• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ገዱ አንዳርጋቸው “መንግሥት አለመኖሩን” አመነ

February 21, 2017 10:00 pm by Editor Leave a Comment

የካቲት 13፣ 2009 ደመቀ መኮንን፣ ገዱ አንዳርጋቸውና የጎንደር ከተማ ከንቲባ ተቀባ ተባባል በአንድነት የጎንደር ከተማ ነዋሪዎችን ባንጋገሩበት ወቅት ገዱ አንዳርጋቸው “መንግሥት የለም” እየተባለ የሚነገረውን የሚያረጋግጥ አስተያየት መስጠቱ ተስማ።

እንደ ፋና ዘገባ ከሆነ ከተሰብሳቢው ለደመቀ በርካታ ጥያቄዎች ቀርበውለታል፡፡ ፋና ይፋ ባያደርገውም በውይይቱ የከረሩ ጉዳዮች መነሳታቸው ከአንዳንድ ምንጮች ለመረዳት ተችሏል፡፡

ደመቀ በገለጻው “ጥልቅ ተሃድሶ፤ መልካም አስተዳደር፤ የህዝብ ተሳትፎ፤ …” በማለት ተሰብሳቢውን ለማሳመን ጥረት ቢያደርግም የተቻለው እንዳልሆነ ፋና ራሱ ከዘገበው ለመረዳት ቻላል፡፡

“… ተሃድሶው አንዱን አመራር ወደ ሌላ ስፍራ ከመቀየር የዘለለ ለውጥ እያመጣ አይደለም” የሚል አስተያየት ከውይይቱ ተሳታፊዎች መነሳቱን የጠቆመው የፋና ዜና ለዚህ ጥያቄ ደመቀም ሆነ ገዱ ወይም ከንቲባው የመለሱትን አልዘገበም።

ሁለቱ የኢህአዴግ ባለሥልጣናት መድረኩ ላይ እርስበርሱ የሚጣረስ ሃሳብ ሲሰጡ ተሰምተዋል፡፡ ደመቀ “ባለፉት ወራትም ሀገሪቱ ወደነበረችበት ሰላም መመለስ ችላለች” በማለት ቢናገርም ገዱ አንዳርጋቸው በበኩሉ፥ “ባለፉት ስድስት ወራት በጎንደር የኢንቨስትመንት ጥያቄ ቀንሷል፤ ስለ ጎንደር የሚነሱ አሉባልታዎችን ወደጎን በመተው የከተማዋን ገፅታ መቀየር ይኖርብናል” በማለት የደመቀን “ሰላም ነው” ንግግር ውጤት አልባ አድርጎታል።

ከዚህ በተጨማሪም ገዱ አስተዳድረዋለሁ በሚለው ክልል እርሱ “አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች” በማለት የጠቀሳቸው “የሚጠበቅባቸውን ግብር እየከፈሉ” አይደሉም በማለት መናገሩን የዜና ዘገባው አስረድቷል።

“መንግሥት ባለበት እና የመንግሥት መዋቅር ባለበት ቦታ ሕግ አለ፤ በሕጉ መሠረት ግብር ይሰበሰባል፤ ነገር ግን በሕዝብ አስተሳሰብ ውስጥ መዋቅር ፈርሷል፤ መንግሥት የለም፤ ወዘተ የመሳሰሉ አስተሳሰቦች በሚሰርጹበት ጊዜ ህዝብ እንደዜጋ የሚጠበቅበትን ግብር አልከፍልም ወደማለት ይሄዳል” በማለት ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የሕግ ባለሙ ለጎልጉል አስያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ይህ የገዱ አንዳርጋቸው ንግግር ጎልጉል (የካቲት 13፤ 2009ዓም፤ February 20, 2017) ከሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ መረጃ በመሰብሰብ ያጠናቀረውን ዘገባ የሚያረጋግጥ ሆኗል፡፡ ዘገባው ህንን ይል ነበር፤

“… በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል አስቸጋሪ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥ ያላቸዉን ስፍራዎች በተለይም ታች አርማጭሆ፣ ምዕራብ አርማጭሆ፣ ጠገዴ፣ መተማ፣ ወገራ፣ ምዕራብና ምስራቅ በለሳ ወረዳዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮች በዋናነት  የእምቢተኛነቱ እምብርት እንደሆኑ የሚጠቀሱ ሲሆን፣ በዝርዝር ባይገለጽም ጎጃም አንዳንድ አካባቢዎችና ሰሜን ሸዋ የኅቡዕ ጥቃት እንደሚፈጸም ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። በሰሜኑ ምዕራብ የአገሪቱ ክፍል በሚገኙ ወረዳዎች ከአርሶ አደሮች መሰብሰብ የነበረበት የ2008 ዓ.ም የመሬት ግብር እና የማዳበሪያ ዕዳ እስካሁን ሊሰበሰብ አለመቻሉ ትልቁ የመዋቅር መሰበር አመላካች ተደርጎ መወሰዱን የጎልጉል የአካባቢው መረጃ አቀባይ አስታውቋል። መረጃ አቀባዩ እንዳለው ራቅ ባሉ የገጠር ቀበሌዎች የማህበራዊ ተቋማት (ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት፣ የግብርና ጣቢያዎች) ወደ ቀድሞ መደበኛ ሥራቸዉ መመለስ አልተቻላቸውም።”

ከበርካታ ቦታዎች ውጥረት ውስጥ የገባው ህወሃት/ኢህአዴግ መጪውን የማሟያ ምርጫ ለማለፍ በተለያዩ አቅጣጫዎች እየተጋ ይገኛል፡፡ በዳያስፖራ ያለው ኃይል ተባብሮ መሥራት አቅቶት ነው እንጂ ከሕዝባዊ እምቢተኝነቱ በኋላ ይህንንም ያህል አይቆይም የተባለለት ህወሃት/ኢህአዴግ ዕርቅ፣ ሽምግልና፣ ድርድር፣ አብሮ መሥራት፣ ህዝባዊ ተሳትፎ፣ ሕገ መንግሥት ማሻሻል፣ … የመሳሰሉ ዕቅዶችን ወጥኖ ሕዝቡን ለማሳመን እየጣረ ነው፡፡

በአማራና በኦሮሚያ በግፍ ያፈሰሰውን ደም በገንዘብ መተካት የሚችል ይመስል ለወጣቶች ሥራ ዕድል እፈጥራለሁ እያለ ነው፡፡ በዚሁ ጎንደር ላይ በተደረገው ስብሰባ እነ ደመቀ በመላው ኢትዮጵያ 3ሚሊዮን፤ በአማራ ክልል ደግሞ ለ800 ሺህ ወጣቶች የሥራ እድል እንፈጥራለን በማለት ህዝቡን ለመደለል ሲሞክሩ ተሰምተዋል።

የዛሬ ዓመት አካባቢ ህወሃት/ኢህአዴግ በኦሮሚያ ላፈሰሰው ደም በ2.4 ቢሊዮን ብር ሥራአጥ ወጣቶችን ባለሃብት አደርጋለሁ በማለት በኦህዴድ በኩል ሲያስነግር መቆየቱ የተዘገበ ጉዳይ ነበር፡፡

“መንግሥት የለም” የሚለው አካሄድ በሕዝቡ ዘንድ የፈጠረው የስነልቦና ተጽዕኖ ህወሃት/ኢህአዴግን ክፉኛ ችግር እንደሆነበት ከተለያዩ ቦታዎች የሚሰሙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (http://staging.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News, Politics Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule