አጼ ምኒልክ በሕይወት ዘመናቸው የሰሯቸውን ድንቅ ተግባራት በደማቅ ብእርና ብራና የተከተቡ ናቸው! 1835 ዓ.ም. -------------ወፍጮ (በ1835ዓም ገደማ የሸዋው ንጉሥ ሣህለሥላሴ ነበሩ በውሃ የሚሥራ ወፍጮ ያስተክሉት ሆኖም በደረሰባቸው ተቃውሞ ሳይሳካላቸው ቀረ:: ተቀውሞውን አሸንፈው ምኒልክ በ1893ዓም አዲስ ወፍጮ አስተከሉ) 1882 ዓ.ም. -------------ስልክ 1886 ዓ.ም. ------------ፖስታ 1886 ዓ.ም. ------------ባህር ዛፍ 1886 ዓ.ም. ------------ገንዘብ 1886 ዓ.ም. ----------የውሃ ቧንቧ 1887 ዓ.ም. -----------ጫማ 1887 ዓ.ም. --------------ድር 1887 ዓ.ም. -------------የሙዚቃ ት/ቤት 1887 ዓ.ም. ----------የፅህፈት መኪና 1889 ዓ.ም. … [Read more...] about እምዬ ምኒልክ የኢትዮጵያ መሐንዲስ!
News
ዜና
ያለ ውክልና ግብር እየሰበሰበ ያለው ህወሓት ባዲስ የጀመረው የገቢ ግብር ሕይወት አጠፋ
አንዳች የሕዝብ ውክልና ሳይኖረው በተገንጣይ ነጻ አውጪ ስም ኢትዮጵያን በግፍ እየገዛ ያለው የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር ህወሓት ሰሞኑን በአዲስ አበባ አነስተኛ ነጋዴዎች ላይ እየጣለ ያለው የግምት ገቢ ግብር ሕዝቡን አማርሯል ለሞትም ዳርጓል፡፡ አዲስ አድማስ ያተመው ዘገባ እንዲህ ይነበባል:- የአዲስ አበባ ገቢዎች ባለስልጣን ሰሞኑን በአነስተኛ ነጋዴዎች ላይ እየጣለ ያለው አዲሱ የግምት የገቢ ግብር ተመን ከፍተኛ መደናገጥን የፈጠረ ሲሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ውስጥ ከዚሁ የቀን ገቢ ግምት ጋር በተያያዘ ምክንያት የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የተጣለባቸውን የቀን ገቢ ግምት ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጥሮባቸው በድንገት ወድቀው ህይወታቸው ያለፈው አቶ አጎናፍር፤ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 በሰፈር ውስጥ በከፈቷት የሸቀጣሸቀጥ ሱቅ ነበር … [Read more...] about ያለ ውክልና ግብር እየሰበሰበ ያለው ህወሓት ባዲስ የጀመረው የገቢ ግብር ሕይወት አጠፋ
የተማሪዎች ዕውቀት ደረጃ “150 ዓመታት ወደ ኋላ” ቀርቷል!
“የትምህርት ጥራቱ እጅግ አሳፋሪ ደረጃ ላይ ደርሷል” ዶ/ር መስፍን “ከኮሌጅ ተመርቀው 7ኛና 8ኛ ክፍሎችን ለማስተማር ዝግጁ ከሆኑ መምህራን የ12ኛ ክፍል ፈተናን ብቻ ሳይሆን የ8ኛ ክፍል ፈተና ማለፍ አልቻሉም” “የኢትዮጵያ 7ኛና 8ኛ ክፍል ተማሪዎች አስተሳሰብ፣ አሜሪካ፣ ሲንጋፖርና መሰል አገራት የ1ኛ ክፍል ተማሪዎች አስተሳሰብ ጋር እኩል ነው” የግንቦት 20 መርዛማ ፍሬዎችን በተከታታይ ባተምንበት ጊዜ ከፍሬዎቹ መካከል “ትውልድ አምካኝ የትምህርት ፖሊሲ” አንዱ እንደነበር መግለጻችን ይታወሳል፡፡ ሕወሓት ሆን ብሎ በሚከተለውና አዲሱን ትውልድ ከማንኛውም ዓይነት የፖለቲካ አስተሳሰብም ሆነ አመለካከት ለመነጠል በሚያራምደው ፖሊሲ በድንቁር ተገዢ አድርጎ የመግዛቱን ዓላማ በፖሊሲ ደረጃ ሲተገብረው ቆይቷል፡፡ በድንቁርና ጭለማ ውስጥ ያሉትን ሹማምንቱን “ተፈጭና ተመረቅ” … [Read more...] about የተማሪዎች ዕውቀት ደረጃ “150 ዓመታት ወደ ኋላ” ቀርቷል!
ራስ እምሩን በተመለከተ፤
የኢትዮጵያ አርበኞች ቀን ሚያዚያ 27፤2009 የተከበረበትን ዕለት ምክንያት በማድረግ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በዕለቱ (May 5, 2017) “የኢትዮጵያ አርበኞች ውለታና የባንዳዎች ዕዳ!” በሚል ርዕስ አንድ ጽሁፍ ለኅትመት አቅርቦ ነበር፡፡ የጽሁፉ ዓላማ በዚህ መልኩ ቀርቦ ነበር፤ “በየዓመቱ ሚያዝያ 27 የሚከበረው የድል ቀን በኢትዮጵያ የቀን መቁጣሪያ (ካሌንደር) ላይ ሥራ ተዘግቶ እንዲከበር ቢደረግም ትውልዱ የቀደሙ እናትና አባቶቹን የተጋድሎ ታሪክ እንዲያወቅ የሚያስችል የበዓል አከባበር አይታይም፡፡ ዕለቱም እንደአንድ ተራ የረፍት ቀን ያልፋል፡፡ በአንጻሩ አንዳች አገራዊ ፋይዳ የሌላቸው የህወሃት፣ የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ … የምሥረታ ቀን እየተባለ በብዙ ሚሊዮን ገንዘብ የሚወጣባቸው ለወራት በዕቅድ ተይዘው የሚደገሱ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ ይደረጋል፡፡ “አዲስ አበባ አራት … [Read more...] about ራስ እምሩን በተመለከተ፤
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች! “ክፋት” – በሁሉም መስክ!!
መርዛማ ፍሬ 11፡ የታሪክ መቃብር! በስሜት በሚነዳ የዘውግ ፖለቲካ ውስጥ ታሪክ ትልቅ ማገዶ ሆኖ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ታሪክ አካታችነት ባለው መልኩ በአጎልባች ሚና (ብሔራዊ ተዋፅዖ) መፃፍ እየተገባው ምክንያታዊነትን አስመንኖ የልዩነት ሃረጎችን ብቻ በመምዘዝ በየአቅጣጫው የሚፃፍ መሆኑ ከተካረረ ሙግት ሊፀዳ አልቻለም። መዋቅራዊ ድጋፍ ባለው መልኩ የታሪክ ሙግቱ እየተካረረ በመምጣቱ ብሔራዊ ርዕይ ርቆን የመንደር አጥር እስከመስራት ደርሰናል። ደርግ በየትኛውም ያህል መጠን አምባገነንና ጨፍጫፊ ሆኖ ቢገኝም የኢትዮጵያን ታሪክ ሲንቅና ሲያንቋሽሽ አልተገኘም። ከቶውንም ለብሔራዊ ርዕይ መፍጠሪያነት እንደግብዓት ተጠቅሞበታል። ከመነሻው ጀምሮ ኢትዮጵያዊ ስሜትን (የጋራ ማንነትን) በመካድ ራሱን ብቸኛ የትግራይ ህዝብ ነፃ አውጭ ግንባር አድርጎ የሰየመው ህወሓት፣ የአገሪቱን የረዥም ጊዜ ታሪክ … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች! “ክፋት” – በሁሉም መስክ!!
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች — የአንድ ጎጥ የበላይነትና የመበታተን አደጋ!
ራሳቸውን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር” ብሎ በመሰየም የትግራይን ሕዝብ ሽፋን በማድረግ፤ “የምታገለው ለአንተ ነጻነት ነው” በማለት፤ መልሶ እታገልለታለሁ ያለውን ሕዝብ ያስጨፈጨፈው፣ ያስራበው፣ የግፈ ሰለባ ያስደረገው፣ … ራሱን ህወሓት እያለ የሚጠራው የወንበዴዎች ቡድን የኢትዮጵያን የሥልጣን መንበር ከተቆናጠጠ በኋላ የትግራይ ሰዎችን በሌላው ኢትዮጵያዊ ለማስጠላትና “ስም ለማሰጠት” እንዲሁም ለማጠልሸት ባለፉት 26ዓመታት ሲሰራ ቆይቷል። እነዚህ በኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ አነጋገር “የሰከረ ርዕዮትዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ ያላት አገር ቤተሰብን የመምራትና የማስተዳደር ተሞክሮ የሌላቸው፣ …” የኢትዮጵያን ሃብት እየዘረፉ በትግራይ ኢንቨስት በማድረግ፣ የትግራይ ተወላጆችን የተለያዩ … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች — የአንድ ጎጥ የበላይነትና የመበታተን አደጋ!
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመንግሥት ውሸት፣ የሃይማኖት ተቋማት ውድቀት፣ … (ክፍል ሦስት)
የትግራይ ሕዝብ “ነጻ አውጡኝ” ብሎ ሳይሰይማቸው፣ ሳይመርጣቸው፣ ሳይጠይቃቸው፣ ራሳቸውን “የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር” ብለው የሰየሙ ወንበዴዎችና ሽፍቶች የምኒልክ ቤተመንግሥት ከገቡ 26 ዓመታት ተቆጥረዋል። በቂም፣ በበቀል፣ በክፋትና በኢሞራላዊ ተግባራት የተሞሉ፤ ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ፈጽሞ የሚያጠራጥር፤ ማንነታቸው ይህ ነው ተብሎ የማይታወቅ፤ በሐሰት ስም ከበረሃ እስከ ቤተመንግሥትና ዓለምአቀፍ መድረክ ላይ የታዩ፤ በሐሰት ፕሮፓጋንዳ የትግራይን ሕዝብ ያስጨፈጨፉ (ሐውዜንን ይጠቅሷል)፤ ሲነሱ አንዳች ገንዘብ ያልነበራቸው መናጢዎች በበረሃ የድሃ ረሃብተኛ እህል ዘርፈው በመሸጥ፤ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ደግሞ የኢትዮጵያን ሐብት ሙልጭ አድርገው ዘርፈው ሲያበቁ “የራሳችን ንብረት ነው” በማለት ኤፈርት የሚባል የወንበዴዎች ሃብት ማከማቻ ቋት የፈጠሩ፤ ከበረሃ እስከ መንግሥታዊ ሥልጣን … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመንግሥት ውሸት፣ የሃይማኖት ተቋማት ውድቀት፣ … (ክፍል ሦስት)
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመሬት ነጠቃና ስደት (ክፍል ሁለት)
የዛሬ 26 ዓመት ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) ብሎ የሰየመ የወንበዴዎችና የሽፍታዎች ስብስብ በምዕራባውያን አንጋሾቹ ታግዞ የምኒልክን ቤተመንግሥት ከተቆጣጠረ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቃላት እንደ እሣት እየተፉ ታሪክ ፈጽሞ ሊረሳው የማይችለውን ንግግር ያደረጉት ድንቅ ኢትዮጵያዊ ነበሩ – ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ!! ስለ ኤርትራ መገንጠል እና ስለ ህወሃት የአስፈጻሚነት ተግባር የቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የትንቢት ያህል፤ ሳግ እየተናነቃቸው ይህንን ነበር የተናገሩት፤ “… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮትዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች – የመሬት ነጠቃና ስደት (ክፍል ሁለት)
የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች! (ክፍል 1)
የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ግምባር (ህወሓት) የተባለ የወንበዴዎች ስብስብ በምዕራባውያን አንጋሾቹ ታግዞ የምኒልክን ቤተመንግሥት ከተቆጣጠረ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት ቃላት እንደ እሣት እየተፉ ታሪክ ፈጽሞ ሊረሳው የማይችለውን ንግግር ያደረጉት ድንቅ ኢትዮጵያዊ ነበሩ – ኮ/ሎ ጎሹ ወልዴ!! ስለ ኤርትራ መገንጠል እና ስለ ህወሃት የአስፈጻሚነት ተግባር የቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ኮሎኔል ጎሹ ወልዴ የትንቢት ያህል፤ ሳግ እየተናነቃቸው ይህንን ነበር የተናገሩት፤ “… ሆን ተብሎ በተቀነባበረ እቅድ ህወሃት አዲስ አበባን እንዲቆጣጠር የተወሰነው ውሳኔ አሳዛኝና ከቶውንም ሊታመን የማይችል ነው። የሰከረ ርዕዮትዓለም የሚከተሉ፣ በብሄርና በጎሳ ፖለቲካ ላይ የተተከሉ ጠባብ ቡድኖች፣ በስታሊናዊ መርህ የተጠመቁ፣ እንኳንስ 50 ሚሊዮን ህዝብ … [Read more...] about የ“ግንቦት 20” ሃያ መርዛማ ፍሬዎች! (ክፍል 1)
ፍልሰት፤ ልመናና የጎዳና ህይወት በአዲስ አበባ!
“በመንገዶች አምራ በፎቆች ተውባ” የህወሃት/ኢህአዴግ ኩራት የሆነችው አዲስ አበባ “አገሪቱ አሁን ያለችበት ሂደት በእሳት ላይ ተጥዶ እንደሚንተከተክ ማሰሮ ትመስላለች” አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ሁሉ ነገር ነች፡፡ ከተማዋ ከፖለቲካ ከተማነቷ ባሻገር የኢኮኖሚና የማህበራዊ ዘርፎች ማዕከል መሆኗ የብዙዎችን ትኩረት እንድትስብ አድርጓታል፡፡ በክልሎች የሚታየው የሥራ ዕድል ዕጦት፣ ይህን ተከትሎ የተፈጠረው ሥር የሰደደ ድህነት አዲስ አበባን የከተማ ስደት መከማቻ ማዕከል አድርጓታል፡፡ በርግጥ የከተማ ስደት ስረ-መነሻ ከቀደሙት ጊዜያቶች ጀምሮ የተለያየ መንስኤ አለው፡፡ የኢትዮጵያን የከተማ ስደት ከአገሪቱ ማህበረ-ኢኮኖሚና የፖለቲካ መዋቅር ጋር አስተሳስረው የሚያጠኑ ምሁራን የከተማ ስደትን ከኢትዮጵያ ከተሞች አመሠራረት ጋር አያይዘው የጥናት ውጤታቸውን ያቀርባሉ፡፡ በጥንቱ … [Read more...] about ፍልሰት፤ ልመናና የጎዳና ህይወት በአዲስ አበባ!










