• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ጉዞ . . .

July 21, 2015 11:35 pm by Editor Leave a Comment

“…ከዚህ በኋላ ህዝብ ሰብስቦ ማውራት ላቆም ነው። ጊዜው ተቀይሯል።  ትግል ለደካማ መንፈስ አይሆንም። ትግል መውደቅን ይጠይቃል። ሲወድቁ ግን ለመነሳት መሞከርን ይጠይቃል። ስንወድቅ ልታዩን ትችላላችሁ ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ … ”  ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ይህንን የተናገሩት የአስመራ ጉዟቸው ከመሰማቱ ጥቂት ቀናት በፊት ነበር።  ንግግሩ ለብዙዎች ግርታ መፍጠሩ አልቀረም።  ከቀናት በኋላ የኤርትራን ምድር ሲረግጡ “ስንነሳ ግን ታዩናላችሁ…” ማለታቸው ግልጽ ሆነ።

ከምርጫ 97 በፊት ዶ/ር ብርሃኑ በፖለቲካ ስብእናቸው የሚታወቁት ለሰላማዊ ትግል ባላቸው የከረረ አቋም ነበር። በእስር ቤት ሆነው በጻፉት “የነጻነት ጎሕ ሲቀድ፤ …”  መጽሐፋቸው ሰላማዊ ትግል ያለውን የሞራል፣ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ የበላይነት ምሳሌ እያስቀመጡ ዘርዝረዋል።

ለዚህም ነበር ከሰላማዊ ትግል ወጥተው “ሁለገብ ትግል” ለማካሄድ ማቀዳቸውን ሲገልጹ ለብዙዎች ድንገተኛ እና አስደንጋጭ የሆነው። የጦርነትን አስከፊ ገጽታ ሲነግሩን የነበሩ እኝህ ምሁር በአንድ ግዜ ወደ ተቃራኒው የትግል ስልት ሲዞሩ ያቀርቡት የነበረው ምክንያት በወቅቱ ብዙዎችን ሊያሳምን አልቻለም። ምክንያቱም አመጽ ወይንም ጦርነት ከባድ ነገር ነው። ገንዘብ እና ግዜን ይበላል። ከሁሉም በላይ የህይወት መስዋእነትን ይጠይቃል። የሰላማዊ ትግሉ ስልቶች ገና በደንብ አልተፈተሹም የሚሉም ጥቂቶች አልነበሩም።

ከአምስት ግዜ ምርጫ በኋላም ህወሃት ሕዝብ ላይ መቀለዱን አላቆመም። በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትንም ጭራሽ ወደ ጫካ እንዲገቡ፣ አልያም እንዲሰደዱ አማራጭ መስጠት ያዙ። የትጥቁን መንገድ “ጨርቅ ያርግላችሁ” ሲሉም አሾፉ።

የ”ምርጫ 2007″ ውጤት በተሰማ ማዕግስት ከዴንቨር-ኰሎራዶ አንድ የቀድሞ ህወሃት ታጋይ ስልኬ ላይ ደውሎ እንዲህ አለኝ። “ግዜው የኛ ነው። ገና መቶ አመት እንገዛችኋለን። ታዲያ ስንገዘችሁ ዝም ብለን አይደለም።  እየረገጥን እንገዛችኋለን…”  ሰውየው እኔ እንድናገር እንኳን እድል አልሰጠኝም። ስለምርጫው ውጤት በድረ-ገጾች ላይ የሰጠሁት አስተያየት እንዳበሳጨው ገባኝ።  በትግርኛ እና በአማርኛ እያቀላቀለ ተሳደበ። ዘር እና ሃይማኖትን ጭምር እየጠራ ተሳደበ። በትእቢት የተወጠረው ይህ ሰው ሙሉ ስሙን እና አድራሻውን ሳይቀር ይናገር ነበር። “ከፈለግክ ቅዳኝ። ማንንም አንፈራም!” ይል ነበር።  እርግጥም ድምጹ በቴሌፎኔ መቅጃ ሳጥን ውስጥ ቀርቷል። ይህንን አጸያፊ ስድብ መልቀቁ ወገን ከወገን ማጋደል ይሆናል በሚል እሳቤም ለግዜው ይዤዋለሁ።

ማንነትን የሚፈታተን፣ ክብርን የሚነካ ንግግር ነው። ስድቡን ሁሉ በትእግስት ከሰማሁ በኋላ አንድ ቃል ብቻ ተናግሬ ስልኩን ዘጋሁት። “ትዕቢት ውድቀትን ትቀድማለች።”

የያዝኩትን ትንሽ መረጃ በመንተራስ ስለሰውየው ማንነት አንዳንድ ነገር ማወቅ ቻልኩ።  ሰባት አመት የህወሃት ትግል ውስጥ የነበረ ሰው ነው።  ይህ ግለሰብ ዴንቨር ኮሎራዶ ከአመታት በፊት ሲገባ ባዶ እጁን ነበር። አሁን ግን ሚሊየነር ሆኗል። የህወሃትን የተዘረፈ ገንዘብ በዶላር ለማጽዳት ወደ ዴንቨር የሚላኩ ሰዎች ቀጥር ቀላል አይደለም። እየረገጥን ገዝተን፣ እየረገጥን እንዘርፋለን፣ ይህንንም አሜን ብላችሁ ተቀበሉ ነው የሚሉን። ከባዶ ተነስተው መጠን የሌለው ስልጣን እና ገንዘብ ሲያካብቱ፤ በያዙት ነገር ይታወራሉ። ድንቁርና ሲታከልበት ደግሞ ስልጣናቸው ዘለአለማዊ፣ ሃብታቸውም የማያልቅ ይመስላቸዋል።

እንደዚህ አይነቶች ወንድነትን እና የሃገርን ክብር የሚፈታተኑ ነገሮች ተቆጥረው አያልቁም። ተሳፋሪዎችን ይዞ እየበረረ ያለ የአየር መንገድ አውሮፕላን በአንድ ካድሬ ትዕዛዝ እንዲመለስ የሚደረግባት ሃገር ሆናለች ኢትዮጵያ። ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ያገኘሁት አንድ መረጃ የሚያሳየን ይህንኑ ነው። ከአዲስ አበባ ናይሮቢ-ኬንያ ይጓዝ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራውን ከጀመረ በኋላ እንዲመለስ መደረጉ እና በዚህም ምክንያት አየር መንገዱ የሁለት መቶ ሺህ ዶላር ኪሳራ ደርሶበታል። ይህ የሆነው ድምጻዊ ቴዲ አፍሮ አውሮፕላኑ ውስጥ ስለነበር ብቻ ነው። እነዚህ ሰዎች ሃገሪጥዋን የግል ንብረታቸው አድርገዋታል።

በፈለጉ ግዜ፣ የፈለጉትን ያስራሉ። በፈለጉ ግዜ የፈለጉትን ይለቅቃሉ።  በእስር ላይ ከሉ 19 ጋዜጠኞች ይልቅ ለአንድ  ባእድ መሪ ክብር የሚሰጡ፣ በአልሻባብ ከሚገደልው ሰራዊት ይልቅ ለአሜሪካ ብሄራው ጥቅም የሚጨነቁ የውስጥ ባዕዳን ናቸው ስልጣኑን በሃይል ያየዙት።

20 አመታት በአንድ ርእዮተ-ዓለም፣ በአንድ አገዛዝ፣ በአንድ ሰው አስተሳሰብ መዝለቅ እጅግ እጅግ ይከብዳል። በተለይ ደግሞ በምእራቡ አለም ውስጥ ለሚኖር ሰው ፍጹም የማይታሰብ ነገር ነው። በ97ቱ ግድያ እጅግ ተቆጥቶ የነበረው ሰር ቦብ ጌልዶፍ “መቼ ነው የምታድጉት? እስቲ እደጉ!” ብሏቸው ነበር። አሁንም አላደጉም። አሁንም ሰው እየገደሉ ነው።  ለማደግ የምኒሊክ ቤተ-መንግስት ሃያ አመታት መቆየት አያስፈልግም። ለእድገት ለውጥ ያስፈልጋል። የስርዓት ለውጥ፣ የሰው ለውጥ፣ የአስተዳደር ለውጥ፣ የአቅጣጫ ለውጥ፣ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል።

በርካቶች በሰላማዊ መንገድ ለውጥ ለማምጣት እጅግ ጣሩ። ጥረታቸው ግን እንደ ደካማነት ተቆጠረባቸው። በያዙት የጦር መሳርያ ብቻ የሚተማመኑ ጉልበተኞች ቀለዱባቸው። የህዝብን ድምጽ እየሰረቁ መቀመጣቸው ሳያንስ መራጩን ሕዝብ እያሳደዱ መበቀል ያዙ። ኢትዮጵያ በሰላማዊ ትግል ለውጥ ማምጣት ምርጫ ለአምስተኛ ግዜ ተሞከረ። አምስቱም ተጭበረበረ። ከአሁን በኋላ በምርጫ ለውጥ እናመጣለን ብሎ ማሰብ የማይቻልበት ደረጃ ላይ እንደሆነ የምርጫ 2007ቱ ትዕይንትን ብቻ ማጤኑ ይበቃል። በታሪክ 100% አሸነፍኩ ብሎ የተናገረ አንባገነን መንግስት በኛው ምድር ተፈጠረ። ይህ ሕዝብ ላይ ማፌዝ ነው። ትዕቢት፣ ድፍረት እና ንቀት የተሞላበት ፌዝ። “ምንም አታመጣም!” አይነት ንቀት!

በፖለቲካ አግባብ ጦርነት የዲፕሎማሲ ጣርያ፣ የሰላማዊ ትግል መጨረሻው አማራጭ ነው።

ከዚህ የአገዛዝ ንቀት በኋላ ህዝብ ለአመጽ ቢነሳ ተጠያቂው ያለህዝብ ይሁንታ ስልጣን ላይ ያለው ስርዓት ብቻ ነው። ህዝቡን ወደ ስደት እና ወደማይፈልገው አመጽ እየመሩት ያሉት እነዚያው የስልጣን እና የንዋይ ጥመኞች ናቸው።  ይህ ንቀት ከትጥቅ ትግል ጋር ችግር አለብኝ የምንል ወገኖችን እንኳን የሚፈታተን ነገር ነው።

ዶ/ር ብርሃኑ ሲተቹበት የነበረው ሌላው ጉዳይ ደግሞ ትግሉን ከርቀት መምራት ያለመቻሉ ነገር ነበር። በሻእቢያ ላይ ያለው ጥርጣሬ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ ይህ ጉዞ በዶ/ር ብርሃኑ ላይ ይነሳ የነበረውን የሞራል እና የሃላፊነት ጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል። ለሰራዊቱ የመተማመን፣ ለህዝቡም የመነሳሳት ስሜት ይፈጥራል።

ከ21 ዓመት በላይ ያለ ለውጥ መቀመት በጣም ያሰለቻል። 21 አመት እየረገጡ እና እየዘረፉ መቀመጥ ይበዛል። ኢትዮጵያ ለውጥ ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ህዝብ ፍትሃዊ ስርዓት ያስፈልገዋል። በሰላማዊው መንገድ ለለውጥ የተሰለፉ ሃይሎች እየታፈኑ፤ እየተሰቃዩ፣ እየተገደሉም ነው።  እየተገደሉ የሚገድሉ ሲነሱ “ባንደግፋቸውም አንቃወማቸው” ያለው ማን ነበር?

ለነጻነት ሲባል ራሳቸውን ለመሰዋዕትነት የሚያቀርቡ ወገኖች የሚያምጹት ያለ ምክንያት አይደለም። በሁሉም ውስጥ ቁስል አለ!

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Right Column - Primary Sidebar

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule