በቅርቡ በሥልጣን ላይ እያሉ በምርጫ መሸነፋቸውን ባመኑበት ጊዜ ሥልጣናቸውን ያስረከቡት የናይጄሪያው ጉድላክ ዮናታን በአፍሪካ የ65 ዓመታት የምርጫ ዴሞክራሲ ጉዞ ከሚጠቀሱ ጥቂቶች መካከል አንዱ ሆነው ሰንብተዋል፡፡ ይህም ተግባራቸው በናይጄሪያ ብቻ ሳይሆን በመላው አፍሪካ ታላቅ ሥፍራ የሚሰጣቸው የፖለቲካ ሰው አድርጓቸዋል፡፡ በአፍሪካ በተካሄዱ በርካታ ምርጫዎች የሕዝብን ድምጽ በማክበር ሥልጣናቸውን ለተቀናቃኛቸው በማስረከብ የሕዝባቸውን ድምጽ ያከበሩ መሪዎች በጣም ጥቂቶች ናቸው፡፡ ሁሉንም ለአሁኑ ማቅረብ ባንችልም የተወሰኑት ተጠቃሾች እነዚህ ናቸው፡- 1. ኤደን አብዱላ ኦስማን ዳር (ሶማሊያ) - በተለምዶ ኤደን ዳር ተብለው የሚጠሩት እኚህ ፖለቲካኛ የሶማሊያ የመጀመሪያው ፕሬዚዳንት ነበሩ፡፡ በሥልጣን በነበሩበት ጊዜ ሶማሊያን እኤአ ከ1960 እስከ 1967 መርተዋል፡፡ (በዚህ ጽሁፍ … [Read more...] about መሸነፍን በአሸናፊነት የተቀበሉ መሪዎች
Archives for May 2015
የመሪዎች እምባ
ከስም ልጀምር፣ የዛሬ ወጣቶች በተለይ ዘፋኞች ስማቸው በመጠኑ ተቆርጦ ወይም አንሶ ሲጠሩ እየሰማን ነው፤ ቴዎድሮስ - ቴዲ ብዙ ባያስከፋም ተያይዘው የቀጠሉት ዘፋኞች ግን እስከ አባታቸው ስለሚያሳንሱት ኢትጵያዊ ስም መሆኑ ራሱ አጠራጣሪ የሆነብኝ ጊዜ አለ። እስቲ አሁን ጃህ ሉድ አጥሮ ነው ወይስ ተቆርጦ ቻቺ፣ ጃኪ፣ ጂጂ፣ አቢ፣ ኢሚ፣ ዮሲ፣ ጃኪ-ጎሲ፣ ሚሊ፣ ሚኪ፣ ዮኒ፣ ... ልተዋቸው። እንደውነቱ ከሆነ ይህ በፊትም እንዳለ የሚጠቁሙ ማስረጃዎች አሉ አጼ ቴዎድሮስ (መይሳው) መዩ ይባሉ ነበር። ገብርዬም ስማቸው አጥሮ ነው ገብርዬ የሆኑት፣ ኃይለሥላሴም ኃይሌ፣ መንግሥቱም መንጌ ተብለዋል። መለስን መሌ ሲባሉ ባልሰማም ሊባልላቸው ይችል ነበር። በረከት ቤኪ፣ ተፈራ ተፌ ... መባላቸውን ግን ሰምቻለሁ። የኃይለማርያም ደሳለኝ ስም ረዥም ነው መቆረጥ ይገባዋል፤ ኃይሌ ሊባል ይቻል ነበር፤ ግን … [Read more...] about የመሪዎች እምባ
“ለመተማመን እንነጋገር”
በጀርመን የኢትዮጵያውያን የትብብር መድረክ ሜይ 2 ቀን 2015 ዓመተ-ምህረት ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በአካሄደ እለት እውቁ የኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብት አቀንቃኝና ለአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) መስራችና መሪ አቶ ኦባንግ ሜቶ እና እውቁ የምሥራቅ አፍሪካ ፖለቲካ ተንታኝና አሰባሳቢ ማንነት በአንድነት መጽሀፍ ደራሲ አቶ የሱፍ ሃሰን በክብር እንግድነት ተገኝተዋል። ስብሰባው በቅርብ በየመን፣ በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ ባሰቃቂ ሁኔታ ለተሰዉት ወገኖች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት በማድረግ የተጀመረ ሲሆን፣ የትብብር መድረኩ ሰብሳቢ አቶ ጌታሁን አሰፋ በመክፈቻ ንግራቸው እዳስረዱት፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የምትገኝበትን የፖለቲካ፣ ማህበራዊ፣ የጎሳና የሃይማኖት ቀውስ፣ እጅ የከፋ ደረጃ ላይ በመድረሱ፣ የዜጎችና የሀገራችን ህልውና አደጋ ላይ ወድቋል ብለዋል። አያይዘውም፣ … [Read more...] about “ለመተማመን እንነጋገር”
“ጸርሁ በዓቢይ ቃል”
“ርኢኩ ታህተ ምስዋዕ ነፍሶሙ ለእለ ተቀትሉ በእንተ ቃለ እግዚአብሔር ወበእንተ ዘአቀቡ ህጎ። ወጸርሁ በቃል ዓቢይ ወይቤሉ እስከ ማእዜኑ እግዚኦ ቅድስ ወጻድቅ፤ ኢትትቤቀሎሙኑ ወኢትኴንኖሙኑ በእንተ ደምነ እምእለ ይነብሩ ዲበ ምድር” “ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ! እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም? ደማችንንስ በምድር ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” እያሉ ከመሰዊያ በታች ሆነው የታረዱት ነፍሳት በታላቅ ድምጽ ሲጮኹ አየኌቸው (ራዕ 6፡9-10)። ዓለም በግልጽ ያያቸው በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በየደረሱበት የታረዱትን ብቻ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በውስጥም የተገደሉትን ሁሉ የኢትዮጵዮውያ ነፍሳት ሲጮሁ ማየት አለብን። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያናችን(ገአረ ኢየሱስ በህማሙ። ወጸርሀ ኀበ አቡሁ. . . ወእንዘ ሀሎ ህየ ጸርሀ ሀበ አዳም ገብሩ፤ ወሀበ ኩሎሙ ደቂቁ(ሰለስቱ … [Read more...] about “ጸርሁ በዓቢይ ቃል”
በየመን የሚታየው ምስቅልቅል እየሰፋ ስለመጣው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጥረት ምን ያስተምረናል?
በተለያዩ ሀገሮች የሚካሄዱ እንቅስቃሴዎች ያለፉባቸውን ጥምዝምዞች፣ የገጠማቸውን ደጋፊና አደናቃፊ ሂደቶች መመርመር ባንድ ሀገር ውስጥ ለሚካሄደው ትግል ታላቅ ጠቀሜታ አለው። በዚህ አንጻር በ2011 የአረብ ስፕሪንግ ካምባገነናዊ ስርአት ወደ ዴሞክርሲ ልትሸጋገር ነው ተብላ ተስፋ የተጣለባት የመን፣ እነሆ ዛሬ በእርስ በርስ ጦርነት ተናውጣ እንኳንስ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርአት ልትሸጋገር ከራሷም አልፋ አካባቢውን ለማመስ የቻለ ሁኔታ ውስጥ ገብታለች። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ ብሎ መመርመር ለሀገራችን ዴሞክራሲያዊ ትግልም ሆነ ባካባቢው መረጋጋት ላይ ሊኖረው ለሚችለው እንደምታ ታላቅ ትምህርት ይሰጣል። በዚህ አኳያ በዚህ ጽሁፍ ውስጥ የየመንን ተመክሮ በመመርመር ለኢትዮጵያ ሁኔታ የሚኖረውን ትምህርት አመለክታለሁ። በርግጥ ይህ ጽሁፍ ሰፊ የሆነውን የሁለቱን ሀገሮች ውስብስብ የታሪክ፣ የፖለቲካ፣ … [Read more...] about በየመን የሚታየው ምስቅልቅል እየሰፋ ስለመጣው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጥረት ምን ያስተምረናል?
እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፭
ከአዘጋጆቹ፤ባለፈው ጊዜ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፬” በሚል ለቀረበው ምላሽ በድረገጻችን በመላክና በፌስቡክ ላይ በመለጠፍ የተሳተፋችሁትን በሙሉ እናመሰግናለን፡፡ በተለይ በግጥም ምላሻችሁን ለሰጣችሁ በሙሉ ከፍያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ የቅንብሩ አዘጋጅ ወለላዬ በቁጥር አስራ አራት ለቀረበው ጥያቄ ምላሻቸውን በሚከተለው መልኩ በግጥም አስፍረዋል፡፡ መልስ የወልደጊዮርጊስ ቢታይ ምስላቸው ሁሉም ሰው አወቀ እስከታሪካቸው እንደዚህ በሥራው ያገኘ ሰው ሞገስ ምንግዜም ይኖራል በጥሩ ሲታወስ ወልደዮሀንስም በልጃቸው ሥራ አብረው ይጠራሉ ይዘው ትልቅ ስፍራ ላሁኑ “እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፭” ደግሞ ወለላዬ የሚከተለውን አቅርበዋል፡፡ ምላሻችሁን በግጥም በመመለስ ለዝግጅቱ ውበት እንድትሰጡ ለማደፋፈር እንወዳለን፡፡ በሚቀጥለው መልሱን በግጥም … [Read more...] about እኚህ ሰው ማናቸው? – ፲፭
የመጨረሻው ደወል !
ኳ! ኳ! ኳ! ይላል፤ በማርያም ደጃፍ - በገብርኤል፤ በጎርጊስ ደጅ - በሩፋኤል፤ በጨርቆስ ደጃፍ - በአማኑኤል፤ በተክልዬ - በሚካኤል፤ ኳ! ኳ! ኳ! እያለ፤ የመጨረሻው ደወል ተደወለ፤ አትንበርከክ በቃ ! ቆመህ የጴጥሮስን ሞት ሙት አለ:: (ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ) … [Read more...] about የመጨረሻው ደወል !
እረኛ የሌለው ከብት እና መሪ የሌለው ሕዝብ አንድ ናቸው
ባለፈው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ከኢትዮጵያ ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በተደጋጋሚ የደረሱባቸው ከፍተኛ ሰቆቃዎች አሉ። አምና በሣዑዲ ዓረቢያ፣ ባለፉት ሁለት ወራት ደግሞ በየመን በሚኖሩ የዕለት እንጀራ ፈላጊ በሆኑ በመቶ-ሺዎች በሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የተጸፈመባቸው ግፍ የተሞላበት ግድያ እና ስቃይ፣ መንስዔው ኢትዮጵያ መሪ አልባ አገር በመሆኗ ነው። የደረሰው ሳይበቃ፣ በዚህ ምክንያትም ኢትዮጵያውያን ከደረሰብን መከራ ሳናገግም፣ ስቃዩ እና አሟሟቱ ከዐይናችን ሥር ሳይጠፋ፣ እናቶች የለበሱት የሐዘን ጨርቅ ሳይለወጥ፣ ሌላ መዓት በደቡብ አፍሪቃ በሚኖሩ መሪ አልባ ወንድም እና እህቶቻችን ላይ የተፈጸመው አሠቃቂ ግድያ የንብረት መውደም ተከተለ። ሰሞኑን ደግሞ ኢትዮጵያዊ እና ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ፣ ፴(ሰላሣ) ኢትዮጵያውያን በሊቢያ እስላማዊ ጽንፈኞች እንደገና ጠቦት መታረዳቸውን … [Read more...] about እረኛ የሌለው ከብት እና መሪ የሌለው ሕዝብ አንድ ናቸው
በመጨረሻም በግብጽ ነጻ ወጡ . . .
* ሕንጻና መንገድንማ ቅኝ ገዥዎችም ሰርተዋል የፌስቡክ አርበኛው ቴድሮስ አድሃኖም ቦሌ ሄደው ከሊብያ ነጻ የወጡ ዜጎችን ሲቀበሉ አየን። እፊታቸው ላይ የማፈር ሳይሆን የጀግንነት ስሜት ይነበባል። አቀባበላቸውም 90 ደቂቃ በእንቴቤ የሚለውን ታሪክ ይመስላል። ኡጋንዳ ላይ የታገቱ ዜጎችዋን ለማስለቀቅ እስራኤል ያደረገችው ገድል። ቴድሮስ አድሃኖምም በኩራት እና በድል አድራጊነት ስሜት ነው ስደተኞቹን የተቀበሉት። መቼም ሼም የሚባል ነገር ከነሱ ዘንድ ጠፍቷል። በስራቸው ማፈር ሲገባቸው አይናቸውን በጨው እያጠቡ የሌላውን ድል እንደራስ ያጣጥሙታል። ህሊና ያለው ሰው ያሳደዳቸውን እና በባእድ ነጻ የወጡ ዜጎቹን ሲመለከት ብርክ ነው የሚይዘው። አልገባቸው ይሆናል እንጂ ክብራቸውን የሚቀንስ ማንነታቸውን የሚፈትን ድርጊት ነው። አስቀድመን በግብጽ መገናኛ ብዙሃን ዜናውን ባንሰማ ኖሮ ደግሞ ሌላ … [Read more...] about በመጨረሻም በግብጽ ነጻ ወጡ . . .
ምርጫው አዲስ “ጠቅላይ ሚ/ር” አግኝቷል
በሊቢያ ታፍነው የነበሩ ወደ 30 የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን በግብጽ ጦር ኃይል ነጻ አውጪነት መለቀቃቸውን የግብጽ መንግሥት አስታወቀ፡፡ የግብጹ ፕሬዚዳንት አልሲሲ የተለቀቁትን ኢትዮጵያውያን አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ በመገኘት አቀባበል አደረጉላቸው፡፡ ኢህአዴግ እንደተለመደው “የተለቀቁት ኢትዮጵውያን መሆናቸውን አጣራለሁ” እንደማይል ተገምቷል፡፡ “ተይዘን የነበረው በሊቢያ የኢሚግሬሽን ባለሥልጣናት ነበር” ከተለቀቁት አንዱ ኢትዮጵያዊ፡፡ በተለያዩ የዓለም መገናኛ ብዙሃን ሐሙስ በተሰራጨው የዜና መረጃ መሠረት በሊቢያ ደርና እና ምስራታ በተባሉ ከተሞች ታፍነው የነበሩ 30 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን በግብጽ ጦር ኃይል እና በሊቢያ ድጋፍ ነጻ መለቀቃቸው ተሰምቷል፡፡ ዜናውን ከካይሮ አውሮፕላን ማረፊያ የግብጽ የዜና አውታሮች በቀጥታ ለአገራቸውና ለዓለም ሕዝብ እንዲሰራጭ አድርገውታል፡፡ … [Read more...] about ምርጫው አዲስ “ጠቅላይ ሚ/ር” አግኝቷል










