ፈላጊና ተፈላጊን የሚያገናኙ ደላሎች እስከ 60 ሺህ ብር ኮሚሽን ይከፈላቸዋል ባሎቻቸው ሳያውቁ በውጭ አገር ማህፀን አከራይተው የተመለሱ ሴቶች አሉ ማህፀን ማከራየትም ሆነ መደለል ህገወጥ ነው - የህግ ባለሙያ ማህፀን ለመከራየት ከአሜሪካና ከአውሮፓ ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ ባለትዳሮች በመበራከታቸው ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ እንደተስፋፋ ደላሎች የተናገሩ ሲሆን፤ የማህፀን ኪራይና የማህፀን ኪራይ ድለላ ህገ-ወጥ እንደሆነ የህግ ባለሙያ ገለፁ፡፡ የዛሬ 3 ዓመት ወደ ህንድ ሄዳ የማህፀን ኪራይ አገልግሎት እንደሰጠች የተናገረች አንዲት ወጣት፤ የ11 ወር ወጪዋ ተችሎ 250ሺ ብር እንደተከፈላት ገልፃለች፡፡ አሁን ክፍያው በእጥፍ አድጐ 500ሺ ብር መድረሱን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የማህፀን አከራይዋንና ተከራዮቹን የሚያገናኙ ወኪሎች፤ክፍያው ከሌሎች አገራት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ … [Read more...] about የማህፀን ኪራይ ክፍያ 500ሺ ብር ደርሷል
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር ሁለት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ "የእንዳልካቸው አባት የእንዳልካቸው ልጅ መውለድ አስተካክሎ እንደዚህ ነው እንጂ" በማለት አዝማሪ የገጠመላቸው ቢትወደድ መኮንን ማለት እኚህ ናቸው እኚሁ ትልቅ ሰው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ብዙ መጽሐፍትን የጻፉም ነበሩ። ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፫
በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ወራሪው ማን ነው? ተወራሪዎቹስ?
በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ታላቅ የሕዝብ ቅልቅል ተካሂዷል። ከእነዚህ ምክንያቶች መካከል፦ የአህመድ ግራኝ ወረራ፣ የኦሮሞ ወረራ፣ በዘመነ መሣፍንት የነበሩት የእርስ በእርስ ጦርነቶች፣ ፈፃሜ-ዘመነ መሣፍንትን ያበሠሩት የማዕከላዊ መንግሥትን እንደገና የማዋቀር ጦርነቶች እንዲሁም ሁለቱ የኢጣሊያ ወረራዎች የሚጠቀሱ ናቸው። እነዚያ ጦርነቶች እና የእርስ በእርስ ግጭቶች ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሕዝብ ክፍል ሕይዎት እንዳሣጡ አይካድም። ያንንም ተከትሎ ከኑሮ አስገዳጅነት እና በአገዛዝ ኃይሎች የበላይነት የያዘው አካል በሚፈጥረው የፖለቲካ አሠላለፍ መለዋወጥ ምክንያት የአንዱ ጎሣ ወይም ነገድ አባሎች በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመጥፋት ጉዳት ደርሶባቸዋል። በዚህ ረገድ ከኢትዮጵያ ዋና ዋና ነገዶች እና ጎሣዎች መካከል፦ በምዕራብ ኢትዮጵያ ነዋሪ … [Read more...] about በዘመናዊት ኢትዮጵያ ታሪክ ወራሪው ማን ነው? ተወራሪዎቹስ?
የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ ለምን አይቋጭም?
መለስ በሁለቱ አገሮች ድንበር ላይ “የጅራፍ ድምጽ እንኳን አይሰማም” በማለት ሲመጻደቁበት የነበረው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በ"ወረራ" እና "ወረራን መቀልበስ" በሚል ድራማ ተጀምሮ ከተቋጨ አስራ አምስት ዓመት አልፎታል። ኢህአዴግና ሻዕቢያ ጉዳያቸውን በጠረጴዛ ዙሪያ ወይም በጡንቻ መቋጨት ያልቻሉበት ምክንያት ለብዙዎች እንቆቅልሽ ሆኖ እስካሁን አለ። ሁለቱም ወገኖች ድንበር ላይ ወታደር አፍስሰው መቀመጣቸውን አስመልከቶ "አውቀው ነው" ከሚለው ውሃ የማይቋጥር አስተያየት ጀምሮ በርካታ ጉዳዮች በገሃድና በሹክሹክታ ሲሰማ ቆይቷል። የጎልጉል የዜና ምንጮች ሰሞኑን ከአዲስ አበባ የላኩት መረጃ ግን በይዘቱ የተለየ ነው። ይህንኑ አዲስ ጉዳይ የሚመለከታቸው ክፍሎች አስተያት እንዲሰጡበት ያደረግነው ሙከራ ባይሳካም ዜናው ለውይይት የሚጋብዝ በመሆኑ አትመነዋል። የድንበር ውዝግቡ አንዲቋጭ … [Read more...] about የኢትዮ-ኤርትራ የድንበር ጉዳይ ለምን አይቋጭም?
“አባ” ግርማ! እንኳን ለግንቦት ፳ አደረሰዎ!
ወያኔ አሁን ደኅና ልማታዊ መነኵሴ አገኘች! ጎሽ! የለንደኑ ኤምባሲዋ፣ አዲሱን ወዶ-ገባ ለግንቦት ፳ አሰልጥና አስመረቀች! በድንኳን ባደረገቸው ድግስ ላይ በግልጽ ለዕይታ አበቃች። ማብቃቷንም በራሷ የሚዲያ መረብና እና በዓይጋ ድረ-ገጿ በተነች። “አባ” ግርማ፣ የለንደኗን ርዕሰ አድባራት ደብረጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ሕንጻና ንብረቷን፣ እጅ መንሻ አድርገው በማቅረባቸው፣ አሁን የወያኔ ባለውለታ አሽከርነታቸውን አረጋገጠዋል። እንዲያ ነው እንጂ! ማጥ ውስጥ ከወደቁ አይቀሩ በቅጡ መንከባለል ይሻላል። ለወያኔ አድረዋል ስንል፣ “ስም አጥፊዎች” ተባልን። አሁን ደጋፊዎቻቸው ምን ይበሉ? በየሳምንቱ፣ የጥበቃ ዘበኞችን ቀጥራ ስታስጠብቃቸው የነበረችው በከንቱ አልነበረም። በነዚህ ፈርንጆችና ሶማሌ እንግዶች መሀል የሚታዩት ሁሉቱ ከሀዲ ግርማዎች ናቸው - ግርማ ከበደና፣ ግርማ ቡፋ … [Read more...] about “አባ” ግርማ! እንኳን ለግንቦት ፳ አደረሰዎ!
የእናት ሀገር የድረሱልኝ ጥሪ ???…
ባለፈው ሰሞን ወያኔ ኢሕአዴግ ላለመው የጥፋት ተልእኮ ወሳኝ ክንውኑን መተግበሩ ይታወሳል፡፡ ወያኔ ለጥፋት ተልእኮው በእጅጉ የሚረዳውን ወሳኝ የጥፋት ሥራ የመሥራቱን ያህል ከእምነተ-አሥትዳደር (ፖለቲካ) ፓርቲዎች (ቡድኖች) አንሥቶ እስከ ሕዝባዊ ማኅበራት (Civic organizations) ድረስ ያሉ ሁሉ ልብ ሳይሉት ወይም በቅጡ ሳይረዱት ቀርተው ይሁን ምን አላውቅም ተገቢውን ትኩረት ሳይሰጡት ሲቀሩ ሳይ እጅግ ተገርሜያለሁ፡፡ ወያኔ በአሩሲ ሔጦሳና በሐረር ጨለንቆ ላይ ፋሽትት ጣሊያን ለሰበው የቅኝ ግዛት ይዞታ ዘለቄታ ሲል በነበረው ስልት (Strategy) ተአማኒነት እንዲኖረው በእውነተኛው ታሪካችን ላይ ሆን ብሎ በክፋት የፈጠረውን ፈጠራ በርዞ የሕዝባችንን አንድነት፣ ሰላም፣ ጥምረት፣ ወንድማማችነት (እኅትማማችነት)፣ መተማመን ለመፈረካከስና ለአገዛዙ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲጠቀምበት … [Read more...] about የእናት ሀገር የድረሱልኝ ጥሪ ???…
አባ ዱላና ከንቲባ ድሪባ የቁም እስረኛ ሆኑ፣ ፓስፖርታቸው ተቀማ
አባ ዱላ ገመዳና የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ ፓስፖርታቸውን ተነጥቀው የቁም እስረኞች መሆናቸው ከተለያዩ ምንጮች እየወጡ ያሉ መረጃዎች አመልከተዋል። የጎልጉል ምንጮች ግን ኦህዴድ ውስጥ በከፍተኛ አመራሮች ደረጃ እየተካሄደ ያለው ግምገማ ሲጠናቀቅ በርካታ ባለስልጣኖች ክስ እንደሚመሰርትባቸው ተናግረዋል። በቀድሞው የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት አባ ዱላ ገመዳና በአቶ ድሪባ ላይ ይህ ውሳኔ የተላለፈው አገር ጥለው እንዳይወጡ በሚል ነው። ጎልጉል በቅርቡ ካገር መውጣት የማይችሉ ባለሥልጣኖች እንዳሉ ጠቅሶ መዘገቡ ይታወሳል። ውሳኔው የተላለፈው ሰሞኑን የአዲስ አበባን አዲስ ማስተር ፕላን ለመተግበር የኦሮሚያ ክልል ከተሞች መካተታቸው ይፋ መሆኑን ተከትሎ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ነው። ከሁለቱ ባለስልጣናት በተጨማሪ ከፍተኛ የክልልና የዞን የኦህዴድ አመራሮችም በደህንነት ቅርብ ክትትል … [Read more...] about አባ ዱላና ከንቲባ ድሪባ የቁም እስረኛ ሆኑ፣ ፓስፖርታቸው ተቀማ
ክስ
ለአንድ ዘጠኝ ቀናት በግል ጉዳይ ምክንያት ወደ ገጠር ወጣ ብየ ነበር፡፡ ሀገር ሰላም ብየ ከሄድኩበት ስመለስ ከሁለት ወራት በፊት “የተገነቡትና በመገንባት ላይ ያሉ የመታሰቢያ ሐውልቶች የሠማዕታት ወይስ የቅሱፋን” በሚል ርእስ በጻፍኩት ጽሑፍ ምክንያት የዕንቁ መጽሔት ዋና አዘጋጅ ኤልያስ ገብሩ እና ዋና ሥራ አስኪያጁ ፈቃዱ ምኅተመወርቅ ማዕከላዊ ተብሎ በሚጠራው ፖሊስ ጣቢያ ተጠርተው ከሔዱ በኋላ መከሰሳቸው ተነግሯቸው የእኔን ሙሉ የመኖሪያ አድራሻ ተጠይቀው እነሱም ከስልኬ በቀር የመኖሪ አድራሻየን እንደማያውቁ ሥራ የምንሠራው በስልክ እየተደዋወልን ቢሮ በመገናኘት እንጂ መኖሪያ ቤቴ ድረስ በመምጣት አለመሆኑን ሲገልጹ የተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥሬን እንዲሰጡ በመጠየቃቸው ስልኬን መስጠታቸውን፤ በዚያ ስልክ ቁጥር መሠረትም ጣቢያው ድረስ ስለምፈለግ እንድቀርብ ለመንገር ለዚያ ክስ ጉዳይ የተመደቡ … [Read more...] about ክስ
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፩” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አንድ ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ ሲጠሩ የኖሩ - በዶክቶር ማዕረግ የውጪ ጉዳይን - የመሩልን በወግ በጥሩ ስራቸው - የሚነሱ ሁሌ ስማቸው ምናሴ - አባታቸው ኃይሌ ተብለው ሚጠሩ ባለስልጣን ናቸው ምስላቸው ተለቆ - ሳምንት ያየናቸው ለዚህ ሳምንት “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪” ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ የዛሬ ሳምንት መልሱን በግጥም እናቀርባለን፡፡ እኚህ … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፪
የኢትዮጵያ መሰረታዊ የልማት ችግር የት ነው? እንዴትስ ይፈታል?
ስለ ልማታዊ መንግስት (developmental state) ስናወራ ልማታዊ የሚለው ቅጽል ስም ገላጭ በመሆኑ መጀመሪያ “ልማታዊ” ሲባል ምን ማለት ነው? ብለው ሰዎች እንዲጠይቁን ያደርጋል። ኣንዱ የዚህ ጥያቄ ምንጭ በኣሁኑ ዘመን ልማት ለሚለው ስያሜ ሰፊ ትርጉም ስለተሰጠው ሲሆን ኣንድ መንግስት ዛሬ ላይ ሆኖና ብድግ ብሎ “ልማታዊ መንግስት ነኝ” ሲል ማን ልማታዊ ያልሆነ ኣለ ብለው ሰዎች እንዲነሱ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሹ የሚያደርግ ጥያቄ ለማኝ ጉዳይ ነገር ያንጠለጠለ በመሆኑ ነው። ሁሉ እንደሚያውቀው በኣሁኑ ጊዜ ልማት ለሚለው ጽንሰ ሃሳብ የተሰጠው ትርጉም ሰፊ ሲሆን የሰው ልጆችን ሁለንተናዊ ኣዎንታዊ እድገት ይጠቀልላል። የኢኮኖሚ እድገት፣ ትምህርት፣ ጤና፣ ዴሞክራሲና መልካም ኣስተዳደር፣ ወዘተ. ይሸፍናል። በመሆኑም ኣንድ መንግስት በዚህ በኣሁኑ ጊዜ ልማታዊ ነኝ ሲል ማንም … [Read more...] about የኢትዮጵያ መሰረታዊ የልማት ችግር የት ነው? እንዴትስ ይፈታል?










