ከአምስት ወር በፊት የሕዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች የአዲስ ዓመት የሥራ ዘመን መጀመር አስመልክቶ በጋራ ባአካሂዱት ጉባዔ አዲሱ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመም ፕሬዚዳንታዊ የመክፈቻ ንግግር ማድረገቸው የሚታወቅ ነው፡፡ የፕሬዚዳንቱ የንግግር ይዘት መንግሥት በ2006 ዓ.ም. ትኩረት ሊያደርግባቸው የሚገቡ ዋና ዋና ተግባሮች ላይ ብቻ ያተኮረ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ የፕሬዚዳንቱ ንግግር በሕግ መንግስቱ በተሰጣቸው ሥልጣንና ተግባር መሠረት የተደረገ ንግግር ስለመሆኑ የሚያመላክት አንዳችም ነገር አላየሁበትም፤ በመሆኑም የፕሬዚዳንቱ ንግግር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢነገር የተሻለ ይሆን ነበር ግን በሁለቱም ቢነገር ውጤቱ ዉሃ ቢወቅጡት እንቦጭ ነው፡፡ በዚህም መሠረት ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ባቀረቡት የመክፈቻ ንግግር ላይ ሊካተቱ የሚገባቸው ነገር ግን ያልተካተቱ፣ እንዲሁም … [Read more...] about ኳሱ በማን እጅ ነው?
ሁሉም አይነት አክራሪ መስመሮች ይጎዱናል!!!
(ይህንን ጽሁፍ በከፊል ከሁለት ዓመት በፊት በ16-08-2011. "ሁለቱም መስመሮች ይጎዱናል" በሚል አርዕስት አውጥቼው በተለያዩ የኢንተርኔት ድኅረ ገጾች ተነቦ የነበረ ቢሆንም፣ አብዛኛው ጽንሰ ሃሳብ፣ ሰሞኑ እየተካሄደ ካለው ጽንፈኛ የጎጥ ፖለቲካ ጋር፣ ብዙ ተያያዥነት ያለው ስለሆነ፣ አንዳንድ ከወቅቱ ሁኔታ ጋር የማይሄዱትን አስተካክዬ፣ ካሁኑ ሁኔታ ጋር አያይዤ ነው ያቀረብኩት፡፡ ፒዲኤፉ ብቻ ስለሆነ በእጄ የቀረውና ከፊሉን ማረም ስላልቻልኩኝ፣ ስለጥራቱ አስቀድሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡) ሰሞኑን በዲያስፖራ የፓልቶክ የውይይት መድረኮች፣ የአጼ ሚኒሊክንና እና ቴዲ አፍሮን በሚደግፉና በሚቃወሙ፣ በመቶዎች በሚቆጠሩ ታዳሚዎች መሃከል ይካሄድ የነበረውን ውንጀላና፣ መከላከልን እኔም ለጥቂት ቀናት እያዳመጥኩኝ ስከታተል፣ ሁኔታው እንዳሳዘነኝ የገባት ባለቤቴ፣ ወንበሯን ስባ ተጠግታኝ፣ እሷም … [Read more...] about ሁሉም አይነት አክራሪ መስመሮች ይጎዱናል!!!
ዳር ሆነው የሚመለከቱት የጎሳ ፖለቲካ ምሱ “ደም”!!
"ህወሃት" የሚባለው የትግራይ ነጻ አውጪ ትግራይን መቼና ከማን ነጻ እንደሚያወጣ በውል የተቆረጠ ቀን ባይኖርም ህገ መንግስታዊ ዋስትና ግን አለው በሚል እየተተቸ 23 ዓመታትን አስቆጥሯል። አገር እየመራም ነጻ አውጪ፣ በረሃም እያለ ነጻ አውጪ፣ በአህጉርና በዓለም አቀፍ ደረጃ ሲወከልም ነጻ አውጪ!! ይህንን የተለመደና ግራ የሚያጋባ እውነት ያነሳነው ወደን አይደለም። ይህ የህወሃት ግልጽ መለያና ከመለያው የሚነሳው ትንታኔ ለማንም የተወሳሰበ ይሆናል ብለንም አንገምትም። ኢህአዴግ የሚባለው የ"ሎሌዎች" ስብስብ ያበጀውና የሚመራው ህወሃት ከሌሎቹ በተለየ በነጻ አውጪ ስም 23 ዓመት አገር ሲገዛ ሌሎቹ "የነጻ አውጪ" ስም አለመያዛቸው ግን ሁሌም ሊመረመር የሚገባው ጉዳይ ይመስለናል። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ "ነጻ" መውጣት ያለባቸው ህወሃቶች ሳይሆኑ ሌሎች የአገራችን ህዝቦች፣ የትግራይን … [Read more...] about ዳር ሆነው የሚመለከቱት የጎሳ ፖለቲካ ምሱ “ደም”!!
ደቡብ ሱዳን በጎሣ ፖለቲካ እሳት እየተበላች ነው!
ከተመሠረተች ምንም ያህል ያልሰነበተችው ደቡብ ሱዳን ሕዝቧ ሰላሙንና ነጻነቱን በደስታና በጸሎት አጣጥሞ ሳይጨርስ በእርስበርስ ጦርነት ውስጥ ከወደቀች አንድ ወር አልፏታል፡፡ ጎሣን መሠረት በማድረግ የተቀሰቀሰው ፍልሚያ ግን የተጀመረው ገና ደቡብ ሱዳን አገር ከመሆኗ በፊት እንደሆነ ብዙዎች ይስማሙበታል፡፡ በደቡብ ሱዳን ሣር ላይ የኃያላኑ ዝሆኖች የእጅ አዙር ጠብና ፍጥጫም አብሮ የሚጠቀስ ነው፡፡ አፍሪካ ከምዕራባውያን ቅኝ ግዛት ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ የመፈንቅለ መንግሥትና የእርስበርስ ጦርነት ትዕይንቶችን ስታስተናግድ ቆይታለች፡፡ ይህን “coup-civil war trap” አዙሪት በአብዛኛው የመከሰቱን ሁኔታ የፖለቲካ ተኝታኞች የሚስማሙበት ነው፤ ዋንኛውንም ምክንያት ጠንካራ ተቋማት ያለመመሥረታቸው ውጤት እንደሆነ ያሰምሩበታል፡፡ አዲስ አገርም ሆነ መንግሥት ምስረታ ወቅት የሚከሰቱ ሁለት … [Read more...] about ደቡብ ሱዳን በጎሣ ፖለቲካ እሳት እየተበላች ነው!
እስክንድር ነጋ የ2014 የነጻነት ወርቅ ብዕር ተሸላሚ ሆነ
የዓለም የጋዜጦችና ዜና አታሚዎች ማኅበር (WAN-IFRA) የ2014 የነጻነት ወርቅ ብዕር ሽልማቱን ለኢትዮጵያዊው ጋዜጠኛና አሳታሚ እስክንድር ነጋ እንዲሰጥ መወሰኑን ባወጣው መግለጫ አስታውቆዋል:: ህወሃት/ኢህአዴግ "የጸረ ሽብር ሕግ" በማለት ባወጣው አዋጅ ሰበብ እስክንድር ነጋ 18 ዓመት እንዲታሰር የተበየነበት መሆኑን መግለጫው ጨምሮ ገልጾዋል:: መግለጫው እስክንድርን ጨምሮ ሰሎሞን ከበደ፣ ውብሸት ታዬ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና ዩሱፍ ጌታቸው ከእስር እንዲፈቱ አሳስቦዋል:: ኢትዮጵያን በቅርቡ የጎበኙት የማኅበሩ ፕሬዚዳንት በአገሪቱ የሚገኙ ጋዜጠኞችና አታሚዎች በፍርሃት የጋዜጠኝነታቸውን ሞያ እንደሚያከናውኑ መታዘባቸውን አስታውቆዋል:: ሽልማቱ በሰኔ ወር በቶሪኖ ጣሊያን በሚደረገው የዓለም የጋዜጦች ኮንግረስ፣ የዓለም አርታኢዎች መድረክ እና የዓለም ማስታወቂያ ሥራ መድረክ ጣምራ … [Read more...] about እስክንድር ነጋ የ2014 የነጻነት ወርቅ ብዕር ተሸላሚ ሆነ
መቼ ነው?
መቼ ነው ይሄ ቀን - ከኛ ቤት ’ሚያልፈው ለመኖር መደፋት - ተረት የሚሆነው? መቼ ነው ወገኔ - መኖር የሚችለው እንደሰው ለመኖር - ሰውን እሚመስለው? መቼ ነው ረሃቡ - ተረታሁ የሚለው እሳቱ እሳት ሁኖ - ኑሮን ’ሚያበስለው? መቼ ነው ይሄ ቀን - ተረት እሚሆነው መኖር አለመኖር - መሆኑ እሚያከትመው? … [Read more...] about መቼ ነው?
23 ዓመት + አስደንጋጭ + አሳዛኝ = ወዴት እየሄድን ነው?
ተማሪዎች ያለዕድሜያቸው ጫት፣ ሲጋራና ልቅ ወሲብ ይጀምራሉ ሴት የቢሮ ሠራተኛ ሴቶች በወሲብ ንግድ ኑሮአቸውን ይደጉማሉ ኢትዮጵያ ልጆችዋን እየከሰረች ነው ትግራይ ጫት መቃም ክልክል ነው "በስነምግባር የታነፁ ዜጐችን በማፍራት ረገድ አገሪቱ ፈታኝ ሁኔታ ላይ ናት" በአዲስ አበባ ከአንደኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች፤ ለከፍተኛ የስነ ምግባር ጉድለቶች እንደተጋለጡ ጥናቶች አመለከቱ፡፡ ሰሞኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር “ስነምግባር ለእድገት ሁሉ መሠረት ነው” በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ በቀረቡት ጥናቶች በተለይ የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፤ በየትምህርት ቤቶቹ አካባቢ ባሉ ህገወጥ የአልኮል፣ የአደንዛዥ እጽ መጠቀሚያ እና የወሲብ ፊልሞች ማሣያ ቤቶች መበራከት የተነሣ ለችግሩ ተጋላጭነታቸው … [Read more...] about 23 ዓመት + አስደንጋጭ + አሳዛኝ = ወዴት እየሄድን ነው?
“ቀዶ ጥገና ካላገኙ በኦሮሚያ 200 ሺህ ያህል ሰዎች የዓይን ብርሃናቸውን ያጣሉ” ቢቢሲ
በኦሮሚያ ክልል ውስጥ የምትገኘው የኩዩ ቀበሌ ግማሽ ያህል ነዋሪዎቿ አይነ ስውር የመሆን አደጋ የተጋረጠባቸው ናቸው ይላል የቢቢሲ ዘገባ፡፡ በዚሁ መንደር በሚገኘው የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ተማሪ የሆኑ ህጻናት በቤተሰባቸው ውስጥ የዓይን ችግር ያለበት ሰው እንዳለ ሲጠየቁ 20 ያህል ህጻናት እጃቸውን ያወጣሉ ይላል ዘገባው፡፡ የዚህ ሁሉ መነሾው ደግሞ ትራኮማ ነው፡፡ ቢበዛ በ10 ደቂቃ የቀዶ ጥገና ህክምና ሊፈወስ የሚችለው ትራኮማ አንዳንዶች የድህነት በሽታ ይሉታል፡፡ በዓለማችን 2.2 ሚሊየን ህዝብ በትራኮማ ምክንያት የዓይን ብርሃኑን ያጣ ሲሆን በኢትዮጵያ ትራኮማ እጅጉን የተስፋፋው በኦሮሚያ ክልል እንደሆነ ይታወቃል፡፡ 10 ደቂቃ የማይሞላውን ቀላል የቀዶ ጥገና ህክምና ካላገኙ 200 000 ያህል የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች የዓይን ብርሃናቸውን ያጣሉ የሚለው … [Read more...] about “ቀዶ ጥገና ካላገኙ በኦሮሚያ 200 ሺህ ያህል ሰዎች የዓይን ብርሃናቸውን ያጣሉ” ቢቢሲ
“ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”
ፈጣሪ በየትውልዱ የራሱን ድምጽ ያወጣልፍቅር ያሸንፋል-- የኔ ሳይሆን የትውልድ ድምጽ ነውእዳ አለ የምንል ከሆነም፤ እዳ የሚከፈለውና የሚሸፈነው በፍቅር ብቻ ነው የፍቅር ጉዞ ከሚለው ሃሳብ እንጀምር፡፡ መነሻው ምንድነው? “አቦጊዳ ብዬ፣ ፊደል “ሀ”ን ቆጥሬ፤ የፍቅርን ትርጉም ለልቤ አስተምሬ፣ ይዤሽ በአኮፋዳ እንደቆሎ ተማሪ፣ አቦጊዳ ልበል የፍቅር ጀማሪ…” እንዲህ ነው የኔ የዘፈን ህይወት የሚጀምረው። አሁን የፍቅር ጉዞ ላይ ደርሷል፡፡ ሁላችንም፣ በተለያዩ የታሪክ አጋጣሚዎች ውስጥ እናልፋለን። ብዙ ቅሬታና ብዙ ደስታ፣ ብዙ ትክክል የሆኑ ነገሮችና ብዙ ትክክል ያልሆኑ ነገሮች አሉበት - ያለፍንበት ታሪክ፡፡ ትልቁ ነጥብ፣ ካለፍንበት ታሪክ ተነስተን ለሚቀጥለው ጊዜ ምን እናድርግ የሚለው ነው፡፡ ያዘንበትን ነገር በይቅርታ ሰርዘን፣ የወደድነውን ነገር ደግሞ አሳድገን … [Read more...] about “ከወረስነው ቂም ይልቅ የምናወርሰው ፍቅር ይበልጣል”
የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ወጣቱ ትውልድ ራሱን ከፅንፈኞች ማራቅ ታሪካዊ ግዴታው ነው !
ከጠባቦችና የግንጠላ አራማጆቸ ጎራ እንደሚስተጋባው ከንቱ ታሪክ አገራችን ኢትዮጵያ በድንገት የዛሬ መቶ አመት የተከሰተች ሳይሆን በብዙ ዘመናት የዜጎች መስዋዕትነት የተገነባች አገር ናት። ኢትዮጵያን ኢትዮጵያ ለማድረግ የብዙ ሚሊዮንና የአያሌ ትውልድ ኢትዮጵያውያን ህይወት ተገብሮባታል። ይነሰም ይብዛም፣ ይጉላ ይደብዝዝ፣ ሁሉም ህዝብ ለዚያች አገር ግንባታ አሰተዋፅኦ አድርጉአል። በሌሎች አገሮች ታሪክም እንደተከሰተው ሁሉ በኢትዮጵያም ታሪክ ጦርነት የሀገር ግንባታው ሂደት አካል ሆኖ ተገኝቷል። በሂደቱ ለጠፋው ህይወትና ለደረሰው በደል የዛሬው ትውልድ ከቶም ተጠያቂ ሊሆን አይችልም ብሎ ኢወክንድ ያምናል። (ሙሉውን ጽሁፍ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስከበር ወጣቱ ትውልድ ራሱን ከፅንፈኞች ማራቅ ታሪካዊ ግዴታው ነው !










