በአፍሪካ ህብረት 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ ከሚገኙት የተለያዩ እንግዶችና ባለስልጣናት በተጨማሪ አራት ታላላቅ መሪዎች እንደሚገኙ እየተነገረ ነው። በዋናነት የሚጠቀሱት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ኦባማ ሲሆኑ፣ የቻይና አቻቸውም ዋናውና ታላቁ እንግዳ እንደሚሆኑ ይጠበቃል። የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባለፈው ረቡዕ ለአሜሪካ ኮንግረንስ ኮሚቴ የተናገሩትን በመጥቀስ ዜናውን የላኩልን ክፍሎች እንዳሉት ኦባማ ወደ ኢትዮጵያ ሊያመሩ ይችላሉ። ውጪ ጉዳይ ሚ/ሩ ኦባማ ኢትዮጵያ ስለመሄዳቸው ፍንጭ ቢሰጡም ስለጉዞው ዝርዝር አለመናገራቸው ታውቋል። የቻይና በአፍሪካ ሚና መጉላት ውሎ አድሮ የጠዘጠዛት አሜሪካ፣ በመጪው ወር በሚካሔደው የአህጉሩ 50ኛ ዓመት ክብረ በዓል ላይ በፕሬዚዳንቷ ለመወከል መወሰኗ "ጉባኤ አድማቂ" አሰኝቷታል። "በአፍሪካ ብዙ የምንሰራው ስራ አለን" ሲሉ የተናገሩት ኬሪ … [Read more...] about ኦባማ አርፍደው ወደ ኢትዮጵያ?
Full Width Top
“ማፈናቀሉ የሚካሄደው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው፤ ወደ ክስ እናመራለን”
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ከ2000 ሺህ በላይ ትግሬዎች ባለይዞታ መሆናቸውንና ማንም ሳይነካቸው በሰላም እንደሚኖሩ፣ በቶጎ ወረዳ ከስልሳ በላይ ነባር የህወሃት ታጋዮች ሰፋፊ የእርሻ መሬት ወስደው በባለሃብት ደረጃ እንደሚገኙ የመኢአድ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል አስታወቁ። ከሌሎች ብሔረሰቦች ተለይቶ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመበት ያለውን የአማራ ብሔረሰብ በድጋሚ ለማስወጣት መታቀዱንም በመረጃ ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል። በቦታው በመገኘት አስፈላጊውን መረጃ እንደሰበሰቡ ለአሜሪካ ሬዲዮ የገለጹት የመኢአድ ስራ አስፈጻሚ በክልሉ ከሚኖሩት የተለያዩ ብሔረሰቦች ተለይቶ የአማራ ብሔረሰብ እንዲፈናቀልና እንዲሰቃይ የሚደረገው በማዕከላዊ መንግስት ትዕዛዝ እንደሆነም አመልክተዋል። መኢአድ ያሰራጨውን መግለጫ ተከትሎ በተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ የሰጡት አቶ ሃይሉ ሻወል፣ ድርጊቱ በበታች … [Read more...] about “ማፈናቀሉ የሚካሄደው በመንግሥት ትዕዛዝ ነው፤ ወደ ክስ እናመራለን”
ኢህአዴግን በጓሮ ድርድር የጠየቀበት ሰነድ ተተረጎመ!
በልማትና ኢንቨስትመንት ስም ኢህአዴግ ለውጪና ለራሱ ሰዎች እየቸበቸበ ያለውን መሬት አስመልክቶ የኦክላንድ ተቋምና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ በጋራ ያዘጋጁት ጥናታዊ ዘገባ አማርኛ ትርጉም በሳምንቱ መጨረሻ ይፋ ይደረጋል ተባለ። የመሬት ነጠቃ ዜጎችን እያፈናቀለና ውድ የተፈጥሮ ሃብትን እየበላ ነው። እመራቸዋለሁ ለሚለው ህዝብና አገር ደንታ የሌለው ኢህአዴግ፣ በመረጃ ለሚያጭበረብራቸው ዜጎች የተሟላና የተመጣጠነ ዘገባ እንደሚያቀርብ የተነገረለት ይህ ሰነድ በአማርኛ ተተርጉሞ ይፋ እንደሚሆን የገለጸው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ የሚዲያና የህዝብ ግንኙነት ዴስክ ነው። የጋራ ንቅናቄው የህዝብ ግንኙነት ዴስክ በተለይ ለጎልጉል በሰጠው መረጃ በጥናቱ ሰለባዎች፣ የኢህአዴግ ባለስልጣናት፣ ኢንቨስተሮች፣ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች፣ የቅርብ ምስክሮች፣ የተለያዩ ከዓለምአቀፍ ተቋማት … [Read more...] about ኢህአዴግን በጓሮ ድርድር የጠየቀበት ሰነድ ተተረጎመ!
“አማራንና አማርኛን ማጥፋት የህወሃት ፕሮግራም ነው”
አማርኛ ተናጋሪዎችን የማመናመን፣ የማደህየት፣ የማራቆትና ክልላቸውን እያሳነሱ የማጥፋት እቅድ በህወሃት መርሃግብር ውስጥ የተካተተ ዋና ተግባር እንደሆነ ተገለጸ። አማርኛ ቋንቋንም ማሽመድመድ የዚሁ እቅድ አካል መሆኑ ተዘግቧል። አቶ ገ/መድህን አርአያ ከኢሳት ሬዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ በህወሃት ፕሮግራም ገጽ 18 አካባቢ "አማራ የትግራይና የኤርትራ ህዝብ ጠላት እንደሆነ ተመልክቷል" ብለዋል፡፡ አያይዘውም አማራ ማጥፋት የቅስቀሳው ዋና መሳሪያ ቢሆንም የትግራይ ህዝብ አልተቀበለም ብለዋል። ቅስቀሳውን አንቀበልም ያሉ "የትግራይ ሸዋ" ተብለው መገደላቸውን ይፋ አድርገዋል። በተለይ የድርጊቱ ዋና አስተባባሪ በማለት የጠቀሷቸው አቶ መለስ ዜናዊ፣ አቶ ስብሃት፣ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ አባይ ጸሐዬን የጠቀሱት አቶ ገ/መድህን፣ በ1972 በሰሜን ጎንደር የዘር ማጥፋት ወንጀል መፈጸሙን … [Read more...] about “አማራንና አማርኛን ማጥፋት የህወሃት ፕሮግራም ነው”
መሬት ነጠቃ ለአሜሪካ ም/ቤት ሊቀርብ ነው
በመጪው ሰኞ ሚያዚያ7፤2005ዓም (April 15፣ 2013) በአፍሪካ ስለሚደረገው የመሬት ነጠቃ አስመልክቶ የአሜሪካ ም/ቤት የፖሊሲ አውጪዎችና በጉዳዩ ላይ የሚሟገቱ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችን እንዲሁም ባለሙያዎችን ሃሳብ ለማዳመጥ ስብሰባ መጥራቱ ታወቀ፡፡ በአሜሪካ የተወካዮች ምክርቤት በአፍሪካ፣ በዓለምአቀፍ ጤና፣ በዓለምአቀፍ የሰብዓዊ መብቶችና ዓለምአቀፋዊ ድርጅቶች ንዑስኮሚቴ ሊቀመንበር የሆኑት ክሪስ ስሚዝ ከፍተኛ አማካሪና የአፍሪካ ኤክስፐርት የሆኑት ግሬጎሪ ሲምፐኪንስ ስብሰባውን እንደሚመሩትም ከወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በአፍሪካ የሚካሄደውን የመሬት ነጠቃ አስመልክቶ በተጠራው ስብሰባ ላይ መግለጫ ከሚሰጡት አፍሪካውያን መካከል ጋናዊው ምሁር ዶ/ር ጆርጅ አዪቴ የሚገኙበት ሲሆን ከኢትዮጵያ ብቸኛው ተጠቃሽ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር … [Read more...] about መሬት ነጠቃ ለአሜሪካ ም/ቤት ሊቀርብ ነው
የሌንጮ ለታ አዲሱ ትግል – እንዴት?
ላለፉት አርባ ዓመታት ለኦሮሞ ህዝብ ነጻነት ሲታገል የቆየው ኦነግ አመራሮቹ ሲጣሉና ሲታረቁ መስማት የተለመደ ነው። የግለሰብ ጸብ የሚመስለው የድርጅት በሽታ ሲንጠው የቆየው ኦነግ በውል ባይታወቅም ተሰነጣጥቆ ለሰሚው ግራ የሚያጋባ ድርጅት ከሆነም ዓመታት ተቆጥረዋል። ስህተትን ገምግሞ የትግል አቅጣጫና ፕሮግራም ከመቀየር ይልቅ ጊዜው ባለፈበት አስተሳሰብ ባለበት ሲረግጥ እድሜውን የፈጀ ድርጅት እንደሆነ ተደርጎም ይወሰዳል። ስለ ኦነግ ሲነሳ አብዛኞች በመገረም የሚናገሩትና ሚዛን የሚደፋው አስተያየት የሚሰነዘረው በድርጅቱ መከፋፈልና መበጣጠስ ሳይሆን ተለያይተውም አስመራን የሙጥኝ ያሉበት ምክንያት ነው። ኢህአዴግ ህጻን እያለ ሻዕቢያ እንዳሻው ይነዳው እንደነበር የሚያስታውሱ አስተያየት ሰጪዎች ከሽግግር መንግስት ምስረታ በኋላ ኦነግ አገር ለቆ እንዲወጣ መንገዱን የጠረገው ሻዕቢያ መሆኑንን … [Read more...] about የሌንጮ ለታ አዲሱ ትግል – እንዴት?
መንግስት አቀባባይ የሆነበት የእህቶቻችን ስቃይ
"በግል ጥሪ የላከልኝ የለም። ያገባኛል የምትሉ እንድትገኙ የሚል መልዕክት ሰማሁና መጣሁ። የማውቀውንና ያየሁትን እውነት ተናገርኩ። ስቃዩ ከሚነገረው በላይ ነው። የሚነገረውና በተግባር የሚደርሰው በእጅጉ የተለያየ ነው ..." በማለት ምስክርነቷን ችግሩን ለመፍታት መንቀሳቀስ ለጀመሩት ወገኖች ማካፈሏን የምትናገረው ወ/ት ዘቢባ ዘለቀ ናት። በንግግሯ ሁሉ መፍትሔ አንዲፈለግ አበክራ ትጠይቃለች። በቡድን ተደፍረው፣ በመከራ አልፈው፣ በስልክ የሚጠየቀው ተከፍሎላቸው ጂዳና ሪያድ የሚገቡትን እህቶች አግኝታ አነጋግራለች። በቡድን የተደፈሩት እህቶች መንፈሳቸው የተሰበረ ነው። በፍጹም ስነ ልቦናቸው የሚያገግም አይመስልም። ጭው ባለ በረሃ መጫወቻ ሆነው ያሰቡበት ደርሰው ያገኘቻቸው የሚነገራቸውና የሚያጋጥማቸው ፈጽሞ የተለያየ እንደሆነ ለጎልጉል በስልክ አስታውቃለች። በህጋዊ መንገድ በኤጀንሲ ካገር … [Read more...] about መንግስት አቀባባይ የሆነበት የእህቶቻችን ስቃይ
ኢህአዴግን “አድርባይ” አመራሮች አስግተውታል
ኢህአዴግ አመራሮቹን “አድርባይነት የተጠናወታቸው” ሲል ፈረጀ። የከፍተኛ አመራሮች የግምገማ ውጤት የሆነውን ፍረጃ የሰሙ “የኢህአዴግ አባል ለመሆን አንዱና ዋናው መስፈርት አድርባይነት ነው” በማለት አድርባይነትን የፈጠረውና ያስፋፋው ራሱ ኢህአዴግ፣ በተለይም ህወሃት እንደሆነ አመለከቱ። በባህር ዳሩ የኢህአዴግ ጉባኤ ላይ ተገኝቶ የነበረ ጋዜጠኛ በምሥጢር የላከው ዜና “አድርባይነት” ኢህአዴግን በሚፈታተን ደረጃ መስፋፋቱ መገለጹ አብዛኞችን የድርጅቱን አባላትን አስገርሟል። ኢህአዴግን የፈጠረውና ከላይ ሆኖ የሚመራው ህወሃት “ነጻ” አመለካከት የማይወድ፣ የነጻ አስተሳሰብ ባህል የሌለው፣ ራሳቸውን የቻሉ ድርጅቶችን፣ ፓርቲዎችንና ማህበራትን አጥብቆ የሚጠላ፣ ሁሉም ለሱ እያጎበደዱ በሚሰፈርላቸው ቀለብ እንዲኖሩ ሌት ከቀን የሚሰራ መሆኑ እየታወቀ ማንን? ለምንና እንዴት አድርባይ በሚል … [Read more...] about ኢህአዴግን “አድርባይ” አመራሮች አስግተውታል
ወ/ሮ አዜብ ተጨንቀዋል!
አቶ መለስ ከሞቱ ጀምሮ በተለያዩ መድረኮች ንግግርና መዕልክት የሚያስተላልፉት ወ/ሮ አዜብ መስፍን መረጋጋት እንደማይታይባቸው ተገለጠ። አሁንም በባለቤታቸው ስምና መንፈስ ሙግትና ማብራሪያ ከማቅረብ አልተላዘቡም። ይህን የሚያደርጉት ከጭንቀት የተነሳ እንደሆነ ተመልክቷል። ሰሞኑንን በተጠናቀቀው የኢህአዴግ ጉባኤ አቶ መለስን አስመልክቶ ወ/ሮዋ የተናገሩት ንግግር በጭንቀት ውስጥ ስለመሆናቸው ማሳያ እንደሆነ የተናገሩት አብረዋቸው ባህር ዳር ስብሰባ የተቀመጡ የድርጅታቸው ኢህአዴግ “ባልደረቦቻቸው” ናቸው። በጉባኤው ወቅት አቶ መለስ ዜናዊን በማወደስ የተዘጋጀው “ዝክረ – መውደስ” ታሪካዊ ሰነድ እንዲሆን ከመጽደቁ በፊት ወ/ሮ አዜብ በሰጡት አስተያየት “በፔሮል የሚከፈለው ብቸኛ መሪ መለስ ብቻ ነው” በማለት ራሳቸውን ጨምሮ ሌሎች አመራሮች በፔሮል በሚከፈላቸው ገንዘብ ብቻ እንደማይኖሩ … [Read more...] about ወ/ሮ አዜብ ተጨንቀዋል!
ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሶስት)
ሀገሬ አንዳንዴ ከሰሜን ወደ ደቡብ፣ ከምስራቅ ወደ ምእራብ የዘረጋሻቸውን ጎዳናዎች፣ ልታነጥፊያቸው ደፋ ቀና የምትይላቸውን ሀዲዶች ስመለከት ደስ ይለኛል። የአዲስ አበባን አስፋልትና በየአስፋልቱ ዳር ያቆምሻቸውን ህንፃዎች አዲስነት ስመለከት ደግሞ፣ ‹‹ቆይ ሀገሬ፣ መንገድም፣ ህንፃም አልነበራትም እንዴ?›› ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ። እውነቴን ነው የምልሽ ሀገሬ ግንባታሽን ለተመለከተ ፈርሶ የሚሰራ ሀገር ነው እኮ የምትመስይው! ግን እኔ ልማትሽን፣ እድገትሽን፣ ትራንስፎርሜሽንሽን . . . አልነግርሽም! እንደነገርኩሽ ጉዳዬ ከገመናሽ ነው። ለልማት ለትራንስፎርሜሽንማ ራዲዮና ቲቪሽ መች አነሰሽ! ዋናው ራዲዮና ቲቪ አልበቃ ብሎ ኤፍ.ኤም፣ ኢቲቪ1፣ ኢቲቪ 2 . . . ልማትና እድገትሽ ራስምታትሽ እስኪሆን ይነግርሽ የለ! ነጋሪ ያጣው እኮ ገመናሽ ነው! እና እኔ ልጅሽ ልንገርሽ! በትልልቅ … [Read more...] about ሀገሬ ገመናሽ (ክፍል ሶስት)










