• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ድንቄም ሀዘን!

March 15, 2017 11:23 pm by Editor 1 Comment

ሲሉ ሰምታ ዶሮ ሞተች ከቋት ገብታ ይሉ ነበር ሳይማሩ የተማሩት ጠቢባን የሆኑ ቀደምት እናትና አባቶቻችን። ድህነት ዛዝላውን ጭኖባቸው የመከራ ኑሮ የነበሩ ወገኖቻችንን መንግስት የቆለለው የቆሻሻ ምርት ተጭኗቸው ሲያልቁ መንግስት የሶስት ቀን ሀዘን ተቀመጠ የሚል አስቂኝ ወሬ በሰማሁ ጊዜ ነበር የጠቀስኩት የዶሮዋ ምሳሌ ትዝ ያለኝ። ሀገር አለን ብለው እንደወግና ስርአታቸው አደባባይ ሊውሉ የወጡ ወገኖቻችንን ባልተደበቀ ሸር በቢሸፍቱ ከተማ እንደወጡ ያስቀረው መንግስት በወቅቱ የሶስት ቀን ሀዘን በማወጅ በሙታንም ህያዋንም ላይ ቀልዶ ነበር። እነሆ አሁን ደግሞ በከመረው ቆሻሻ ህፃናትና ስቶችን ጨፍልቆ ከፈጀ በኋላ ሳቂታውን ፓርላማ ሰብስቦ በሉ አሁን ደግሞ የሀዘን ሰአት ነው አለ አሉ። እንዴት ያለ ቀልደኛ መንግስት ነው ጃል? ለገደለው ህዝብ ሆዱ የሚባባ ሩሩህ መንግስት! የዚህ አይነቱ ቀልድስ የሚያበቃው የት ላይ ይሆን?

በመሰረቱ የአንድ ከተማ አስተዳደር ሀላፊነት ቆሻሻ መቆለል ሳይሆን ከተማውን ማፅዳትና ህዝብንም ከበሽታ መከላከል አልነበረም? ከዚህ ቀደም የአፍሪካ መዲና የሆነችውን ታላቅ ከተማ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በማቆሸሽ ህዝብ ባ ባጣዳፊ ተቅማጥና ሁከት ማለቅ ሲጀምር “እጃችሁን ታጠቡ” ሲል የአንደኛ ክፍል የሳይንስ መፅሃፍን  በማጣቀስ ያላቅሙ የሚያስተዳድረውን ህዝብ ሲመክር ያልገረመው አልነበረም። ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ። በከተማ ንፅህና ጉድለት የመጣውን ችግር እጃችሁን ሳትታጠቡ እየበላችሁ በሽታ አመጣችሁብን ሲል እንደልማዱ ለህዝብ ያለውን ንቀት ደገመው። ምን ደገመው ብቻ ደጋገመው ልበል እንጂ።

ነገሩማ የተባለውን ቀርቶ መስማት የሚፈልገውን ብቻ የሚሰማ መንግስት የህዝብን ችግር በበትክክለኛ ስሙ እንዲጠራ እንዴት መጠበቅ ይቻላል? ነፃነት አጣን ሲባል ስራ አጣን ነው ያላችሁኝ ይልና ስራ እንደሚያመጣ ሁሉ ወደጓዳ ገብቶ ጠመንጃ ይዞ ይመጣል። ስኳር ጠፋ ሲባል እኔ ስልጣን ከያዝኩ ጀምሮ ገበሬው ስኳር መጠጣት ስለጀመረ ነው አለ። ኧረ መብራት ተቸገርን ሲባል ምንላድርግ ልማቱ እኮ ነው ሲል አስረዳ። ሰብዓዊ መብት ለምን ይረገጣል ሲባል በህግ የበላይነት የሚያምንና ሃላፊነት የሚሰማው መንግስት ስላለን እኮ ነው ሲል አስተማረን። እንዴት ያለ ጉድ እኮ ነው ጎበዝ!

ከተነሳሁበት ነጥብ ወጣሁ መሰለኝ፤ የክምር ቆሻሻው ጉዳይ። መከራ በተጫነው ህዝብ ላይ ቆሻሻ ጭኖ ከገደሉ በኋላ ባንዲራ ማውረድና ሀዘን ማወጅ የቀበሮ ባህታዊነት ይመስለኛል። ሃላፊነት የሚሰማው መንግስት ተግባር ሰው እንዳይሞት መጠበቅ እንጂ ገድሎ ማጠን አይደለም። በዚህ ክስተት መንግስት ማዘን ሳይሆን ማፈር አለበት። ያውስ ሃፍረት የባህሪው ከሆነ አይደል? ጎበዝ ማለት ለጥፋቱ ሀላፊነት ወስዶ ይቅርታ መጠየቅና ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ሙሰኛ ተሿሚዎቹን መቅጣት ነው። ብቻ ይኅስ ቢሆን ለመገዛት እንጂ ገዢዎቹን በህግ ለመጠየቅ የታደለ ህዝብ በሌለበት ሀገር እንዴት ይታሰባል። እና እባካችሁ እንደፈረደብን ዝም ብለን እንሙትበት፤ እየሳቃችሁ አትዘኑልን በሏቸው። ጥያቄም አለኝ፤ ሀገር መምራቱስ ቢቀር፣  ቤት ጠርጎ መኖር እንኳን እንዴት ተሳናችሁ የሚል። የወገኖቻችንን ነፍስ ይማር።

ህሩይ ደምሴ (zobar2006@gmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. Tadesse says

    March 19, 2017 12:22 am at 12:22 am

    ewnet gud new,asafari, new,hezbun cheresut tegrewm sayker.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule