በጋምቤላ የአኙዋክ ተወላጆች ተጨፍጭፈውና ከመሬታቸው ተፈናቅለው “ለሰፋፊ እርሻ” በሚል ሲቸበቸብ ከነበረው መሬት “ወደ ሥራ የገባው” 15በመቶው ብቻ መሆኑን ህወሃት/ኢህአዴግ አስታወቀ፡፡ ለ“እርሻ ልማት” በሚል 5ቢሊዮን ብር ብድር ተሰጥቷል፡፡ የመሬት ካርታ “ከቢሮ ውጪ በመኖሪያ ቤቶችና በጫት ቤት ውስጥ” ሲሰራ ቆይቷል፡፡ የቀድሞው የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኃላፊ የነበረው ኢሳያስ ባህረ ከሥልጣኑ የተነሳው “ብድር በመስጠቱ ሂደት ለተወሰኑ የባለሃብቶች ቡድን በማድላቱ ነው” ተባለ፡፡ በጋምቤላ በደል ደረሰብን በማለት አቤቱታ ያሰሙ የትግራይ “ባለሃብቶች” ለሃይለማርያም የቀረበው ሪፖርት “የተዛባ ነው” አሉ፡፡ በጋምቤላ ይህ ነው የማይባል ግፍና የዘር ማጽዳት ተካሂዶ ከምስኪን ረዳተቢሶች የተነጠቀው መሬት ከጥቅም ውጪ ሆኗል፡፡ ገና ከጅምሩ አሠራሩ ሁሉ ትክክል እንዳልሆነ በተለያዩ ሪፖርቶች … [Read more...] about በጋምቤላ የከሸፈው “ኢንቨስትመንት”
Politics
ዛዲግ አብርሃ – የነገሪ ሌንጮ “ምክትል”?
አምልኮተ መለስ የተጠናወተውና የህወሃት አባል የሆነው ዛዲግ አብርሃ "የጥልቅ ተሃድሶ" ውጤት ተብሎ የተመደበው የነገሪ ሌንጮ ምክትል ሆኖ በሃይለማርያም ደሳለኝ መሾሙን Ethiopia Observer ዘግቦታል። ኦሮሞው ሌንጮ በአፈቀላጤነት በየሚዲያው ፊቱን ሲያስመታ የድርጅት ሥራውን የሚያከናውነው መለስን ማንነቴ ነው መንፈሴን ይቀሰቅሰዋል የሚለው ህወሃቱ ዛዲግ ይሆናል። ከዚህ በፊት ስለ መለስ የተናገረውን እዚህ ላይ ማንበብ ይቻላል። "ጥልቅ ተሃድሶ" በጥልቅ መበስበስ ይቀጥላል! ጎልጉል … [Read more...] about ዛዲግ አብርሃ – የነገሪ ሌንጮ “ምክትል”?
የጣና በለስ ታሪካዊ የልማት ፕሮጀክት፤ ከመፈራረስና ውድመት እስከ መሸጥ
የጣና በለስ ፕሮጀክት አጭር ታሪክ የጣና በለስ ፕሮጀክት ልማታዊ ግቦች/ህልሞች ምን ነበሩ? የጣና በለስ ፕሮጀክት በአፄው ስርዓት ተጠንስሶ፥ በደርግ አብቦ፥ በህወሀት/ኢህአዴግ እንዴትና ለምን ፈራረሰ? ዛሬ በጣና በለስ ላይ የተጋረጠው አዲስ እና አስደንጋጭ አደጋስ ምንድን ነው? መፍትሄውስ? መግቢያ የአባይ ተፋሰስ ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ተፋሰሶች የላቀ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ፋይዳ ያለው ልዩ ቦታ በመሆኑ በርካታ ጥናቶች ተደርገውበታል። የመጀመርያው የአባይና ጣና ዳሰሳ ጥናት የተካሄደው በእንግሊዞች ነበር። ቀጣዩ ዝርዝርና ጥልቅ ጥናት የተካሄደው በአጼ ኃይለሥላሴ ልዩ ጥያቄ ሲሆን ምክንያቱም አወዛጋቢው የእንግሊዝና ጣልያን በ1925 ዓ.ም የተፈራረሙት ውል ነበር። ይህ የወራሪ ሃይሎች ውል ጣልያን ኤርትራ የሚገኘውን ቅኝ ግዛቷንና ሶማሌ ያለውን ቅኝ … [Read more...] about የጣና በለስ ታሪካዊ የልማት ፕሮጀክት፤ ከመፈራረስና ውድመት እስከ መሸጥ
ስለ ካስትሮ ምን ተባለ?
ዶ/ር ደስታው አንዳርጌ ይህንን ጽፈዋል፣ ፊደል ካስትሮ፦ የኢትዮጵያና አፍሪካ የቁርጥ ቀን ወዳጅ፤ የክፍለዘመኑ ዳዊት የ፳ኛው ክ/ዘ ካፈራቸው ታላላቅ መሪወች ውስጥ ሁልጊዜም ፍትህና ነጻነት ከሚሹት ጋር በመቆም፤ ሁሌም በትክክለኛው የታሪክ ገጽ በመገኘት ፊደል ካስትሮን የሚስተካከል ማን አለ? ከኒካራጓና ቺሌ እስከ ቬትናም ከፍልስጤም እስከ አልጀሪያ ብሎም ደቡባዊ አፍሪካ ነጻነት ለናፈቃቸው ሁሉ የካስትሮን ያህል ታላቅ ድጋፍ ያደረገ ሌላ መሪ ማንም የለም። በተለይ የአፍሪካ አገራት ከኢምፔሪያሊስቶች ጋር ባደረጉት ትንቅንቅ የካስትሮና የኪውባ ቁርጠኝነት ከጉዳዩ ባለቤቶች ያልተለየ ነበር። ኪውባ ለአንጎላ ያደረገችው እጂግ መጠነሰፊና ከአስር አመት በላይ የዘለቀ ድጋፍ ለዚህ አይነተኛ ማሳያ ነው። ካስትሮ አንጎላ ከፖርቹጋል ቅኝ ነጻ ለመውጣት ካደረገችው ተጋድሎ ጀመሮ በአሜሪካ ድጋፍ … [Read more...] about ስለ ካስትሮ ምን ተባለ?
ፕ/ር መረራ ጉዲና ታፍነዋል
የመድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ዛሬ ረቡእ ማምሻውን በደህንነት ሃይሎች ታፍነው መወሰዳቸውን ለማረጋገጥ ችለናል። በዛሬው እለት ፕ/ር መረራ ጉዲና መኖርያ ቤት በደህንነቶች እና ከባድ መሳርያ በታጠቁ የአጋዚ አባላት ተከብቦ መዋሉን የአይን እማኞች ገልጸዋል። ብእር ብቻ ለያዘ አንድ ሰላማዊ ሰው ይህን ሁሉ ሃይል ማሰማራት ስርዓቱ ምን ያህል እንደተብረከረከ የሚያሳይ መሆኑን እማኞቹ ጨምረው ገልጸዋል። በአውሮፓ ህብረት ጥሪ ተደርጎላቸው ሃገሪቱ ስላለችበት መስቀለኛ መንገድ ገለጻ አድርገዋል። ከዚያም በሆላንድ፣ በጀርመን እና በስዊዘርላንድ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋር ስለ ሃገሪቱ ሁኔታ መወያየታቸው ይታወሳል። የኢትዮጵያ ችግር በሰላማዊ መንገድ መፍትሄ ያገኛል ብለው በምርጫ እና በሰላማዊ አግባብ ሲታገሉ የነበሩት ፕ/ር መረራ ጉዲና ለምን እንደታፈኑ … [Read more...] about ፕ/ር መረራ ጉዲና ታፍነዋል
“የታሪክ ሂሳብ ማወራረዱን አቁሙ!” ፕ/ር መረራ ጉዲና
"በውይይት የማይፈታ ችግር የለም። ስትወያዩ ግን የታሪክ ሂሳብ ማወራረዱ ላይ አታተኩሩ። ትኩረታችሁን አሁን የተጋፈጥናቸው ችግሮች ላይ አድርጉ።" ሲሉ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አስታወቁ። ፕሮፌሰሩ ይህንን የገለጹት በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በኔዘርላንድ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያ ጋር በትላንትናው እለት 20 November 2016 በአምስተርዳም ባደረጉት ውይይት ላይ ነው። በውይይቱ የኦሮሞ አክቲቪስቶችም ተገኝተው ሃሳባቸውን አካፍለዋል። ስለ ሃገሪቱ ፈታኝ ሁኔታ እና ስለወደፊቱ እጣ ፈንታ በስፋት ያብራሩት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ - ፕ/ር መረራ ጉዲና ከተሰብሳቢው ለቀረቡላቸው በርካታ ጥያቄዎችም ምላሽ ሰጥተዋል። "አዋጁ እና ኮማንድ ፖስቱ ሕዝባዊ አመጹን ያበርደዋል ወይ?" ተብለው ሲጠየቁ፣ ሃገሪቱ አሁን በመስቀለኛ መንገድ ላይ መሆንዋን ገልጸው አሁን ያለው ሁኔታ ላይ እንዲህ … [Read more...] about “የታሪክ ሂሳብ ማወራረዱን አቁሙ!” ፕ/ር መረራ ጉዲና
ጎሠኛነት በባዶ ሜዳ!
በተለያዩ የኢትዮጵያ አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ሁሉ የሚደረገው ውይይትና ክርክር እንደተጠናቀቀ ተቆጥሮ የአማራና የኦሮሞ ጎሠኛነት ትልቁ አንገብጋቢ ጉዳይ እየሆነ ነው፤ (ስለ ኢትዮጵያ ለማያውቅ ሰው በኢትዮጵያ ውስጥ ከጠሩና ከጸዱ አማራና ኦሮሞዎች በቀር በአገሪቱ ውስጥ ሌላ ሰው ያለ አይመስልም!) ጎሠኛነት ጉዳያችን ያልሆነው ኢትዮጵያውያን የዳር ተመልካች መሆኑ እየሰለቸን ነው፤ ምንም እንኳን አማራና ኦሮሞ የተባሉት ጎሣዎች በብዛት ከሁሉም ቢበልጡም ከሰማንያ በላይ የሚሆኑ ጎሣዎች እንደሌሉና በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ ቃል እንደሌላቸው ተደርጎ የሚጎነጎነው የሚስዮናውያንና የስለላ ድርጅቶች ታሪክ ለኢትዮጵያውያን ባዕድ ነው፡፡ ሌላው የሚያስደንቀውና ዓይን ያወጣው ነገር እነዚህ ኢትዮጵያን በጠዋቱ ለመቃረጥ እየተነታረኩ ያሉ በአማራና በኦሮሞ ጎሣዎች ስም መድረኩን የያዙት ሰዎች በውጭ አገር … [Read more...] about ጎሠኛነት በባዶ ሜዳ!
ሕዝብ ላይ የሚፈጸም የፖለቲካ ውርጃ!!
አሁን የሚፈለገው የሚያሻገሩ መሪዎችን ማግኘት ብቻ ነው። ሕዝብ በፖለቲካ መሪዎች ሃፍረትን እየተግሞጠሞጠና ደሙ ደመ ከልብ እየሆነ የሚኖርበት ዘመን እንዲያከትምለት ይፈልጋል። የአንተ ደም የእኔ ደም ነው በማለት የችግሩ ጉያ ውስጥ ሆኖ አጋርነቱን፣ አንድነቱን ሲያሰማ ሩቅ ተቀምጦ እንደ ቅጥረኛ የወገንን ሞራል ማላመጥ አግባብ አይሆንም። ውሎ አድሮ ከገዳዮቹ በላይ ያስጠይቃል። በቅጥረኛነትም ያስመድባል። ከአገራችንም ሆነ ከዓለም ዘመን የማይረሳቸው የውብ ስብእና ባለቤቶች ሕዝባቸውን አሻግረዋል። ክፉዎች የቀበሩትን የቂምና የጥላቻ ገመድ በጣጥሰው አገራቸው በልዕልና፣ ሕዝባቸው በሰላም እንዲኖር አስችለዋል። በቀናነት ጀምረው፣ በቀናነት ጨርሰዋል። በታማኝነት ሃላፊነትን ተረከበው በታማኝነት አለፈዋል። ዝርዝር ውስጥ ባንገባም በህይወት ያሉም አሉ። እንዲህ ያሉትን የሚያስቡ “እኛንስ ማን … [Read more...] about ሕዝብ ላይ የሚፈጸም የፖለቲካ ውርጃ!!
Ato Emmanuel Abraham (1913-2016)
Ato Emmanuel Abraham who had served his country in a number of important diplomatic and ministerial posts for nearly four decades and half (1931-1974) has died at a great age of 103 on Wednesday. Emmanuel was ambassador to Britain and Italy and cabinet minister and director general at the Ministry of Foreign Affairs and director general of the Ministry of Education and Fine Arts, Minister of Posts, Telegraphs and Telephones; Minister of communications and Transport; and finally, minister of … [Read more...] about Ato Emmanuel Abraham (1913-2016)
ኢንተርኔት በመዘጋቱ በትንሹ 9 ሚሊዮን ኪሣራ ደርሷል
ኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ውስጥ ለ30 ቀናት የኢንተርኔት አገልግሎትን በማቋረጧ ወደ 9 ሚሊዮን ዶላር ገደማ ማጣቷን መቀመጫውን በዩናይትድ ስቴትስ ያደረገው ብሮኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ባለፈው ሳምንት ይፋ ያደረገው ጥናት ጠቋሟል። የብሩኪንግስ የፖሊሲ ጥናት ተቋም ምክትል ፕሬዝዳንት ዳረል ዌስት ባቀረቡት ጥናት በቅርብ ዓመታት ተጠቃሚዎች የሚገለገሉባቸውን የተወሰኑ አፕልኬሽኖች፤ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት አሊያም መላውን የኢንተርኔት አገልግሎት መንግስታት ማቋረጥ እና መዝጋት እየተለመደ የመጣ ክስተት መሆኑን አትተዋል። ከእነዚህ አገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ ነች። ከሰኔ 24 ቀን 2007 ዓ.ም. እስከ ሰኔ 23 ቀን 2008 ዓ.ም. ባሉት ጊዜያት ለ30 ቀናት በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን ይኸው ጥናት ጠቁሟል። «መንግስታት ብሔራዊ እና የሕብረተሰብ … [Read more...] about ኢንተርኔት በመዘጋቱ በትንሹ 9 ሚሊዮን ኪሣራ ደርሷል










