የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባር ከፍተኛ አመራርና ጸሐፊ የነበሩት አቶ ሌንጮ ለታ አዲስ ያቋቋሙትን ድርጅት ይዘው አዲስ አበባ እንደሚገቡ አስረግጠው ተናገሩ። አቶ ሌንጮ ድርጅታቸው ኢትዮጵያ ገብቶ ለመታገል መወሰኑ ለምን ወሬ እንደሚባል እንዳልገባቸውም አመላክተዋል። በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ኢትዮጵያ መግባታቸውን ኦነግ እንደሚቀበለው ተጠይቀው "ኦነግን ጠይቅ" በሚል ጠበቅ ያለ መልስ ሰንዝረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ እንደሌለው አመልክቷል። ጥር 5 ቀን ከጀርመን ድምጽ የአማርኛ ፕሮግራም ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አቶ ሌንጮ "ኖርዌይ ተቀምጠን ምን እናደርጋለን? ሃገር ቤት ገብተን እንታገላለን" ሲሉ ወደ አገር ቤት ለመመለስ መወሰናቸውን ግልጽ አድርገዋል። "ይሳካል?" በማለት ጠያቂው ላቀረበው “ይሳካል አይሳካም ተብሎ ወደ ትግል አይገባም” በማለት አቶ ሌንጮ ማምረራቸውን በሚያሳብቅ … [Read more...] about “ወሬ አይደለም፤ አገር ቤት አንገባለን” ሌንጮ ለታ
Full Width Top
ፕ/ር በየነ “የአካኪ ዘራፍ ትግል አክሳሪ ነው፤ የስሜት ፖለቲካ ያብቃ” አሉ
“የአካኪ ዘራፍ ፖለቲካና ከስሜት ያልጸዳ የፖለቲካ ትግል መሪውንም ሆነ አምኖ የሚመራውን ህዝብ ለድል” እንደማያበቃ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ገለጹ። ከኤርትራ ጋር ስምምነት ቢደረግ መልካም መሆኑን፣ ነገር ግን ስምምነቱ የመሪዎችና የፖለቲከኞች ሳይሆን የህዝብን ስሜት የጠበቀ ሊሆን እንደሚገባውም ጠቁመዋል። ከጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጋር በተለይ ቃለ ምልልስ ያደረጉት ፕ/ር በየነ "አሁን ያለው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሁኔታ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስተዋይነት የሚፈልግ፣ ዘመናዊ የትግል ስልት የሚጠይቅ ነው" በማለት ተናግረዋል። በቃለ ምልልሳቸው ደጋግመው "አሁን በተያዘው የአካኪ ዘራፍ መንገድ የትም አይደረስም" በማለት ምክንያታቸውን ዘርዝረዋል። ትንንሽ ጠርዝ በመያዝ የትም የማይደርስ ትግል ከየአቅጣጫው እንደሚፈለፈል ፕ/ር በየነ አመልክተዋል። በዚሁ የተነሳ ስትራቴጂካልና ታክቲካል ጉዳይ … [Read more...] about ፕ/ር በየነ “የአካኪ ዘራፍ ትግል አክሳሪ ነው፤ የስሜት ፖለቲካ ያብቃ” አሉ
አፈንዲ፣ ጃዋር መሐመድ እና የቴዲ አፍሮ ጉዳይ
የሰሞኑ የነ ጃዋር ሲራጅ ግርግር ለኛም ስም አትርፏል፡፡ እንደፈቀደው ይሁን፡፡ እኛ ጉዳያችን ሞልቶልናል፡፡ የታቀደው የቴዲ ኮንሰርት በመሰረዙ በጣም ደስተኞች ነን፡፡ በኮንሰርቱ ታክኮ ሊከሰት የሚችለው የህዝብ መተላለቅ በመቅረቱ እሰየው ነው፡፡ ብርና ዝና ብቻ እያሰቡ የህዝብ መጨራረስን ሊጋብዙ የነበሩ ሰዎች ተንኮላቸው ስለከሸፈባቸው አላህን በጣም ነው የምናመሰግነው፡፡ ታዲያ ያስገረመኝ ነገር ስሜት እውነትን ለመሸፈን ምን ያህል ጉልበት እንዳለው መረዳቴ ነው፡፡ አጃኢብ ነው! ግጭትና ትርምስ ሲሰበክ የነበረው በውሸት የተፈጠረውን ወሬ እንደ ሰበብ በማድረግ ነው፡፡ ውሸቱን ለማዳመቅ በግርግሩ ውስጥ የገቡ ሀይሎች አበዛዝም ያስገርማል፡፡ ከአሜሪካ እስከ ኖርዌይ፣ ከለንደን እስከ ሸገር እየተጠራሩ ሽብሩን ለማጋጋል የተደረገው ጥረት አስደናቂ ነበር፡፡ ለወትሮው በአንድ ብሄር ላይ የሚደረግ … [Read more...] about አፈንዲ፣ ጃዋር መሐመድ እና የቴዲ አፍሮ ጉዳይ
ዋናውን “ሌባ” ማን ይከሰዋል?
ኢህአዴግ ልዩ ምክንያት ከሌለው በስተቀር የውጪ ጠላት አያፈራም የሚሉ በርካታ አስተያየት ሰጪዎች አሉ። ምክንያት ካለው ግን ቅንድቧን አንደተላጨችው ነገረኛ ሴት ለመጋጨት ይፈጥናል። ከፊትለፊቱ ገንዘብ ካየ ደግሞ ኢህአዴግ ገደል ሜዳው ነው የሚሉም አሉ። ገንዘብ በሌለበት ቦታ ኢህአዴግ አይታይም በማለት ከበረሃው ኑሮ ጀምሮ የሚከሱት ጥቂቶች አይደሉም። በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ ምድር በሁለት ምድብ ተከፍለው የሚሰቃዩትን ወገኖች አስመልክቶ የያዘው አቋምም ከዚሁ መርሁ የተቀዳ እንደሆነ የሚከራከሩ በርካታ ናቸው። "ምን ያድርግ የኖረው የአገሪቱ ችግሮች ሁሉ ተቆልለው እሱ ላይ ወደቁ" በማለት ኢህአዴግን ለኢትዮጵያ የተቀመጠ "የተቀባ" መፍትሔ አድርገው የሚያወድሱ አሉ። ኳስ ሜዳ ያደገችው ኑሪያ መሐመድ አሁን የምትኖረው ኳታር ነው። ኑሮ እንዳሰበችው የተመቻቸ ባይሆንላትም ወደ አገርዋ ለመመለስ … [Read more...] about ዋናውን “ሌባ” ማን ይከሰዋል?
በከፊቾ ዞን የጽላት ዝርፊያና ቀበኞቹ
በደቡብ ብሔር ብሔረሰቦች ክልል በከፊቾ ዞን በጥንታዊ አድባራት ጽላት መዘረፉን እናውቃለን ያሉ ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ገለጹ። የዜናው ምንጮች የዞኑ አገረ ስብከት በዞኑ በሚገኙ አድባራት ላይ ምርመራ እንዲያካሂድ ጠይቀዋል። ዝርፊያውን የሚያካሂዱት "ባለሃብቶች" መቀመጫቸውን አዲስ አበባና ጅማ ከተማ ያደረጉ የክልሉ ተወላጆች መሆናቸውን አስታውቀዋል። ነዋሪነታቸው ቦንጋና ጊምቦ እንደሆነ የሚገልጹት የዜናው ምንጮች "ቀበኞች" በማለት የሚጠሯቸውን የጽላት ዘራፊዎች የዝርፊያ ስልት ተናግረዋል። በመጀመሪያ እድሜ ጠገብ የሆኑትን አድባራት ይለያሉ። በቃፊሮቻቸው አማካይነት መረባቸውን ዘርግተው ሰዎችን ያጠምዳሉ። ህዝበ ክርስቲያን በሚሰበሰብበት ወቅትና ዓመታዊ የበዓላትን ቀን መርጠው በርዳታና በእድሳት ስም ውዳሴ ይቀበላሉ። በዞኑ የሚገኙት አቢያተ ክርስቲያናት እድሜ ጠገብ በመሆናቸው በርካታ … [Read more...] about በከፊቾ ዞን የጽላት ዝርፊያና ቀበኞቹ
ከአቶ አያሌው መነሳት ጀርባ የአቶ ደመቀ ሚና
በአማራ ክልል የተካሄደውን ሹም ሽር ተከትሎ የተሰጠው ሹመትና የሹም ሽሩ አካሄድ መነጋጋሪያ ሆነ። "በቃኝ አሉ የተባሉትን ባለስልጣን አውርዶ እንደገና መሾም የተነቃበት የህወሃት የማረጋጊያ ጨዋታ ነች" ሲሉ ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ተናገሩ። በሹም ሽሩ የአቶ ደመቀ መኮንን እጅ እንዳለበትና መንስዔውም "የቆየ ቁጭትና ቁርሾ" እንደሆነ ተጠቆመ። የአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አያሌው ጎበዜ ከመንበራቸው እንዲነሱ ተደርጓል። የመንግስት ልሳን መገናኛዎች እንዳመለከቱት አቶ አያሌው ከሃላፊነታቸው የተነሱት ታህሳስ 9/2006 በተጠራ አስቸኳይ የክልሉ ጉባኤ ነው። አዲስ ሹመት ያስፈለገው አቶ አያሌው ባቀረቡት "የመተካካት" ጥያቄ እንደሆነም ተመልክቷል። ምትካቸው የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነዋል። አቶ ገዱ ፕሬዚዳንትነታቸው በጉባኤ ተወስኖ ይፋ ከመደረጉ ጎን ለጎን ዜና … [Read more...] about ከአቶ አያሌው መነሳት ጀርባ የአቶ ደመቀ ሚና
ኦባንግ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጋር ተነጋገሩ
* “ባለውለታችሁ የኢትዮጵያ ህዝብ አዝኖባችኋል፣ አርቃችሁ እዩ” “በትግሉ ወቅት ለነጻነት ስትዋደቁ ኢትዮጵያ በጋምቤላ አኙዋክ ምድር ላይ ሙሉ ከለላና ዋስትና በመስጠት ያበረከተችው አስተዋጽኦ የሚረሳ ነው? ከነጻነት ታጋዮችችሁ ጎን በመሰለፍ ብረት ያነሱ የአኙዋክ ኢትዮጵያውያን ልጆች መስዋዕትነት ይዘነጋችኋል? አሁን ድረስ የትግሉ የመስዋዕትነት ቁስላቸው ያልዳነ የአኙዋክ ልጆች እንዳሉ ትዘነጋላችሁ?" በማለት የተናገሩት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ /ጥቁሩ ሰው/ ናቸው። በታላላቅ መድረኮችና በበርካታ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ተሰሚነታቸውና ስብዕናቸው እየጎላ የሄደው ጥቁሩ ሰው ለጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ እንደተናገሩት፣ ከላይ የተገለጸውን ህሊና የሚፈታተን ጥያቄ ያቀረቡት ለደቡብ ሱዳን የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ባርናባ ማሪያል ቤንጃሚን ነው። ለረዥም … [Read more...] about ኦባንግ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጋር ተነጋገሩ
በደቡብ ሱዳን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከሸፈ
በደቡብ ሱዳን የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪርን መንግሥት ለመገልበጥ እሁድ ማታ ለሰኞ አጥቢያ ሙከራ ተደርጎ መክሸፉ ተሰማ፡፡ ፕሬዚዳንቱ ሙከራው መክሸፉንና መንግሥት ሁሉንም ነገር በቁጥጥር ሥር ማዋሉን በመግለጽ ለደቡብ ሱዳን ሕዝብ መግለጫ ሰጡ፡፡ በዋንኛው ጎሣ ዲንቃ እና ኑዌር ጎሣ መካከል የተከሰተው ፍጥጫ እስካሁን የለየለት መስመር አልያዘም፡፡ ከወራቶች በፊት የደቡብ ሱዳን ነጻ አውጪ ንቅናቄ (ኤስ.ፒ.ኤል.ኤም.) ዋና ጸሐፊ የሆኑት ፓጋን አሙን የአመራር ብክነትና ሌሎች ችግሮች አሉባቸው በሚል እንዲገመገሙ ፕሬዚዳንቱ የመርማሪ ኮሚሽን አቋቁመው ነበር፡፡ ኮሚሽኑ ዋና ጸሐፊው የአመራር ጉድለት የታየባቸው በመሆኑ ከሥልጣን እንዲነሱ የውሳኔ ሐሳብ ሰጥቷል በሚል ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ዋና ጸሐፊውን ጨምሮ የአገሪቱን ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሬይክ ማቻር ከሥልጣናቸው ባለፈው ሐምሌ ወር … [Read more...] about በደቡብ ሱዳን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ከሸፈ
ኢህአዴግ ከብሔር “ተኮር” ተቃዋሚዎች ጋር ሊሸማገል ነው
ኢህአዴግ በብሔርና በክልል ደረጃ ከተደራጁ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ለሚንቀሳቀሱት ቅድሚያ በመስጠት ለመደራደር የሚያስችለውን ቅድመ ሁኔታ በማመቻቸት ላይ መሆኑን የጎልጉል ምንጮች ገለጹ። ምንጮቹ እንደጠቆሙት ኢህአዴግ ለዚህ ተግባሩ ወዳጅ ጎረቤት አገሮችን፣ አንጋፋ የጎሳ መሪዎችንና ያፈገፈጉ የቀድሞ ተቃዋሚ መሪዎችን እየተጠቀመ ነው። ህወሃት አሁን በአገሪቱ ከቀን ወደ ቀን እየተስፋፋ የሄደው አለመረጋጋት እንዳሳሰበው የጠቆሙት የኢህአዴግ ሰው ድርጅቱ እርቅ ላይ ከመቼውም በላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት ስትራቴጂ መንደፉን አመልክተዋል። "ከውጥረት ለመውጣት ወይም ውጥረትን ለመቀነስ" በሚል ኢህአዴግ ትኩረት ሰጥቶ የጀመረው አዲሱ የ"ሰላም" መንገድ ህብረ ብሔር ድርጅቶችን ያላከተተበትን ምክንያት አልተብራራም። ይሁን እንጂ ከኢህአዴግ ባህሪ አንጻር … [Read more...] about ኢህአዴግ ከብሔር “ተኮር” ተቃዋሚዎች ጋር ሊሸማገል ነው
ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ አጎታቸውን ገደሉ!
ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ጆንግ ኧን አጎታቸውንና በሰሜን ኮሪያ የሥልጣን እርከን ሁለተኛ የነበሩትን ጃንግ ሶንግ-ታዬክ አስገደሉ፡፡ ግድያውን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ቢሆንም የመንግሥት ሚዲያ እንዳለው ከሆነ አጎትየው ጃንግ “መንግሥት ለመገልበጥ ሙከራ በማድረግ አስጸያፊ ወንጀል ሰርተዋል” ብሏል፡፡ ሰሜን ኮሪያን ለረጅም ዓመታት ሲመሩ የነበሩትንና ሥልጣናቸውን ከመጀመሪያው የሰሜን ኮሪያ ፕሬዚዳንት ኪም ኤል ሱንግ የተረከቡት ኪም ጆንግ ኢል ባልተጠበቀ ፍጥነት ሲሞቱ ወጣቱ ኪም ጆንግ ኧን ሥልጣን መንበር ላይ ተቆናጠጡ፡፡ በወቅቱ በሃያዎቹ መጨረሻ ዕድሜ ላይ የሚገኙት ኧን ከልምድ ማነስ ችግር ውስጥ እንዳይገቡ በማሰብ አባታቸው ኪም ጆንግ ኢል አስቀድመው ከጎናቸው የሚሆኑ ሞግዚትና አለማማጅ አዘጋጅተው ነበር፡፡ ኪም ጆንግ ኢል የጤናቸው ሁኔታ … [Read more...] about ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ አጎታቸውን ገደሉ!










