የአዲስ አበባ ከተማ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጥንታዊው የሼክ አህመድ ሳለህ አልዛህሪ (ሎምባርዲያ ሬስቶራንት የሚገኝበት) ሕንፃ ቅርስ መሆኑን በባለሙያዎች አረጋግጦ ክብካቤና ጥበቃ እንዲደረግለት ሲያሳስብ ቢቆይም፣ ሰሞኑን ባወጣው ሰርኩላር ሕንፃው ቅርስ አይደለም በማለት የቀድሞውን ውሳኔ ሽሯል፡፡ ቢሮው ታህሳስ 25 ቀን 2006 ዓ.ም. ለአዲስ አበባና ዙርያዋ ኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ የጋራ ልማት ፕላን ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ጽፎ በነበረው ደብዳቤ፣ ሕንፃው ቅርስ መሆኑን ገልጾ በማስተር ፕላኑ በቅርስነት እንዲያዝ አስታውቆ ነበር፡፡ ቢሮው በጻፈው ደብዳቤ ከፌዴራል ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን፣ ከቅርስ ምዝገባ፣ ቁጥጥርና ደረጃ ማውጣት ዳይሬክቶሬትና ከቅርስ ጥገናና እንክብካቤ ዳይሬክቶሬት፣ እንዲሁም ከራሱ ቢሮ በተውጣጡ ባለሙያዎች በዝርዝር ተጠንቶ የቅርስ መሥፈርት እንደሚያሟላ … [Read more...] about ቱሪዝም ቢሮ የቀድሞ ውሳኔውን በመሻር ሎምባርዲያ የሚገኝበት ሕንፃ ቅርስ አይደለም አለ
News
ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ
ራሳቸውን ራስ ገዝ አገር አድርገው በማስተዳደር ላይ ያሉት ሶማሌላንድና ፑንትላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ውህደት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ሰነድ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) ማቅረባቸው ተሰማ። ሰነዱ ለእንግሊዝና ለሌሎች የአውሮፓ ሃያል አገራት መቅረቡም ታውቋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች "እንሰጋለን" ሲሉ የውህደት ጥያቄው ሊተገበር የሚገባው እንዳልሆነ አመልክተዋል። ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ ጥያቄ ያቀረቡት ሁለቱ የሶማሌ ጠቅላይ ግዛቶች የተጠቀሰውን ሰነድ ማቅረባቸውን የተናገሩት የጎልጉል ምንጮች፣ የሰነዱን ዝርዝርና ውህደቱ በምን መልኩ ሊከናወን እንደሚችል ዝርዝር መረጃ ለጊዜው ከመስጠት ተቆጥበዋል። ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ራሳቸውን ከተበጠበጠችው እናት አገራቸው ነጥለው አገር ማስተዳደር ከጀመሩ ዓመታት ቢያስቆጥሩም እስካሁን ድረስ በአገርነት እውቅና … [Read more...] about ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ
ለነዋሪዎች አማራጭ የለም!
በአዲስ አበባ ያለው የመጸዳጃ ቤት ችግር ከልክ ያለፈና መሆኑን የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ዘገበ። ሐሙስ በወጣው የጋዜጣው ድረገጽ ላይ እንዳስነበበው ከ3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርባት አዲስ አበባ ውስጥ ለሕዝብ መገልገያነት የዋሉት መጸዳጃ ቤቶች 63 ብቻ መሆናቸውን ዘግቧል። አማራጭ ያጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ ከተማዋ ወደ መጸዳጃ ቤትነት እየተለወጠች መሆኗን በምሬት ገልጸዋል። ጋርዲያን “Wash Ethiopia Movement” የተባለ አገር በቀል ድርጅት ጠቅሶ እንደዘገበው በከተማዋ ከ10 ቤተሰቦች 9ኙ የጉድጓድ መጸዳጃ ቤት እንደሚጠቀሙና መቀመጫ ባለው መጸዳጃ ቤት የሚጠቀሙት ከ25 ቤተሰቦች አንዱ ብቻ መሆኑን ተናግሯል። በዘገባው መሠረት የከተማዋ ባለሥልጣናት የዛሬ ዓመት ይገነባሉ በሚል የ100ሚሊዮን ብር ዕቅድ የተያዘላቸው መጸዳጃ ቤቶች እንዳሉ መናገራቸውን … [Read more...] about ለነዋሪዎች አማራጭ የለም!
አነጋጋሪው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የፖሊሲ ስልጠና
ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሁለት ሳምንታት የፖሊሲ ስልጠና ላይ መሆናቸውን መንግስት አስታውቋል ። ነሐሴ የተጀመረው ይኽው ስልጠና ተማሪዎች በግዳጅ የሚሳተፉበት መሆኑን አንዳንድ ተማሪዎችና ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይናገራሉ። መንግሥት ግን ይህን ያስተባብላል። ተማሪዎችና የፖለቲካ ተቋዋሚ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ፖሊሲ ላይ ያተኮረው ለከፍተኛ ትምሕርት ተቋማት ተማሪዎች የሚሰጠውሥልጠና ከጥሪው አንስቶ በግዳጅ የሚካሄድ መሆኑን ነው የሚናገሩት። በተለይ በስልጠናው የማይሳተፉ ተማሪዎች በመጪው አመት የትምህርት እድል እንደማያገኙ ይገልፃሉ ።ከዚህ በተጨማሪ የትምህርት ነጻነትና ፖለቲካዊ … [Read more...] about አነጋጋሪው የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የፖሊሲ ስልጠና
የተማሪዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል
የኢትዮጵያ የባህር በር ለኤርትራ መሰጠቱ ስህተት ነው የኢኮኖሚ እደገቱ እውነት አይደለም የትምህርት ስርዓቱ ወድቋል የተማረ ሰው ክብር አይሰጠውም አዲስ አበባ ውስጥ ሳውዝ ካምፓስ (ልደታ)፣ አቃቂ (AASTU)፣ ፍቼ የግብርና ኮሌጅ፣ ስድስት ኪሎ፣ አምስት ኪሎ፣ አራት ኪሎ፣ የአዲስ አበባ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስት ትምህርት ክፍልና ሌሎችም አካባቢዎች ከነሃሴ 15 ጀምሮ ስልጠና ላይ የሚገኙ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች ተቃውሟቸውን ማሰማታቸውን እንደቀጠሉ የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገለጹ፡፡ ተማሪዎቹ ገዥው ፓርቲ አለ በሚለው እድገት፣ የባህር በር፣ የተማረው የማህበረሰብ በሚደርስበት በደል፣ የትምህርት ጥራት፣ የመምህራን የእውቀት ደረጃ ማነስ፣ ድህነትና አጠቃላይ ኢኮኖሚ ውድቀት ላይ ጠንከር ያለ አስተያየትና ተቃውሞ መሰንዘራቸውን ተገልጾአል፡፡ የኢኮኖሚ እድገት ተቃውሞ … [Read more...] about የተማሪዎች ተቃውሞ ተጠናክሮ ቀጥሏል
የውሸት አባት 2ኛ ሙት ዓመት
ግንቦት 20፣ 1983ዓም መለስ ወይም ለገሠ ወይም አስረስ ወይም ዜናዊ ወይም … ትክክለኛ ስሙን በውል የማናውቀው ከነጭፍሮቹ ቤተመንግሥት ገብቶ ራሱን አጼያዊ ፕሬዚዳንት፣ ቀጥሎም አጼያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ … በማድረግ ከሾመበት ቀን ጀምሮ የኢትዮጵያ ሕዝብ በኦፊሴል እንደ ሻማ ወይም እንደ ኩራዝ ተለኩሷል። አቀጣጣዮቹ ምስለኔዎች ከሻማና ከኩራዝ ከፍ ብለው ብርጭቆ የለበሱ ፋኖሶች ሆነዋል። ለመለስና ለጭፍሮቹ የሚያበሩ ፋኖሶቹም (ኦህዴድ፣ ብአዴን፣ …)፣ ኩራዞቹም፣ ሻማዎቹም የበራላቸው ማሾዎች (ህወሃቶች) ሁሉም በአንድነት ዛሬ ላይ ደርሰዋል። ለኳሹም ተለኳሹም እያበሩ የአስለኳሹን ሁለተኛ ሙት ዓመት “እያከበሩ” ነው። በሌላ አነጋገር ለሙት መንፈስ እሣት አንድደው እየሰገዱ ነው። ተገድዶ እየነደደ ያለውን ሕዝብ፣ አዳዲሶቹ አስለኳሾች (የኃይለማርያም ደቦ አስተዳደር) ሕዝብን ሻማ … [Read more...] about የውሸት አባት 2ኛ ሙት ዓመት
በሳውዲ አፈሳው ተጠናቅሮ ቀጥሏል
ማለዳ የሳውዲ ፀጥታ ሃይሎች በሪያድ ከተማ በኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ አፈሳ ማድረጋቸውን የሪያድ ምንጮች ገለጹ። የሳውዲ አረቢያ መንግስት ያለመኖሪያ ፈቃድ የሚኖሩ ህገወጥ የውጭ ሃገር ዜጎች ሃገሪቱን ለቀው እንዲወጡ የሚገልጸውን መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ የፀጥታ ሃይሉ በወሰዱት እርምጃ ከ1 መቶ 80 ሺህ በላይ እትዮጵያውያን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሳውዲን ምድረ ለቀው ወደ ሃገር መመለሳቸው ይታወሳል። ይህ በዚህ እንዳለ የሳውዲ ከስደት ተመላሽ ወገኖችን መልሶ የማቋቋም ከፍተኛ ሃላፊነት የተጣለበት የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም ለማድረግ በተደጋጋሚ ቃል ቢገባም በወቅቱ የዓለምን ህዝብ ትኩረት ስቦ የነበረው የኢትዮጵያውያኑ ጉዳይ እስኪረጋጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ቴድሮስ አድሃኖም ከስደተኛው ጋር ፎቶ በመነሳት በኢቲቪ ሲሰራጭ ከነበረው ሰፊ የዜና ሽፋን … [Read more...] about በሳውዲ አፈሳው ተጠናቅሮ ቀጥሏል
የዋሽንግተኑን የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ተቃወሙት
ኢትዮጵያውንና ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያን በዛሬው እለት በዋሽንግተን ዲሲ የተከፈተውንና በዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ከአፍሪቃ መሪዎች ጋር የሚያደርጉትን ጉባኤ በመቃወም አደባባይ ወጥተዋል። “በኢትዮጵያ የሚታየው የሰብዓዊ መብት ረገጣ እንዲቆም አዎንታዊና ተጨባጭ ግፊት በማድረግ ፋንታ፤ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶቹን አራማጆች በመደገፍ ሁኔታው ይበልጥ እንዲባባስ እያደረገ ነው፤” ሲሉ ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመጡ መሆናቸውን ያስታወቁት የሰልፉ ተሳታፊዎች የኦባማን አስተዳደር ኮንነዋል። ስብሰባውን አስመልክቶ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ወደ ርዕሰ-ብሔርነቱ በዘለቁ ወቅት ሃገራቸው ከነበረችበት የምጣኔ ኃብት ድቀት አሁን እያገገመች በመሆኗ ትኩረታቸውን ለአፍሪካ እየሰጡ መሆኑን የሚያሳዩ ክንዋኔዎችን እያደረጉ ነው በማለት ቀድሞ በኢትዮጵያ የአሜሪካ … [Read more...] about የዋሽንግተኑን የአፍሪቃ መሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ተቃወሙት
ሳውዲ የሚገኙት በረከት ስምዖን ጤና እያነጋገር ነው
እሁድ ከአዲስ አበባ አንድ የጦር ሃይሎች ሆስፒታል ዶ/ር አስከትለው በሼክ አላሙዲን የግል አይሮፕላን እኩለ ሌሊት ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ለህክምና በድብቅ እንደገቡ የሚነገርላቸው አቶ በረከት ስሞኦን በተለምዶ ብግሻን እየተባለ የሚጠራ አንድ ሪፈራል ሆስፒታል ውስጥ የልብ ደም ቧንቧ ለማስፋት ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን ከሳውዲ አየር መንገድ ምንጮቻችን ለማረጋገጥ ተችሏል። የበረከት ጤንነት በአሁኑ ሰዓት በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ የሚገልጹት እነዚህ ምንጮች ዛሬ ጠዋት ከመካ የዒድ አል ፈጠር የፀሎት ስርዓት በኋላ ሼክ አላሙዲን በስልክ እንዳነጋገሯቸው ይናገራሉ። አቶ በረከት ስምኦን ለህክምና ወደ ሳውዲ አረቢያ በድብቅ መምጣታቸውን የሚናገሩ እነዚህ የሳውዲ አየር መገድ ምስጢራዊ መረጃ አቀባዮች ባለስልጣኑ በአሁኑ ሰዓት ጅዳ ሆስፒታል መተኛታቸው በተለያዩ የዜና ማስራጫዎች በመዛመቱ … [Read more...] about ሳውዲ የሚገኙት በረከት ስምዖን ጤና እያነጋገር ነው
ተሰባሪ መንግሥታትና የመሰበራቸው ምክንያቶች
በዓለማችን የመክሸፍ አደጋ የሚታይባቸውን አገራት ዝርዝር በየዓመቱ በማውጣት የሚታወቀው የውጭ ፖሊሲ መጽሔት ሰሞኑን አደጋው የሚታይባቸውን አገራት በዝርዝር አውጥቷል። በዚህ የ178 አገራትን ዝርዝር በያዘው ዘገባ መሠረት ቁጥር አንድ የአደጋው ተጋላጭ ደቡብ ሱዳን ስትሆን ኢትዮጵያ ደግሞ 19ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ጠቁሟል። ባለፈው የአውሮጳውያን ዓመት 2013 መረጃ ላይ ተመርኮዙ የወጣው ዘገባ 12 መስፈርቶችን በግብዓትነት የተጠቀመ መሆኑን አስታውቋል። እነዚህም፤ የስነሕዝብ ተጽዕኖ፡ ከህዝብ ብዛት ጋር በተያያዘ የምግብ ዕጥረት፣ የሟቾች ቁጥርና ፍጥነት፤ ስደተኞችና በአገር ውስጥ የሚፈናቀሉ፡ በስደት ወደ አገር የሚገቡና በአገር ውስጥ ከየቦታው የሚፈናቀሉ፤ የቡድን (የሕዝብ) ሃዘን፡ በአገር ውስጥ ባሉ ቡድኖች መካከል ያለው ውጥረትና ጠብ፤ አገር ጥለው የሚሄዱና … [Read more...] about ተሰባሪ መንግሥታትና የመሰበራቸው ምክንያቶች










