• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የሆላንዱ ወርክሾፕ – ኢትዮጵያ እና መጭው የርስበርስ ጦርነት

September 25, 2016 01:52 am by Editor 2 Comments

ሃገራችን በከፍተኛ ፖለቲካዊ ቀውስ ውስጥ ነው ያለችው። ይህ ቀውስ ወደ እርስበርስ ጦርነት እያመራ ይገኛል። ጉዳዩ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን በኢትዮጵያ ላይ ጥቅም ያላቸው የውጭ ዜጎችንም ማሳሰቡ አልቀረም። በሆላንድ፣ ዘ ሄግ ከተማ፣ ዲያማንት ኮሌጅ 24 ሴፕቴምበር 2016 በተደረው በዚህ ወርክሾፕ በርካታ ኢትዮጵያውያን እና የሆላንድ ዜጎች ተገኝተው ነበር። በወርክሾፑ እንዲወያዩ የተጋበዙት ታዋቂው ፕሮፌሰር ጆን አቢንክ፣ መስፍን አማን እና ገረሱ ቱፋ ናቸው። አወያዮቹ ሚ/ር ፍራንስ እና አብይ አሸናፊ ነበሩ።

ethi-holland2ተናጋሪዎቹ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ከፍተኛ ቀውስ በማስረጃ እያጣቀሱ ካብራሩ በኋላ የገዥው ፓርቲ አጠያያቂ ህጋዊነት እና የማክተሙ አዝማምያን ያመላከተ ድምዳሜ ሰጥተዋል።

መጪውን ሁኔታ የሚጠቁሙ ሶስት ቢሆኖች (Scenarios) ላይም የውይይቱ ተሳታፊዎች አስተያየቶቻቸውን ሰጥተዋል።

አንደኛው ቢሆን (Scenario) የፕ/ር መስፍን ወልደማርያም፣ ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ እና የዶ/ር ዳዊት ወልደጊዮርጊስ በመገናኛ ብዙሃን የተሰራጩ አስተያየቶች ሲሆኑ፤ በጥቅሉ ኢትዮጵያ ወደ እርስበርስ ጦርነት እንደምታመራ የሚጠቁመው እይታ ነው።

ሁለተኛው ቢሆን በገዥው ፓርቲ እየተነገረ ያለው የተሃድሶ ለውጥ የሚለው እንቅስቃሴ ሲሆን፤

ሶስተኛው ቢሆን ደግሞ የሽግግር መንግስት ይቋቋማል፣ ከዚያም ፍትሃዊ ምርጫ ይደረጋል የሚለው ግምት ነው።

ሶስቱም ተናጋሪዎችም ሆኑ በአዳራሹ ያሉ ተሳታፊዎች ሁለተኛው እና ሶስተኛው ቢሆኖች የማይታሰቡ እንደሆኑ አስምረውበታል። በተለይ ሁሉንም አካላት ያካተተ የሽግግር መንግስት ተቋቁሞ ፍትሃዊ ምርጫ ቢደረግ ችግሩ እንደሚፈታ ፕ/ር ጆን አቢንክ ተናግረዋል። ነገር ግን ከገዥው ፓርቲ የረጅም ግዜ ተመክሮ እና  ባህርይ አንጻር ይህ ሊሆን አይችልም። ገዥው ፓርቲ ለትይታ ብቻ የሚሆን ቅርጻዊ ለውጥ (cosmetic changes) በማድረግ መቆየት መርጣል ይላሉ።

መስፍን አማን እና ገረሱ ቱፋም አንደኛው ቢሆን ላይ ነው የሚያመለክቱት፣ “ከሁሉም ቢሆኖች እርስበርስ ጦርነቱ መጥፎው አማራጭ ቢሆንም፣ ይህ ሊሆን ግድ ሆኗል። ጠቅላይ ሚንስትሩ የህዝቡን ጥያቄ ለማፈን ሰራዊቱን ሲያዙ ነው ጦርነት ያታወጀው።  ሃገሪቱ አንደኛውን በርስበርስ ጦርነት ውስጥ ገብታለች” ባይ ናቸው።

የዲያስፖራው ሚናም በውይይቱ ተነስቷል። ዲያስፖራው ከዘር እና ከጎሳ ውይይት አልፎ በጋራ ችግሮች፣ በብሄራዊ ጉዳዮች ላይ እንዲወያይ ፕሮፌሰር አቢንክ መክረዋል።

ገረሱ ቱፋ  እና ከመስፍን አማንም የኦሮሞ እና አማራ ተወላጆች በግል የማንስማማባቸው ብዙ ጉዳዮች ቢኖሩም በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጠን በሃገሪቱ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር እና መፍትሄ ለመፈለግ ችግር የለብንም ብለዋል። ከስብሰባው በኋላ የኦሮሞ እና አማራ ኮሚኒቲ አባላት የጋራ መድረክ ለመመስረት ተስማምተዋል።ethi-holland3

እንደዚህ አይነት የኢትዮጵያ የፖለቲካ ውይይት ሲካሄድ የሆላንድ ዜጎች በተለምዶ ተገኝተው አያውቁም ነበር። በዚህ ውይይት ላይ አሁን ለመገኘት የፈለጉበት ምክንያትም ግልጽ ነው። በሃገሪቱ እየተካሄደ ያለው ህዝባዊ አመጽ የሆላንድን ብሄራዊ ጥቅም ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን የዳች ሜዲያ ተቋማት እየገለጹ ነው። በአስር ሚሊዮን ዩሮ ኢንቨስትመንት  ከአመት በፊት ኢትዮጵያ በመግባት አበባ ምርት የተሰማራው ኩባንያ በባሕርዳር ህዝባዊ አመጽ ሙሉ በሙሉ ወድሞ ስራውን በይፋ አቁሟል። ጊንጪ ላይም የሆላንድ የእርሻ ኩባንያ ከጥቅም ውጪ መሆኑ በዜና ተሰምቷል። ይህ ጉዳይ ሄነከን ቢራን ጨምሮ ለተቀሩት 130 የሚሆኑ የሆላንድ ኩባንያዎች ላይ ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል።

ክንፉ አሰፋ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Mulugeta Andargie says

    September 26, 2016 07:18 pm at 7:18 pm

    ጓዶች!! የሌለ ነገር እየፈጠራችሁ ሰው አታደናግሩ! ሁሉም ሰው በሰላም ለመኖር ይፈልጋል! የምትጠቅሷቸው ሰዎች ሁሉ ፋይዳ ሰጪዎች አይደሉም!! ወሳኙ ሃገር ውስጥ ያለው ህዝብ ነው!

    Reply
    • ማህሌት says

      September 29, 2016 07:47 am at 7:47 am

      የምትሰጠው አስተያየት ማንነትህን ስለሚያሳይ መልስ ባያስፈልግህም የበላህን እያከከው እንደሆነ ያስታውቃል ወያኔ ሞቱ ደርሶ ሲፈራገጥ እንዳንተ ያሉ ደጋፊዎቹ እውነቱ አልዋጥም ቢላችሁ አይገርምምናት!!

      Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule