• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሃት በሕዝብ ላይ የደገሰው በዶ/ር ደብረጽዮን አንደበት

August 20, 2016 09:54 am by Editor 1 Comment

ባለፈው ሳምንት ጌታቸው ረዳ ከአልጃዚራ ቴሌቭዥን ጋዜጠኛ ጋር ተጋፍጦ ነበር። አንድ ጥያቄ ቀረበለት። “በራሳችሁ የምትተማማኑ ከሆነ ለምን የተባበሩት መንግስታት ታዛቢዎች እንዳይገቡ ከለከላችሁ?”

ሚኒስትር ጌታቸውም። “የተባበሩት መንግስታት አያስፈልገንም። እኛው ራሳችን ከህዝቡ ጋር እንነጋገራለን።” ሲል ነበር የድፍረት መልስ የሰጠው።

ይህ የትእቢት መልስ ለጋዜጠኛዋ እንግዳ አይሆንም፣  ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ግልጽ ነበር። እነሆ ከህዝብ ጋር ንግግር  መጀመራቸውን እያሳዩን ነው።  እንደ ፋሺሽት ጣልያን በከባድ መሳርያ ሕዝብን ለመደብደብ ቆርጠው መነሳታቸውን ተመልከቱ።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነት ማእረግ ሃገሪቱን የጠቆጣጠሩት ዶ/ር ደብረጽዮን በዛሬው እለት በፌስቡክ ገጻቸው ላይ አንድ የጦር አዋጅ አስነብበውናል። በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የታወጀ ጦርነት። የጦርነት መግለጫው እንዲህ ይነበባል፤

“ጀግናው የመከላከያ ሠራዊታችን የሀገራችንን ሰላም ለማረጋገጥ ከመቸውም ጊዜ በላይ በነቃ እና በተጠናከረ ሁኔታ በመንቀሳቀስ፤ በቅርቡ በሃገራችን የተከሰቱ አመፆችን ስልታዊ በሆነ መልኩ ሥርዓት በማስያዝ ላይ ይገኛል። በየክልሉ የሚነሡ ረብሻዎችን ሰበብ በማድረግ በአንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ ጥቃት በመካሄድ ላይ ይገኛል። በተለይም ብጥብጡ ከበረታባቸው አካባቢዎች የጎንደር ነውጥ በጉልህ የሚጠቀስ ሲሆን ሠራዊታችን ከነውጠኞች ጋር ያደረገውን ፍልሚያ በጀግንነት እየተወጣ ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ አመፅ ፈጣሪ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት የጦር መሣርያ የማስፈታቱ ሂደት የመንግሥት የቅርብ የቤት ሥራ ይሆናል። እንደዚህ ዓይነት ሥርዓት አልበኝነትን የማክሸፉ ሂደት በተጠናከረ ሁኔታ የሚቀጥል ነው የሚሆነው። ድል ለመከላከያ ሠራዊታችን!”

የዚህ “አዋጅ” ትርጉም ግልጽ ነው። የሕዝብን ጥያቄ በመሳሪያ ለመስበር ከመቸውም ጊዜ በላይ መነሳታቸውን ነው ደብረጽዮን ያሳወቁን። በአጭሩ ለአራትና አምስት ሰዎች ደህንነት ሲባል በመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ጦርነት ለመግጠም የተሰጠ መግለጫ ነው።

ከዚህ ቀደም ውስጥ ለውስጥ ይናገሩት የነበረውን ምስጢራቸውን አሁን በይፋ በአደባባይ መናገር መፈለጋቸው አንድ ከበድ ያለ ችግር ውስጥ እንዳሉ ያሳየናል። እንዲህ አይነት ድፍረት የተሞላበት ንግግር በአደባባይ ወጥተው የመናገራቸው ምክንያትም ምስጢር አይደለም። የህወሃት የውስጥ ምስጢሮች ሁሉ በራሳቸው ሰዎች እየሾለኩ ወደ መገናኛ ብዙሃን መድረሳቸው ይመስላል ለእንዲህ አይነት ንቀት እና ድፍረት ያበቃቸው።

የፌስቡኩ ሚንስትር ቴድሮስ አድሃኖምም ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ የጦር አዋጅ አሰምቶን ነበር፤ tedros a voa

“… ይህንን ምክንያት በማድረግ የሚነሡ ረብሻዎችን መንግሥት ለመታገስ የሚቸገር በመሆኑ ሕግ የማስከበር ኃላፊነቶቹን በመወጣት ላይ ይገኛል። ነፍጠኛ አመለካከት ባላቸው ኃይሎች የሚነሣ አመጽ ምንጊዜም ቢሆን መድረሻው ከሁለትና ሦስት ቀን ያልበለጠ ግርግርና ረብሻ ነው። … በመሆኑም መንግሥታችን ነፍጠኝነትን ለአንዴና ለመጨረሻ ከሀገሪቱ ለማጥፋት በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል”።

ልብ በሉ ሕዝባዊ አመጹ እየተካሄደ ያለው በመላው ኢትዮጵያ ነው።  እነዚህ  የህወሃት ሚኒስትሮች እየነገሩን ያለው ደግሞ ይህንን ህዝብ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ግዜ እንደመስሰዋለን  ነው።

እነዚህን ጠባቦች እንደ መንግስት ለሚመለከቱት ሁሉ ጄኔራል ፃድቃን ገብረተንሳይ መልስ የሰጠ ይመስለኛል። በቅርቡ በኢንተርነት በለቀቀው ጽሁፍ ጄኔራል ፃድቃን እንዲህ ብሎናል።

“… በርከት ባሉ የትግራይ ተወላጆች የሚነሳ አንድ ጥያቄ አለ። ይኸውም አሁን ባለው መንግስት ላይ ያለንን “የበላይነት” ካጣን ጠቅላላ መብቶቻችን አንድናጣ መልሰን እንድንጨቆን አድልዎ እንዲፈፀምብን ቢደረግስ ምን ዋስትና አለን? የሚል ነው። ዋስትናችን በትግላችን ያገኘነው አሁንም ከሌሎች ህዝቦች ጋር ሆነን እየታገልን የምንጠብቀው ሕገ-መንግስታችን ያለምንም ማቅማማት ተግባራዊ ማድረግ ነው።…”

ሕገ-መንግስታችን የሚሉት ስልጣን ለማለት ነው። የስልጣን ወይም ሞት ምስጢሩም ይህ ነው።

በሕዝብ ላይ ጦርነቱን ጀምረውታል። ውጤቱን ደግሞ በቅርብ የምናየው ይሆናል። ከህዝባቸው ጋር ውግያ ገጥመው የዘለቁ አንባገነኖች ከተፈጠሩ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ይሆናሉ።


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ፡፡ ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Comments

  1. በለው! says

    August 22, 2016 02:03 pm at 2:03 pm

    >>> በደርጉ ዘመን አንድ ቀልድ ነበር የወይዘሮ ውብአንቺ ብሻው ጎረቤት እሳቸውን ሁልጊዜ ቡና ስትጠራ ኮ/ል መንግሥቱ ኀይለማርያምን አትጠራም ውብአንቺ ተቆጭተው “ምነው ባሌን አንድ ቀን እንኳን ኑ ቡና ጠጡ አለማለትሽ? ታዘብኩሽ” ቢሏት እሷም “ጠልቻቸው አደለም ግን ሥማቸውን ከእነሥልጣናቸው እስክጠራ ቡናው እንዳይቀዘቅዝብን ፈርቼ ነው “አለች አሉ

    “Dr. Debretsion Gebremichael, Minister of Communication and Information Technology and coordinator of finance and economic cluster with the rank of deputy prime minister, ”
    በቀጥታ ወደ ገደለው አሉ
    ,*Dr. Debretsion commented “If the wolkait issue was a question of identity, it would have been raised by the people of Wolkait themselves in Wolkait, not in Gondar”
    —– ክልል ለከብቶች ጋጣ ነው ። አንዱ ለሌላው መብት እንዳይቆም በቋንቋ ፡በነገድ ፡በአመጋገብ ፡በአለባበስ ፡በጫካ ማኒፌስቶ ተብትባችሁት ለእያንዱንዱና ለሁሉም ማን ከማን መግጠም እንዳለበት ቀይ መሥመር ወየናችሁበት አደለም እንዴ ?
    *Debretsion also said that the people of Kimant has raised an identity question themselves and that was handled as per the constitutional procedure. The same goes for Wolkait.

    —- ታዲያ ወልቃይት ለብቻው ሆነ ከጎንደር ገጠመ ችግሩ ያለው ፈጣን ምላሽ በተወካዮቹ አማካኝነት ያላገኙትን ሕጋዊ መብትና የማንነት ጥያቄ የእናቱን ልጅ ተበደልኩ ያልነበርኩትን በግድ መሆን አለብህ ብለው ከማስፈራራት አልፈው ገደሉኝ ጎንደሬ አድነኝ ቢል ክፋቱ ምንድነው ? ህወሓት ለኤርትራውያን ነፃነት የትግራይን ወጣት ለቦንብና አዳፍኔ ማግዶ የለምን ? ዛሬም ትሸጡት የለምን !?

    * Even more “ethnicity is not something we created or strengthened. It was there all along history and the federalism was the only option for our country to continue intact” he added.
    — ብሔር ነበር: አለ: ይኖራልም ! ብሔርተኝነት የወርቅ እና የመዳብ ያደረጋችሁት እናንት ትንሽ ጠባቦች ናችሁ ። ኤርትራን እና ትግራይን በማጥበብ ለትውልዱ ምን አተረፋችሁለት ?የክልላዊ ሕዝብን በዘር ቋንቋ አለባበስና አመጋገብ መመደቡ መታወቂያ መሠጠቱ እራሱን አግልሎ የበይ ተመልካች እንዲሆን እርስ በእርሱ እንዲባላ በጠላችሁት ግዜ ግንባሩና ልቡን በጥይት ለመበተን አደለምን!?

    * According to the deputy premier, “the federalism answered the national question and brought stability for 25 years”
    —- መቼም ድምፅ ማጉሊያ እና ጭብጨባ ለእናንተ ህወሃት/ኢህአዴግ ብቻ ስለሆነ ከመደንዘዝም አልፎ ተባራሪ ጄኔራሎችን ጨምሮ ደንቁራችኋል። ይህ ማዕበል ድሃውን ሳይነካው ትቢተኞችን ያስተንፍስልን! ይህ ከባድ የሕዝብ ንቀትና ትውልዱን ከሰው አለመቁጠር የመነጨ ጉራ ለከት ሊበጅለት ይገባል ።አራት ነጥብ ።
    * He underlined that the Wolkait issue is a political propaganda ploy designed to bring discord between the people of Amhara and Tigray.”
    —- ሕዝብ ለማጫረስ ያሰበ ያሳሰበ ይቀጣል ! ህወሓት /ኢህአዴግ የትግራይን ሕዝብ ለፓለቲካ ፍጆታ ማንቀሳቀሱ ቀድሞ በአውዜን ገበያ ላይ ያደረገውን የትግራይ ሕፃናት እናቶች ዕልቂት ለመድገም ስለሆነ ከተጠያቂነት አያመልጥም ።ለአማራ የጋጣ ክልል ነዋሪ ደህንነት ብአዴን ሙሉ ኀላፊነት ነበረበት ችግሩ በሌላ ክልል አደጋ የደረሰባቸውን አማሮች በአውሮፕላን አደለም በመኪናም በፈረስም አልታደጋቸውም ጭራሽም በሰው ክልል መብት የለንም ሲል የህወሓት መጋዣ አለምነው መኮንን በአፉ ተፀዳዳ ።
    ***** በእኔ ዕምነት ዋናው ወንጀለኞች ለማናቸውም የሰውና የንብረት ጥፋት: ላለፉት 25 ዓመት ለትውልድ መምከን እና መባከን: ለትግራይ ሕዝብ ጠላት ያፈራችሁለት ምንም ለውጥና ሀገራዊ መግባባት ሳትፈጥሩ ፡በብሔር ብሔረሰብ ጭፈራ ፡በአብዮታዊ ዴሞክራሲ ጭልፊት ፡ በሙስና መር ኢኮኖሚ ፡ በዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት እንቁልልጮሽ ፡ የብድርና የልመና ምትሃታዊ ዕድገት:፡ያልተመጣጠነ የሀብትና ውሳኔ አሰጣጥ ፡ ዕንቁላል ዕንቍ በሆነበትና የሀብት ክፍፍሉ በተዛባ ግዜ ” የጠየከውን የብሔር ማንነት ሰጥተንሃልና ዝም ብለህ እንድትኖር ፈቅደንሃል ለሕጋችን (የተገንጣይ ማኒፌስቶ ) ወደህ! አፍቅረህና ፈቅደህ ልትገዛ ተስማምታችኋልና ውልፍት የለም!!
    ሲሉ ጢቅ አሉ ።ደርጎችም ብለው ነበር !።ወሳኙና አዛዥ መሆን ያለበት ሕዝብ እንጂ ፓርቲ አደለም አይሆንም ።አራት ነጥብ።

    “ሰዶ ማሳደድ ሲያምርህ ሀገርህን በክልል ለውጥ ” ያልነው ለዚሁ ነበር ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule