የዑጋንዳው ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ “አከራካሪ” ሲባል የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊ ህግ በፊርማቸው አጸደቁ፡፡ ግብረሰዶማውያንን “ከተፈጥሮ ውጪ የሆኑ” እና “አጸያፊ” ሲሉ ገልጸዋቸዋል፡፡ ግብረሰዶማዊነት በምዕራቡ ዓለም አማካኝነት ወደ አፍሪካ እየተስፋፋ የመጣ ነው ብለዋል፡፡ ለበርካታ ዓመታት አከራካሪ ሆኖ የቆየውን የጸረ ግብረሰዶማዊነት ሕግ ትላንት ዑጋንዳ አጽድቃለች፡፡ ከምዕራቡ ዓለም እና ሰዶማዊነት የመብት ጉዳይ እንደሆነ ከሚከራከሩ ተቋማት የደረሰባትን ውትወታ ወደ ጎን በማለት ዑጋንዳ በሕግ ማጽደቋ የበርካታ ዓለምአቀፍ መገናኛ ብዙሃንን ሽፋን የሰጡበት ርዕስ ሆኗል፡፡ የሕጉን መጽደቅ አስመልክቶ ጥቂት ዑጋንዳውያን ተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ሲሆን በርካታዎች ደግሞ ድጋፋቸውን ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡ ሕጉን በፊርማቸው ያጸደቁት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ሲኤንኤን ላይ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ … [Read more...] about “ግብረሰዶማውያን ከተፈጥሮ ውጪና አጸያፊ ናቸው”
Full Width Top
ዓለም ባንክ ኢህአዴግን በረበረው – ከዚያስ?
ኢህአዴግ "አልመረመርም፣ አልበረበርም" በማለት ሲያንገራግር ከቆየ በኋላ በዓለም ባንክ ቀጭን ትዕዛዝ ለመበርበር መስማማቱን ገልጾ በተለያዩ አካላት ምርመራ ተካሂዶበታል። በተከታታይ ሲካሄድ የነበረው ምርመራ አካል የሆነው የመጨረሻ ምርመራ ባለፈው ሳምንት አጋማሽ ተጠናቋል። የጎልጉል ታማኝ ምንጮች እንደተናገሩት ስድስት አባላትን ያካተተው የዓለም ባንክ የምርመራ ቡድን ኢህአዴግን መርምሮ ተመልሷል። የሚጠበቀው የመጨረሻው ሪፖርትና ሪፖርቱ የሚቀርብለት የዓለም ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ውሳኔ ነው። በቅርቡ የሚወጣውን ውሳኔ አቅጣጫ ለማስቀየር በማሰብ ኢህአዴግ ለመርማሪው ቡድን ራሱ የፈጠረውን “የተጭበረበረ ሪፖርት” አቅርቦ ነበር፡፡ ኢህአዴግ ምርመራውን በተቀነባበረ የፈጠራ ሪፖርት ለማምለጥ ሞክሮ እንደነበር የጠቆሙት የመረጃው ምንጮች "የመርማሪዎቹ ቡድን ሪፖርቱን አንቀበልም፣ የችግሩ … [Read more...] about ዓለም ባንክ ኢህአዴግን በረበረው – ከዚያስ?
ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ
ኢህአዴግ የተፈጥሮ ሃብትን በትክክለኛ መንገድ ለሕዝብ ጥቅም መዋሉን በመከታተል ለአገራት እውቅና የሚሰጠው The Extractive Industries Transparency Initiative (EITI) ለተሰኘ ዓለም ዓቀፋዊ ተቋም ያቀረበው የእውቅና ጥያቄ ማመልከቻ ከተገመገመ በኋላ መመዘኛዎቹን ማሟላት ባለመቻሉ መውደቁ ተሰማ። ኢህአዴግ የእውቅና ማመልከቻ በድጋሚ ማስገባቱን አስቀድሞ ያወቀው ዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch) ጉዳዩን ከሚከታተሉ ጋር ባገኘው መረጃ ኢህአዴግ የEITI መስፈርት የማያሟላና በሰብአዊ መብት ጥሰት የተወነጀለ ድርጅት መሆኑንን ማስረጃ አስደግፎ በመጥቀስ መሟገቻ ደብዳቤ ለድርጅቱ አስገብቶ ነበር። EITI የዛሬ 11ዓመት አካባቢ የተቋቋመ በተፈጥሮ ሃብት ዙሪያ ዕውቅና የሚሰጥ ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ የተፈጥሮ ሃብት የህዝብ … [Read more...] about ኢህአዴግ ራሱ ባወጣው አፋኝ ሕግ ታፈነ
የመኖሪያ ፈቃድ – ከራስ ወዳድነት ያልራቀው የስደተኞች የመጨረሻ ግብ
ከራሳቸው አልፎ ባህር ውስጥ ቢደፉት የማይጎድል ሃብት አላቸው። ከሃብታቸው ብዛት የተነሳ ተጨማሪ የነዳጅ ክምችት አግኝተው ጉድጓድ ለመቆፈር ተቃውሞ በመነሳቱ ሪፈረደም አካሂደዋል። ከነዳጅ ይልቅ ውሃ ውስጥ ያለው ህይወት አንደሚብስባቸው በማስታወቅ ድምጽ የሰጡ በመብዛታቸው ነዳጁ ባለበት እንዲቆይ ተወስኗል። ይህ ዜና በተሰማበት ሰሞን ያልተገረመ አልነበረም። ሃብት ካለ ምን ችግር አለ? አንግዲህ እንደዚህ "ብር ይብቃን፤ አሳና የባህር ውስጥ ፍጡራን እንቁራሪትን ጨምሮ ይበልጡብናል" የተባለባት አገር ኖርዌይ ናት። በተቃራኒው ደግሞ ብር ካየ የሚገባበትን ጉድጓድ፣ የሚፈጽመውን ጥፋት የማይለካው ኢህአዴግ የሚመራት ኢትዮጵያ ያፈራቻቸው ስደተኞች ኖርዌይን ተጠልለዋል። ከአራት ሺህ በላይ ወገኖች ኖርዌይ በጡረታ መልክ እየቆረሰችላቸው ወይም ስራ እየሰሩ ህይወታቸውን ይመራሉ። በኖርዌይ መወልወያና … [Read more...] about የመኖሪያ ፈቃድ – ከራስ ወዳድነት ያልራቀው የስደተኞች የመጨረሻ ግብ
መንታ መንገድ – የኢህአዴግና የአሜሪካ ወዳጅነት ወዴት?
“አሜሪካኖች ነጻ እንድታወጡን አንጠይቃችሁም። የኢትዮጵያ ህዝብ እንዴት ነጻ እንደሚወጣ ያውቃል። እናንተ ግን በነጻነት መንገዱን ላይ ዕንቅፋት አትሁኑበት ... ዶናልድ ያማሞቶ ከዛሬ ስምንት ዓመት በፊት ኢትዮጵያ በመንታ መንገድ ላይ ነች ብለኸን ነበር መቼ ነው መንገዱን የምናቋርጠው? ከመንገዱ ላይ ገለል በሉልን” አቶ ኦባንግ ሜቶ እንዴት እዚህ ተደረሰ? የኢህአዴግን የአገዛዝ ዘመን ተቃዋሚዎችን አጃቢ አድርጎ የህግ ሽፋን በመስጠት የሚያራዝመው ዋና ተቋም ምርጫ ቦርድ፣ የፕሬስ ነጻነት፣ የመናገርና የመሰብሰብ ነጻነት፣ የህግ የበላይነት፣ ሕግን የማክበርና የማስከበር ሃላፊነት፤ ወዘተ በኢትዮጵያ ነጻ ከሆኑ ኢህአዴግ ከፊትለፊቱ ካለው ምርጫ የመዝለል አቅም እንደሌለው ይታመናል። ስለዚህም እነዚህን ጉዳዮች ለድርድር አያቀርባቸውም። ኢህአዴግ ከጅምሩ በህዝብ የማይታመነውና እውቅና … [Read more...] about መንታ መንገድ – የኢህአዴግና የአሜሪካ ወዳጅነት ወዴት?
የአፍሪካ 100 ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች
በዓለማችን የሚገኙ የትምህርት ተቋማትን በማወዳደር ደረጃ የሚያወጣው (4 International Colleges & Universities (4icu)) የአፍሪካ ምርጥ የተባሉትን ዩኒቨርሲቲዎችን ዝርዝር ከጥቂት ሳምንታት በፊት አውጥቶ ነበር፡፡ ድርጅቱ በርካታ መረጃዎችን በመሰብሰብ እንዲሁም ለማንም ወገን ያላዳላ ጠለቅ ያለ ሒሳባዊ ትንታኔ በማድረግ ደረጃውን እንደሚያወጣ በድረገጹ ላይ ጠቁሟል፡፡ ከአንድ እስከ ሃያ ባሉት ዝርዝር ውስጥ የደቡብ አፍሪካና የግብጽ ዩኒቨርሲቲዎች ደረጃውን በብዛት ተቀራምተውታል፡፡ ታንዛኒያ፣ ናይጄሪያ፣ ዩጋንዳ፣ ቦትስዋና እና ኬኒያ እስከ ሃያ ባለው ደረጃ በመግባት የአገራቸውን የትምህርት ተቋማት ብቃት አስመስክረዋል፡፡ ከተመሠረተ 60ዓመታት ያለፉት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (በቀድሞ ስሙ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ዩኒቨርሲቲ) እስከ መቶ ባሉት ዝርዝር ውስጥ … [Read more...] about የአፍሪካ 100 ምርጥ ዩኒቨርሲቲዎች
ኦሞት ኦባንግ – የታዳኝ አዳኝ ድራማ
"ሁሉም ከህግ አያመልጡምና ዜጎች መረጃ በመሰብሰብ የቤት ስራችሁን ስሩ" ኦባንግ ሜቶ ኦሞት ኦባንግ በዓለም ዓቀፍ ተቋማት ለፍርድ እንዲቀርቡ እየታደኑ ነው ሰሞኑን አገር ጥለው መኮብለላቸው የተደመጠው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦሞት ኦባንግ በተለያዩ የዓለም ዓቀፍ ተቋማት ክትትል እየተደረገባቸው እንደሆነ ታወቀ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ፍትህ የተዛባባቸው ዜጎች ሁሉ መረጃ በማሰባሰብና ለድርጅታቸው በመላክ የዜግነት የቤት ስራቸውን እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ ኦሞትን ፍትህ ደጅ ለማቆም ከ19 ዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር በኅብረት እየሰሩ መሆናቸውም አመልክተዋል። በሌላም በኩል ኢህአዴግም “ነገር ሳይበላሽ” እያደናቸው እንደሆነ ተሰምቷል፡፡ በ2003 በጅምላ ለተጨፈጨፉና በሺህ ለሚቆጠሩ የአኙዋክ ተወላጆች … [Read more...] about ኦሞት ኦባንግ – የታዳኝ አዳኝ ድራማ
የ2014 የዓለም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ
በያዝነው የአውሮጳውያን ዓመት ሊከሰቱ የሚችሉ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋዎች ይፋ ሆኑ፡፡ በርካታዎቹ በአፍሪካ አገራት ሲሆኑ አደጋው ካንዣበበባቸው አገራት መካከል ኢትዮጵያ 25ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በአሜሪካ የፖለቲካ ሳይንቲስት የሆኑት ጄይ ዑልፌልደር የተለያዩ የሒሳብ ስሌቶችን በመጠቀም የ2014ዓም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያቸውን ሰጥተዋል፡፡ እንደ እርሳቸው ትንበያ ከሆነ 40 አገራት ቀይ የአደጋ ምልክት በርቶባቸዋል፡፡ ስለ ጉዳዩ ሲናገሩ መፈንቅለ መንግሥት እንዲሆን የሚመኙት ነገር ባይሆንም የመከሰቱ ጉዳይ ግን መነገር ያለበት ነው ይላሉ ምሁሩ፡፡ በተለያዩ የአሜሪካ አንጋፋ ጋዜጦች ላይ የተዘገበው ይኸው ጥናት እንደሚያመለክተው በዓለማችን ላይ 40 አገራት ከፍተኛ የመፈንቅለ መንግሥት አደጋ ያነጣጠረባቸው መሆናቸውን በጥናቱ ተገልጾዋል፡፡ አብዛኛዎቹም ከአፍሪካ መሆናቸው አሁንም … [Read more...] about የ2014 የዓለም የመፈንቅለ መንግሥት ትንበያ
ደቡብ ሱዳን በጎሣ ፖለቲካ እሳት እየተበላች ነው!
ከተመሠረተች ምንም ያህል ያልሰነበተችው ደቡብ ሱዳን ሕዝቧ ሰላሙንና ነጻነቱን በደስታና በጸሎት አጣጥሞ ሳይጨርስ በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ከወደቀች አንድ ወር አልፏታል፡፡ ጎሣን መሠረት በማድረግ የተቀሰቀሰው ፍልሚያ ግን የተጀመረው ገና ደቡብ ሱዳን አገር ከመሆኗ በፊት እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ በደቡብ ሱዳን ሣር ላይ የኃያላኑ ዝሆኖች የእጅ አዙር ጠብና ፍጥጫም አብሮ የሚጠቀስ ነው፡፡ አፍሪካ ከምዕራባውያን ቅኝ ግዛት ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ የመፈንቅለ መንግሥትና የእርስበርስ ጦርነት ትዕይንቶችን ስታስተናግድ ቆይታለች፡፡ ይህን “coup-civil war trap” አዙሪት በአብዛኛው የመከሰቱን ሁኔታ የፖለቲካ ተኝታኞች የሚስማሙበት ነው፤ ዋንኛውንም ምክንያት ጠንካራ ተቋማት ያለመመሥረታቸው ውጤት እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡ አዲስ አገርም ሆነ መንግሥት ምስረታ ወቅት የሚከሰቱ ሁለት … [Read more...] about ደቡብ ሱዳን በጎሣ ፖለቲካ እሳት እየተበላች ነው!
ፕሮፌሰሩ – ሰክነው ማዳመጥ ለሚችሉ መናገር ያስደስታቸዋል
ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያ ሶሻል ፓርቲና የደቡብ ህብረት ፓርቲ መሪ ናቸው። በግል የመድረክ መስራች ሲሆኑ፣ የሚመሩት ድርጅትም በመድረክ ጥላ ስር ከተሰባሰቡት ፖለቲካ ድርጅቶች መካከል ይገኝበታል። ፕ/ር በየነን ጨምሮ ላለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ኢህአዴግን በመቃወም የሚታወቁ ፖለቲከኞች ተተኪ ፖለቲከኞች አላዘጋጁም በሚል ይወቀሳሉ። በዚህ ጉዳይ ስማቸው ከሚነሱት መካከል አንዱ ፕ/ር በየነ ናቸው። ፕ/ር በየነ አሜሪካ ለሥራ መምጣታቸውን ተከትሎ የጎልጉል ዘጋቢ ቃለ ምልልስ አድርጎላቸዋል። ፕ/ር በየነ በቃለ ምልልሳቸው ወቅት በተደጋጋሚ "እኔ የምናገረው ሰክነው ማዳመጥ ለሚችሉት ነው" በማለት ያሳስባሉ። ለምን? ጎልጉል፡- ስለ መንግሥትና ተቃዋሚዎች እርቅ ጉዳይ ወሬ ይወራል የሰሙት ነገር አለ? ፕ/ር በየነ፡- የለም። ምንም አልሰማሁም። ጎልጉል፡- እርስዎ የሚመሩት ፓርቲ ጥያቄው … [Read more...] about ፕሮፌሰሩ – ሰክነው ማዳመጥ ለሚችሉ መናገር ያስደስታቸዋል










