• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የህዝባዊ ማህበራት ሚናና የ2015 የኢትዮጵያ ምርጫ”

February 19, 2015 01:53 am by Editor Leave a Comment

ለዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሙሉ

ላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ስለ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምንነት ማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ በየዓመቱ የአለም አቀፍ የሴቶችን ወር ምክንያት በማድረግ በመጋቢት ወር ላይ ጉባኤ በማዘጋጀት ሴቶችን በሚመለከቱ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎችን እንዲያቀርቡና፣ ለችግሮቹ መፍትሔ እንዲጠቁሙ በማድረግ ማህበረሰባችንን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሴቶች በማህበራዊ፣ በኤኮኖሚና በፖለቲካ የሚደርስባቸውን ችግሮች በተለይም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በአረብ አገራት ተሰደው ስላሉ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች መብትን አስመልክቶ በየጉባኤዎቹ ሰፋ ያለ ትምህርታዊ ውይይቶች አካሂዷል።

Conference_Flyer_2015ዘንድሮም የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ለ፬ኛ ጊዜ የሚካሄድ ዓመታዊ ጉባኤ አዘጋጅቷል፡፡ የዚህ የ፬ኛው የኢትዮጵያ ሴቶች ጉባኤ መሪ ቃል የህዝባዊ ማህበራት ሚናና የ2015 የኢትዮጵያ ምርጫ ነው። (THE ROLE OF CIVIL SOCIETY IN THE UPCOMING 2015 ETHIOPIAN ELECTION)

እንደሚታወቀው ሕዝባዊ ማህበራት ለአንድ ሀገር የዲሞክራቲክ ሥርዓት ምሥረታ ምሰሶ ናቸው፡፡ በሀገራችን ሰብአዊ መብት ለማስከበር በቆሙ ሕዝባዊ ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ የጣለው በ2009 የወጣው ሕግ (The Charities and Societies Proclamation) ጸድቆ ተግባራዊ በመሆኑ ስለ ሰብአዊ መብቶችና የሴቶች መብት የማስከበር ስራ መስራት የማይቻልበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን፡፡

ስለዚህም ጉባኤው ስለሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መጠበቅና የመጻፍ፣ የመደራጀትና የመሰባሰብ መሠረታዊ መብቶች በሌሉበት አገር ምን ዓይነት ምርጫ ይካሄዳል? በሚለው ጥያቄ ላይ የሚያጠነጥን ጥልቅ የሆነ ወቅታዊ ውይይት የሚካሄድበት ሲሆን፣ ምሁራን ጥናቶቻቸውን የሚያቀርቡበት በመሆኑ በዝግጅቱ ላይ የሁላችሁም መገኘትና ተሳትፎ ወሳኝ ነው። ስለዚህ ውድ ወገኖቻችን በዝግጅቱ ላይ በመገኘት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

ዝግጅቱ የሚካሄድበት ቦታ በSILVER SPRING SHARATON HOTEL ሲሆን
ቀኑ፦ ቅዳሜ MARCH 7, 2015 ነው፡፡
አድራሻው፦ 8777 GEORGIA AVENUE SILVER SPRING MD, 20910 ሲሆን ከመስብሰቢያ ሆቴሉ ጀርባ ነፃ የመኪና ማቆሚያ አለ፡፡
ሰዓቱ፦ ከጥዋቱ 9AM እስከ 5PM ነው፡፡
የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule