የህወሓት ዘመን ማብቂያው አካባቢ ኃይለማርያም ደሳለኝ “ከሥልጣኔ ለቅቄአለሁ” ካለ በኋላ ለጠ/ሚ/ር ቦታ በተደረገው ሽኩቻ ዶ/ር ዐቢይ (የለማ ቡድን) አሸንፎ በወጣ ጊዜ የህወሓት ቡድን ወደ መቀሌ ሄዶ ሲመሽግ ስብሃት ነጋ በተፈጠረው ተናድዶ የሚከተለውን መናገሩ ታማጭ የመረጃ ምንጫችን አስታውቆናል። ስብሃት ነጋ በትግሪኛ የተናገረውና በአማርኛ ተተርጎመው የስብሃት ንግግር እንዲህ ይነበባል፤ “(ደመቀ) ለትህነግ ታማኝና ታዛዥ ነበር። ፈፅም! የተባለውን ነገር ለመፈፀም 'ለምን?' ብሎ እንኳን አያውቅም። አንድ ቀን ግን የሱዳን ግዛት የሆነውን አዋሳኝ መሬት ለመስጠት ‘ፈርም’ ሲባል ‘አይሆንም አልፈርምም!’ ብሎ አሻፈረኝ ሲል ያኔ ይህ ሰው አንድ ቀን እንደሚሸውደን እርግጠኛ ሁኜ ለጓዶቼ ነግሬያቸው ነበር። ሁሉም የእኔን እይታ ሳያቅማሙ ሲቀበሉኝ ጌታቸው (አሰፋ)ግን ‘አታስብ እሱ … [Read more...] about ስብሃት ነጋ ስለ ደመቀ መኮንን፤ “ደመቀ የሸወደንን ያክል መሰሪው ጀበሃ (ሻእቢያ) እንኳን አልሸወደንም!”
sibhat
ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”
እንደ ህወሓት ያለ አስገራሚ የፖለቲካ ቡድን ያለ አይመስለኝም። በጣም ገራሚ ነው። ከአመታት በፊት ያስቀመጥከው ቦታ ቁጭ ብሎ ይጠብቅሃል። በራሱ ምንም ዓይነት ለውጥ እንዲመጣ አይሻም። ከራሱ ባለፈ በሌሎች ዘንድ ምንም ዓይነት ለውጥና መሻሻል እንዲኖር አይፈቅድም። ከሁለት አመት በፊት ህወሓት “ቆሞ-ቀር” እንደሆነ የሚገልፅ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። ዛሬም ቢሆን ከነበረበት ቦታ ንቅንቅ አላለም። ህወሓት ፀረ-ለውጥ ድርጅት ከመሆኑ በተጨማሪ ሥር የሰደደ የአመራር ችግር አለበት። በመሆኑም ህወሓት ራሱን ለለውጥ ማንቀሳቀስ ሆነ መምራት አይችልም። በተለይ የመለስ ዜናዊ ህልፈትን ተከትሎ ህወሓት “በቁሙ መሞት” ጀምሯል። ከመለስ ዜናዊ ቀጥሎ የህወሓት ሊቀመንበር የሆኑት አባይ ወልዱ ናቸው። ሰውዬው እንደ መለስ ዜናዊ ሸርና አሻጥር መጎንጎን አልቻሉበትም። በመሆኑም የመለስ ዜናዊ የነፍስ አባት … [Read more...] about ህወሓት፤ “ቆሞ ቀር” ብቻ ሳይሆን “ቆሞ ሙት”


