በኔዘርላንድ በሚደረግ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል 50ኛ ዓመት ክብረበዓል ላይ ለመገኘት ተጋብዞ የነበረው እስክንድር ነጋ ሐሙስ ሌሊት ለአርብ ጠዋት ቦሌ ላይ ከአገር እንዳወጣ ታግቷል። ጎልጉል ባገኘው መረጃ መሠረት ጉዳዩ ህወሓትን ትልቅ ቅርቃር ውስጥ ከቶታል። ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩት የመብት ተሟጋቹ አቶ ኦባንግ ሜቶ በፌስቡክ ገጻቸው እንደገለጹት ይህ ፈጽሞ መከሰት ያልነበረበት ጉዳይ መሆኑን በመጥቀስ ጠ/ሚ/ር አብይ በጉዳዩ ላይ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡበት ጠይቀዋል። ሌላው ለጉዳዩ ቅርበት ያለውና ክስተቱ እንደተፈጸመ አጭር ዘገባ ያሰራጨው ጋዜጠኛ ክንፉ አሰፋ “ከሌሊቱ 8 ሰዓት ቦሌ ያሉ የደህንነት አካላት ፓስፖርቱን ቀምተው አትሄድም ብለውታል። የከለከሉበትን ምክንያቱን ግን አልገለጹም” ብሏል። ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ ከቦሌ አካባቢ ባገኘው መረጃ መሠረት እስክንድርን … [Read more...] about ህወሓት እስክንድርን ከአገር እንዳይወጣ በመከልከል ባላሰበው ማነቆ ውስጥ ገባ

