ወያኔ በለስ ቀንቶት የኢትዮጵያን በትረ ስልጣን ከተቆጣጠረ ጊዜ አንስቶ ከጫካ አዝሎት የመጣውን አብዮታዊ ዲሞክራሲና የአንድን ጎሳ ሁለንተናዊ የበላይነት የማስፈን ዓላማ ለማሳካት ባለው አቅም ሁሉ ሲሰራ ኖሯል። ዘረኛው ወያኔ የትግሬ ጎሳን በመሣሪያነት ለመጠቀም ሲል ጎሳውን በሞራል፤ በኢኮኖሚ፤ በጤናና በትምሕርት ከሌላው የላቀ ደረጃ ላይ ማድረስ በሚለው መርሁ መሠረት የሃገሪቱን ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊ፤ ወታደራዊና የደህንነቱን ዘርፍ ሁሉ በትግሬዎች ቁጥጥር ሥር እንዲውል በማድረግ በኢትዮጵያ ውስጥ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓትን ዘርግቶ ይገኛል። ይህ ብቻም አይደለም የወያኔ አገዛዝ መሣሪያ ይሆነኛል ከሚለው ከትግሬ ህዝብና ከትግራይ ክልል በዘለለ ኢትዮጵያ ስለምትባል ሃገርም ሆነ ኢትዮጵያዊ ስለሚባል ሕዝብ ዘለቄታዊ ጥቅምና ጉዳት ባለማሰብ የሥልጣን ዘመኑን ዘለዓለማዊ ለማድረግ ያስችለኛል … [Read more...] about የወያኔ የጎሳ አፓርታይድ ሥርዓት በዲያስፖራው ኢትዮጵያዊ ላይ
ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ
ራሳቸውን ራስ ገዝ አገር አድርገው በማስተዳደር ላይ ያሉት ሶማሌላንድና ፑንትላንድ ከኢትዮጵያ ጋር ውህደት ለመፈጸም የሚያስችላቸውን ሰነድ ለአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መ/ቤት (ስቴት ዲፓርትመንት) ማቅረባቸው ተሰማ። ሰነዱ ለእንግሊዝና ለሌሎች የአውሮፓ ሃያል አገራት መቅረቡም ታውቋል። ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች "እንሰጋለን" ሲሉ የውህደት ጥያቄው ሊተገበር የሚገባው እንዳልሆነ አመልክተዋል። ከኢትዮጵያ ጋር ለመዋሃድ ጥያቄ ያቀረቡት ሁለቱ የሶማሌ ጠቅላይ ግዛቶች የተጠቀሰውን ሰነድ ማቅረባቸውን የተናገሩት የጎልጉል ምንጮች፣ የሰነዱን ዝርዝርና ውህደቱ በምን መልኩ ሊከናወን እንደሚችል ዝርዝር መረጃ ለጊዜው ከመስጠት ተቆጥበዋል። ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ራሳቸውን ከተበጠበጠችው እናት አገራቸው ነጥለው አገር ማስተዳደር ከጀመሩ ዓመታት ቢያስቆጥሩም እስካሁን ድረስ በአገርነት እውቅና … [Read more...] about ፑንትላንድና ሶማሌላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የመዋሃጃ ሰነድ አቀረቡ
ምሽት ዳንኪራ ከዲያስፖራ
ያለሁት ካናዳ፤ ቶሮንቶ ነው፡፡ ከጥቂት ሳምንታት ቆይታ በኋላ ትላንት ማታ አንዱ የኢትዮጵያ ምግብና ዳንኪራ ቤት ለማምሸት ከዘመድ እና ሰሞኑን ከተዋውቅኳቸው ጥቂት ሰዎች ጋር ሄድኩ፡፡ ቤቱ በአንድ ሰሞን በአንድ ዜማ እጅግ ታዋቂ ሆኖ በነበረ ወጣት ድምፃዊ የሚተዳደር ነው፡፡ ስገባ ወጣቱን ድምፃዊ አየሁት፡፡ እንግዶቹን ዞር ዞር እያለ ሰላም ይላል፡፡ ከማውቀው ወፍሯል፡፡ ዘመናዊም ባህላዊም ዘፈን በዲጄ ሲለቀቀቅ ጠባቧ ቤት ንዝረቷ ይጨምራል፡፡ ከምሽቱ አምስት ሰአት ገደማ ቤቷ ሞላች፡፡ ከሀበሻ ውጪ ሌላ ዘር ያለው ሰው ግን አላየሁም፡፡ ስድስት ሆነን ከተቀመጥንበት ጠረጴዛ ጀርባ ባለጌ ወንበርና ጠረጴዛ ላይ አንዲት በህንድ ዘዬ የተሰራ “እዩኝ እዩኝ” ሆደ- ግልብ ብልጭልጭ ልብስ የለበሰች ረጅምና ቀጭን፣ ቆንጅዬ ልጅ ተቀምጣ ቢራ ትጠጣለች፡፡ አላግባብ ተከምሮ ሳር ከጫነ መኪና … [Read more...] about ምሽት ዳንኪራ ከዲያስፖራ
የዛፍ ጥላ ስር ትምህርት ቤቶች
ጠመዝማዛ ባላዎች ላይ የቆመው ክፍል በደደሆ ዛፍ ቅጠል የተሠራ ጣሪያ አለው፡፡ ክፍሉ ውስጥ ከ20 የማይበልጡ ትንንሽ ድንጋዮች ላይ ኩርምት ኩርምት ብለው የተቀመጡ ተማሪዎች ይታያሉ፡፡ ደብተሮቻቸውን በየጉልበታቸው ላይ አድርገው ከፊት ለፊታቸው ያለውን መምህር ያዳምጣሉ፡፡ ከመሬት ብዙም የማይርቀው የክፍሉ ጣሪያ መምህሩን ጐንበስ ብሎ እንዲያስተምር ግድ ብሎታል፡፡ መምህሩ ለማለቅ በተቃረበ ነጭ ጠመኔ ያረጀ ሰሌዳ ላይ ቁጥሮች እየጻፈ ድምፁን ከፍ አድርጎ ሒሳብ ያስተምራል፡፡ የክፍሉ ጣሪያ በሳሳበት አቅጣጫ የተቀመጡ ተማሪዎች ጸሐይ ይመታቸዋል፡፡ ተማሪዎቹ ድንጋዩ ጐርበጥ ሲያደርጋቸው ወደ አንድ ወገን ገደድ እያሉ ለመመቻቸት ይጣጣራሉ፡፡ እነዚህ በዛፍ ጥላ ስርና በዳስ የሚማሩ ተማሪዎች የመኪና ድምጽ በሰሙ ቁጥር አንገታቸውን አጠማዘው ይመለከታሉ፡፡ ግድግዳ በሌለው ክፍላቸው አቅራቢያ … [Read more...] about የዛፍ ጥላ ስር ትምህርት ቤቶች
የአረብ ሃገሩ ክፉ ስደት!
ገና ረፋዱ ላይ ጸሃዩ ናላን ያዞራል ... የቢሮ የቤት ማቀዝቀዣዎች እንኳ ሙቀቱን ተቋቁመው የማብረድ ስራቸውን እንዳይከውኑ የሳውዲ ጅዳ በጋ ሃሩር ጸሃይ ፈተና ሆኖባቸዋል! ... በዚህ የቀለጠ የበርሃ ሃሩር ጤነኛ መቋቋም ያልቻለው ሙቀት በአንዲት ሰውነቷ የደቀቀ እህት ይወርድባታል ... ቦታውም ከጅዳ ቆንስል ግቢ የቅርብ ርቀት በሚገኝ የአንድ አረብ ግቢ በር ላይ ነው .... ስለዛሬው የማለዳ አሳዛኝ አጋጣሚ ላጫውታችሁ...! ያሻችሁ ተከተሉኝ! የኩባንያ ስራየን በመከዎን ላይ እንዳለሁ እግረ መንገዴን ቀዝቃዛ ውሃና ማኪያቶዋን ለመነቃቂያ ፉት ልበል ለማለት በጅዳ ቆንስል ቅጽር ግቢ ውስጥ ወደሚገኘው የኮሚኒቲ ካፍቴርያ ብቅ ብየ ያችኑ ማኪያቶ አዘዝኩ ... ማኪያቶየን እየቀማመስኩ እንደኔው የካፍቴሪያ ታዋቂ ደንበኞች ከሆኑ ወዳጆቸ ጋር ስንጨዋወት አንድ ሌላው ወዳጃችን ግዙፍ ሰውነቱ … [Read more...] about የአረብ ሃገሩ ክፉ ስደት!
ቴዲ አፍሮ – በሁለት ጽንፎች
ኢትዮጵያ ውስጥ ፈጽሞ ሊተቹ የማይችሉ ሶስት ግዝፍ ነገሮች አሉ። እነዚህም 1ኛ - ሃይማኖት 2ኛ - መንግስት 3ኛ - ቴዲ አፍሮ ናቸው። ከእንግዲህ ቴዲ አፍሮ ዘፋኝ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ መቆራቆዣ ተቋም ሆኗል። ይህን አስመልክቶ ወዳጃችን Girmabbaacabsaa Guutamaa እንዲህ ይላል.... "ቴውድሮስ ካሳሁን aka ቴዲ ኣፍሮ ዘፋኝ ብቻ ኣይደለም። በሃገሪቱ ውስጥ ካሉት ይልቁንም ባብዛኛው ሊታረቁ የማይችሉ (divergent) ማህበረ-ፖለቲካዊ እሳቤዎችን በሚያራምዱ ኤሊቶች ከሚመሩት የተለያዩ ቡድኖች መካከል የኣንዱ ግሩፕ political ideologue ነው ቴዲ።" ይህ ብያኔ (Definition) የተለጠጠ ቢሆንም ውሸት ግን አይደለም። ቴዲ በሁለት ጽንፍ የቆሙ የፖለቲካ ወገኖች መቆራቆዣ አእማድ (Pillar) ሆኗል። የቴዲን ዘፈኖች መተቸት … [Read more...] about ቴዲ አፍሮ – በሁለት ጽንፎች
የእርቅ ማኒፌስቶ፦ ወደ ዲሞክራሲ የሚያደርስ አማራጭ መንገድ
ያለፉት 23 አመታት በመንግስትና ተቃዋሚ መካከል ያለው ቅራኔ መፍትኤ አላመጣም። በጦርነት ስልጣን የያዘ መንግስት ዲሞክራሲ ይኸሁላችው ብሎ ይሰጥ ዘንድ አይቻለውም። በጦርነት መንግስት ለመቀየር የሚታገለውም ስልጣኑን ሲይዝ ከዚህ የተለየ አያደርግም። ኢትዮጵያ መውጫ ቀዳዳ ያጣች ትመስላለች። እሺ ብንል እርቅና መግባባት ዲሞክራሲን ለመውለድ ብቸኛ መንገድ ነው። እንዴት ማለት ጥሩ ነው። ሁላችንም የምንጠለልባት፦ በፍቅር ተሳስረን የምንኖርባትን ቤተ ኢትዮጵያን እንዴት እንገንባት? 1ኛ/ ሰላምን ብቻ መምረጥ ላይ መድረስ፦ የቤተ ኢትዮጵያ መሰረት። የስላሙን ትግል ከትግሎች ውስጥ እንደ አንዱ ሳይሆን እንደ ብቸኛ አማራጭ መውሰድ ይገባል። ኢትዮጵያ ለዚህ አይነት ሰላም ራሳቸውን የሰጡ ሰላማዊ ተቃዋሚ ልጆች አላት። ሰላምን ብቻ መምረጥ ወደ ዲሞክራሲ የሚያደርሰው የእርቅና መግባባት አስተሳሰብ … [Read more...] about የእርቅ ማኒፌስቶ፦ ወደ ዲሞክራሲ የሚያደርስ አማራጭ መንገድ
ለነዋሪዎች አማራጭ የለም!
በአዲስ አበባ ያለው የመጸዳጃ ቤት ችግር ከልክ ያለፈና መሆኑን የእንግሊዙ ዘ ጋርዲያን ጋዜጣ ዘገበ። ሐሙስ በወጣው የጋዜጣው ድረገጽ ላይ እንዳስነበበው ከ3 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ በሚኖርባት አዲስ አበባ ውስጥ ለሕዝብ መገልገያነት የዋሉት መጸዳጃ ቤቶች 63 ብቻ መሆናቸውን ዘግቧል። አማራጭ ያጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ ከተማዋ ወደ መጸዳጃ ቤትነት እየተለወጠች መሆኗን በምሬት ገልጸዋል። ጋርዲያን “Wash Ethiopia Movement” የተባለ አገር በቀል ድርጅት ጠቅሶ እንደዘገበው በከተማዋ ከ10 ቤተሰቦች 9ኙ የጉድጓድ መጸዳጃ ቤት እንደሚጠቀሙና መቀመጫ ባለው መጸዳጃ ቤት የሚጠቀሙት ከ25 ቤተሰቦች አንዱ ብቻ መሆኑን ተናግሯል። በዘገባው መሠረት የከተማዋ ባለሥልጣናት የዛሬ ዓመት ይገነባሉ በሚል የ100ሚሊዮን ብር ዕቅድ የተያዘላቸው መጸዳጃ ቤቶች እንዳሉ መናገራቸውን … [Read more...] about ለነዋሪዎች አማራጭ የለም!
ኢትዮጵያዊነት . . . ( ክፍል ፪ )
ባለፈው ጽሑፌ ኢትዮጵያዊነት ማለት ምን ማለት እንደሆነ፤ ከልቤ ያማምንበትን በጥቅሉ አስፍሬ ነበር። በዚያ፤ ኢትዮጵያዊያንን መውደድ ማለት፤ ታሪካቸውን፣ ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውን፣ መላ የኑሮ ሁኔታቸውን ጨምሮ ማለት ነው። ሀገራችንን ኢትዮጵያን ማፍቀር ደግሞ፤ ዳር ደንበሯ፣ የተፈጥሮ ሀብቷ፣ ወንዞችና ተራሮቿ፣ ደጋ፣ ወይነደጋና ቆላ ምድሯ፣ አራዊቷ፣ የሚለዋወጡ አራቱ የሀገራችን አየር ጠባይ ወቅቶችን ማለት ነው። ሀገር ያለ መንግሥት ችግር ነው። መንግሥት ደግሞ በዚህ በሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን፤ በሕዝብ ፈቃድና ፍላጎት ኃላፊነቱ ተሠጥቶት የሚያስተዳደር ሀገራዊ ተቋም ነው። በዚህ ሂደት መንግሥት፤ ለመረጠው ሕዝብ ተንቆጥቁጦ ሥራውን ያከናውናል። በተገላቢጦሽ ሕዝብ መንግሥቱን ፈርቶ የሚኖርበት ሀገር፤ ለውጥ በሩን እያንኳኳ ነው። የዚህ አስፈላጊ ተቋምና የሕዝቡ ግንኙነት ይህ ነው። እናም … [Read more...] about ኢትዮጵያዊነት . . . ( ክፍል ፪ )
Getting to know me better
I am in the process of weaning myself from my daily dose of reading about the madness of Woyane. It is not easy. After over two decades of being visually, mentally and spiritually assaulted regarding the evil nature of the Tigray peoples liberation front I am desperately trying to go cold turkey. There was no one spared from informing me everything about the all-powerful, omnipotent Woyane and its evil ways. Even the ‘venerable’ VOA was caught spinning. It wasn’t not long ago that I used to … [Read more...] about Getting to know me better










