“ሙሉ ኢትዮጵያዊ ነኝ” ትላለች። የተወለደችው ዱከም ነው። በቀድሞው አጠራር በኢትዮጵያ የተለያዩ ጠቅላይ ግዛቶች ኖራለች። ሐረር፣ ባህርዳር፣ አስመራ፣ አዲስ አበባን በመጥቀስ ልዩ ትዝታዎች እንዳሏት ትናገራለች። ከዛሬ ሃያ ዓመት በፊት አሜሪካ ከትማለች። “ፖለቲከኛ አይደለሁም፣ እኔ አገር ወዳድ ነኝ። አገሬ የማንኛውም ጉዳዮቼና የውሳኔዎቼ በሙሉ መለኪያ ሚዛኔ ናት" ትላለች። ለአገሯ ማድረግ የሚገባትን እንዳላደረገች ይሰማታል። የይሉንታ ፖለቲካ ችግርና መዘዝ ያሳስባታል። በመናገርና ሃሳብን በነጻነት ስለመግለጽ ያላት አቋም የጸና መሆኑን አትደብቅም። በማህበራዊ ገጾች ንቁ ተሳታፊና መረጃ በማስተላለፍ በርካታ ተከታታዮች አሏት። በኢትዮጵያውያን የወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ አስተባባሪ ከሆኑት አንዷ ኃላፊ (አድሚን) ናት። ቤተሰቦቿ ካወጡላት መጠሪያዋ ይልቅ ራስዋ ለራስዋ ስም ተክላለች። … [Read more...] about “የይሉኝታ ፖለቲካ ይገድላል”
Full Width Top
ሼኽ አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን ካሩቱሪን ለመጠቅለል አስበዋል
በኢትዮጵያ ባሏቸው ኢንቨስትመንቶች መልከ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው የሚነገርላቸው ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን የካሩቱሪን የእርሻ መሬት ለመግዛት ከድርድር ላይ ናቸው ተባለ። ድርድሩ በስምምነት ከተቋጨ የሳዑዲን የምግብ አቅርቦት ለመሸፈን የሚንቀሳቀሱት "ባለሃብት" በጋምቤላ ብቻ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ ድንግል መሬት ባለቤት ይሆናሉ። በድርድሩ መሰረት እስከዛሬ ከወሰዱት በተጨማሪ ብድርም ከንግድ ባንክ ያገኙበታል። የሳዑዲን የምግብ ኮታ ለመሸፈን ታስቦ እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሳዑዲ ስታር አግሮ ኢንዱስትሪ በ2001 ዓ ም 10ሺህ ሄክታር መሬት ተረክቦ በጋምቤላ ስራ ሲጀምር ተጨማሪ 500 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚሰጠው ቃል ተገብቶለት እንደነበር በወቅቱ የተለያዩ መገናኛዎች ዘግበው ነበር። ሳዑዲ ስታር የስራ አቅሙ ተገምግሞ መሬት እንደሚጨመርለት ቃል ቢገባለትም … [Read more...] about ሼኽ አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን ካሩቱሪን ለመጠቅለል አስበዋል
በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ ዓመጽ ተካሯል
አመጹ ከካምፕ ወደ ካምፕ እየተዛመተ ነው በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ተመዝግበው በትግራይ-ኤርትራ ድንበር ዳርቻ በስደት ማቆያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ የኤርትራ ተወላጅ ስደተኞችና በኢህአዴግ መካከል የተፈተረው አለመግባባት ተካሯል። የሰው ህይወት ማለፉና ነጻ እንቅስቃሴ መከልከሉ ተሰምቷል፤ እስካሁን ስድስት ሞተዋል፤ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ በርካታዎች ቆስለዋል። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውና በአውሮፓ ተቀምጠው ጉዳዩን የሚከታተሉ የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኦክቶበር 5 ቀን 2013 ምሽት ላይ በትግራይ ማይ ዓይኒ ወረዳ በሚገኝ የስደተኞች ካምፕ የተቀሰቀሰው ረብሻና ተቃውሞ ወደ ሌሎች ካምፖችም ተዛምቷል። በተለይም በትላንትናው እለት ሽሬ አካባቢ በሚገኘው አድ ሃሪሽ ካምፕ የተነሳው ተቃውሞ ጋብ ሊል የቻለው ኢህአዴግ ሃይል በመጠቀሙ እንደሆነ ተመልክቷል። በዚህም የሃይል ርምጃ … [Read more...] about በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ ዓመጽ ተካሯል
የምርትና የሕዝብ እድገት እሽቅድድም
እአአ በ1798 (ከሁለት መቶ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት) መምሬ ቶማስ ሮበርት ማልቱስ የሚባል የ32 ዓመት የብሪታንያ ቄስ የዘመኑን የነገረ ንዋይ አስተሳሰብ የለወጠ አዲስ ሀሳብን የያዘ መጽሐፍ አሳተመ፤ ሀሳቡ በጣም ግልጽ ነበረ፤ የሰው ልጆች ቁጥር እድገት መጠኑ እያጠፈ የሚሄድ ነው፤ የሕዝብ ቁጥር 1፣ 2፣ 4፣ 8፣ 16፣ 32፣ 64፣ 128፣ እያለ የሚጨምር ነው፤ ከእርሻ የሚገኘው ምርት ደግሞ የእድገቱ መጠን አያጥፍም፤ 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 8፣ 9፣ 10፣ እያለ የሚሄድ ነው፤ የመምሬ ማልቱስን ሀሳብ በሌላ መንገድ ካየነው የበላተኞች ቁጥር እያጠፈ ሲያድግ የምግቡ አቅርቦት የሚያድገው ግን በጣም በዝግተኛ ፍጥነት ነው፤ የሚል ነው፤ እንግዲህ የሕዝብ ቁጥርና የምርት አቅርቦት እኩል መጓዝ ሲገባቸው የሕዝቡ ቁጥር እየቀደመ ስለሚገኝ፣ መምሬ ማልቱስ የደረሰበት … [Read more...] about የምርትና የሕዝብ እድገት እሽቅድድም
ተስፋዬ ገ/አብ እንደ “ካቡጋ”
በጋዜጠኛነት ስም መድረክ በማበጀት በኢትዮጵያዊያን ሚዲያ ኢትዮጵያን ለማፈራረስና ህዝቧ እርስ በርስ እንዲባላ ተልዕኮውን ሲያስፈጽም የነበረው ተስፋዬ ገብረ አብ በሰነድ የተረጋገጠ ማንነቱ ገሃድ ሆነ። ዜናውን የሰሙ እንዳሉት ተስፋዬ ካሁን በሁዋላ "በቁሙ ሞተ" ነው የሚባለው ሲሉ ተደምጠዋል። በኢትዮጵያ የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት ይሰሩ እንደነበር የገለጹ የጎልጉል መረጃ ሰጪ "ተስፋዬ አስቀድሞም ቢሆን ሆን ብሎ በተቀነባበረ ስልት ጦርነቱ ሊጠናቀቅ ሲል ወታደር እንዲሆን የተደረገ የሻዕቢያ ሰላይ እንደነበር ይታወቃል" በማለት ለጎልጉል ተናግረዋል። "ተስፋዬ አሁንም በደም ከሚገናኛቸው የህወሃት ሰዎችና የደህንነት የላይኛው መረብ ጋር ግንኙነት አለው" ያሉት እኚሁ ሰው አጋጣሚው “በወያኔ ላይ ጠጠር የሚጥል ሁሉ …” በሚል ጭፍን አመለካከት በጅምላ ለምንነዳ ወገኖች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ … [Read more...] about ተስፋዬ ገ/አብ እንደ “ካቡጋ”
ድሆችን ያፈናቀለው “ኢንቨስትመንት” ዕዳ ዋጠው
"መሬታችንን ለምን እንነጠቃለን?” በማለት የጠየቁ ተገድለዋል። ተገርፈዋል። ታስረዋል። አሁን ድረስ እስር ላይ የሚገኙ አሉ። ባዕድ እንኳን ባልሞከረው የከፋ ጭካኔ በከባድ መሳሪያ በተደገፈ የጦር ሃይል የተወለዱበትን መሬት እንዲለቁ የተገደዱ አዛውንቶች ላይ የተፈጸመው ግፍ እስከ ወዲያኛው የሚያሽር አይደለም። በሌሊት እርቃናቸውን ከሚያርፉበት ታዛ ስር ነፍጠኛ ሰራዊት እንዲከባቸው እየተደረገ የተፈጸመው አስነዋሪ ግፍ ጊዜ የሚጠብቅ እንደሆነ በየጊዜው የሚገለጽ ነው። “የዘራሁትን ሳላነሳ በዶዘር ማሳዬን ጠረጉት፣ በዶዘር እርሻዬ ውስጥ ገብተው አረሱት፣ መሬቴን ለምን ትወስዳላችሁ? የት ልትወስዱኝ ነው? ያሸተውን በቆሎዬን መነጠሩት። ምን ላደርግ እችላለሁ። መሳሪያ የያዙ ወታደሮች ከበውኛል፣ ጠዋት ስነሳ ማሳዬ ባዶ ሆኖ አገኘሁት … " ይህ ሁሉ የበደል ሰቆቃ ነው። በምስል ተደግፎ የቀረበ … [Read more...] about ድሆችን ያፈናቀለው “ኢንቨስትመንት” ዕዳ ዋጠው
“ወሲባዊ ጂሃድ (ጂሃድ አል-ኒቃ)” በሶሪያ!
የቱኒዚያ ሴቶችና ልጃገረዶች በሶሪያ የአሳድን መንግሥት እየተፋለሙ ከሚገኙት እስላማዊ አማጺያን ጋር “ወሲባዊ ጂሃድ” በመፈጸም በጦርነቱ ላይ ተሳትፏቸውን እየገለጹ መሆናቸው ተነገረ፡፡ በሌላ በኩል በዚሁ ጦርነት ላይ በሳውዲ አረቢያ የሞት ፍርድ የተበየነባቸው ወንጀለኞች እንዲሳተፉ እየተላኩ መሆናቸው ተረጋገጠ፡፡ በያዝነው የመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ የቱኒዚያው የአገር ውስጥ ሚኒስትር ሎትፊ ቢን ጄዱ በአገሪቱ ፓርላማ ፊት ቀርበው እንደተናገሩት በጦርነቱ ከፍተኛ መስዋዕትነት እየከፈሉ ለሚገኙት ተዋጊዎች ማደፋፈሪያ እንዲሆንና በትግሉ የነርሱንም ድርሻ ለመወጣት የቱኒዚያ ሴቶችና ልጃገረዶች ራሳቸውን በ“ወሲባዊ ጂሃድ” በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡ በአረቡ ዓለም በሚገኙ የዜና ማሰራጫዎች በሰፊው የተዘገበው ይህ ዜና እንደሚያስረዳው ሚኒስትሩ ጉዳዩ አሳሳቢ ደረጃ ላይ … [Read more...] about “ወሲባዊ ጂሃድ (ጂሃድ አል-ኒቃ)” በሶሪያ!
ሙስሊም ወንድማማች ዕገዳ ተጣለበት
የካይሮው አስቸኳይ ጉዳዮች ፍርድቤት የሙስሊም ወንድማማችን እና ከእርሱ ጋር ግንኙነት ያላቸውን መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን በሙሉ ከማንኛውም እንቅስቃሴ አገደ፡፡ የመካከለኛው ምስራቅ የዜና አገልግሎትን ጠቅሶ አልጃዚራ እንደገለጸው ዕገዳው መሐመድ ሙርሲ ይመሩት የነበረውን እና ከሙስሊም ወንድማማች ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያለውን የእስላማዊው እንቅስቃሴ የፖለቲካ ክንፍ የነጻነትና ፍትሕ ፓርቲንም ሊጨምር ይችላል፡፡ በሕዝብ ድምጽ ሥልጣን የተረከቡትን መሐመድ ሙርሲ በመፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ከተወገዱ በኋላ የሙስሊም ወንድማማች ደጋፊዎችና ከፍተኛ አመራሮች አሁንም እየታሰሩና እየተገደሉ ይገኛል፡፡ ከፖሊስና፣ ከደኅንነትና ከመፈንቅለ መንግሥቱ ደጋፊዎች ጋር የሚደረገው ውዝግብ ደም አፋሳሽ ከመሆን አልፎ በወንድማማቾቹ እንቅስቃሴ ላይ “የአሸባሪነት” ታርጋ አስለጥፎበታል፡፡ ከዚሁ ጋር … [Read more...] about ሙስሊም ወንድማማች ዕገዳ ተጣለበት
አሳዛኙ የወገናችን ኅልፈት!
ዲፕሎማቱ እጅ ላይ ያረፈችው ኢትዮጵያዊት ወጣት ሬሳ ትላንት ከሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወሰደ ። ቀን መስከረም 8: 2006 ለ5ኛ ግዜ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግዜያዊ መጠለያ ኮኔትነር ውስጥ፡ የአንዲት ኢትዮጵያዊት አስዛኝ፡ ህልፈተ ህይወት የአካባቢውን ማህበረሰብ እምባ ሲያራጭ፡ ደረት ሲያዳቃ መዋሉን የአይን ምስክሮች ገለጹ። ወጣቷ በቤት ሰራተኝነት ኮንትራት የመጣች የክርስትና እምነት ተከታይ መሆኗን የሚናገሩት እነዚህ የአይን እማኞች የወጣቷ ሬሳ እስካሁን በውል ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዱን አረጋግጠዋል። የእህቶቻችን ሞት ከሚፈበረክበት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር የስደተኞች ጊዜ ያዊ መጠለያ ኮንቴነር፡ ያለምንም ህክምና እና በቂ መሰረታዊ ፍጆታ በለሌለበት ሁኔታ እንደ ወንጀለኛ የኮንቴነር የብረት በር ተከርችሞባቸው ከሚገኙ እህቶቻችን መሃከል አንድ … [Read more...] about አሳዛኙ የወገናችን ኅልፈት!
“የበሰበሱት” ህወሃት እና ሻዕቢያ
አምባገነነኖች ከሚታወቁበት አንዱና ዋንኛ መለያቸው መካከል ሁለተኛ ሰው አለማዘጋጀታቸው ነው። አቶ መለስ በድንገት ሲስፈነጠሩ በውል የታየው አስከሬን ደብቆ ድብብቆሽም የዚሁ ውጤት ነው። ኢሳያስ ከስልጣን ቢወገዱ ማን ይተካቸዋል? የሚለው ችግርም ጎልቶ የሚታየው ከዚሁ የአምባገነኖች በሽታ አንጻር ነው። ግጭትና ችግር ከመፈጠሩ በፊት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ደወል የሚያንጫርረው ዓለምአቀፉ የግጭት ቡድን (International Crisis Group) ፍርሃቻም ከዚሁ የመነጨ ይመስላል። በኤርትራ ህዝቡ በቃኝ ወደ ማለቱ ደረጃ መቃረቡን የሚጠቁመው የዘንድሮው ዓመት ሪፖርት ኤርትራ በቅርቡ መንግስት አልባ የመሆን እድሏ ሰፊ እንደሆነ ያወሳል። በቅርቡ "የሚከሽፉ መንግስታት" በሚል ስማቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ አገሮች መካከል ኢትዮጵያም ተመልክታለች። እኩል ወደ ስልጣን የመጡት ሻዕቢያና ወያኔ … [Read more...] about “የበሰበሱት” ህወሃት እና ሻዕቢያ










