በሃገራችን ኢትዮጵያ ወያኔ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በኣስከፊ ሁኔታ አየተባባሰ የመጣው የዜጎች መብት ረገጣ ፣ በተለይም በዚ ስርአት ዋነኛ ተጎጂ የሆኑት ሴት አህቶቻችን በሀገር ውስጥ በመንግስት አካላት በሚደርስባቸው ጥቃት ለ አካል አና ስነልቦና ጉዳት ሰለባ የተዳረጉትን እና ገዢው ፓርቲ ባመቻቸው አና በከፍተኛ ሁኔታ አየተስፋፋ የመጣው ህገወጥ የሰው ዝውውር ዘመናዊ ባርነት ወደ አረብ ህገራት በዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው ከፍተኛ ሰቃይ፣ አንግልት፣ አስር፣ ሞት አና የመሳሰሉት ችግሮች በየጊዜው የምንሰማው እና እልባት ያልተገኘለት መራር አውነት የሚያሳይ የፎቶ ኣውደርዕይ እና ገለጻ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሴቶች ክፍል ኣዘጋጅነት በኦስሎ ከተማ ተደረገ ። በዝግጅቱ ላይ ከቀረቡት ፎቶዎች መሀከል ሴቶች በሀገር ውስጥ የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ ናቹ በሚል … [Read more...] about የኢትዮጵያዊያን ሴቶች አሰቃቂ ሂወት በሀገር ውስጥ እና በስደት ኣውደርዕይ
መቋጫ ያጣው የወገኖቻችን ስቃይ እና በደል በሳውዲ አረቢያ አሁንም ቀጥሏል!
ትላንት አመሻሹ ላይ ሪያድ ከተማ በተለምዶ መንፉሃ እየተባለ የሚጠራ አካባቢ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን አገርሽቶ በዋለው ተቃውሞ የሞተ ባይኖርም ኢትዮጵያውያኑ ድምጻቸውን ከፍ አድረገው አማራው አንድነን … ትግሬውም አንድነን … ጉራጌው አንድነን ... መብታችን ይከበር ... እኛም ሃገር አለን ወዘተ... በሚል መፈክር ታጅበው ብሶታቸውን ሲያሰሙ መዋላቸውን የሚገልጹ የአይን እማኞች የሳውዲ የጸጥታ ሃይሎች ተቃውሞውን ለመበተን በከፈቱት ተኩስ አካባቢውን ወደ ጦርነት አውድማ ለውጦት ማምሸቱን ይገልጻሉ። የጸጥታ ሃይሉ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ አውቶማቲክ የጦር መሳሪያ የታጠቁ ተጨማሪ ልዩ ፈጥኖ ደራሽ፡ ኮማንዶዎች በመታገዝ የኢትዮጵያውያኑን ተቃውሞው መግታት ተችሏል ብለዋል። እነዚህ ምንጮች ትላንት ተቀስቅሶ በነበረው ሁከት ጥቂት ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱን በማውሳት ሰሞኑን የሳውዲ አረቢያ … [Read more...] about መቋጫ ያጣው የወገኖቻችን ስቃይ እና በደል በሳውዲ አረቢያ አሁንም ቀጥሏል!
የሳዑዲ ስታር ፕሮጀክት የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ መግባቱ ተሰማ
በጋምቤላ ክልል በግብርና ሥራ የተሰማራው የሼክ መሐመድ አል አሙዲ ኩባንያ ሳዑዲ ስታር የግብርና ልማት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ የፋይናንስ ቀውስ ስላጋጠመው ፕሮጀክቱ ከመጓተቱም በላይ ከሁለት ሺሕ በላይ ሠራተኞች ከሥራ መፈናቀላቸው ታወቀ፡፡ ችግሩ ቢኖርም መፍትሔ እንደሚፈለግም እየተነገረ ነው፡፡ አሥር ሺሕ ሔክታር መሬት በመስኖ ለማልማት ሳዑዲ ስታር ሥራ የጀመረው ከአምስት ዓመት በፊት በ2001 ዓ.ም. አካባቢ ነበር፡፡ ከፕሮጀክቱ ጥቂት ፈቀቅ ብሎ ደግሞ በደርግ መንግሥት የተገነባው የአልዌሮ ግድብ ተንሰራፍቶ ይገኛል፡፡ ግድቡ በዋናና መጋቢ ቦዮች አማካይነት የሳዑዲ ስታርን የሩዝ እርሻ በመስኖ ለማልማት ብቸኛው የውኃ ምንጭ በመሆኑ፣ ለሩዝ እርሻው ወሳኝነቱ ጥያቄ እንደሌለው በቅርብ የሚያውቁት ይናገራሉ፡፡ ወደ ሥራው ከመገባቱ ቀድሞ ጥናት እንዲያጠና የተወከለው የፓኪስታን … [Read more...] about የሳዑዲ ስታር ፕሮጀክት የፋይናንስ ቀውስ ውስጥ መግባቱ ተሰማ
የነፍስ ስደተኞች (the immigrants of survival)
ባገሩ የሚኮራ ፤ ሀገሩን አፍቃሪ ለወገን ሟች ስፍሱፍ ፤ አብሮነት ዘማሪ የነፍስ ስደተኛ ፤ እውነት አስመስካሪ የሀገሩ ነገር ፤ የወገኑ እጣ ሁሌ የሚያስጨንቀው ፤ ሲበዛ ግፍ ጣጣ ስለተገለለ ፤ አማራጭ ስላጣ እኛን ካልሆንክ ተብሎ ፤ ሕሊናው ተሸጣ ደሞ ስለተገፋ ፤ ታይቶ እንደ ባላንጣ አላፈናፍን ተብሎ ፤ ጅቡ እየተቆጣ አላቃምስ ተብሎ ፤ በራብ እየተቀጣ ወገን ሲለይበት ፤ ሆኖ ዘር መረጣ ቢብሰው ተነሣ ፤ ለስደት ጎረፈ ከሞት ጋር ተፋጦ ፤ ሞትን እያለፈ ግፍ እየተጋተ ፤ እየተቀሰፈ ገና ባልጸናለት ፤ በጨቅላ ትከሻ ስንት ስቃይ ዐየ ፤ የጣር መጨረሻ ወገኑን እያጣ ፤ የዓሣ ሲሳይ ሆኖ በአራዊት ተበልቶ ፤ በድንገት ታድኖ ስለተደፈረ ፤ እራሱን ኮንኖ በራብ በውኃ ጥም ፤ እየቀረ ደብኖ በኢሰብአዊ … [Read more...] about የነፍስ ስደተኞች (the immigrants of survival)
Shame on US!
‹‹የሳውዲ መንግስት በአገሩ የአሰሪና ሰራተኛ ህግ መሰረት እርምጃ የመውሰድ ሉአላዊ መብት እንዳለው እንገነዘባለን፤ ...>>/cf. Shimelis/ One can only be furious on what is going over there! - A clear case. Ethiopia is quasi a colonial region of the Saudis , by proxy of Ala Moudin’ s economic empire and de facto Power in alliance with TPLF! This Man, a dummy figure ( Shimelis divulges what they think behind closed doors, he talks exactly the opposite of what the Foreign Minister, Tewodros has (click here to read more) … [Read more...] about Shame on US!
ኢህአዴግ ከሳዑዲ ጋር መቆሙን አረጋገጠ!
አዲስ አበባ ላይ በሳዑድ አረቢያ ኤምባሲ አጠገብ ሊካሄድ የነበረ የተቃዉሞ ሰልፍ በፖሊስ ተበተነ። አሶሺየትድ ፕረስ እንደዘገበዉ ፖሊስ በመቶዎች የሚቆጠሩን ሰልፈኞች ለመበታተን ኃይል ተጠቅሟል። መንግስት ፈቃድ እንዳልተሰጠዉ በማመልከት ቁጥራቸዉን ባይጠቅስም የታሰሩ መኖራቸዉን ገልጿል። ሰልፉን ያስተባበረዉ የተቃዉሞ ወገን ሰማያዊ ፓርቲ በበኩሉ ሁለት ሊቃነመናብርቱን ጨምሮ አንድ መቶ ሰዎች ገደማ መያዛቸዉን አመልክቷል። የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ ሽመልስ ከማል ፀረ አረብ ስሜት ሊፈጥር የሞከረ ያሉት ተቃዉሞ ሰልፍ አዘጋጆች ከሚመለከተዉ አካል ፈቃድ ባለማግኘታቸዉ እንደሚከሰሱ ለአዣንስ ፍራንስ ፕረስ ገልጸዋል። በፖሊስ ከተደበደቡት አንዱ እንደሆነ የገለጸዉ አስፋዉ ሚካኤል፤ መንግስት የሳዉዲ አረቢያን ድርጊት ላይ የቀረበዉን ተቃዉሞ ለምን ማገድ እንደፈለገ እንዳልገባዉ ለዜና ወኪሉ … [Read more...] about ኢህአዴግ ከሳዑዲ ጋር መቆሙን አረጋገጠ!
ጭንቁን ቀን እንዴት እንለፍ!?
ጥላቻው እያደገ ሔዷል፣ ሳውዲ አሰሪዎች ኢትዮጵያውያን የቤት ሰራተኞቻቸውን ድሮ ድሮ በአረቦች ዘንድ የተከበርን፣ የታፈርን የእኛን የሃበሻ ልጆች "ጨካኞች ፣ የማይታመኑ!" እያሉ ጥላቻቸውን መገልጽ ጀምረዋል። November 14,2013 የወጣው አረብ ኑውስ Recent clashes make Saudis wary of Ethiopian maids በሚል ርዕስ ስር ሳውዲ አሰሪዎች ኢትዮጵያን ሰራተኞችን ለማባረር እየዛቱ ነው! ይህ የአረብ ኒውስ ዘገባ በሹክሹክታ የምንሰማው ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። የሪያድ መንፉሃን ግጭት ተከትሎ ደም እድገብሮም ለኢትዮጵያን ተሰጠው ወደ ሃገር ቤት የመግባትን እድል ለመጠቀም ከሃያ ሽህ በላይ ኢትዮጵያውያን የሪያድ መጠለያዎችን አጨናንቀዋል። እንዲውም በሪያድ የኢትዮጵያ አምሳደር ቁጥሩን ወደ ሃያ ሶስት ሽህ እንደሆነ ረቡዕ November 14,2013 ለወጣው አረብ … [Read more...] about ጭንቁን ቀን እንዴት እንለፍ!?
ሰባተኛው የለውጥ መዘውር ነጥብ እየቀረበ ይሆን?
ኢትዮጵያ የዘውድ ስርዓት ከወረደ በኋላ ባልተረጋጋ የለውጥ ማዕበል ውስጥ መናጥ ከጀመረች 40 ዓመታት እየደፈነ ነው። የየካቲት 1966 ዓም አብዮት ዘንድሮ 40 ዓመት ይሞላዋል። ከ 1966 ዓም በፊት በነበሩት ስልሳ አመታት ውስጥ ሀገራችን ከሁለት መቶ አመታት በላይ በዘመነ መሳፍንት የእርስ በርስ ግጭት ከቀረው ዓለም ጋር የነበራት ግንኙነት በብዙ መልኩ የተለያየ እና ጠንካራ የማይባል ነበር። ከ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመርያ እስከ አጋማሹ ማለትም 1966 ዓም በነበሩት ዓመታት ውስጥ ሀገራችን ፍፁም ከሆነው የፊውዳል ስርዓት ወደ ዘመናዊነት ለመግባት ብዙ ነገሮች በየዘርፉ የጀመረችባቸው አመታት ነበሩ። ዘመናዊ መንግስት ስርዓት- እንደ ፓርላማ፣ ዩኒቨርስቲዎች፣ የአየር መንገድ አገልግሎት፣ የመብራት ኃይል ማስፋፋት፣ በዓለም አቀፍ ግንኙነትም ሆነ በአህጉራዊ እና አካባቢያዊ ፖለቲካ ውስጥ … [Read more...] about ሰባተኛው የለውጥ መዘውር ነጥብ እየቀረበ ይሆን?
የኢትዮጵያን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ ከተነሱት ስዊድናዊ ጠበቃ ጋር ውይይት ተደረገ
ቅዳሜ ኖቬምበር 2 ቀን 2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ መድረክ በስዊድን የወያኔን መንግስት በዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ለማቅረብ የተጀመረውን ክስ መነሻ በማድረግ የክሱን ሂደት ከሚመሩት ከስዊድናዊው ጠበቃ ከስቴላ ያርዴና ከሌሎች እንግዶች ጋር በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት ወይይት አደረገ። ውይይቱ ከቀኑ 14፡00 ሰዓት የተጀመረ ሲሆን ውይይቱን የከፈቱት የመድረኩ ሊቀ መንበር ም/ኢኒስፔክተር ሚሊዮን ብሩ ናቸው። ኢኒስፔክተር ሚሊዮን በንግግራቸው መክፈቻ ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶችና ተሰብሳቢውን ህዝብ አመስግነው መድረኩ የተቋቋመበት ዓላማ በሀገር ውስጥና በውጪ የሚደረገውን የነጻነት ትግል የተደራጀ መልክ ይዞ የሚጓዝበት መንገድ ለማመቻቸትና በየጊዜውም ይህንን መሰል ውይይት በማድረግ ትግሉን ለመርዳት መሆኑን ገልጸው የዛሬውንም ስብሰባ የዚህ መነሻ እንደሆነ … [Read more...] about የኢትዮጵያን መንግስት ለፍርድ ለማቅረብ ከተነሱት ስዊድናዊ ጠበቃ ጋር ውይይት ተደረገ
ሰላማዊ ሰልፍ በባዕድ ሀገራት እና “አስራ አንደኛው ቀን” በሳውዲ አረቢያ
በሳውዲ አረቢያ በወንድምና እህቶቻችን ላይ እየተፈፀመ ያለውን አሰቃቂ ግፍና መከራ ለመቃወም በትላንትናው እለት ህዳር 5 ቀን 2006 ዓ.ም በጀርመን ፈራንክፈርት ሳውዲ አረቢያ ቆንስላ በተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ተገኝቼ ነበረ። (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about ሰላማዊ ሰልፍ በባዕድ ሀገራት እና “አስራ አንደኛው ቀን” በሳውዲ አረቢያ










