ከአዲስ አበባ በስተደቡብ ቅሊንጦ የሚባል ጫካ አለ እዚያ ጫካ ውስጥ በርካታ ጥቁር አንበሶች አሉ፡፡ ለጥቂት ቀናት እዚያ ጫካ ውስጥ ከትቸ ነበር፡፡ በገባሁ በዐሥረኛ ቀኔ ትቻቸው ወጣሁ፡፡ እዚያ በነበርኩበት ወቅት ካገኘኋቸው አናብስት የሁለቱን ታሪክ ብቻ በአጭር በጭሩ ላጫውታቹህ፡፡ አንደኛው አበበ ካሴ ይባላል፡፡ ተወልዶ ያደገው ጎንደር ነው፡፡ አምና 2006ዓ.ም. ጥር 12 ቀን ነበር የተያዘው፡፡ ወደዚህ ጫካ ከመምጣቱ በፊት በተለያዩ ሀገሪቱ ውስጥ ባሉ የማሰቃያ ቦታዎች ሰቆቃ ሲፈጸምበት ቆይቶ በመጨረሻ ነው እዚህ ጫካ ውስጥ የታሰረው፡፡ አበበ ካሴ የግንቦት 7 ቆራጥ ታጋይ ነው፡፡ ከዚያ በፊት ከ1981-1993ዓ.ም. ድረስ የቀድሞው ኢሕዴን የአሁኑ ብአዴን ታጋይ ሆኖ ለ12 ዓመታት አገልግሏል፡፡ ከዚያ በኋላ እሱና ጓዶቹ ታግለው ለዚህ ያበቋቸው መሪዎቹ ከዚህ በስተቀር የማይባል … [Read more...] about የቅሊንጦ አንበሶች
Opinions
THE ACME OF EVIL IGNORANCE:
Thirty to fifty years ago the TWINS, the shabia (EPLF) and the weyyane (TPLF) discovered that one of their formidable and impregnable enemies was RECORDED HISTORY. In their boundless ignorance they believed they could wipe out RECORDED HISTORY by destroying the books on Ethiopia. They started their destructive campaign in London and Washington DC. The University of London and the Library of Congress were, I believe, their first targets. This is a consequence mainly attributable to … [Read more...] about THE ACME OF EVIL IGNORANCE:
“አሸባሪው” የ72 ዓመት አዛውንት
የ72 አመቱ አቶ ቀኖ አባጆቢር የሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ውስጥ የጥበቃ ሰራተኛ ናቸው፡፡ የሚኖሩት ከ10 አመት ልቻቸው ጋር ነው፡፡ ይህን ልጅ እሳቸው ብቻ ነው የሚያሳድጉት፡፡ ትናንት ሰላማዊ ሰልፈኞቹ ከታፈሱ ከሰዓታት በኋላ ስራ ውለው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ በደህንነቶች ታፈኑ፡፡ አቶ ቀኖ የጥበቃ ስራ ከመስራት ውጭ ሰልፉ አስተባባሪም ተሳታፊም አልነበሩም፡፡ ግን ታጥሮ ከሰነበተው የሰማያዊ ቢሮ የወጣ ሁሉ ሲለቀም ነበርና እሳቸውንም አፈኗቸው፡፡ ምን አልባትም ተደብድበው ይሆናል፡፡ ይህ ስርዓት እነ ይልቃልን፣ ብርሃኑን፣ አቤልን፣ በላይን፣ ጣይቱዎቹን . . . ሰማያዊን ብቻ አይደለም የሚፈራው፣ የሚያፍነው፣ የሚያፍሰው፣ የሚደበድበው፡፡ አቶ ቀኖንም የሆነ ነገር ያደርጋሉ ወይንም አድርገዋል በሚል (በራሱ ትርጉም) አፍኖ አስሯቸዋል፡፡ አሁን አቶ ቀኖ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛሉ፡፡ … [Read more...] about “አሸባሪው” የ72 ዓመት አዛውንት
ቴዲ አፍሮን ቦሌ ላይ ለምን አገቱት?
ወደ አውሮፓ የሚያስገባውን ቪዛ እና ትኬት ይዞ ከወዳጆቹ ጋር ጉዞውን ለመጀመር ወደ ቦሌ አለም-ዓቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ አቀና። እዚያው እንደደረሰ የተለመደው የፓስፖርትና ትኬት ቁጥጥር ተደረገ። ሁሉም የተሟላ ነበር። ቴዲ ሸኚዎቹን ተሰናብቶ ወደ ውስጥ ጋባ። እለተ ሐሙስ፣ ህዳር 28 ቀን 2007 ዓ.ም.። የአውሮፓው ኮንሰርት በፊንላንድ፣ ሄልሲንኪ ቅዳሜ፤ ህዳር 28 ቀን ይጀምራል። ፊንላንድና አካባቢው ያሉ የቴዲ አድናቂዎች ትኬት ቆርጠው አርቲስቱን በጉጉት እየተጠባበቁት ነው። የቴዲ አፍሮ ማናጀርም አቡጊዳ ባንድን ይዞ ሄልሲንኪ ላይ ለቅዳሜው ስራ በልምምድ ላይ ይገኛል። ቴዲን ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ተሰናብተው የተመለሱ ወዳጆቹ አውሮፓ ደውለው አርቲስቱን ሄልሲንኪ ላይ እንዲቀበሉት ተናግረው ነበር። ነገሩ እነሱ እንዳሰቡት ግን አልነበረም። ዘግየት ብሎ ሌላ ነገር መጣ። ሰዎቹ ቦሌ ላይ … [Read more...] about ቴዲ አፍሮን ቦሌ ላይ ለምን አገቱት?
Ethiopia: Making Reconciliation Work
The reconciliation dialogue needs to progress in parallel on two fronts: (1) among the several opposition groups; and, (2) between the government and oppositions. Allow me to be pragmatic by putting myself in the shoes of both the government and the opposition to deal with the reconciliation dialogue on the latter front. Since there is so much mistrust between the government and oppositions, tossing the word “reconciliation” around will not get us anywhere. It means different things for … [Read more...] about Ethiopia: Making Reconciliation Work
ዘመነ መሳፍንትና የፖለቲካ መሪዎቻችን የወረሱት ቅርስ
በዘመነ መሳፍንት ወቅት፤ ለስሙ በዙፋኑ ላይ የዘር ግንድ ያለውን ሰው አስቀምጠው፤ ራሳቸውን እንደራሴ በመሾም፤ ጉልበተኞች ያደረጉት ሁሉ ግልጽ ነው። የውጭ ሀገር መንግሥታት ደግሞ በወኪሎቻቸው አማካኝነት ፀረ-ኢትዮጵያ ሚና ተጫወቱ። በደንብ በዝርዝር የሚያስረዳ መዝገብ ግን አላገኘሁም። ከዚህም ከዚያም ለቃቅሜ የተገነዘብኩትን ይዣለሁ። የእስክንድርያውን የኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን በመጠቀም፤ ግብፅና ቱርክ በአንድ በኩል፣ በፖርቹጋሎች የተጀመረውን ግንኙነት በመጠቀም፤ የካቶሊክ ቤተክርስትያን በሌላ በኩል፣ በእንግሊዝና በፈረንሳይ በኩል ደግሞ የፕሮቴስታንትና የአድቬንቲስት ተቋሞች በማዕከላዊው የሀገራችን ክፍል ያላደረጉት ተንኮል የለም። የሁሉም ጥርቅም ጥረት፤ ክርስትናን ወይንም እስልምናን ተከትለው፤ የፈጣሪያቸውን ሥራ ለማስተማር ሳይሆን፤ ጠንካራ ኢትዮጵያ እንዳትኖር ለማድረግ ነበር። አባይን … [Read more...] about ዘመነ መሳፍንትና የፖለቲካ መሪዎቻችን የወረሱት ቅርስ
ግልጽ ደብዳቤ ወይዘሮ ገነት ዘውዴ
የዱሮ ወዳጄ ሰላምታዬ ይድረሽ። እንደምታውቂው ከተያየን ከሁለት አስርት አመታት በላይ ሆኗል። እኔም ካገሬ ከወጣሁ 21 ዓመት አለፈኝ። በጤናና በምቾት እንደምትኖሪ እሰማለሁ። እግዚአብሄርም መንግስትም ጥሩውን ነገር ሁሉ አብዝቶ እንዲሰጥሽ ምኞቴ ነው። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጓደኝነት ከምቀርባቸውና ከማከብራቸው ስዎች ውስጥ አንቺ አንዷ እንደነበርሽ ራስሽም ብዙ ሰዎችም ያውቃሉ። ከጊዜ ብዛትና በስልጣንም ርቀት ምክንያት ጓደኝነቴን ብትረሽውም አልፈርድብሽም። እኔ ግን ከሀገሬ ባለስልጣኖች አንዷ በመሆንሽ አልፎ አልፎም ቢሆን ስላንቺ የሚባለውን ከፉም ደግም እሰማለሁ። ብዙ ጊዜ ሰዎች ስላንቺ ክፉ ሲናግሩ ስሰማ የጓደኝነት ነገር እየሆነብኝ ደስ አይለኝም። ተሳክቶልኝ እንደሆን ባላውቅም ስላንቺ የማውቃቸውን በጎ ነገሮች በማንሳትም ልሟገት የሞከርኩበት ጊዜ ጥቂት አይደለም። ብዙ ሰዎች ያኔ 41 … [Read more...] about ግልጽ ደብዳቤ ወይዘሮ ገነት ዘውዴ
ለለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
መልዕክቱን አባዝቶ ለሌሎች በማዳረስ ለ24 ሰዓቱ ሰልፍ ቅስቀሳ የበኩላችሁን እገዛ እንድታደርጉ ጥሪ እናስተላልፋለን! ያለመስዋዕትነት ድል የለም! … [Read more...] about ለለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያውያን በሙሉ
የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር
ማስታወሻ፡ ይህች ጽሁፍ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከተከሰሰባቸው ሁለት መጣጥፎች አንደኛዋ ናት። በመጭው ወር በአሶሳ የሚደረገውን የብሄር ቀን ድራማ እሳቤ በማድረግ - በርካታ አንባብያን በጠየቁት መሰረት እነሆ በድጋሚ ለንባብ አቅርበናል። "እኛ ጭቁን ብሄረሰቦች ከዚህ ቀደም በየሰው ቤት ተቀጥረን የምንሰራ፣ አሽከሮች እየተባልን ነበር የኖርነው። አሁን ግን ይኸውና ህገ-መንግስታችን መብታችንን ሰጥቶናል... ኑሯችንም ተሻሽሎ ዛሬ ዘመናዊ ኑሮ እየኖርን ነው።" እያለ የሚናገርን አንድ ጎልማሳ የቴሌቪዥኑ መስኮት ያሳያል። የደቡብ ቅላጼና ዘዬ ባለው አማርኛ ከደቡብ የመጣ ጎልማሳ ነው በቴሌቪዥን ቀርቦ መግለጫ እየሰጠ ያለው። ከአነጋገሩ በቀን ሶስቴ የሚበላ፣ የባቡር ሃዲድ እና የኤሌክትሪክ መስመር ገብቶለት፣ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም... ይመስላል። የዚህ ምስኪን ሰው ገጽታ … [Read more...] about የብሄር ነጻነት እስከ መጨፈር
የተዘጋውን የአረብ ሀገራት የኮንትራት ሰራተኛ አቅርቦትን ለመክፈት የወጣው ረቂቅ!
* ስለ ሰራተኞች መብት ጥበቃ መነሳቱ አልተዘገበም * በተወያይ ኤጀንሲዎች በኩል ግን ረቂቁ ውዝግብ አስነስቷል * ከዚህ ቀደም ያለ በኮንትራት ለተበተኑትስ ዜጎችስ ምን ታስቧል? አዲሱን መረጃ ያገኘሁት ሃገር ቤት ከሚታተመው ከአድማስ ጋዜጣ ላይ ነው፣ እንዲህ ይላል "ወደ አረብ አገራት የሚሄዱ ሰራተኞች ላይ የሚደርሰውን ችግርና እንግልት ለማስቀረት በሚል ከአንድ ዓመት በላይ ተቋርጦ የቆየውን አሰራር ለማስጀመርና ለመቆጣጠር የተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ውዝግብ አስነሳ፡፡" ... ወረድ ብለን ዝርዝር መረጃውን ስንቃኝ በዋናነት መታየት ያለበት አንኳሩ የሰራተኞች ይዞታና የመብት ጥበቃ ጉዳይ በዘገባው ላይ አልተካተተም። ይህም ይሁን ብለን ዝርዝሩን ስንቃኝ ከዚህ ቀደም በነጻ ያገኙትን ቪዛ በደላላ በየገጠር ከተሞች ሰብስበው እህቶቻችንን ከመላካቸው አስቀድሞ ፈቃድ ሲያወጡ ለመንግስት … [Read more...] about የተዘጋውን የአረብ ሀገራት የኮንትራት ሰራተኛ አቅርቦትን ለመክፈት የወጣው ረቂቅ!










