ትላንት ረቡዕ በአዘርባዣን የተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ነጻና ፍትሓዊ እንደማይሆን የብዙዎች ግምት ነበር፡፡ ከ10ዓመት በፊት ከአባታቸው ሥልጣን በውርስ የተረከቡት ፕሬዚዳንት ዒልሃም አሊዬቭ የጋዜጠኞችን እና የተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ በመገደባቸው የምርጫው ውጤት ምን እንደሚሆን ለመገመት ያዳገተ አልነበረም፡፡ እንደ ኢቲቪና ሬዲዮ በአገሪቷ መንግሥት የሚቆጣጠረውና ለገዢው ፖለቲካ መሣሪያነት የዋለ ሚዲያ በመኖሩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች የነጻ ንግግር ገደብ እንዳሳሰባቸው ሲጠቁሙ ቆይተዋል፡፡ ቢቢሲም የምርጫው ውጤት አስቀድሞ የተወሰነ መሆኑን ዘግቦ ነበር፡፡ ምርጫ ተካሂዶ ቆጠራው ከመፈጸሙ በፊት የአዘርባዣን ማዕከላዊ የምርጫ ኮሚሽን ለብልህስልኮች (smartphones) አዘጋጅቶ የለቀቀው ግብረታ (app) ፕሬዚዳንቱ በ72.76 በመቶ ማሸነፋቸውን የሚያሳይ ነበር፡፡ እኤአ በ2003 … [Read more...] about የአዘርባዣኑ ኢህአዴግ
“የይሉኝታ ፖለቲካ ይገድላል”
“ሙሉ ኢትዮጵያዊ ነኝ” ትላለች። የተወለደችው ዱከም ነው። በቀድሞው አጠራር በኢትዮጵያ የተለያዩ ጠቅላይ ግዛቶች ኖራለች። ሐረር፣ ባህርዳር፣ አስመራ፣ አዲስ አበባን በመጥቀስ ልዩ ትዝታዎች እንዳሏት ትናገራለች። ከዛሬ ሃያ ዓመት በፊት አሜሪካ ከትማለች። “ፖለቲከኛ አይደለሁም፣ እኔ አገር ወዳድ ነኝ። አገሬ የማንኛውም ጉዳዮቼና የውሳኔዎቼ በሙሉ መለኪያ ሚዛኔ ናት" ትላለች። ለአገሯ ማድረግ የሚገባትን እንዳላደረገች ይሰማታል። የይሉንታ ፖለቲካ ችግርና መዘዝ ያሳስባታል። በመናገርና ሃሳብን በነጻነት ስለመግለጽ ያላት አቋም የጸና መሆኑን አትደብቅም። በማህበራዊ ገጾች ንቁ ተሳታፊና መረጃ በማስተላለፍ በርካታ ተከታታዮች አሏት። በኢትዮጵያውያን የወቅታዊ ጉዳዮች መወያያ መድረክ አስተባባሪ ከሆኑት አንዷ ኃላፊ (አድሚን) ናት። ቤተሰቦቿ ካወጡላት መጠሪያዋ ይልቅ ራስዋ ለራስዋ ስም ተክላለች። … [Read more...] about “የይሉኝታ ፖለቲካ ይገድላል”
ሼኽ አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን ካሩቱሪን ለመጠቅለል አስበዋል
በኢትዮጵያ ባሏቸው ኢንቨስትመንቶች መልከ ብዙ ችግሮች እንዳሉባቸው የሚነገርላቸው ሼኽ መሐመድ ሁሴን አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን የካሩቱሪን የእርሻ መሬት ለመግዛት ከድርድር ላይ ናቸው ተባለ። ድርድሩ በስምምነት ከተቋጨ የሳዑዲን የምግብ አቅርቦት ለመሸፈን የሚንቀሳቀሱት "ባለሃብት" በጋምቤላ ብቻ ከ230 ሺህ ሄክታር በላይ ድንግል መሬት ባለቤት ይሆናሉ። በድርድሩ መሰረት እስከዛሬ ከወሰዱት በተጨማሪ ብድርም ከንግድ ባንክ ያገኙበታል። የሳዑዲን የምግብ ኮታ ለመሸፈን ታስቦ እንደተመሰረተ የሚነገርለት የሳዑዲ ስታር አግሮ ኢንዱስትሪ በ2001 ዓ ም 10ሺህ ሄክታር መሬት ተረክቦ በጋምቤላ ስራ ሲጀምር ተጨማሪ 500 ሺህ ሄክታር መሬት እንደሚሰጠው ቃል ተገብቶለት እንደነበር በወቅቱ የተለያዩ መገናኛዎች ዘግበው ነበር። ሳዑዲ ስታር የስራ አቅሙ ተገምግሞ መሬት እንደሚጨመርለት ቃል ቢገባለትም … [Read more...] about ሼኽ አላሙዲ በዕዳ የተያዘውን ካሩቱሪን ለመጠቅለል አስበዋል
The Secret (ሚስጢሩ…)
ሚስጢሩ አሁን በሀይለኛ ሂደት ላይ ወቷል። እርስዎም የውለታ ምስጋናን፤የሚፈልጉትን ነገር በዓይነ ህሊና አስቀድሞ ማየትን፤የተግባር ሀይልን ሂደቶች የሚረዱበት ምዕራፍ ላይ ደርሰዋል ማለት ነው።ለመሆኑ አስቀድመው ይሄን ሁኔታ የተሸጋገሩ ምን ይላሉ? ያሁኑ ማንነታችን ያለፈው አመለካከታችን ውጤት ነው። ቡድሃ የየቀኑ ምስጋናህ ፀጋ ወደ አንተ የሚመጣበት ማስተላለፊያ ቀዳዳ ነው ዋላስ ዋትልስ መተንበይ ሁሉንም ነገር ነው።የህይወት መጻኢ መስህቦች ቅድመ እይታ ነው። አልበርት አንስታይን ሀይለኛው ሂደት የምትፈልገውን አጥብቀህ መጠበቅ ሊረዳህ ይችላል ፍላጎት እንዳይርቅ ስትተኛም ሆነ ጠዋት ስትነሳ በያንዳንዱ ነገር ማመስገን አትርሳ በጅህ ባለ ነገር ማመስገን ስትጀምር መንገድ ትፈጥራለህ ሌላ ለመጨመር የምትፈልገውን በዓይነ ህሊና አስቀድመህ አይተህ አስተካክለውና ማግኘትህን … [Read more...] about The Secret (ሚስጢሩ…)
ፓለቲካዊ መግባባት እና 18 የፓልቶክ ታዳሚዎች
ይህ ጥያቄ እና መልስ ከ18 የፓልቶክ ታዳሚዎች ጋር ስለ ፓለቲካዊ መግባባት ("ብሄራዊ መግባባት") የተደረገ ነው። ጥያቄ እና መልስ የተደረገበት ጊዜ ከSeptember 16-20, 2013 ሲሆን ፡ ጠያቂ አቶ ያዬ አበበ ነው (Paltalk nick name: Beruhan)። የዚህ ጥያቄ እና መልስ አላማ የፓልቶክ ታዳሚዎች ስለ ፓለቲካዊ መግባበት ያለቸውን ግንዛቤ ለማሰስ ሲሆን ፡ በተጨማሪ የአሰሳውን ውጤት በመጠቀም ስለ ፓለቲካዊ መግባባት በዲያስፓራ መወያያ መድረኮችና ሚዲያዎች ግንዛቤ የሚያስጨብጥና ጥልቀት ያለው የፓለቲካ ውይይት የሚፈጥር ጥንስስ ለመጀመር ነው። ((ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ)) … [Read more...] about ፓለቲካዊ መግባባት እና 18 የፓልቶክ ታዳሚዎች
አባ አጋግዮስ
ባለፈው ሳምንት የዘንድሮውን የደመራ በዓል አከባበር በዜና ማሰራጫዎች የተመለከቱ ግሪካዊ ቄስ ባነሱት ጥያቄ የተቀሰቀሰብኝን ስሜት፤ ለዚህች ክታብ መግቢያ ላደርገው ፈለኩ። “ባገርህ የተደረገውን የመስቀሉን በዓል በመገናኛ ዘዴወች አይቼው በጣም ደስ ይላል። ሄደህ ነበር? ብለው ጠየቁኝ። “አልሄድኩም” አልኳቸው። “ለምን አልሄድክም? ብለው መልሰው ጠየቁኝ። ያሰለቼኝ ጥያቄ ስለሆነ የጥያቄቸውን መስመር በመቀየር “እርስዎን ምኑ ነው ያስደሰተዎ? ብየ ጠየኴቸው። “አከባበሩ ደስ ይላል” አሉኝ። “የእርሰዎ መንፈስ የተማረከው ባከባበሩ መብልጭልጭ ነው። የኔን መንፈስ የሚማርከው ደግሞ በበዓሉ የሚወሱት እነ ቆስጠንጢኖስ፤ ዲዮቅልጥያኖስ፤ እነ ቅድስት እሌኒና የአባ አጋግዮስ አስከፊ ባህርይ ነው። ከዚህም ጋር ደመራ የሚለው የበዓሉ መጠሪያ እንደሚያመለክተው፤ ከልጅነት ጀምሮ ለበዓሉ የክብር መርገፎች … [Read more...] about አባ አጋግዮስ
በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ ዓመጽ ተካሯል
አመጹ ከካምፕ ወደ ካምፕ እየተዛመተ ነው በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን ተመዝግበው በትግራይ-ኤርትራ ድንበር ዳርቻ በስደት ማቆያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ የኤርትራ ተወላጅ ስደተኞችና በኢህአዴግ መካከል የተፈተረው አለመግባባት ተካሯል። የሰው ህይወት ማለፉና ነጻ እንቅስቃሴ መከልከሉ ተሰምቷል፤ እስካሁን ስድስት ሞተዋል፤ ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ በርካታዎች ቆስለዋል። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸውና በአውሮፓ ተቀምጠው ጉዳዩን የሚከታተሉ የጎልጉል ምንጮች እንዳሉት ኦክቶበር 5 ቀን 2013 ምሽት ላይ በትግራይ ማይ ዓይኒ ወረዳ በሚገኝ የስደተኞች ካምፕ የተቀሰቀሰው ረብሻና ተቃውሞ ወደ ሌሎች ካምፖችም ተዛምቷል። በተለይም በትላንትናው እለት ሽሬ አካባቢ በሚገኘው አድ ሃሪሽ ካምፕ የተነሳው ተቃውሞ ጋብ ሊል የቻለው ኢህአዴግ ሃይል በመጠቀሙ እንደሆነ ተመልክቷል። በዚህም የሃይል ርምጃ … [Read more...] about በትግራይ የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞች ካምፕ ዓመጽ ተካሯል
መንገድ ወድቆ አየሁት
ርሃብ፣ ድካም እና ሰቆቃው ለላፉት 12 ወራት ተፈራርቀውበታል። አንዴ በሰሃራ በረሃ ሌላ ግዜ ደግሞ በሜዲትራንያን ባህር የሰው አእምሮ ሊቀበለው የማይችል ስቃይ አልፎ እግሩ አውሮፓን ምድር ከረገጠ እነሆ አንድ ሌሊት አለፈ። ሰነድ ገብረጻድቅ ይባላል። ፊቱ እጅግ ተጎሳቅሏል። ከሰውነቱ ላይ አጥንቶቹ ይቆጠራሉ። ወጣቱ ተስፋ ወዳደረገባት የአውሮፓ ምድር ለመግባት የተነሳው ከአመት በፊት ነው። እንብርቱ የተቀበረችበትን ሃገር ተሰናብቶ ከወጣ ጀምሮ የደረሰበት መከራ ይህ ነው አይባልም። ሰነድን እመንገድ ወድቆ ነበር ያገኘሁት። ለጥቂት ደቂቃ አነጋገርኩት። ንግግሩ የሚረብሽ ነው። አጭር የቪዲዮ ቆይታችንን ለማየት እዚህ ላይ ይጫኑ። ከ 300 በላይ የኢትዮጵያውያ እና የኤርትራ ተወላጆች የፈጀው የላምፔዱሳ እልቂት በአለም አቀፍ ዜና እየታወጀ ባለበት ሰዓት፤ ሌላ መርከብ ከሊቢያ ተነስታ … [Read more...] about መንገድ ወድቆ አየሁት
አደባበዬቻችን እና መንገዶቻችን መሉሱልን?!
‹‹ ዲሞክራሲ የሚመሠረተው መንግስት ሕዝቡን ሊያገለግል የቆመ ነው በሚል መሠረት ሃሳብ ላይ ነው፡፡ ይህም ማለት ሕዝብ መንግሥትን ለማገልገል የተፈጠረ አይደለም፡፡ በሌላ አነጋገር ህዝብ የአንድ ዲሞክራሳዊ አገር ዜጋ እንጂ ተገዥ አይደለም፡፡ መንግስት የህዝብን መብት በሚያስጠብቅበት ወቅት ህዝብ ደግሞ በልዋጩ ለመንግስት ታማኝነቱን ይገልፃል፤በጨቋኝ ሥርዓት ግን መንግስት ራሱን ከህዝብ በማግለል ታማኝነትን ከህዝብ ይሻል ፤መንግስት ውሳኔ የሚወስነው ተገቢውን የህዝብ ድጋፍና ተሳትፎ ሳያገኝ ከሆነ የህዝብ ታማኝነት መመኘት ከንቱ ቅዠት ይሆናል፡፡ ›› (what is democracy) ከሚለው መፃፍ የተወሰደ ነው፡፡ ጥላቻ ሁለተኛ ከባዱ የሰው ልጅ ስሜት ነው፤ፍቅር የመጀመሪያ ነው፡፡ ጥላቻ በፍራቻ በእውቀት ማነስና በተጠራጣሪነት የሚመጣ ነው፡፡ ጥላቻ ይቅር ባይነትና መግባባትን ያሣጣል፡፡ … [Read more...] about አደባበዬቻችን እና መንገዶቻችን መሉሱልን?!
የምርትና የሕዝብ እድገት እሽቅድድም
እአአ በ1798 (ከሁለት መቶ አሥራ አምስት ዓመታት በፊት) መምሬ ቶማስ ሮበርት ማልቱስ የሚባል የ32 ዓመት የብሪታንያ ቄስ የዘመኑን የነገረ ንዋይ አስተሳሰብ የለወጠ አዲስ ሀሳብን የያዘ መጽሐፍ አሳተመ፤ ሀሳቡ በጣም ግልጽ ነበረ፤ የሰው ልጆች ቁጥር እድገት መጠኑ እያጠፈ የሚሄድ ነው፤ የሕዝብ ቁጥር 1፣ 2፣ 4፣ 8፣ 16፣ 32፣ 64፣ 128፣ እያለ የሚጨምር ነው፤ ከእርሻ የሚገኘው ምርት ደግሞ የእድገቱ መጠን አያጥፍም፤ 1፣ 2፣ 3፣ 4፣ 5፣ 6፣ 7፣ 8፣ 9፣ 10፣ እያለ የሚሄድ ነው፤ የመምሬ ማልቱስን ሀሳብ በሌላ መንገድ ካየነው የበላተኞች ቁጥር እያጠፈ ሲያድግ የምግቡ አቅርቦት የሚያድገው ግን በጣም በዝግተኛ ፍጥነት ነው፤ የሚል ነው፤ እንግዲህ የሕዝብ ቁጥርና የምርት አቅርቦት እኩል መጓዝ ሲገባቸው የሕዝቡ ቁጥር እየቀደመ ስለሚገኝ፣ መምሬ ማልቱስ የደረሰበት … [Read more...] about የምርትና የሕዝብ እድገት እሽቅድድም










