• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“… ተድብድቤ በቃሬዛም ቢሆን ያምጡኝ እንጂ ካሁን በኋላ በራሴ ፈቃድ ‘ወደ ችሎት’ አልመጣም” በቀለ ገርባ

April 13, 2017 08:21 pm by Editor Leave a Comment

“… ተድብድቤ በቃሬዛም ቢሆን ያምጡኝ እንጂ ካሁን በኋላ በራሴ ፈቃድ አልመጣም” በፍርድ ሂደቱ ሲሉ መሰላቸታቸውን አቶ በቀለ ገርባ ተናገሩ። አቶ በቀለ ይህንን የተናገሩት ሃሙስ ባስቻለው ችሎት የመናገር እድል እንዲሰጣቸው ጠይቀው ሲፈቀድላቸው ነው።

ከሁለት ቀን በፊት አቃቤ ህግ በማስረጃነት አቀርበዋለሁ ሲለው የነበረውን የድምጽ ከምስል ማስረጃ አስተርጉሞ እንዲያቀርብና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኤጀንሲ ሃላፊ ችሎት እንዲገኙ ትዕዛዝ ሰጥቶ ነበር። ይሁን እንጂ በቀጠሮው በትዕዛዙ መሰረት ዓቃቤ ሕግ በእነ አቶ በቀለ ገርባ ላይ ያቀረበውን የድምፅ ከምስል ማስረጃ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዛሬም እንዳላስተረጎመው አሳውቋል።

የኤጀንሲው ሃላፊ ችሎት አለተገኙም። የክልሎች ቋንቋ ሃላፊ ጸጋ ልዑል ወልደኪዳን “ብቁ ጋዜጠኞች ስለሌሉ አልተተረጎመም” በማለት የሰጡትን ምክንያት ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል። ቀደም ሲል ከሳሻቸው ትርጉሙ ሳይገባው እንዴት ሊከሳቸው እንደቻለ ሊገባቸው እንዳልቻለ፣ ይልቁኑም “ታስሮ የቀመጥ” ከሚል እሳቤ በመነሳት የሚፈጸም እንደሆነ ያስታወቁት አቶ በቀለ ገርባ በዛሬው ችሎት የመናገር እድል ጠይቀው ምሬት የተሞላበት መልዕክት አስተላልፈዋል።

“ተደብድቤ በቃሬዛም ቢሆን ያምጡኝ እንጂ በራሴ ፈቃድ ካሁን በኋላ አልመጣም” በማለት አቶ በቀለ ገርባ ሲናገሩ ችሎቱ ላይ የነበረ ለዛጎል እንደገለጸው እሳቸው ይህንን ሲናገሩ በዳኞቹ ላይ የጭንቀት ስሜት ይታይ ነበር ብሏል።

ቀደም ሲል የድምጽ ከምስል ማስረጃው ቢተረጎም እሳቸውን እንደሚጠቅማቸው ያመለከቱት አቶ በቀለ ኤጀንሲው ሶስተኛ ወገን ሆኖ ጉዳዩን እያጓተተው መሆኑንንም አመልክተዋል። ምን ያህል በቀጠሮ እየተንገላቱ እንደሆነ ሲገልጹ “ለናንተ እተወዋለሁ” ብቻ ነው ያሉት።

ጠበቆቻቸውም “ጉዳያቸን ከኤጀንሲው ጋር አይደለም” ሲሉ ሶስተኛ ወገን ሆኖ ኤጀንሲው የሚያደርገውን የቀጠሮ ማንዛዛት እንዲቆም ጠይቀዋል። ፍርድ ቤቱ በአቃቤ ህግ የቀረበውን ምክንያት ውድቅ በማድረግ ለመጨረሻ ብይን ለግንቦት 7 ቀጠሮ ሰጥቷል።

የቪኦኤ የድምፅ ፋይል እዚህ ላይ ያዳምጡ፡፡

http://staging.goolgule.com/wp-content/uploads/2017/04/b28506e0-9ddf-4e5f-9a33-86f46180f113_32k.mp3

“…ንፁሃን ሰዎችን እስር ቤት ወርውረው እንደ ትልቅ ጀብድ ነው የሚያዩት… ” አቶ በቀለ ገርባ

“…ከሳሼ ያቀረበውን ማስረጃ ትርጉሙን ሳያውቅ፤ ይዘቱ ምን እንደሆነ ሳያውቅ ነው እንዴ የከሰሰኝ? ትርጉሙን ሳያውቅ እንዴት ወንጀል ነው ብሎ ትርጉሙን በማያውቀው ማስረጃ ክስ ይመሰርታል? በእውነቱ በሃገራችን የፍርድ ሂደት አዘንን፤ እኛስ ትንሽ ነን በዚህ አይነት ስንት ሚሊዮኖች ናቸው መከራቸውን የሚያዩት? የኛ ጉዳይ ዝም ብለው ታስረው ይቆዩልን አይነት ነገር ነው። እቤታቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በኛ ስቃይ እና መከራ ይደሰታሉ። ማስረጃው እንደሚባለው ተተርጉሞ ቢቀርብ ለኔ ይጠቅመኝ ነበር። የኔን ንፅህና ነበር የሚያስረዳው። ጉዳዩ ከሚንጓተት ይቅርና በተሰሙት ማስረጃዎች ውሳኔ እንዲሳጥ ነው የምጠይቀው”

“ፍ/ቤቱ ሌሎች አማራጮችን ይጠቀም።” ኢብኮ

አስተርጓሚዎች ቀርበው ማስረጃው በችሎት እየታየ እንዲተረጎም ተለዋጭ ቀጠሮ ይሰጥ።” አቃቤ ህግ

የእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ ለሚያዚያ 2, 2009 ተቀጥሮ የነበረው አቃቤ ህግ በማስረጃነት ያቀረባቸው በኦሮምኛ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ የተሰሙ የድምፅ ከምስል ማስረጃዎችን የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በፍርድ ቤቱ የስራ ቋንቋ ተርጉሞ እንዲያቀርብ ነው። ሆኖም እንዲተረጎሙ የተላኩትን ሶስት ሲዲዎች ለመተርጎም ሰፊ ጊዜ የሚወስዱ በመሆናቸው እና ባለሙያዎች የስራ መደራረብ ስላለባቸው ፍ/ቤቱ ሌሎች አማራጮችን እንዲጠቀሙ የሚገልፅ በ29/7/2009 ከኢብኮ የተፃፈ ደብዳቤ መቅረቡን ዳኞች ተናግረዋል። በተጨማሪም ለትርጉም ስራ ህጋዊ ፈቃድ አውጥተው የሚሰሩ አካላት እንዳሉ ከኢብኮ የተላከው ደብዳቤ ይጠቁማል።

አቃቤ ህግ በጉዳዩ ላይ ያለውን አስተያየት ሲጠየቅ፤ የእንግሊዘኛ እና የኦሮምኛ አስተርጓሚ ተፈልጎ ማስረጃው በድጋሚ በችሎት እየታየ እንዲተረጎም ጠይቋል። የተከሳሽ ጠበቆች በበኩላቸው የትርጉም ስራውን በተመለከተ ተደጋጋሚ ቀጠሮ እየተሰጠ መሆኑ ገልፀው፤ ከሳሽ አቃቤ ህግ ሃላፊነቱን እንዳልተወጣ እና ማስረጃዎቹን በፍ/ቤቱ የስራ ቋንቋ ተርጉሞ ማቅረብ እንዳልተፈለገ ተቆጥሮ ማስረጃው ውድቅ እንዲደረግ እና በቀረቡ ማስረጃዎች ብይን እንዲሰጥ ያመለከቱ ሲሆን ዘንድሮ ኢትዮጵያ ውስጥ የቻይንኛ ትርጉም እንኳን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሁለት የቪዲዮ ማስረጃዎች የቀረቡባቸው የኦፌኮ ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር በቀለ ገርባ “እቤት ያሉ ሰዎች ንፁሃን ሰዎችን እስር ቤት ወርውረው እንደ ትልቅ ጀብድ ነው ሚያዩት። በሰው ስቃይ የመደሰት ነገር ነው የማየው። ከሳሼ ያቀረበውን ማስረጃ ትርጉሙን ሳያውቅ፤ ይዘቱ ምን እንደሆነ ሳያውቅ ነው እንዴ የከሰሰኝ? ትርጉሙን ሳያውቅ እንዴት ወንጀል ነው ብሎ ትርጉሙን በማያውቀው ማስረጃ ክስ ይመሰርታል? በእውነቱ በሃገራችን የፍርድ ሂደት አዘንን፤ እኛስ ትንሽ ነን በዚህ አይነት ስንት ሚሊዮኖች ናቸው መከራቸውን የሚያዩት? የኛ ጉዳይ ዝም ብለው ታስረው ይቆዩልን አይነት ነገር ነው። እቤታቸው ከቤተሰቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በኛ ስቃይ እና መከራ ይደሰታሉ። ማስረጃው እንደሚባለው ተተርጉሞ ቢቀርብ ለኔ ይጠቅመኝ ነበር። የኔን ንፅህና ነበር የሚያስረዳው። ጉዳዩ ከሚንጓተት ይቅርና በተሰሙት ማስረጃዎች ውሳኔ እንዲሳጥ ነው የምጠይቀው።” የሚል አስተያየታቸውን አቅርበዋል።

የኦፌኮ አመራር እና 2ኛ ተከሳሽ የሆነው ደጀኔ ጣፋም “የአቃቤ ህግን ማስረጃ ፍ/ቤት ያሰባስብ የሚል ህግ የለም። ፍ/ቤት እያደረገ ያለው ማረጃ የማሰባሰብ ነገር ነው። ማስረጃዎቹ በፍ/ቤት የስራ ቋንቋ ተተርጉመው መቅረብ የነበረባቸው ከክሱ ጋር ነው። የአቃቤ ህግ ማቋቋሚያ አዋጅ ክስ በቅንንነት መቅረብ እንዳለበት ይጠቅሳል። ማስረጃዎች የሚጎሉ ከሆነ ክሱን አለማቅረብ ይቻል ነበር። ተተርጉሞ እንዲቀርብ ፍ/ቤት ካዘዘ ቆይቷል። አቃቤ ህግም በባለፈው ቀጠሮ ማስረጃዎቹን ኢብኮ እንዲተረጉም መላኩን ተናግሯል። በሃገሪቷ የተቋም አለመታዘዝ አለ። የአቃቤ ህጉንም እጅ የጠመዘዘ እጅ አለ ማለት ነው። ጉልበቱ እና አቅሙ ካላችሁ ያንን እጅ ሰብስቡልን።” ብሏል። አቃቤህግ በማስረጃ አቀራረብ ሂደት ያሳየው ቸልተኝነት እንዳልነበረ ጠቅሶ ተደጋጋሚ ቀጠሮ መሰጠቱን በዚህም ተከሳሾች መንገላታታቸው የማይካድ መሆኑን ተናግሯል። ከክሱ ጋር የተያያዙ የሰነድ ማስረጃዎችን በተመለከተ በፍ/ቤቱ የስራ ቋንቋ ተተርጉመው ለተከሳሾች መድረሳቸውን ጠቅሶ የድምፅ ከምስል ማስረጃዎች ግን ከዚህ ቀደም በፍ/ቤቱ የተለመደው አሰራር በችሎት በሚታይበት ወቅት ከአስተርጓሚ ጋር የሚቀርብ እንደሚሆን ገልፇል። በዚህ መዝገብም የድምፅ ከምስል ማስረጃ በሚሰማበት ወቅት አስተርጓሚ እንዲቀርብ አድርጎ የነበረ መሆኑን አቃቤ ህግ አስታውሶ፤ በእለቱ ችሎቱ ማስረጃው ከተሰማ በኋላ ተተርጉሞ ቢቀርብ ይሻላል ብሎ በመወሰኑ እየተተረጎመ የመሰማት ሂደቱ እንደቀረ ተናግሯል። በመሆኑም ሌላ ቀጠሮ እንዲሰጥ እና ማስረጃው በችሎት እየታየ አስተርጓሚዎችም ቀርበው በችሎት እንዲተረጎም አቃቤ ህግ ጠይቋል።

ዳኞች የግራ እና የቀኙን ክርክር ከሰሙ በኋላ የነሱን አስተያየት እና ትእዛዝ ሰጥተዋል። አቃቤ ህግ ክስ ሲመሰርት የሰነድ ማስረጃዎችን ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ማስረጃ በፍ/ቤቱ የስራ ቋንቋ አስተርጉሞ ማቅረብ እንደነበረበት፣ ፍ/ቤቱ እየሰራ ያለው መረጃ ማሰባሰብ ሳይሆን የፍትህ ስርአቱን የማገዝ ስራ እንደሆነ እንዲሁም ኢብኮም የፍትህ ስርአቱን የመተባበር ግዴታ እንዳለበት ገልፀዋል። በዚህም መሰረት ከኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (ኢብኮ) የሚመለከተው ሃላፊ ሁለት አስተርጓሚዎችን(አንድ የኦሮምኛ እና አንድ የእንግሊዘኛ ቋንቋ) ይዞ በመጪው ሃሙስ (ሚያዚያ 5, 2009) እንዲቀርብ ጥብቅ ትእዛዝ መስጠታቸውን ተናግረዋል— ዳኞች። በተጨማሪም ተርጓሚዎቹ በቀጠሮው እለት ሲቀርቡ የትርጉም ስራውን በተቀላጠፈ እና በፍጥነት እንዲሰሩት የድምፅ ከምስል ማስረጃዎቹ ከቀጠሮው ቀደም ብሎ እንዲደርሳቸው ታዟል።

ምስጋና  ለየኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፕሮጀክት

(ምንጭ: ዛጎል)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Law, News, Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule