• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ከህወሃት የአናሳዎች ቁማር ጨዋታ ይጠንቀቁ!!

September 27, 2016 08:46 pm by Editor 2 Comments

በቅርቡ ብዙዎቻችሁ እንደተመለከታችሁት፣ ህወሃት ሶማሊዎች ኦነግን ወይም ግንቦት ሰባትን በመቃወም ወጡ የሚል ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ነው። መታወቅ ያለበት እውነት እንዲህ ዓይነቱን የህወሃት ድራማ እየተጫወቱ ያሉት ክልሉን አስተዳድራለው የሚለው አሻንጉሊት ፓርቲ አባላት ብቻም ሳይሆኑ፣ ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ፣ ከሶማሊ ላንድ እንዲሁም ከኬኒያ የመጡ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች መሆናቸውን ነው።

እብደት፣ ንዝላልነትና ስርዓት አልበኝነት የተጠናወተው የክልሉ የህወሃት ቅጥረኛ ፕሬዚዳንት አብሲ ኢሌ፣ ዛሬ የቡና ቤት ሰራተኞች ሳይቀር በማስገደድ ሰልፍ አስወጥቷል። የህወሃት አገዛዝ ይህንን ለምን አደረገ?

በመጀመሪያ ይህ የሚያሳየው ህወሃት በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች ባበጃቸው ታዛዥና አሻንጉሊት የነበሩ ፓርቲዎችም ጭምር ሳይቀር መተፋቱንና ተስፋ መቁረጡን ነው። በነዚህ ሁለት ትልልቅ ክልሎች (ኦሮሚያና አማራ) ስርዓቱ የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ቢጠራም አንድም ወደ ተቃውሞ ይቀየራሉ በሚል ስጋት ሰርዟቸዋል ወይም ደግሞ ማንም ሰው ባለመገኘቱ የድጋፍ ሰልፎቹ ከሽፈዋል።

ጉዳዩ ግን ከዚህም በላይ ክፉ (sinister) እሳቤ ያለበት ነው። ጉዳዩ ህወሃቶች የሞት ሽረት ትግል (existential fight) የሚያደርጉበት የአናሳዎች (minority) ፖለቲካዊ ቁማር ጨዋታ አካል ነው። የዚህ ዓይነቱን ቆሻሻ ቁማር ካርድ ከሁለት ሳምንታት በፊት ስዩም መስፍንና አባይ ጸሃዬ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ መዝዘውት ነበር። ይሄን ለማድረግ ሁለት ተልዕኮ ነበራቸው፥

የመጀመሪያው፣ ከዓለምዓቀፉ ዳተኛ ማህበረሰብ (liberal international community) “ትግሬዎች ላይ በሁለቱ ትልልቅ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች (ኦሮሞና አማራ) አጋርነት የዘር ማጥፋት ዘመቻ እየተካሄደ ነው” በሚል የድረሱልን ጥሪ ለማስተላለፍ ተፈልጎ ነው። ወያኔዎች ለዓለምዓቀፍ ዲፕሎማቶች “ትግሬ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የሃገሪቱ አናሳ ቡድኖችም ጭምር ለጥቃት እየጠጋለጡ ነው” በሚል ከፍተኛ አቤቱታና ውትወታ እያቀረቡ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።

ሁለተኛው ምክንያት ግን ህወሃት ከበረሃ አንስቶ ሲሰራበት የነበረውና የኦሮሞንና የአማራን የተባበረ ጫና (concerted impact) ለመቋቋም ሌሎች የሃገሪቱን አናሳ ቡድኖች አደራጅቶና በነሱ ላይ የበላይ ሆኖ (ዶሚኔት አድርጎ) ማንቀሳቀስ የሚለው ሸፍጠኛ ፖሊሲው ነው። ይሄ ከትግሉ ዘመን ጀምሮ ሲያራምዱት የነበረ ስትራቴጂ ነው። ትግራይን ከቤኒሻንጉልና በምዕራብ ታች ጋምቤላ ድረስ ወርዶ እንዲሁም በምስራቅ በኩል በአፋርና ሶማሌ ላይ የሚያገናኘው ካርታ የተሰራው በተራ ስህተት ሳይሆን ከ1970ቹ ጀምሮ ታቅዶ የተሰራበት ፕሮጀክት ነው። በትግራይ ልሒቃን የኢኮኖሚ ስግብግብነት የተነሳ ባይሳካላቸውም፣ በከተሞች ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ አናሳ ቡድኖችንም ከጎናቸው ለማሰለፍ ህወሃቶች ጥረው ነበር።

በእርግጥ ግን ህወሃት በኢትዮጵያ የአናሳ ቡድኖች አጋር ነውን? ስራው የሚያሳየው ግን እንዳልሆነ ነው። ምሳሌዎችን እንጥቀስ፥

+ የህወሃት ሰራዊት በሶማሊ ክልል ዘር ማጥፋትን ጨምሮ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽሟል። ይሄንን አሰቃቂ ወንጀል ደግሞ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በሰፊው የዘገቡት ሲሆን ያሁኑ የክልሉ ፕሬዚደንት አብዲ ኢሌ በቅጥረኛ ነፍሰገዳይነት እንደተባበረ እልፍ አእላፍ መረጃዎች አሉ።

+ በ2003 በጋምቤላ ክልል በአኙዋኮች ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ያካሄደ ሲሆን፣ ይሄንኑ ዓይነት ጭፍጨፋ እስካሁንም ቀጥሎበታል።

+ በ2002 ሎቄ ላይ ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ሲዳማዎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ አካሂዷል።

+ አሁን በዚህ ወቅት እንኳን የኮንሶ ህዝብ ራስን በራስ ለማስተዳደር ስለጠየቀ ብቻ የህወሃት ሠራዊት መንደሮቹን በእሳት እያጋየ ነው።

+ ሙርሲዎችን በገፍ ገድሏል፣ የተቀሩትን ደግሞ እንደ ጥንት ዘመን ባሮች አጠላልፎ በማሰር የሰው ልጅ በዚህ ዘመን ሊያየው በማይገባ ሁናቴ አስሮ እያሰቃያቸው ነው።

+ የስልጤና ጉራጌ ነጋዴዎችን ከንግድ ስርዓቱ በማስወጣት በትግሬዎች ተክቷል።

+ የአፋርን መሬት ትግሬዎች መቀራመት ብቻም ሳይሆን ሲፈልጉም የሱማሌ ኢሳዎችና ሌሎች እንዲቀራመቱት አድርገዋል።

+ ወዘተርፈ……

በሚቀጥሉት ሳምንታትና ወራት የኦሮሞና የአማራ አክቲቪስቶችና የነጻነት ቀንዲሎች የተባበረ ክንዶቻቸውን ማሳረፍ ሲቀጥሉ፣ ህወሃት የአናሳዎችን ቁማር ካርድ ይበልጥ እንደምትመዝ ይጠበቃል። የዚህ ዓይነቱ አስነዋሪ ቁማር ደግሞ በኢትዮጵያ ባሉት ሌሎች አናሳ በሔረሰቦች እንዲሁም በኦሮሞና በአማራ መካከል ቅራኔና ቁርሾ ለመፍጠር ያለም ነው የሚሆነው።

በዚሁ መሰረት ወያኔ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሱትን እኩይ ተግባራት ለመፈጸም ይችላልና እንንጠቀቅ፥

+ በዳያስፖራም ሆነ በተወሰኑ ያገር ውስጥ አካባቢዎች ተመሳሳይ የሆኑ ኦሮሞንና አማራን ለማናደድ (offend) ያለሙ ሰልፎችን ሊያዘጋጅ ይችላል፤

+ ተንኳሽና ቆስቋሽ ቃላትን በመጠቀም ፕሮፓጋንዳ የመንዛት ዘመቻው ሊጧጧፍ ይችላል፤

+ በሶማሊዎችና በኣማራ እንዲሁም በኦሮሞ መካከል ግጭት ለመፍጠር፣ ግለሰባዊ ትንኮሳዎች እንዲሁም በተቋማት ላይ ሊደረግ የሚችል ጥቃት ሊኖር ይችላል፤

+ በክልሎች የድንበር አካባቢዎች መፍጠር የጀመሩትን ግጭት ይቀጥላሉበታል።

በአማራና በቤኒሻንጉል እንዲሁም በኦሮሚያና በሶማሊ ክልሎች መካከል ህወሃት በቅርቡ የፈጠረችውን ግጭት ይበልጥ እንዲባባስ ልታደገው ትችላለች፤

እነዚህ የህወሃት ሸፍጦች እንዲከሽፉ ተባብረን ካልሰራን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኙ ብሄሮች መካከል የማይሽር ጠባሳ ሊያሳርፉ ይችላሉ። ስለሆነም ይህንን ለመመከት የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይኖርብናል፥

+ የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች በዚህ ዓይነቱ የህወሃት ወጥመድ ውስጥ ላለመውደቅ፣ ከሶማሊ ክልል ካድሬዎችና የአብዲ ኢሌ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች ጋር ውይይትም ሆነ ክርክር ወይም ማናቸውንም ዓይነት መሳፈጥ ማድረግ እንደማያስፈልግ መረዳት ያስፈልጋል፤

+ ይህንን ዓይነቱን ጉዳይ ለአክቲቪስቶችና ለፖለቲካ መሪዎች ተውላቸው። እነርሱ እንዳስፈላጊነቱ ያሳጧቸዋል (debunk)፤

+ የስርዓቱ ቅጥረኞች እንደ ኦሮሞ፣ አማራ ወይም ሶማሊ በመምሰል ግጭት ለመጫር እንደሚተጉም ማስተዋል ያስፈልጋል።

+ ወያኔ ነፍሰ ገዳይ ቅጥረኞችን ልታሰማራ ስለምትችል የታወቁ አክቲቪስቶች እንዲሁም የፖለቲካ መሪዎች በያሉበት መጠንቀቅ አለባቸው።

በኦሮሞም ሆነ በአማራ ኮሚኒቲዎች ውስጥ ያሉ የስርዓቱ ቅጥረኞች ሶማሊዎችን እንዲያጠቁና ግጭት እንዲፈጥሩ ሙከራዎች ሊደረጉ ይችላሉ። የኦሮምና የአማራ ሰዎች ላይም ጥቃት ሊቃጣ ይቻላል። ምንም ሆነ ምን ግን ምላሹ የጋርዮሽ (communal) ሆኖ በሶማሊ ወይም በሌላው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ላይ ያነጣጠረ መሆን አይገባውም። አካሄዳችን የዚህ ዓይነቱን የወንጀል ጥቃት የሚፈጽሙትን ግለሰቦች ነጥሎ በማውጣት ለህግና ፍትህ ማቅረብ መሆን ይኖርበታል። የዚህ ዓይነቱ ያረጀና ያፈጀ የወያኔ ክፉ የከፋፍለህ ግዛ አባዜ የስርዓቱን እድሜ ሊያራዝመው አይችልም። (Jawar Mohammed)

(ፎቶ: ህወሃት ያሰማራቸው የሶማሊ ተወላጆች የህወሃትን ባንዲራ ዘቅዝቀው የተነሱት)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Politics Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. Mohammed says

    September 29, 2016 07:38 pm at 7:38 pm

    Mirga Oromoos ta’e , mirgi Amaaraa ha kabajamu gaafiin mirgaa deebiin rasaasa hin ta’u!

    Reply
  2. Lusif says

    October 1, 2016 01:25 am at 1:25 am

    One thing, we all should understand is to read and hug realty. Anybody who clearly understands reality, can not be distracted by anything else. It is not only human beings, there are also a lot of bizarre things in nature, that distract us to catch up with reality. It is the correct understanding of reality, genuine self-confidence and persistent that matters.
    As a matter of principle, those guys has the same right like everybody else to support or oppose whom they like. It is up to us to show them that they are wrong. Or just ignore them. Sooner or later they will understand that all their futile efforts was only to collect dimension returns. There could be a lot more like this one. Do not sensationalize out of proportion. Please try to be realistic.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule