ባለፈው ሳምንት የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪሎችንና አቶ ስብሃትን ባንድነት በየተራ አናግሮ ነበር። ከውይይቱ የተለመደ ክርክር በዘለለ አቶ ስብሃት እርቅ አስፈላጊ መሆኑንን ማመናቸው የተለየ ጉዳይ ነበር። እንደ እርሳቸው አነጋገር አሁን የተጀመረውን መልካም የልማት ስራ ለማስቀጠል እርቅ አስፈላጊ ነው። የእርቅን አስፈላጊነት በማመን ከባልደረቦቻቸው ጋር በመምከር የእርቅ ጉባኤ ለማዘጋጀት እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል። አቶ ስብሃት “የተቃዋሚ ፓርቲ አለ ብዬ አላምንም” በማለት ተቃዋሚዎችን እንደወትሮው ሁሉ ዘልፈዋል። “መደብ የላቸውም” ሲሉ ተቃዋሚዎችን ጭራሽ እንደ ፓርቲ እንደማይቆጥሯቸው የተናገሩት አቶ ስብሃት ከዘለፋቸው በኋላ ስለ እርቅ አግባብ መናገራቸውን፣ ጠያቂው እሳቸው ባነሱት አዲስ ሃሳብ ላይ በመንተራስ ማረጋገጫ ሲጠይቃቸው “ከጓደኞቼ ጋር መክሬ” በማለት በቅርቡ … [Read more...] about ስብሃት “እርቅን” እንሞክራለን፤ ከባልደረቦቼ ጋር እመክራለሁ አሉ
News
በኢትዮጵያ የኤርትራ ስደተኞች የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ወሰኑ
በሺህ የሚቆጠሩ የኤርትራ ስደተኞች የፕሬዚዳንት ኢሳያስን አስተዳደር በትጥቅ ትግል ለማስወገድ ጠመንጃ ካነሱ ተቃዋሚዎች ጋር ለመቀላቀል መወሰናቸውን ሱዳን ትሪቢውን ገለጸ። ውሳኔው የተላለፈው ኤርትራ ለ23ኛ ዓመት ድል በዓልን ተንተርሶ ነው። ሱዳን ትሪቢውን እንዳለው የኤርትራን ስደተኞች መግለጫ በመጥቀስ እንደዘገበው ኢሳያስ አፈወርቂ ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ አገሪቱን በአንድ ፓርቲ “በረግጠህ ግዛው” አስተዳደር ላለፉት 23 ዓመታት ገዝተዋል። ተያይዞም የአስመራው አገዛዝ በአገሪቱ ዴሞክራሲን፣ የሰብአዊ መብትን፣ ነጻነትን ማጎናጸፍ ባለመቻሉ ስርዓቱ በዚህ መቀጠል እንደሌለበት መስማማታቸውን አመልክቷል። "ከነጻነት" ማግስት የኤርትራ ተወላጆች እጣ ፈንታቸው ስደት፣ መሰወር፣ ጭቆና፣ እስር፣ ውርደት፣ ማስፈራራት እንደሆነ በመግለጫቸው ያመለከቱት ስደተኞች፣ "የኤርትራ ምድር እንጂ ህዝቦቿ … [Read more...] about በኢትዮጵያ የኤርትራ ስደተኞች የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ወሰኑ
የኢህአዴግ የ23 ዓመት “ፌዴራላዊ የዘር አወቃቀር” ውጤት
የጋምቤላ ምርጥ "ቶክ" አንገቱን ደፋ የኢትዮጵያው ቡናው እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተከላካይ የጋምቤላ ምርጥ ውጤት ቶክ ጀምስ ይርጋለም ላይ በአንዳንድ የሲዳማ ደጋፊዎች በዝንጀሮ ድምፅ በቆዳ ከለር ተሰድቧል። በቦታው የነበሩ እንደተናገሩት ኢትዮጵያዊው ቶክ በድንጋጤ ከሜዳው ወጥቶ የተቀያሪ ወንበር ላይ አንገቱን አቀርቅሮም ታይቷል። በአዲስ አበባ ስታዲየም የግለሰቦች ስም እየጠሩ የሚሳደቡ እንዳሉ ይታወቃል። በውጭ አገር ተጨዋቾች በሌሎች አገር ደጋፊዎች ከቆዳ ከለር ጋር በተያያዘ ሲሰደቡ በእኛ አገር ደግሞ ዘረኝነት በራሱ ዜጋ ሲሰደብ ከማየት ምን የሚያስደነግጥ አለ? ቶክ በወገኑ እንደ ዝንጀሮ ተሰድቦ አንገቱ ደፍቷል፤ ይህ ነገር ወደፊት በድጋሚ እንደማይከሰት ምን ማረጋገጫ ይኖራል? (ኢቲዮኪክአፍ እናመሰግናለን) ********** ምንጭ: ድሬ ቲዩብ ላይ ተለጥፎ በነበረ ጊዜ … [Read more...] about የኢህአዴግ የ23 ዓመት “ፌዴራላዊ የዘር አወቃቀር” ውጤት
በአባይ ጉዳይ ኃያላኑ በግብጽ ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው
ምዕራባውያን ሃያላን አገሮች ግብጽ በአባይ ዙሪያ የድርድር ጠረጴዛ ላይ እንድትቀመጥ ጫና እያደረጉ መሆኑ ተሰማ፡፡ ዜናውን የዘገበው አልአህራም ቃል በቃል ግብጽ ላይ ጫና ተፈጠረ ብሎ ባይጽፍም ከዜናው ለመረዳት እንደተቻለው ግብጽ ላይ ጫና እየተደረገባት ነው፡፡ ሃያላኑ ግብጽ ላይ እያሳደሩት ያለው ጫና መነጋገሪያ ሆኗል፡፡ እንደ ጋዜጣው ዘገባ ያለፈው ቅዳሜ የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ከኢትዮጵያ ጋር በአባይ ጉዳይ ለመደራደር አገራቸው ፈቃደኛ መሆኗን ማሳወቃቸውን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ይህንን መግለጫ ከመስጠታቸው በፊት የግብጹ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር መ/ቤት የውሃ ሃብት ልዩ አስተባባሪ ከሆኑት አሮን ሳልዝበርግ እንዲሁም ከአውሮጳ ኅብረት ልዩ ልዑክ አልክሳንደር ሮንዶስ ጋር ውይይት ማድረጋቸው ታውቋል፡፡ በተለይ የአሜሪካው ተወካይ ሳልዝበርግ ወደ ግብጽ ከመሄዳቸው … [Read more...] about በአባይ ጉዳይ ኃያላኑ በግብጽ ላይ ጫና እየፈጠሩ ነው
ደቡብ ሱዳን – የሰላም ድርድር ወይስ ቁማር?
የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ስምምነቱን የማይፈርሙ ከሆነ ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ለዓለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድቤት (ICC) አሳልፈው እንደሚሰጧቸው መግለጻቸውን በጁባ የጎልጉል ምንጭ አስታወቁ፡፡ ሱዳን ትሪቢዩን በበኩሉ ስምምነቱ የማይፈረም ከሆነ እስር እንደሚጠብቃቸው ሃይለማርያም ለሳልቫ ኪር መናገራቸውን ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ አርብ የተፈጸመው የስምምነት ፊርማ ገና ሳይደርቅ ሁለቱም ኃይላት ወደ እርስበርስ ውጊያው ተመልሰው በመግባት እየተካሰሱ ነው፡፡ እጅግ ደም አፋሳሽ በሆነውና ለበርካታ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት የሆነው የደቡብ ሱዳን የእርስበርስ ጦርነት ከጥቂት ቀናት በፊት አዲስ አበባ ላይ በፊርማ ሲጸድቅ ብዙ ተስፋ የተጣለበት ነበር፡፡ ሆኖም ስምምነቱ ከተጽዕኖ ባለፈ መልኩ በዕለቱ በፊርማ ካልጸደቀ ሳልቫ ኪርንም ሆነ ሬክ ማቻርን ሃይለማርያም ደሳለኝ ለዓለምአቀፉ … [Read more...] about ደቡብ ሱዳን – የሰላም ድርድር ወይስ ቁማር?
በሪያድ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች “አሸባሪ” መባላቸው ተቃውሞ አስነሳ
በቅርቡ በሪያ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አዳራሽ የተከበረውን የአባይ የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጫ ግደብ 3ኛ አመት ክብረ በዓል አሰመልክቶ ኤምባሲው በጠራው ስብሰባ ላይ ሪያድ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሃይማኖት አባቶች እና የሃገር ሽማግሌዎች እንዳይገኙ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር መሃመድ ሃሰን ባስተላለፉት ቀጭን ትዕዛዝ አዛውንቱ በአሸባሪነት ተፈርጀው በአሉን እንዳይታደሙ መታገዳቸው ሪያድ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ከፈተኛ ቁጣን ቀስቅሷል። በተለይ ሰሞኑን ውስጥ ወስጡን ሲነገር የነበረው የአምባሳደሩ መሃመድ ሃሰን ነውረኝነት ተግባር አርብ ሜይ 9 2014 ምሸት በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒት አዳራሽ ውስጥ ለአንድ ኢትዮጵያዊ በተዘጋጀ የእርዳታ ገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ላይ ህዝቡ ተቃውሞውን ማሰማቱን ለማወቅ ተችሏል። በወቅቱ አንድ የሃይማኖት አባት ሪያድ ከተማ ውስጥ መኖር … [Read more...] about በሪያድ የሃገር ሽማግሌዎች እና የሃይማኖት አባቶች “አሸባሪ” መባላቸው ተቃውሞ አስነሳ
“ውሃ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው”፤ መፍትሔ መፈለግ “የግድ” ነው፤ አል-ሲሲ
በቅርቡ በግብጽ ለሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ያሸንፋሉ እየተባለ የሚጠበቁት ዕጩ ተወዳዳሪ አብዱል ፈታህ አል-ሲሲ “የውሃ ነገር” ለግብጽ “የህይወትና የሞት ጉዳይ” ሲሉ ገለጹ፡፡ ከኢትዮጵያ ጋር በመሆን መፍትሔ መፈለጉ “የግድ” እንደሆነ አስታወቁ፡፡ በቅርቡ በግድቡ ዙሪያ ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ በውጭ የሚገኙ ሦስት ኢትዮጵያውያን ምሁራን የግድቡ መሠራት ግብጽን “በማይቀር አደጋ” ላይ እንደማይጥላት አስረዱ፡፡ በግብጽ በተላለፈ የቴቪ ስርጭት ትላንት ቃለመጠይቅ የሰጡት የቀድሞው የግብጽ ጦር መሪ ፊልድ ማርሻል አል-ሲሲ ግድቡን አስመልክቶ ሰፊ ትንተና እንዳልሰጡ አልሃራም የቲቪ ስርጭቱን ጠቅሶ ዘግቧል፡፡ ሆኖም ዕጩ ፕሬዚዳንታዊ ተወዳዳሪ “የሌሎችን ፍላጎትና ጥቅም የምንረዳ መሆናችንን ማሳየት ይገባናል፤ (የዚያኑ ያህልም) የራሳችንን ጥቅም ለማስጠበቅ ጽኑ መሆን አለብን፤ (ምክንያቱም) ውሃ … [Read more...] about “ውሃ የህይወትና የሞት ጉዳይ ነው”፤ መፍትሔ መፈለግ “የግድ” ነው፤ አል-ሲሲ
ኦሮሚያ ካለቀሰች በኋላ – ህዝብ ሃሳቡን ሊጠየቅ ነው
በአምቦ ህዝብ አዝኗል። የሟቾች ቁጥር ከ22 በላይ እንደሆነ ይገመታል። በድፍን ኦሮሚያ ከ36 ሰዎች በላይ ተገድለዋል የሚሉ መረጃዎች አሉ። ኢህአዴግ ባወጣው መግለጫ 11 ሰዎች መሞታቸውን አምኗል። ታዛቢዎች እንደሚሉት ኦሮሚያ እያነባች ነው። ህዝብ ለቅሶ ከተቀመጠ በኋላ ኢህአዴግ በቴሌቪዥን ቅስቀሳ ጀመረ። አርብ ሚያዚያ 24፤2006 (2/05/2014) ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በትዊተር ባሰራጩት መረጃ በጉዳዩ ዙሪያ ህዝብ ሃሳቡን እንደሚጠየቅ አመላክተዋል። የዚሁ መነሻ እንደሆነ የተነገረለት የቅስቀሳ ዘመቻ ዛሬ በቴሌቪዥን ተላልፏል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ኩማ የድንበር ጉዳይ እንደማይነሳ በመጥቀስ ተቃዋሚዎችን ወቅሰዋል። ኦሮሚያን ልዩ ዞን ከአዲስ አበባ ጋር ያዋሀደው አዲሱ ማስተር ፕላን ተግባራዊ እንዲሆን እንቅስቃሴ መጀመሩን ተከትሎ በክልሉ ከተካሄዱት ሰላማዊ የተቃውሞ … [Read more...] about ኦሮሚያ ካለቀሰች በኋላ – ህዝብ ሃሳቡን ሊጠየቅ ነው
በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ መካረረ ስጋት ፈጥሯል
በኦሮሚያ የተለያዩ ከተሞች የተቃውሞ ድምጽ ለማሰማት በሞከሩና ተቃውሟቸውን ለመግለጽ ሰልፍ በወጡ ወገኖች ላይ አገዛዙ የ"ከፋ" ነው የተባለ ሃይል መጠቀሙ ተሰማ። ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ታስረዋል። ለተቃውሞ መነሻ በሆነው አዲሱ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ላይ ኦህአዴድ ተመሳሳይ አቋም መያዝ አልቻለም። ችግሩን በሰላማዊ መንገድ መፍታት ያልቻለው ኢህአዴግ ጉልበት መምረጡ አገሪቱ ውስጥ ካለው የተከማቸ ብሶቶች ጋር ተዳምሮ አለመረጋጋቱን ያሰፋዋል የሚል ስጋት አለ። ከኦሮሚያ ክልል አስተዳደር የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት በአቀራረቡ ቢለያይም ከተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰሙት ዜናዎች ሊስተባበሉ የሚችሉ አይደሉም። በታችኛው እርከን የሚገኙትን ጨምሮ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ በጥቅሉ፣ ገሃድ አይውጣ እንጂ በመዋቅር ውስጥ ያሉ ሰራተኞችና ካድሬዎች የተቃውሞው ተሳታፊና ደጋፊ … [Read more...] about በኦሮሚያ የተጀመረው ተቃውሞ መካረረ ስጋት ፈጥሯል
ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ – ኢህአዴግ አሁንም በሶማሊያ ያስፈራራ ይሆን?
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የኢትዮጵያ ጉዞ በርካታ ጉዳዮች የሚከናወኑበት እንደሆነ ተጠቆመ። የዘወትር የጎልጉል ምንጭ አንዳሉት የኬሪ አዲስ አበባ ጉዞ አስቀድመው የተሰሩ ስራዎች ውጤት ነው። ጥቁሩ ሰው "ውሻ ምንም ሳይመለከት አይጮህም" ሲሉ አገር ቤት ያሉ ተቃዋሚዎች ራሳቸውን ብቃት ያላቸው አማራጮች መሆናቸውን እንዲያሳዩ ጠይቀዋል። ኢህአዴግ አሜሪካንንና የምዕራቡን ዓለም እንደለመደው "ከሶማሊያ ጦሬን አወጣለሁ" በማለት መደራደሪያ ከማቅረብ ውጪ ሌላ አቅም እንደሌለው ተገለጸ። ኢህአዴግ የዞን9 ጦማሪዎችና ጋዜጠኞች "አገር በማተራመስ" ወንጀል ክስ መሰረተባቸው። የድረገጽና የማህበራዊ ገጽ የኢህአዴግ ደጋፊዎችና የስርዓቱ ተጠቃሚ አባላት ባይዋጥላቸውም አሜሪካና ኢህአዴግ የነበራቸው ግንኙነት እየሻከረ መሔዱን ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በተደጋጋሚ ሲገልጽ እንደነበር ይታወሳል። … [Read more...] about ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ – ኢህአዴግ አሁንም በሶማሊያ ያስፈራራ ይሆን?










