካሚዎች እንደ ደረጃ መዳቢ የተሰጠ ስም ነው። ታሪኩ ዘግናኝ፣ ኅሊናን የሚፈትን፣ ወዴት እያመራን እንደሆነ ግራ የሚያጋባ፣ መፈጠርን የሚያስጠላ፣ ሲሰሙት ግራ የሆነ፣ ቃላት ሊገልጹት የማይችል የክሽፈታችን ሁሉ ከሽፈት ነው። አማኑኤል ሆስፒታል ተኝቶ ለመታከም አርባ ሺህ ብር እንደሚከፈል ከመስማት በላይ ዘግናኝ ጉዳይ የለም። ጎልጉል ባሰባሰበው መረጃ ሌሎችም ጉዳዮች አሉ። በአማኑኤል ሆስፒታል ሴት የአዕምሮ ህመምተኞች መደፈራቸውን፣ ሲያረግዙ ጽንስ የሚቋረጥበት ክሊኒክ በውስጥ በተደረገ ስምምነት ይሰጥ እንደነበር ይፋ በተሰማ ጊዜ ጫጫታ ተሰምቶ ነበር። ጉዳዩን በወቅቱ ይፋ ያደረጉት አንድ የሆስፒታሉ ነርስ ነበሩ። ዛሬ ያ ግፍ ተመርምሮ መልስ ሳያገኝ ተጨማሪ ጉድ እየሰማን ነው። የሟቹ መለስ ዜናዊ ባለቤት የበላይ ጠባቂ ሆና ስትመራው … [Read more...] about እንባ ካለ አሁን እናልቅስ!! ሊታመን ባይችልም አማኑኤል ሆስፒታል እንዲህ እየሆነ ነው!
የኢትዮጵያ አርበኞች ውለታና የባንዳዎች ዕዳ!
ረዥሙ የኢትዮጵያ ታሪክ ከነፍጥ፤ ከሞፈርና ከመስቀል ጋር ተዛማጅነቱ ፍፁም ነው ማለት ይቻላል፡፡ ለዚህ ይመስላል አባ ዳኘው (ዳግማዊ አጤ ምኒልክ) የአድዋ ጦርነት ዘመቻ ዝግጅት ላይ “… ሀገር የሚያጠፋ፤ ሃይማኖት የሚለዉጥ ጠላት…” መጥቷልና ከርስትህና ከሚስትህ ሳትነቀል የሚል ይዘት ያለው አዋጅ በወቅቱ እንዲነገር ያደረጉት፡፡ በጊዜ ሂደት ሀገሪቱ ከታሪኳ መድረክ “መስቀል”ን ገለል ብታደርግም ነፍጥና ሞፈር (ርስት) የአገሪቱ ህያው አምሳያ የታሪክ አካል ሆነዉ ቀጥለዋል፡፡ ወራሪ ኃይል በመጣ ቁጥርም እነዚህ የአገሬው ማታገያ አብይ አጀንዳዎች ሆነው ሲነሱ ኖረዋል፡፡ የነጮቹ ቅርጫ የሆነችው አፍሪካ በቅኝ ግዛት ክፉ ዕጣ ውልቅልቋ ሲወጣ፤ ኢትዮጵያ አድዋ ላይ በጀግኖች አባቶቻችን ተጋድሎ ሉአላዊነቷን ማስከበር ችላ ነበር፡፡ ፋሺስት ጣሊያንም ሽንፈቷን በእልህና በቁጭት ለመቀበል አርባ … [Read more...] about የኢትዮጵያ አርበኞች ውለታና የባንዳዎች ዕዳ!
የነፃነት ኃይሎች ጥቃት ከዳር ወደ መሀል!
ጎንደርና ባህርዳር ከተማ ውስጥ በሁለት ወር ብቻ 9 የቦምብ ፍንዳታ ደርሷል! “ህወሃት የሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያን ክፍል የበቀል መወጫ እያደረገው ነው”፤ ነዋሪዎች ላይቆም የተቀጣጠለው የሰሜን ምዕራብ ብረት አከል ህዝባዊ አመፅ የትግል ስልቱን እየቀያየረ ባህርዳር ደርሷል፡፡ አስር ወራትን ያስቆጠረው የነፃነት ኃይሎች እንቅስቃሴ ከገጠር ሽምቅ ውጊያ ወደ ከተማ የደፈጣ ቦምብ ጥቃት ተሻግሯል፡፡ በሁለት ወር ጊዜ ውስጥ ዘጠኝ የቦምብ ፍንዳታ ደርሷል፡፡ ድርጊቱ ሰላም የነሳው ህወሃት “የአማራ ክልልን የበቀል መወጫ እያደረገው” መሆኑ ይነገራል፡፡ ህወሓት/ኢህአዴግ ሙሉ የደህንነት አቅሙንና የበዛ የመከላከያ ኃይሉን አማራ ክልል ላይ ቢያደርግም የነፃነት ኃይሎች ተከታታይነት ያለው ጥቃት ከመፈፀም ያገዳቸው ኃይል የሌለ መሆኑ እየታየ ነው፡፡ የመጀመሪያዉ ዙር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ … [Read more...] about የነፃነት ኃይሎች ጥቃት ከዳር ወደ መሀል!
ኦባንግ ሜቶ ከከፋ አደጋ ተረፉ!
“ዳግም የመኖር እድል ተሰጠኝ፤ ተማርኩበት፤ እናንተም ተማሩ” “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ በሁሉም ስፍራ፣ በየትኛውም አጋጣሚ ለሚፈልጋቸው ሁሉ “አለሁ” የሚሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ዘረኝነትን፥ ዘውገኝነትን፥ ጎሠኝነትን አጥብቀው ይዋጋሉ። ይጸየፉታል። ከዘር ቆጠራና ከቂም የጸዳች ኢትዮጵያን ማየት ህልማቸውና የመጨረሻ ግባቸው ነው። ሰብዓዊነት ለአፍታም ከአንደበታቸው የማይለይ፣ በሚያውቋቸው ሰዎች ሁሉ የሚወደዱ፣ ግልጽ ተናጋሪነታቸው ልዩ የሚያደርጋቸው ኦባንግ በዚሁ ባህሪያቸው “አባ ነቅንቅ” የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። በስደት ለሚሰቃዩ የኢትዮጵያ ልጆች /እሳቸው ቤተሰቦቼ የሚሏቸው/ በጠሯቸው ቦታና ሁሉ በመገኘት ለሚያሳዩት ትጋት አቻ የላቸውም። ኢትዮጵያን በመወከል በከፍተኛ ቦታዎች የሚሟገቱ፣ ያዘነውን የሚጎበኙ፣ ለሴት እህቶቻችን ቀድመው የሚደርሱ እኚህ ውድ ሰው በድንገተኛ የመኪና አደጋ … [Read more...] about ኦባንግ ሜቶ ከከፋ አደጋ ተረፉ!
“ግድያው ተገቢና ሕጋዊ ነው” የህወሃት “ሰብዓዊ” ኮሚሽን
ህወሃት/ኢህአዴግ በንፁሐን ደም ላይ ማላገጡን ቀጥሏል!! በኢትዮጵያ ለሩብ ክፍለ ዘመን የተከማቸው የግፍ አገዛዝ በምሬት የታጀበ ህዝባዊ አመጽ አስነስቷል። ህዝባዊ አመጽ ደግሞ ለኢትዮጵያ አዲስ ክስተት ባይሆንም በአገሪቱ ዉስጥ በሁለንተናዊ ዘርፍ ተጽዕኖ መፍጠር ከሚችሉት ሁለቱ ክልሎች (የኦሮሞና የአማራ፤ የደቡብ ኮንሶንና ጌዴኦን ተቃውሞዎች ሳንዘነጋ) ተከታታይነት ባለው መልኩ የአገዛዙን ማህበራዊ መሰረት በሚንድ ሁኔታ አመጽ መቀስቀሱ ይህኛዉን ክስተት የተለየ ያድርገዋል። በዚህ ህዝባዊ አመፅ ህወሃት ከበረሃ የሽምቅ ባህሪው በተሻገረ የ“መንግስት” ባህሪ የሌለው መሆኑን ለወዳጅ ጠላቶቹ ያስመሰከረበትን መንግስታዊ ፍጅት በዜጎች ላይ ፈጽሟል። በገዛ ዜጎቹ ላይ የከፈተውን ጦርነትና ጅምላ እስር ዘግይቶም ቢሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሥም ህጋዊ ሽፋን ሲሰጠው ታይቷል። ድርጊቱንም … [Read more...] about “ግድያው ተገቢና ሕጋዊ ነው” የህወሃት “ሰብዓዊ” ኮሚሽን










