• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የትግላችን መነሻና መዳረሻ ምንድነው?

March 31, 2018 07:41 am by Editor Leave a Comment

ብቅ ብቅ ባለ ሣር የተሳበ በሬ፡አፏን ከከፈተች መሬት ይተርፍ ይሆን!

ለምን ሕዝባዊ ትግል አስፈለገ?መስዋዕትነቱስ የሚከፈለው ምንስ ለመቀዳጀት ይሆን?

ህይወት፤ ዕውቀት፤ጊዜና ገንዘብለሰው ልጅ እጅግ አስፈላጊ ነገሮች ናቸው። የሰው ልጅ እነዚህን መሠረታዊ ሀብቶቹን አሳልፎ መስጠት ካለበት በአንጻሩ ብልጫ ያለው ካልሆነም ተመጣጣኝ የሆነ ምላሽ መሻት ይገባዋል።

ብሶት ብዙ ጊዜ የሚፈጥረው ትግል፤ በአግባቡ ካልተደራጀና ከታች ወደ ላይ ከላይ ወደ ታች በሚንቀሳቀስ አካሄድ ካልተመራ፣ትግሉ ያልተቀነባበረና ግብታዊነት የሰፈነበት ይሆናል።በንቃት የተደራጀ ከሆነ ቀጣዩን ትግል መልክ ለማስያዝ ጠንካራ ድርሻ ይኖረዋል። በዚህ መልክ ትግሉ ከተመራ የሚከፈለው መሰዋዕትነት በዉጤት የጎመራ ይሆናል።

እዚህ ላይ ልናስተውለው የሚገባ ዐብይ ጉዳይ  በተበታተነ መልክ ለሚደረግ ትግል የሚከፈለውመሰዋዕትነት በራሱ ብቃት የሌለው ባዶነው ማለት ሳይሆን፤ለተከታዩ ትግል አስተዋጾ እንዲኖረው በማድረግ በኩል ከፍተኛዉን ሚና መጫወት የሚገባቸዉ አለሁልህ፣መሪህ ነን ፣የሚሉት የፓለቲካ ተዋኒያን የሚጠበቅባቸዉን ማድረግ የተሳናቸዉ መሆኑንነዉ።እንደውም አንዳንዴ አመራር ሰጭ ድርጅቶች ሲታዩ ሌላውን መምራት ቀርቶ እራሳቸውን ለመምራት መሪ የሚያሻቸው ይመስላሉ።

ይህን ለማለት የገፋፋኝ ዐላማን፤ጽኑ እምነትንና ራዕይን ሰንቆ አመራር መሰጠት የሚችል ድርጅት እና የዚሁ ድርጅት አካል የሆኑት የፖለቲካ ተዋንያን ሀላፊነታቸውን ለመወጣት ያላቸዉ ብቃትና ዝግጁነት ጥያቄ ዉስጥ በመግባቱ ነዉ። ይህም ሆኖ፣

የኢትዮጵያ ህዝብ  የሚደረሰበትን እንግልት፤ ግፍና ስቃይ በተናጠልም ሆነ በቡድን እየተቃወመ በሀገሬ ባይተዋርና ሁለተኛ ዜጋ ሆኜ መታየትን አልፈቅድም በማለት ህዝባዊ መስዋዕትነት በመክፈል ላይ ነዉ።

የህዝቡን ትግል እናደራጃለን የሚሉ ድርጅቶች፤ተሞክሮአቸዉ የሚያሳየዉ አብዛኞቹ እንደ ስልት በጋራና በህብረት ትግል  (ሸንጎ፤ ጥምረት፤ የሲያትሉ ትብብር….) የሚያራምዱትም፣ ሆነ በራሳቸዉ የቆሙት ፣ህብረብሔራዊ አጀንዳ ቀርፀዉ ተስማሚ በሆነ ርዮተዓለም ዙርያ ተሰባስበዉ ሲጓዙ አይታይም። እነዚህ በተቃዋሚ ጎራ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች በምን በምን የጋራ መርሃ ግብር አላማናአቋም ነዉ የተሳሰራችሁ? የሚለዉን ጥያቄ ሳያድበሰብሱ መመለስ ይገባቸዋል ።

የኢሕአዴግን ህገ መንስት የተቀበሉና ያልተቀበሉ፣የዘርና ጎሳ ፓለቲካ የተቀበሉና ያልተቀበሉ፣ኢትዮጵያነባር ሀገር ናት፤ የሚሉና እንዲሁም የመቶ ሃምሳ አመት ዕድሜ ዉጤት ናት የሚሉት ፤ይህንን ቅይጥና ዥንጉርጉር አቋማቸው በወንፊት ሳይበጠር በጋራ ሊጓዙ ያበቃቸዉ ሚስጢር ምድር ነዉ?ይህ ጥበብ ወይስ ታክቲክ ተብሎ ሊወሰድ ይችል ይሆን?ሚስጥሩ ሲገለጥ “ልከክልህ እከክልኝ” ወይም አንዳንዶች እንደሚሉት መሞዳሞድ ከሆነስ?

የበግ ለምድ ከለበሱት ዉስጥቓሚዉ እረኛ እዉነተኞችን መለየት ከተሳነዉ የእረኛዉ መፍዘዝ ወይስ ሁሉም አስመሳይ ለምድ የለበሱ በመሆናቸዉ ነዉ?ስልቻም ቀልቀሎ…!ይባል የለታዲያ።

ይህ የመሪ ድርጀት እጦት ሳይበግረዉህዝባችን በየአካባቢው ካለፉት አመታት ጀመሮ እየደረሰበት ያለውን ጥቃት ለመከላከል  በቄሮዎች በፋኖዎችናበጎበዝ አለቆች እየተመራ ከአደባባይ ሰልፍ እስከ ሽምቅ ውጊያ ድረስ ለመዝለቅ ተገዷል። አንዳንዶች ይህንን ሐቅ ከመካድም አልፈዉየሕዝባዊ አመፁን ውጤት እነሱ የፈጠሩት አስመሰለው ከማቅረብ አልቦዘኑም። ከታሪክና ከህዝብ ተሰውሮ መኖር አይቻልምና ህዝባችን በትግሉ ማዕበል ውስጥ በመገኘቱ እውነቱን  በግልጽ ያውቀዋል።  እንዚህ ዋሾዎች ግን ያደቆነ ሠይጣን ሳያቀስ አይለቅም እንዲሉ  የድሉ ቀን ሲመጣ ቆዳቸውን ለውጠው፤ መልካቸውን ቀይረው መምጣታቸው አይቀሬ ነውና፤ ዐመተ ፍዳቸውን እና ዐመተኩነኔያቸው በየፈርጁ ሊከተብ ይገባል። የክህደት ታዋቂነት ከሃዲ ያስብል እንደሆነ እንጂ ሀቀኛ የሚያሰኝ አይደለም።

ሌላው አሳሳቢ ጉዳይ የፖለቲካ ትግላችን አቅጣጫ ነው።

ግባችንደሞክራሲያዊትኢትዮጵያን መገንባት እንደሆነ ብዙዎቻችን በጽንሰ ሐሳቡ ብንግባባም፤ ይህንን ግብ እዉን ለማድረግ ምን ዐይነት አካሄድ መጛዝ አለብን? የሚለው ጥያቄ ግን ትኩረት አግኝቶ የተመለሰ አይመሰልም።

ይህ ጉዳይ ምላሽ ያለማግኘቱ “በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሣታይ” እንዲሉ የሚፈጠሩ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች እያማለሉን የዘነጋነው ወይንም ሆን ብለን ያለፍነው ወይንም ሸፋፍነን በማለፍ የፍርድ ቀን ለመጠበቅ በማሰብከሆነ ውጤቱ የከፋ ይሆናል።

የአገራችንና የሕዝባችን ዋናችግርና አደጋ ኢሕአዴግ የሚከተለው የፖለቲካ መሰመርና ፖሊሲ ነው። ይህ ጎሳን፤ ቋንቋንና ዘርን መሰረት ያደረገና ሀገሪቱንም በክልል የሸነሸነ አገዛዝ ለችግሮቻችን ሁሉ መሰረታዊ ምክንያት ሆኗል። ሕገ መንግስቱም የዚሁ እኩይ የአገዛዝ ውጤት በመሆኑ፤ ከመቅድሙ አንስቶ ‘ብሄር ብሄረሰብ ህዝቦች …” በሚል አባዜ ተጠምዶ ሕዝባችን ከኢትዮጵያዊነት ይልቅ ወደ ጎሰኝነት  እንዲያመዝን ቢያስገድድም ሙከራው ዘለቄታ አልኖረውም። ውሸትና ንጋት እያደር ይገለጥ የለ!

የነገይቷን ኢትዮጵያ ለመገንባት የዛሬው ትግላችን የነባሯ እትዮጵያ ታሪክ በትውልድ ቅብብሎሽ የዳበረ እሴትና አብሮነትን ማዕከል ያደረገ መሆን አለበት። በኢትዮጵያዊነት የሚገለፀዉን ሕብረ-ብሄራዊነት አጀንዳ ለማስፈፀም ካልተባበረና ካልተነሳ በስተቀር የመሰዋዕትነታችን ውጤት አሁንም ፍሬ አልባ ከመሆን አያልፍም። ይህን ሐቅ መቀበል ሊከብድ ይችላል። መድሐኒትስ ይመር የለ! ስለዚህ መፍትሄው እውነትን ተናገሮ የመሸበት ማደር እንዲሉ ለዕውነት መሰዋዕትነት መክፈል ነው።

ዛሬ በምድር ላይ ያለው እንቅስቃሴ ቤተመንግስትን ለመንጠቅ በቀጥታ ያነጣጠረ መሆኑ መልካም  ቢሆንም፤ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያውያኖች ሕልም ግን በ4 ኪሎው ቤተ መንግስት የሚረካ ሣይሆን የዕርካታ ምንጫችን መሠረት “አንድ ሕዝብ ኢትዮጵያውያን አንድ አገር ኢትዮጵያ “ሁላችንም የአንድ አገር ዜጋ በሚል የተግባባና የተቀናጀ ትግል ዙሪያ ፀንቶ መቆም ነው። ከዚህኛው ምንጭ ዳግም የነጻነት ጥማት አይገጥመንምና።

አማራው ለኦሮሞው፤ ኦሮሞው ለትግራዩ፤ ደቡብ ለሰሜን፤ ምእራቡ ለምስራቁ ወዘተ…፤ ወንድማማች ነን መባባሉ ብቻ ዋስትና አይሆነንም።

ወያኔ ተወገደም አልተወገደም ከእንግዲህ “እኛን (ኦሮሚያን) ሊገዛ አይችልም” የሚለዉ አባባል በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የተመሰረተችዉን ኢትዮጵያና ሕዝቧን ይገልፃልን?? ምሳሌ (ከኔ)–አንድ ኢትዮጵያዊነት ፍልስፍናን መሠረት ያደረገ ግዙፍ ተራራ ከመሀል ስፍራ ላይ ቆሟል። በሌላኞው ጠርዝ ደግሞ በጀዋመ (የፈጠራስም)ና ጓደኞቹ በዘር በቋንቋ ማንነትና በክልል አስተዳደር ላይ የተገነባ አስተሳሰብ (ፍልስፍና) አለ። የእነ ጀዋመ አስተሳሰብ ሳይሆን፣ ግዙፍ ተራራ ከሆነ ወደነ ጀዋመ የመጣ ይህ ታክቲክ ወይስ ኢትዮጵያዊነትን ለድርድር ማቅረብ?

እዚህ ላይ ጆሮ ያለዉ ይስማ፣ ግን በአእምሮዉ ያስተዉል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በኢሕዴግና በዘረኞች ተክዷል።ይህ ሀቅ እንጂ ወዳጅነትን ለማብዛት ተብሎ የሚደሰኰር ፕሮፓጋንዳ አይደለም የታክቲክ ዉጤትም አይደለም።

ይህን ስንረዳ ብቻ ነዉ ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመወዳጀት የዘይት ሀብት ላይ ተደግፎ ከመታገል ይልቅ የተጎሳቀለዉንና ሳያጣ ያጣ በሆነዉ ኩሩ ሕዝብ ጉልበት፣ላብና ደም ስንተማመን ነዉ በጋራ ወደፊት መትመም የምንችለዉ።

ማጠቃለያ–

መስዋዕትነታችን ዋጋ እንዲኖረውና ትግላችን በነባሯ ኢትዮጵያ ታሪክ ላይ የተዋቀረ፤ ሕብረ ብሔራዊ አጀንዳ ያነገበ፤ ሉዐላዊነቷ የተከበረ፤ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን  ማቀዳጀት የሚችል የሀሣብ ፣የርዕዮት-ዐለም ፤የተግባር አቅም ያለዉሊሆንይገባል። አካሄዱም ከብሄር ተኮር (ጎሰኛነት) አደረጃጀትና ርዕዮት-ዓለም የፀዳ መሆን አለበት።

ጎሰኝነት የቱን ያህል ህዝቡን ለማነሳሳት የጠቀመ ቢመስልም ውጤቱ ግን አንድነት ሣይሆን ልዩነት ነው። የዘር ማንነት የክልል ፖለቲካ አደረጃጀትን ማዕከል ባደረግ ትግል የቤተመንግስትን ሥልጣን ለመንጠቅ ይቻል ይሆናል፤ግን ፋይዳው ለአንድነት ለዘላቂ ዕድገትና ብልጽግና ዳግም ነፃነትን እንዳንጠማ የተከፈለውን መስዋዕትነት አይከፍልምና እያስተዋልን መጓዝ ይበጀናል። አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ የሚለው አገላለጽ እንዳይመሰክርብን እንጠንቀቅ!!!

ከእዉነቱ ፈረደ

ኢትዮጵያ ለዘለዐለም ትኑር!

አሁንም ለወደፊትምኢትዮጵያዊነት ያሸንፋል!


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule