ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 - በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል። የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ - የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል። ይህ ሰው ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፎላ … [Read more...] about የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ!
Opinions
የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የሕይወት ጉዞ
መግቢያ፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ከተመሠረተ ጀምሮ የተለያዩ ስሞችን፣ መርኆዎችን፣ ተግባራትን፣ ባጠቃላይም ማንነትን ተከናንቧል። ይህ ማለት፤ በሂደቱ እየተቀያየረ የሄደ ድርጅት ነው። ሲነሳ፤ አሁን የያዘው እምነት፣ ግብና አሠራር አልነበረውም። እግረ መንገዱን ለዕለቱ የሚረዳውን የፖለቲካ አቋም እየውለበለበ ተጓዘ እንጂ፤ ዘላቂ የሆነ የፖለቲካ አቋም አልነበረውም። ይህ የሚነግረን፤ ይህ ድርጅት፤ አጋጣሚዎችን ተጠቃሚነትን፣ ሥልጣንን፣ ቂምና በቀልን፣ የሕልውናው መሠረቶች አድርጎ የተጓዘ እንጂ፤ መርኆ ወይንም ሕዝባዊ ግንዛቤ ያላነገበ ድርጅት መሆኑን ነው። ይህን ቡድን የሚያሽከረክረው የማርክሲስት ሌኒኒስት ሊግ ኦፍ ትግራይ ፍጹም ማርክሲስት አይደለም። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር፤ ትግሬዎችን ነፃ ሊያወጣ የተነሳ ድርጅት አልነበረም። በርግጥ ስሙ፤ ከትግራይ ብሔራዊ ድርጅት፤ በብዙ … [Read more...] about የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የሕይወት ጉዞ
በኢህአዴግ ለባርነት የተሸጠችው ወገን ሰቆቃ
ገነት አበበ ሞላ ትባላለች፤ የልጅነት ጊዜዋን ሩጣ ያልጠገበች በአስራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ ኮረዳ ነች። ከዛሬ 3 አመት በፊት ነበር በኑሮ ውድነት የተጎሳቆሉ ቤትሰቦችዋን ከድህነት ለመታደግ በወቅቱ እስከ ገጠር በዘለቀው የአሰሪና ሰራተኛ የደላሎች ዘመቻ ከአርሲ ኮሌ ወረዳ ኩዬ ከተማ ተመልምላ የማይጨበጠውን የአረቡን ዓለም መከራ ለመጋፈጥ ተስፋ ሰንቃ ወደ ሳውዲ አረቢያ ያቀናቸው። በወቅቱ በሰው ልጆች ህይወት ዶላር ለማግበስበስ በየአካባቢው በተከፈቱ የአሰሪና ሰራተኛ ኤጀንሲ ደላሎች ከእናቶቻቸው ጉያ ተነጥቀው ለአቅመ ሄዋን ያልደረሰውን እድሜዎቻቸውን ቆልለው ፓስፖርት የወሰዱ ህጻናት ሳይቀሩ በቀን 1500 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የኮንትራት ሰራተኞች ያለህይወት ዋስትና ወደ ሳውዲ አረቢያ በጅምላ ይላኩ የነበረበት ወቅት በመሆኑ ወጣት ገነትም ሰው እንደሆነው እሆናለሁ ብላ … [Read more...] about በኢህአዴግ ለባርነት የተሸጠችው ወገን ሰቆቃ
Ethiopia shall overcome
In May of 2005 the noble idea of bringing change by peaceful means died a violent death in Ethiopia. The Tigrai People Front declared in no uncertain terms power sharing is not part of the equation. They have proved it three times since then. What part of that do we have a problem accepting? The TPLF party does not just whisper. They shout so loud that the whole body shakes from the vibration caused by the violent, vile and wild savage scream. That did not stop well-meaning and brave … [Read more...] about Ethiopia shall overcome
ሳይገባቸው ቻይና በነገራቸው የሚያውቁትን የሚረሱ ማን ያስተምራቸው!
የጎረቤት ኬንያ ዳኛ ለኬንያ መንግሥት አስፈጻሚው ክፍል ልኩን ነገረው፤ ሕገ መንግሥቱን በመርፌ አስተኝተህ ሕገ መንግሥቱን የሚጻረር ሕግ ለማውጣት አትችልም፤ ስለዚህም የሰነዘርኸውን የጉልበት ሕግ አንሣ፤ አለው፤ ዳኛ አይጥፋ! ሌላ ቢቀር ከጎረቤት ዳኝነትን እንስማ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ዳኛ ቢኖር ስንት ጋዜጠኛ፣ ስንት የሃይማኖትና ስንት የፖሊቲካ መሪዎች ከየወህኒ ቤቱ ይወጡ ነበር! ሁላችንም እንደልባችን ሳንፈራ፣ ሳንፈራራ በሙሉ ነጻነት ችግሮቻችንን የወያኔን ጭቆና ጨምሮ ለመወያየትና መፍትሔዎችን ለመለዋወጥ የምንችልበት መድረክ፣ ጋዜጣ፣ መጽሔት፣ ራድዮና ቴሌቪዥን በኢትዮጵያ ውስጥ ይኖረን ነበር፤ ስንት ሰው ሥራ ያገኝ ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ በየመንገዱ ጠመንጃ የያዘ ሊያስፈራራን የሚሞክር ሆድአደር እያየን፣ እንደዚሁም በየጫካው ያሉትን እያሰብን ሰላማችንን ከምናጣ አበባውን ትተን፣ ሩዙን … [Read more...] about ሳይገባቸው ቻይና በነገራቸው የሚያውቁትን የሚረሱ ማን ያስተምራቸው!
“አሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን (አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን)”
በተለያየ ጊዜ በተለያየ የክህደት አስተምህሮ በመሰናከል በመውደቅ ከዚህች ሐዋርያዊት አንዲት ቤተክርስቲያ እየተለዩ በኑፋቄያዊ አስተምህሮ ጸንተው በመቀጠል ለዚህች አንዲት ሃይማኖት አንዲት ቤተክርስቲያን ጠላቶች የሆኑ ዲያብሎስን የሚያገለግሉ ከ40 ሽህ በላይ ይቆጠራሉ፡፡ ሃይማኖት ነንም ይላሉ፡፡ ክርስቶስ በወንጌሉ ሐዋርያትም በመልእክቶቻቸው እንደተናገሩት ግን ከአንዲቷ በስተቀር ይሄ ሁሉ ሃይማኖት ነኝ ባይ ዝግንትል ሐሰተኛና ዲያብሎሳዊ የክህደትና የጥፋት መንገዶች ናቸው፡፡ የዘመኑ ፍጻሜ ሲቃረብ ብዙዎች ሐሰተኞች መምህራን በየ እልፍኙ የሚሰብኩላቸው ሐሰተኞች ኢየሱሶች ሐሰተኞች ክርስቶሶች ይመጡ ዘንድ እንዳላቸውና ከእነሱም እንድንጠበቅ አስጠንቅቆናል፡፡ ማቴ. 24፤1-28 “አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት” ኤፌ. 4፤5 “መንፈስ ግን በግልጥ በኋለኞቹ ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ … [Read more...] about “አሐቲ ቅድስት ቤተክርስቲያን (አንዲት ቅድስት ቤተክርስቲያን)”
“ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ – ኤ”
ወቅታዊው የቴሌቭዥናችን አዝማች፤ ... ሰማንያ አንድ ዜሮ ዜሮ- ኤ ብለሽ መላዕክት ከላልሽ፣ አባይን ገድበሽ ሽልማት በሽበሽ። .... 8100 .... 8100 .... 8100-A A A የምትለው ዜማ በብዛት ትለቀቃለች። ኮሜዲያን ተሰብሰበው የሰሩዋት ዜማ ናት። ቀልደኞቹን ማኖ ለማስነካት ተብላ የተቀነባባረች ነገር ናት የሚሉም አሉ። የቴሌቭዥኑን ጣብያ ከፍቶ የሚመለከተው ሰው እጅግ ጥቂት ቢሆንም መልእክቱ በማህበራዊ ድረ-ገጾች መደመጡ አልቀረም። የዚህ ማስታወቅያ አላማ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የእጣው ዝርዝር ግን ለብዙዎች እንግዳ ሳይሆን አልቀረም። አንዲት አዛውንት የልጃቸውን ተንቀሳቃሽ ስልክ እያነሱ ይቀጠቅጣሉ። በሳምንት ሶስቴ 8100 እየደወሉ 'A' ፊደልን ይጫናሉ። ከብዙ ግዜ በኋላ ታዲያ ልጃቸው አወቀባቸው። በመገረምም ለምን ይህንን ሁሉ ግዜ መደወል እንደፈለጉ ጠየቃቸው። … [Read more...] about “ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ – ኤ”
የኢትዮጵያ ጉዳይ
ግልፅ ደብዳቤ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ሀገር ማለት ባሕርዳር ዛሬም ስለልጆቿ አነባች የአምባገነኖች አከርካሪ በተባበረ የሕዝብ ክንድ ይሰበራል በሴቶች ላይ የሚፈጸም በደልና ጾታዊ ጥቃት ይቁም ኢትዮጵያዊነት በዘር ማንነት አይደበዝዝም ለነፃነትና ለዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የሚደረገው ትግል በቀላሉ አይቀለበስም ፖሊስና ሰብዓዊ መብት በኢትዮጵያ መጽሔቷ በእነዚህና በሌሎች ጉዳዮች ላይ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ታተማለች፡፡ ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጉዳይ
ህወሃት ምንድን ነው?
በቅርቡ የህወሃት ኣርባኛ ዓመት ለየት ባለ መንገድ መከበሩ ገርሞኛል። በየዓመቱ እንደሚከበር ሁላችን እናውቃለን። ይሁን እንጂ የዓርባኛ ዓመቱ በዓል እንዲህ ለምን እንደተወራለት ለምን የሌላ ኣገር መሪ ሳይቀር እንደተጋበዘበት ኣልገባኝም። ብዙ ጊዜ እንዲህ ዓይነት ለየት ያለ ድግስ የሚደረገው የኢዮቤልዩ በዓል ሲከበር ነው። የሆነው ሆኖ የመነሻ ኣሳቤ ይሄ ኣይደለም። ህወሃት ኣርባኛ ዓመት በዓሉን ሲያከብር እኔ በህወሃት ተፈጥሮ ስደመም ነበር። በርግጥ ኢትዮጵያ ኣሁን ላለችበት የተመሰቃቀለ ህይወት ሲንከባለሉ የመጡ ኣንዳንድ ችግሮች ኣስተዋጾ ቢያደርጉም የችግሩ ከፍተኛ ኣስተዋጾ ኣድራጊ ግን ህወሃት ነው። በየክልሉ የህወሃት ተከታዮች ኣስተዋጾኣቸው እንዳለ ሆኖ የህወሃት ድርሻ ግን በጣም ገዝፎ ይታያል። ግን …ግን ለምንድነው በህወሃት መራሹ መንግስት ጊዜ ኢትዮጵያ እንዲህ ዓይነት ኣስከፊ … [Read more...] about ህወሃት ምንድን ነው?
“የህዝባዊ ማህበራት ሚናና የ2015 የኢትዮጵያ ምርጫ”
ለዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሙሉ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ስለ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምንነት ማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ በየዓመቱ የአለም አቀፍ የሴቶችን ወር ምክንያት በማድረግ በመጋቢት ወር ላይ ጉባኤ በማዘጋጀት ሴቶችን በሚመለከቱ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎችን እንዲያቀርቡና፣ ለችግሮቹ መፍትሔ እንዲጠቁሙ በማድረግ ማህበረሰባችንን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሴቶች በማህበራዊ፣ በኤኮኖሚና በፖለቲካ የሚደርስባቸውን ችግሮች በተለይም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በአረብ አገራት ተሰደው ስላሉ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች መብትን አስመልክቶ በየጉባኤዎቹ ሰፋ ያለ ትምህርታዊ ውይይቶች አካሂዷል። ዘንድሮም የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ለ፬ኛ ጊዜ የሚካሄድ ዓመታዊ ጉባኤ … [Read more...] about “የህዝባዊ ማህበራት ሚናና የ2015 የኢትዮጵያ ምርጫ”










