ረቡዕ መስከረም 8፤2006ዓም ልክ በ6፡08 ሰዓት ላይ በኤርትራ የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱን CMI የተሰኘው የጣሊያን ዜና ወኪል አስታውቋል፡፡ በተለያዩ የዓለም ተቋማት የተገኘው መረጃ እንደሚያብራራው የመሬት መንቀጥቀጡ የተነሳው ከምጽዋ ጥቂት ኪሎሜትሮች ወጣ በማለት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ መጠኑ 5.0 ነው የተባለለት የመሬት መንቀጥቀጥ 18ሺህ ሕዝብ በሚኖርባት ምጽዋም ሆነ ባካባቢው ያደረሰውን ጉዳት ለማወቅ በቂ መረጃ እንደሌለ የዜና ወኪሉ ጠቁሟል፡፡ የመሬት መንቀጥቀጡ በሱዳን መሰማቱንም የሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል፡፡ በተመሳሳይ ሰዓት አካባቢ መድረሱ የጠቆመው ዜና የሱዳን ከርሰ ምድር ጥናት ማዕከል 5.9 መጠን ያለው ስለመሆኑ የሰጠውን ማስረጃ በማከል አቅርቧል፡፡ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር የመሬት መንቀጥቀጥ መድረሱንና ሰዓቱ ከመግለጽ በስተቀር ስለደረሰው ጉዳት የሰጠው መግለጫ … [Read more...] about ከፍተኛ መሬት መንቀጥቀጥ በኤርትራ ተከሰተ
News
ዜና
“የበሰበሱት” ህወሃት እና ሻዕቢያ
አምባገነነኖች ከሚታወቁበት አንዱና ዋንኛ መለያቸው መካከል ሁለተኛ ሰው አለማዘጋጀታቸው ነው። አቶ መለስ በድንገት ሲስፈነጠሩ በውል የታየው አስከሬን ደብቆ ድብብቆሽም የዚሁ ውጤት ነው። ኢሳያስ ከስልጣን ቢወገዱ ማን ይተካቸዋል? የሚለው ችግርም ጎልቶ የሚታየው ከዚሁ የአምባገነኖች በሽታ አንጻር ነው። ግጭትና ችግር ከመፈጠሩ በፊት የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ደወል የሚያንጫርረው ዓለምአቀፉ የግጭት ቡድን (International Crisis Group) ፍርሃቻም ከዚሁ የመነጨ ይመስላል። በኤርትራ ህዝቡ በቃኝ ወደ ማለቱ ደረጃ መቃረቡን የሚጠቁመው የዘንድሮው ዓመት ሪፖርት ኤርትራ በቅርቡ መንግስት አልባ የመሆን እድሏ ሰፊ እንደሆነ ያወሳል። በቅርቡ "የሚከሽፉ መንግስታት" በሚል ስማቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ አገሮች መካከል ኢትዮጵያም ተመልክታለች። እኩል ወደ ስልጣን የመጡት ሻዕቢያና ወያኔ … [Read more...] about “የበሰበሱት” ህወሃት እና ሻዕቢያ
በ2005 እንዲህ ብለን ነበር!
በአዲሱ ዓመት የተመሰረትንበትን አንደኛ ዓመታችንን ምክንያት በማድረግ በተለያዩ ወቅቶች ለንባብ ካበቃናቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል መርጠን ለትውስታ አቅርበናል። ካቀረብናቸውም ሆነ በድረገጹ ላይ ያሉትን ጽሁፎች በመምረጥና በማሰራጨት ልደታችንን ታከብሩልን ዘንድ ግብዣችን ነው። በሌላ በኩል የዝግጅት ክፍላችን ኤዲሪቶሪያል ቦርድ አንባቢዎች በነጻነት አስተያየት እንዲሰጡ፣ አስተያየታቸውም ያለ አንዳች ገደብ እንዲታተም ወስኗል። በመሆኑም ጎልጉልን አስመልክቶም ሆነ በርዕሰ አንቀጽ ላይ ባስቀመጥነው ሃሳብ ላይ በመንተራስ አስተያየት ለምትልኩ "ከስድብና ከዘለፋ" ውጪ በደስታ የሚስተናገድ እንደሆነ አስቀድመን እንገልጻለን። የዓመቱ ምርጥ በማለት "መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ" እና "ጥቁሩ ሰው ይናገራል" የሚሉትን ቃለ ምልለስሶች በስጦታ አቅርበናል። መልካም አዲስ ዓመት፣ ለኛም መልካም አንደኛ … [Read more...] about በ2005 እንዲህ ብለን ነበር!
አዜብ መስፍን ይታሰራሉ?
መለስ ዜናዊ ሆን ብለው ለፖለቲካ ሚዛን መጠበቂያ ሲገለገሉበት በነበረው "የሙስና ባህር" ያልተነከረበት የለም። ባህሩ ውስጥ ያልዋኘ የለም። ከባህሩ ራሳቸውን ያገለሉ ጥቂቶች ቢኖሩም ወ/ሮ አዜብ መስፍን ግን የባህሩ ዋናው አጥማቂና የውሃው ባለቤት እንደሆኑ በርካታ ምስክሮች አሉ። አቶ መለስ "ውርሳቸውን/ሌጋሲያቸውን" ትተው ካለፉ በኋላ አገሩን አከርፍቶት የነበረው የሙስና ባህር በስንጥር መነካካት ተጀመረና አሁን ቁንጮዎቹ ግድም ደርሶ እያሸበረ ነው። ይህንኑ የሙስና ማዕበል ተከትሎ የባለቤታቸውን ውርስ ታኮ ያደረጉት ወ/ሮ አዜብና በተሸናፊው የፖለቲካ መስመር ያሉ ሁሉ ተሸብረዋል። አንዳንድ ጥቆማዎችና የህዝብ አስተያየቶች እንደሚያመለክቱት ወ/ሮ አዜብ ታውከዋል። ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ሃላፊዎችና ከነሱ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ከዋሉት "ባለሃብቶች" መካከል ከወ/ሮ አዜብ … [Read more...] about አዜብ መስፍን ይታሰራሉ?
የኢትዮጵያ መንግሥት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ጥቃት አላደረስኩም ሲል ካደ
በሳምንቱ መጨረሻ ላይ 100 የሚጠጉ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እንደታሰሩና አንዳንዶቹም ክፉኛ እንደተደበደቡ ፓርቲው ገለጸ:: እሁድ ሊካሄድ ለነበረው ሰላማዊ ሰልፍ የተዘጋጁ የድምጽ መሣሪያዎች እንደተወሰዱባቸውና ሰልፉም እንዳይካሄድ እንደተደረገ የፓርቲው ሊቀመንበር ይልቃል ጌታቸው አስታውቀዋል:: የመንግሥት መገናኛ ሚ/ር ሽመልስ ከማል ድርጊቱ አልተፈጸመም ሲሉ የካዱ ሲሆን መንገዱ አክራሪነትን ለመቃወም መንግስት ለጠራው ትዕይንተ ሕዝብ አስቀድሞ ተይዞ እንደነበር መንግሥት አስታውቆዋል:: ኢትዮጵያን የሚገዛው ኢህአዴግ የሕዝቡን ህይወት በተመለከተ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርግ ይታወቃል:: ሰማያዊ ፓርቲ በሰኔ ወር የጠራው ህዝባዊ ተቃውሞ በ1997 ከተደረገውና የመቶዎች ህይወት ከቀጠፈው ሰላማዊ ትዕይንተ ሕዝብ በኋላ የተደረገ የመጀመሪያው ነበር:: ያለፈው ተቃውሞው የመብት ተሟጋቾችና … [Read more...] about የኢትዮጵያ መንግሥት በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ጥቃት አላደረስኩም ሲል ካደ
ካሩቱሪ በኪሳራ ለ“በቃኝ” እያቅማማ ነው!
የኢትዮጵያን ለም መሬት ከተቀራመቱት ኢንቨስተሮች መካካል አንዱ የሆነው የህንዱ ካሩቱሪ ከኢትዮጵያ ለቅቆ የሚወጣበት ጊዜ መቃረቡን ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ክፍሎች ለጎልጉል አስታወቁ። አበዳሪዎችና ባለ አክሲዮኖች ፊታቸውን እንዳዞሩበትም ታውቋል። ከዚህ በተጨማሪም በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ባዶ ዋይታ የሚያሰማው ኢህአዴግ የያዘው አዲስ አቋም ድርጅቱንና ከድርጅቱ ጋር የቀረበ ግንኙነት አላቸው የሚባሉትን ሃሳብ ላይ ጥሏል። በምናምንቴ ዋጋ የኢትዮጵያ ድንግል መሬት ባለቤት የሆነው ካሩቱሪ ለጊዜው በገንዘብ ሊተመን የማይችል የተፈጥሮ ደን ሲያወድም የከለከለው አልነበረም። ለጊዜው ማልማት ከሚችለው አቅም በላይ መሬት ወስዶ የተፈጥሮ ደን የጨፈጨፈው ካሩቱሪ ተቃውሞ የገጠመው ገና ከጅምሩ ነበር። በቦታው ሆነው መረጃ ሲያቀብሉ የነበሩ ወገኖችና ለድርጅቱ ቅርብ የሆኑ እንደሚሉት በጋምቤላ መሬት … [Read more...] about ካሩቱሪ በኪሳራ ለ“በቃኝ” እያቅማማ ነው!
በሰሜን ኮሪያ የደናግላት ቁጥር መመናመን ፕሬዚዳንቱን አሳስቧል!
ወጣቱ የሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ እን ለሚያካሂዱት የዳንስ ስኳድ በቂ ደናግልት ለማግኘት መቸገራቸውን የደቡብ ኮሪያ ዜና ቾሱን ኢልቦ ገለጸ፡፡ ሰሜን ኮሪያ ለፕሬዚዳንቷ ክብር የምትጠቀምባቸው ዳንሰኞች የሚውጣጡት ከደናግልት ሴቶች ነው፡፡ ለዚህ ፕሬዚዳንቱን ለማዝናናት የሚደረገው የዳንስና ሙዚቃ ሙያ አባል ለመሆን የሚችሉ ድንግል ሴቶች በአብዛኛው ወጣቶችና የኮሌጅ ተማሪዎች እንደሆኑ ተዘግቧል፡፡ ክብረንጽህናን መጠበቅም ዋንኛው ቅድመ ሁኔታ ነው፡፡ ሆኖም ሰሜን ኮሪያ ካለባት ከፍተኛ የኢኮኖሚ ችግር ባሻገር አሜሪካንን ጨምሮ ምዕራባውያን በጣሉባት የኢኮኖሚ ማዕቀብ የአገሪቱን ኢኮኖሚ አሽመድምዶታል፡፡ በመሆኑም ሴቶች የትምህርት ወጪያቸውን ለመደጎም እንዲሁም የኑሮውን ውድነት ለመቋቋም በሴተኛ አዳሪነት በመሰማራታቸው የደናግልቱ ቁጥር ባልተጠበቀ ሁኔታ ለማሽቆልቆሉ እንደ ምክንያት … [Read more...] about በሰሜን ኮሪያ የደናግላት ቁጥር መመናመን ፕሬዚዳንቱን አሳስቧል!
ከእሁድ እስከ እሁድ
ነዋሪዎች በውሃ እጦት ተሰቃየን አሉ በሳምንት አንድ ቀን ውሃ ማግኘት ብርቅ የሆነባቸው ሰፈሮች፣ በውሃ እጦት አካባቢያቸውን በመጥፎ ጠረን የሚበክሉ የኮንዶሚኒየም መኖሪያዎች፣ ለተደጋጋሚ አቤቱታ ምላሽ ሳያገኙ በርካታ ወራት እየተቆጠሩ የሚማረሩ ነዋሪዎች የአዲስ አበባ የዘመኑ ገጽታ ሆነዋል፡፡ በቂ ውሃ ስለሌለ በራሽን ለማከፋፈል እየሞከረ መሆኑን የሚልፀው የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በበኩሉ፤ የኤሌክትሪክ መቆራረጥና የአንዳንድ ሰራተኞች እንዝህላልነት፣ ለመንገድ ግንባታ የሚቆፈሩ ቧንቧዎች እንዲሁም በከንቱ የሚባክን ውሃ መብዛቱ የውሃ እጥረትን እንዳባባሱ ይናገራል፡፡ የአገሪቱ እንዲሁም የአህጉሪቱ መዲና በሆነችው ከተማ፣ ለዚያውም በሰለጠነ ዘመን በርካታ ነዋሪዎች የዝናብ ውሃን ደቅኖ ለማጠራቀም ሲሯሯጡና በጀሪካን ተሸክመው ውሃ ሲያመላልሱና የፎቅ ደረጃዎችን ለመውጣት ሲውተረተሩ ማየት … [Read more...] about ከእሁድ እስከ እሁድ
ዋስትናችን እርቅ ብቻ ነው!
እሳት ሲነሳ የመጀመሪያው ተግባር እሳቱን በፍጥነት ማጥፋት ለሚችለው የእሳት አደጋ ብርጌድ መደወል ሲሆን፣ ቀጣዩ ተግባር እሳቱ በተነሳበት አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ነፍስ አትርፈው እሳቱን በተገኘው መንገድ ለማጥፋት መረባረብ ነው። ይህ የተለመደው ተግባር ዛሬ በኢትዮጵያ ስለመስራቱ የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ ዋና ዳይሬክትር ስጋት አላቸው። እናም "እኛ የእሳት አደጋ ብርጌድ የለንምና ዋ!!” የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል ጥሪ ያሰማሉ። "አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ እሳቱ ፊትና መልክ ይዞ ሲቀጣጠል አላነውም እንጂ በርካታ የማቀጣጠያ ቅመሞች ተዘጋጅተውለት ለመንደድ በዝግጅት ላይ ነው። መንደዱ የማይቀረው ይህ እሳት ቢነሳ የሚያጠፋው የለም" የሚሉት አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ ጥላቻው በሰፈር ደረጃ ከርሯል ይላሉ። በየመንደሩ ህዝብ እንዲቧደን ተደርጓል። ሚና ለይቷል። አገር የሚመራው … [Read more...] about ዋስትናችን እርቅ ብቻ ነው!
ሌሊሴ ተፈታች! ቀጥሎስ?
ላለፉት 5 ዓመታት ያህል ከልጆቿና ባለቤቷ ተለይታ በእስር ስትማቅቅ የነበረችው ሌሊሴ ወዳጆ መፈታቷ በርካታ ኢትዮጵያውያንን ማስደሰቱ ተጠቆመ፡፡ የጋዜጠኛ ሌሊሴን መፈታት አስመልክቶ Ayyaantuu News Online ለንባብ ባበቃው ዜና እንዳመለከተው በስደት አውስትራሊያ ከሚኖረው ከባለቤቷና ከልጆቿ ጋር ተቀላቅላለች፤ ድረገጹ ዜናውን በምስል በማስደገፍም አቅርቦታል፡፡ በጋዜጠኝነት ሲያገለግል የነበረው ባለቤቷ ዳቢሣ ዋቅጂራ አገር ጥሎ መሰደዱን ተከትሎ በማታውቀው ምክንያት የኦነግ አባል ነሽ በማለት ኢህአዴግ 10ዓመት ያለ አመክሮ ፈርዶ ወኽኒ እንዳወረዳት ይታወሳል፡፡ ይህንን ህዝብን ያበሳጨና ያስቆጣ ጉዳይ ሌሊሴ ከታሰረችበት ጊዜ ጀምሮ አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ዓለምአቀፉ የጋዜጠኞች መብት ጥበቃ ድርጅት (CPJ) ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ሲያወግዙትና እንድትፈታ ሲሟገቱ መቆየታቸው … [Read more...] about ሌሊሴ ተፈታች! ቀጥሎስ?










