“የደረሰብኝን ስቃይ ለማንም ብናገር ቤተሰቦቼን በሙሉ እንደሚፈጁ አስጠንቅቀውኛል” ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ በዝዋይ እስር ቤት ለወራት ስቃይ የተፈፀመበት ወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ይባላል፤ አርሲ አርባ ጉጉ ተወልዶ አዳማ/ናዝሬት አድጎ፣ በ1998 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሶሲዮሎጂ ተመርቋል፡፡ በ2000 ዓ.ም በባህልና ቱሪዝም ሚ/ር በሲኒየር ካልቸራል ኤክስፐርትነት የስራ መደብ እስከ ሚያዝያ 2003 ሰርቷል፡፡ ሚያዝያ 12 ቀን 2003 ዓ.ም በግልፅ ባልተረዳው ምክንያት የመንግስት ደህንነት ሀይሎች ተያዞ ለ23 ወር በዝዋይ እስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየተፈፀመበት መቆየቱን ይናገራል፡፡ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም ከእስራት ሲለቀቅም አንድ ጊዜም እንኳን ፍርድ ቤት እንዳልቀረበ ለፍኖተ ነፃነት አስረድቷል፡፡ ከወጣት ተስፋዬ ተካልኝ መኮንን ጋር ያደረግነውን ቆይታ … [Read more...] about “ምስጢር ካወጣህ ቤተሰቦችህን እንፈጃቸዋለን”
Interviews
እናውጋ
“ፍትሕ ሁሉን አቀፍ የሆነ መብት ነው”
ዶ/ር ያዕቆብ ኃይለ ማርያም 50ኛ ዓመቱን ለማክበር በዝግጅት ላይ የሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የመጀመርያ ዙር ተመራቂ ናቸው፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን አሜሪካ ከሚገኘው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ያገኙ ሲሆን፣ የፒኤችዲ ዲግሪም ያገኙት እዚያው አሜሪካ ነው፡፡ ዶ/ር ያዕቆብ በቀይ ሽብር ምክንያት ከአገር ከመሰደዳቸው በፊት በሕግ አማካሪነትና በጠበቃነት ያገለገሉ ሲሆን፣ በአሜሪካ ከ20 ዓመታት በላይ በማስተማር ሥራ ላይ ተሰማርተው ቆይተዋል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ፍርድ ቤት ሩዋንዳ ውስጥ በዓቃቤ ሕግነት ለሦስት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ወደ ማስተማር ሥራቸው ተመልሰው ለሁለት ዓመታት ከቆዩ በኋላ በተመድ ግብዣ በናይጄሪያና በካሜሩን መካከል የነበረውን የወሰን ክርክር ለማየት ተቀጥረው ለሁለት ዓመታት ያህል አገልግለዋል፡፡ በአብዛኛው በሰው … [Read more...] about “ፍትሕ ሁሉን አቀፍ የሆነ መብት ነው”
“መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”
ይህንን ቃለምልልስ ያደረግነው ለበርካታ ዓመታት ለኢህአዴግ ሲሰራ ከነበረና በአሁኑ ወቅት ለከፍተኛ ትምህርት ውጪ አገር ከሚገኝ ኢትዮጵያዊ ጋር ነው፡፡ ለደኅንነት ሲባል ስሙን ከመጥቀስ ተቆጥበናል፡፡ ጎልጉል ፦ የጠ/ሚኒስትር መለስ መታመም ድንገተኛ ነው የሚሉ አሉ፤ አሟሟታቸውም ድንገት ነው የሚሉ አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ አጋጣሚው መልካም እንደሆነ የሚጠቁሙ አሉ አንተ ከየትኛው ወገን ነህ? መልስ፦ ቅድሚያ አቶ መለስ ድንገት አልታመሙም። በሽታቸው የቆየ እንደሆነ ይታወቃል። ምስጢርም አይደለም። ለዚሁ እኮ ነው ቤተ መንግስት ውስጥ በአዋጅ የተፈቀደላቸውን ቤት አሰርተው በቅርብ ርቀት እየተቆጣጠሩ ለመኖር ቅድመ ዝግጅት ሲያደርጉ የነበረው። በዚህ ቢስተካከል ለማለት ነው። መለስ ለኢህአዴግ አጋር ድርጅቶች ሁሉ የጋራ ነጠብ ናቸው። በድልድይም ይመሰላሉ። በኢህአዴግ አባል ድርጅቶች፣ በተለይም … [Read more...] about “መለስ የቆፈሩት ጉድጓድ…”
“የኢህአዴግ ባለስልጣናትን ዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት የማቅረቡ ጉዳይ ከመለስ ሞት ጋር የሚሞት አይሆንም።”
በጀርመን አገር የሚታተመው ጥላ መጽሔት የግንቦት 2005 ዕትም በርካታ ጉዳዮችን በመዳሰስ ለህትመት በቅቷል፡፡ አዘጋጆቹ የላኩልንን ሙሉ የመጽሔቱን ዕትም እዚህ ላይ በመጫን ማንበብ ይቻላል፡፡ በመጽሔቱ ከተካተቱት በርካታ ቁምነገሮች መካከል ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ከመጽሔቱ ዋና ሥራአስኪያጅና ጋዜጠኛ መስፍን አብርሃ ጋር ያደረጉት ቃለምልልስ ይህንን ይመስላል፡፡ አቶ ኦባንግ ሜቶ ይባላሉ።የስቃይ ሰለባ የሆኑና እሳቸው የሚመሩትን ድርጅት ድጋፍ ያገኙ ኢትዮጵያውያን “አባታችን“ ይሏቸዋል። እሳቸው ብዙ ሃላፊነት ያለባቸው ሰው በመሆናቸው ዛሬ አፍሪካ ነገ አውሮፓ ከነገወዲያ አሜሪካ ከዛም ኤሺያ የማይዞሩበት ዓለም የለም።ግን የትም ይሂዱ ሁል ጊዜም በራቸው ለሁሉም ዜጋ ክፍት ነው።የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ወይም አክቲቪስት ናቸው።አሁን አሁን … [Read more...] about “የኢህአዴግ ባለስልጣናትን ዓለምአቀፍ ፍርድ ቤት የማቅረቡ ጉዳይ ከመለስ ሞት ጋር የሚሞት አይሆንም።”
ነጋሶ ሞገቱ ወይስ ተሞገቱ?
“ ... አንተም ሆንክ ማንም ኢትዮጵያዊ ውጪ ያሉትን ጨምሮ ቢደግፉን ደስ ይለናል። በዚህ መንገድ ሂዱ ብለው እንዲጠመዝዙን ግን አንፈልግም። … ሰላማዊ ትግል የምትሉት ለውጥ አያመጣም ይሉናል። እንደዚህ የምትሉ ከሆነ ከፈለጋችሁ ገንዘብ አትርዱን እንላቸዋለን … ኢህአዴግን እንደ መንግስት እውቅና አንሰጠውም" ከዶ/ር ነጋሶ የተመረጡ መልሶች መካከል የተጠቀሱ ናቸው። በዚህና በሌሎች ምክንያቶች ዶ/ር ነጋሶ ሊሞገቱ ሄደው ሞገቱ የሚል ርዕስ ለጽሁፌ መረጥኩ። ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ አንድነትን በመወከል ሬዲዮ ፋና በሚያዘጋጀው የ"ሞጋች" ቃለ ምልልስ ክፍለ ጊዜ ላይ ተገኝተው ነበር። ቃለ ምልልሱ ከመጀመሩ በፊት "ጋዜጠኛው" ፕሮግራሙ ፈረንጆቹ እንደሚሉት "ሃርድ ቶክ አይነት ነው" አለ። ይህን ጊዜ ቀልቤን ሳበኝ። የቢቢሲው የሃርድ ቶክ ክፍለጊዜና የጠያቂው ጠልቆ የመግባት ችሎታ ታየኝና ዶ/ር … [Read more...] about ነጋሶ ሞገቱ ወይስ ተሞገቱ?
“ጥቁሩ ሰው” ይናገራል!
“ጥቁሩ ሰው” ይሉታል። ኢትዮጵያዊያን ለሚያሽከረከራት አስፈሪ ፈተና መፍትሄው ሰብአዊነትን ማስቀደም ብቻ ነው የሚል የጸና እምነት አለው። “ከጎሳ በፊት ሰብዓዊነት” በሚል መሪ ዓላማ ከሚመስሉት ጋር በመሆን ድርጅት አቋቁሞ መሥራት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባከናወናቸው ሥራዎች ከፍተኛ እርካታ እንደሚሰማው ያምናል። ኢትዮጵያዊያን ችግር ደርሶባቸዋል በሚባልበት ሁሉ ቀድሞ ደራሽ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩለታል። በዚህና በሰብዓዊ መብት ጉዳይ በሰራቸው ስራዎቹ ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ደጋፊዎችና አድናቂዎች ለማፍራት ቢችልም “ከጀርባው ድብቅ ዓላማና አጀንዳ አለው፣ ብቻውን ይሮጣል” የሚሉትን ጨምሮ በግል አቋሞቹ ዙሪያ ነቀፌታ የሚሰነዝሩበትም አሉ። የወደፊት ዕቅዱና የሚነቅፉት እንደሚሉት መቼ ፖለቲካ ፓርቲ መስርቶ ይፋ ያደርጋል? በሚሉትና በተመሳሳይ ጉዳዮች ዙሪያ ኦባንግ ሜቶ ከጎልጉል … [Read more...] about “ጥቁሩ ሰው” ይናገራል!
“ገበሬው ነጻ እስካልወጣ ችጋር ይቀጥላል”
ሰማያዊ፡- የሰማያዊ ፓርቲ ምሰሶ የሚባሉ ዋና ዋና የሚያራምዳቸው ፖለቲካዊ አቋሞች ምንድናቸው? ኢ/ር፡ ይልቃል፡- ፖለቲካ በየጊዜው እንደሁኔታው የሚለወጥ& የሚሻሻልና የሚያድግ ቢሆንም! ሰማያዊ ፓርቲ ከአጠቃላይ የኢትዮጵያ ታሪክና ካሉብን ችግሮች በመነሳት ዋና ዋና የምንላቸው ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡- አንደኛ፡- ኢትዮጵያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ አብረው የኖሩ የተለያየ ልማድ& ባህል& ቋንቋ እና እምነት ያላቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የጋራ የወል ስነ-ልቦና አዳብረው በአንድነት የሚኖሩበት አገር ነው ብለን እናምናለን፡፡ ይህም ስለሆነ፡- የኢትዮጵያ ፖለቲካ በመሠረቱ ማተኮርና መነሳት ያለበት ከዜግነት እና ከግለሰብ መብት ላይ መሆን አለበት ብለን እናምናለን፡፡ እነዚህም የዜግነት እና ሰብዓዊ መብቶች እስከተከበሩ ድረስ የማይከበር የመብት ዓይነት የለም! ብሎ ነው … [Read more...] about “ገበሬው ነጻ እስካልወጣ ችጋር ይቀጥላል”
ዳምጠው አየለ “ችግሬ እየተቃለለ ነው” አለ
አርቲስት ዳምጠው አየለ አጋጥሞት የነበረው ችግር በኖርዌይ መንግስት ጉዳዩ የሚመለከታቸው ክፍሎች በኩል እየታየና ወደ መፍትሔ እየቀረበ መሆኑን አስታወቀ። በደረሰበት ያልታሰበ እንግልትና በቤተሰብ ናፍቆት የተነሳ ለጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ቃለ ምልልስ ከሰጠ በኋላ በርካታ ወዳጆቹና አድናቂዎቹ መጨነቃቸውን ያስታወቀው ዳምጠው አየለ፣ "ያጋጠመኝ ችግር መስመር እየያዘ ነው፤ በጥሩ ሁኔታ ላይ እገኛለሁ። ስሜታችሁን ለገለጻችሁልኝ በሙሉ ምስጋናዬ ታላቅ ነው" ሲል መልዕክቱን አስተላልፏል። በወቅቱ ከቤተሰብ የቆየ ፍቅር ጋር ተዳምሮ፣ አጋጣሚው ስላበሳጨው ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት በሰጠው ቃለምልልስ አድናቂዎቹና ወዳጆቹ አዝነው በስልክና በተለያዩ መንገዶች ስለላኩለት ማበረታቻ ምስጋና ያቀረበው ዳምጠው፣ በቅርቡ ለወዳጅ ዘመድና አድናቂዎቹ ሰፊ መልዕክት እንደሚኖረው አመልክቷል። ከቃለ ምልልሱ ዋና … [Read more...] about ዳምጠው አየለ “ችግሬ እየተቃለለ ነው” አለ
የዳምጠው አየለ ጥሪ!!
“ሰው ናፈቀኝ፣ ልጆቼና አገሬ ታወሱኝ፣ ባህሌና ልማዴ የት ገባ….?” የሚሉት የአንድ ስደተኛ ጥያቄዎች ለመቶ አለቃ ዳምጠው አየለ ተረት ሆነውበታል። አርቲስት ዳምጠው አየለ ከሁርሶ የመኮንኖች ማሰልጠና ማዕከል የመኮንንነት ትምህርት ተከታትሏል። ለሰላሳ ሁለት ዓመታት በምድር ጦር የሙዚቀኛ ሻለቃ አገልግሏል። በተለይም በባህላዊና አገር በሚያሞካሹ ዜማዎቹ የሚወደደው ዳምጠው አገሩን፣ ሁለት ልጆቹንና ባለቤቱን ጥሎ በስደት ኖርዌይ ከገባ ሰባት ዓመታት አሳልፏል። የስልሳ ሶስት ዓመቱ ዳምጠው ያጋጠመውን ጊዚያዊ ችግር አስመልክቶ ከጎልጉል የአውሮፓ ዘጋቢ ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል። ዳምጠው ችግር እንዳጋጠመው ሲሰማ አስቸኳይ ድጋፍ ላደረጉ ወገኖች፣ ድርጅቶች፣ ማህበሮች፣ ላደረጋችሁት በአርአያነት የሚጠቀስ ተግባር የዝግጅት ክፍላችን በዚህ አጋጣሚ ለማመስገን ይወዳል። “… አዎ፤ እኔም ራሴን … [Read more...] about የዳምጠው አየለ ጥሪ!!







