በሙስና ወንጀል በሚል በርካታ የሳዑዲ ባለሃብቶችን ዘብጥያ የጣሉት የዙፋን ተስፈኛው የሳዑዲ አረቢያ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን በሳዑዲ ሚዲያ ከታዩ አንድ ወር አልፏቸዋል። በአንዳንዶች ግምት በቤተመንግሥት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ ተገድለዋል ይባላል። አልጋወራሹ በህይወት ከሌሉ ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አህመድ አላሙዲንን “አስፈትተው” የመጡት ማንን አነጋግረው ነው የሚል ጥያቄ ተነስቷል። የሳዑዲ መንግሥት አልጋወራሹ በሥራቸው ላይ እንዳሉ የሚያሳይ ቪዲዮ ለቋል። የሳዑዲ የዙፋን ተስፈኛ አልጋ ወራሽ ሞሐመድ ቢን ሳልማን 11 ልዑላንን እና 38 የመንግሥት ባለሥልጣናትን (የቀድሞውን ጨምሮ) እንዲሁም የንግድ ሰዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን፤ ደላላ (ተጠሪ ወይም front man) ባለሃብት እንደሆነ የሚነገርለት በግማሽ ኢትዮጵያዊ የሆነው ሞሐመድ አላሙዲ (አል-አሙዲ) በቁጥጥር ሥር ከዋሉት … [Read more...] about የሳዑዲው አልጋወራሽ ሞተዋል? ወይስ በህይወት አሉ? ጠ/ሚ/ር ዓቢይ አላሙዲንን “ያስፈቱት” ማንን አነጋግረው ነው?
Archives for June 2018
ከዲያስፖራው ጋር የሚደረገው ውይይት ትርጉም እና ፋይዳ ይኖረው ዘንድ በእውነተኛ የለውጥ እርምጃዎች የታጀበ ይሁን!!
ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በመጭው ነሀሴ ወር 2010 ዓ.ም. ወደ አሜሪካን አገር እንደሚመጡ እና ከዲያስፖራው ማህበረሰብ ጋር የመወያዬት እቅድ እንዳላቸው በስፋት እየተነገረ ይገኛል። በአገር ውስጥም ይሁን በውጭ አገር ያሉ ኢትዮጵያዊያንን ማወያዬት የሚደገፍ ሀሳብ ቢሆንም፣ የሚደረጉት ውይይቶች የአገራችንን ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች መሰረታዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት እገዛ የሚያደርጉ መድረኮች ሊሆኑ ይገባል። አገራችን ኢትዮጵያ ስር የሰደዱ፣ ዘመን የጠገቡ እና ዘርፈ ብዙ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች ያሉባት አገር ነች። እነዚህ ችግሮች ደረጃ በደረጃ መፍትሄ ያገኙ ዘንድ አገራችን በትክክለኛው የለውጥ ጎዳና ላይ መጓዝ ይኖርባታል። በመሆኑም፣ ከዲያስፖራው ጋር የሚደረግ ውይይት ከዘላቂ መፍትሄ አኳያ የሚቃኝ እንጂ የአጭር ጊዜ ግብ ለማሳካት የሚደረግ የህዝብ ግንኙነት … [Read more...] about ከዲያስፖራው ጋር የሚደረገው ውይይት ትርጉም እና ፋይዳ ይኖረው ዘንድ በእውነተኛ የለውጥ እርምጃዎች የታጀበ ይሁን!!


