• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

በለገደንቢ “ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ”

May 8, 2018 03:42 pm by Editor Leave a Comment

ወ/ሮ ሑጤ ደንቆ የሁለት ልጆቻቸው ሞት እንዲሁም የሴት ልጃቸው አካል መጉደል ካደርሰባቸው የሐዘን ስብራት ጋር በጉጂ ዞን ኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥ ይኖራሉ። እኚህ እናት የመጀመሪያ ልጃቸውን ሁለት እግሯን አልታዘዝ ከማለት በተጨማሪ በኋላ የወለዷቸው ወዲያውኑ እንደተወለዱ ሞተውባቸዋል።

ወ/ሮ ሑጤ ነፍሰጡር በነበሩበት ወቅት ከባድ የጤና እክል አጋጥሟቸው የነበረ ቢሆንም አሁንም የአጥንት ሕመም ህይወታቸውን አቀበት አድርጎባቸዋል።

የእሳቸውን እና የልጆቻቸውን ጤንነት ይከታተሉ የነበሩ የህክምና ባለሙያዎች የእሳቸው አጥንት ህመምም ሆነ የልጃቸው እግር አጥንት መልፈስፈስ ምክንያቱ ከፋብሪካው የሚወጣው መርዛማ ኬሚካል መሆኑን እንደነገሯቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ወ/ሮ ሑቴ የሚኖሩበት ዲባ በቴ ቀበሌ የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር ለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ የሚገኝበት ነው።

“ነፍሰጡር ሴቶች ያስወርዳቸዋል፤ ሕፃናት ሲወለዱ ያለጭንቅላት ይወለዳሉ። ጭንቅላታቸው መጠኑ በጣም ያነሰ ነው። እጅና አይናቸውም ተጎድቶ ይወለዳሉ። ሰው ታሞ ወደ ሐኪም ቤት ሲሄድ ከ’ነርቭ’ ጋር የተያያዘ ችግር ነው ይባላል።” በማለት የቀበሌው ነዋሪ የሆኑት አቶ ዱቤ ጋሸራ ሚጁ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በዚሁ ቀበሌ ተወልደው ያደጉት እኚህ አዛውንት “ድሮ ይህንን የሚመስል ችግር አልነበረም”ይላሉ።

ዓይናቸው ከማምረቻው ውስጥ በሚወጣ ኬሚካል መጎዳቱን እንዲሁም በአግባቡ ቆመው መሄድ እንደሚያቅታቸው ነግረውናል። በተጨማሪም ከዚሁ ችግር የተነሳ በከብቶች እና በዱር እንስሳት እየደረሰ ያለው እልቂት ለትልቅ ችግር አጋልጦናል ይላሉ።

‘ሳናይድ’ እና የአካል ጉዳተኝነት

የሚድሮክ ለገደንቢ የወርቅ ማምረቻ ወርቅና ነሐስ በሚያመርትበት ወቅት ወርቁን ለማፅዳት የሚጠቀምበት ኬሚካል ‘ሳናይድ’ ይባላል።

ይህ ኬሚካል ራስ ምታት፣የልብ፣ የአእምሮ እና የነርቭ ህመሞች እንደሚያስከትል የኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ጦና ዋሬ ነግረውናል።

ከዚህም ባሻገር የሰው አጥንት ለማጠንከር የሚረዱ እንደ ብረት(አይረን) ያሉ ንጥረ ነገሮች ከሰው እና ከእንስሳት አካል ውስጥ መጠኑን ይቀንሳል።

ይህም ለአጥንት መሳሳት እና መሰባበር እንደሚያጋልጥ አቶ ጦና ዋሬ ያስረዳሉ።

የወርቅ ማምረቻው የሚገኝበት ዲባ በቴ ቀበሌ ውስጥም የአካል ጉዳተኝነት ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው።

የቢቢሲ ሪፖርተር በአካል በቀበሌው ተገኝቶ አንድ ኪሎ ሜትር ባልሞላ መንደር ውስጥ ሶስት የአካል ጉዳት ያለባቸው ህፃናትን አይቷል።

በህፃናት ላይ የሚደርሰው የአካል ጉዳት በቀበሌው ውስጥ በፍጥነት እያደገ በመምጣቱ ነዋሪዎች ወልደው ለመሳም እየተሳቀቁ እንደሆነ ይናገራሉ።

ወ/ሮ ደምበሊ ሔጦ የአካል ጉዳት ያለባት ህፃን አላቸው፤ “ልጆቼ በታመሙ ቁጥር ስጋት ያድርብኛል። ሌላ ተጨማሪ ልጅ ለመውለድ እንደዚሁ ልጅ ይሆንብኝ ይሆን ስል እሰጋለሁ” ይላሉ።

በተጨማሪም ነፍሰጡር ሴቶች ልጃቸውን ወልደው ከአካል ጉዳት ነፃ መሆኑን እስኪያረጋግጡ ድረስ ማርገዛቸውን እንደሚደብቁ፣ የአካል ጉዳት ያለበትን ህፃን የወለዱ እናቶችም ከሰው አይን ከልለው በቤት ውስጥ ደብቀው እንደሚያሳድጓቸውም የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።

በተጨማሪም የሳይናይድ ኬሚካል የተቀላቀለበት ወራጅ ውሃ የሚጠጡ እንስሳት ወዲያውኑ እንደሚሞቱ፣ የተበከለ አየር ውስጥ የሚቆዩት ደግሞ ከወደቁ በኋላ መነሳት እንደማይችሉ፣ አጥንታቸውም በቀላሉ እንደሚሰበር የአካባቢው ነዋሪዎች ያስረዳሉ።

የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች

የፋብሪካው የጥበቃ ሰራተኞች በህብረተሰቡ ላይ ልዩ ልዩ ችግሮችን እንደሚያደርሱ ቅሬታዎች ይሰማሉ። ይህንን ቅሬታ ነዋሪዎች ብቻ ሳይሆኑ የወረዳው አስተዳደር ሰራተኞችም ይጋሩታል።

ለፋብሪካው ከሚደረገው ከፍተኛ ጥበቃ የተነሳ መንግስት በሰጣቸው ኃላፊነት ተጠቅመው በፋብሪካው ውስጥ ገብተው የቁጥጥር እና ክትትል ስራ ማድረግ እንዳልቻሉ የኦዶ ሻኪሶ ወረዳ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ቦሬ ጦና ይናገራሉ።

ሰራተኞችንም በሚቀጥሩበት ወቅት ህጉ በሚያዘው መሰረት እንደማያሳትፏቸወው ከድርጅቱ የሚያገኙት ምላሽም “እኛ በእናንተ ሳእሆን በፌደራል መንግስት ነው የምንመራው” የሚል እንደሆነም ይናገራሉ።

የስራ እድል ማግኘትን ጨምሮ በወረዳው ውስጥ ከሚገኙ የማእድን አምራች ድርጅቶች ጥቅም እያገኘን አይደለም፤ ከዚህም አልፎ ችግር እየደረሰብን ነው በማለት የወረዳው ነዋሪዎች በተለያየ ጊዜ ሰልፍ ወጥተዋል።

ምላሽ

የአካባቢውን ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት ቅሬታ መልስ ለማግኘት ወደ ማእድን ማምረቻው በሄድንበት ወቅት የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠት መልስ የሚሰጡን የስራ ኃላፊዎች እንደሌሉ ነግረውናል።

ነገር ግን ይህ ፅሁፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ከወጣ በኋላ ሚድሮክ ለቢቢሲ በፃፈው ደብዳቤ ጉዳቱን አላደረስኩም ብሏል።

የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር የለገደንቢ ወርቅ ማምረቻ ሳናይድ የተባለው ኬሚካል በሕዝብና በአካባቢ ላይ ጉዳት አለማድረሱን በደብዳቤው ገልጿል።

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን አዶ ሻኪሶ ወርቅ በማምረት የተሰማራው ይህ ኩባንያ አካባቢውን በጠበቀና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ እየሰሩ መሆኑንም ጭምር ገልፀዋል።

“በአካባቢ ላይም ሆነ በሰዎች ላይ ከኬሚካል ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ችግር የለም” ብሏል።

ሚድሮክ በአካባቢው የተባሉት ችግሮች ተከስተው ቢሆን ኖሮ የሚያውቅበትም ዕድል እንደነበር ገልፆ የአካባቢን ጉዳዮች ለመከታተል ራሱን የቻለ ክፍል እንዳቋቋሙ ጠቁሟል።

ከዚህም በተጨማሪ በአዶ ሻኪሶ አካባቢ በማዕድን ማውጣት ስራ ላይ የተሰማራው ሚድሮክ ወርቅ ኩባንያ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ኩባንያዎች በአካባቢው በመኖራቸው ከኬሚካል ጋር ተያይዞ ደረሰ የተባለው ጉዳት በእርግጥ ከሚድሮክ ጋር ብቻ የተያያዘ ስለመሆኑ ማረጋጋጫ የለም ብለዋል።

ሚድሮክ በአካባቢው ልማት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያደረገ መሆኑን ገልጾ፤ ትምህርትቤቶች፣የጤና ኬላዎች፣ የመንገድ ግንባታ ላይ በመሳተፍ ለብዙ ሰዎችም የስራ ዕድል እንደፈጠሩ አስታውቋል።

በማእድን ነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር የአካባቢ እና የማህበረሰብ ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሆኑት ወ/ሮ እናት ፋንታ ግን “እስከ መጋቢት 2009 ዓ.ም ባደረግነው ክትትልና ቁጥጥር መሰረት በኬሚካል የደረሰ ጉዳት አላየንም፤ ከማህበረሰቡም ሆነ ከመንግስት አካል የደረሰንም ቅሬታ የለም” በማለት ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የማዕድን፣ነዳጅ እና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስትሩ አቶ ሞቱማ መቃሳ ግን በሚድሮክ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችችን ለመፍታት ድርጅቱ ከመንግሥት ጋር መስራት አለበት።

ኬሚካል እና ሌሎች ጉዳዮችን በተመለከተ እየደረሰ ያለው ጉዳትም በ አስቸኳይ በገለልተኛ አካል መጣራት አለበት እንዳሉ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዘግቧል።

ይሁን እንጂ ጥያቄው የወርቅ ምርቱ ተጠቃሚነት ሳይሆን በህይወት የመቆየት ስጋት የሆነባቸው የዲባ ባቴ ነዋሪዎች “ከመንግስት በኩል መፍትሄ እንፈልጋለን” እያሉ ነው።

የሚድሮክ ወርቅ ማዕድን ኃላ.የተ.የግ.ማኅበር በ1989 ዓ.ም የለገደንቢን የወርቅ ማእድን ከመንግስት እጅ በ172 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ለ20 ዓመታት በሊዝ ነበር የተረከበው።

ድርጅቱ በ2014 እኤአ በአለም ባንክ በተዘጋጀው ፎረም ላይ ባቀረበው ሪፖርት መሰረት የሚድሮክ ለገደንቢ የወርቅ ማምረቻ እኤአ ከ 1997-2014 ድረስ ባሉት 16 አመታት 52 0444.71 ኪሎ ግራም ወርቅ እንዲሁም 14 670.6 የብር ማእድን አምርቶ 17.24 ቢሊዮን ብር እንደሸጠ ያሳያል።

ድርጅቱ ለ20 ዓመታት የተፈራረመው ውል አሁን በያዝነው የፈረንጆቹ አመት መጨረሻ የሚጠናቀቅ ሲሆን ስምምነቱ እንዲታደስለት አመልክቷል።

መረጃና ፎቶ ምንጭ፤ ቢቢሲ

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Social Tagged With: Full Width Top, gold, legedenbi, Middle Column, midroc, shakiso, tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule