• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ድምጽ የመስረቅ አባዜ

March 2, 2018 05:59 pm by Editor 4 Comments

አይን እና እግር ያወጣ ውሸት ሲሰማና ሲታይ ይህ የመጀመሪያው አይደለም። “ጨፍኑ እናሞኛችሁ” አይነት ንቀት ግን አሁን ላይ ፈሩን እየለቀቀ ይመስላል። ወያኔ እንደለመደው በአደባባይ ህግ አፍርሷል። ይህ ስርዓት ራሱ ያላከበረውን ህገ-መንግስት ሌላው ሕዝብ እንዴት አድርጎ ሊያከብርለት ይችላል?

ሃገሪቷን  በወታደራዊ አገዛዝ ስር የሚያስገባ ሕግ ወጥ አዋጅ በተጭበረበረ ድምጽ ዛሬ አጽድቀዋል።ይህ በታሪክ መዝገብ ላይ ከሚሰፍሩ የጨለማ ቀናት አንዱ ነው።

የካቲት 23 ቀን 2010 ዓ.ም፣ 122ኛው የአድዋ በዓል ከወትሮ ለየት እና ደመቅ ብሎ ተከብሯል። ይህ ቀን ለወያኔ ምኑም አልነበረም። ህወሃት የአድዋ ድል ቢቻል ባይነሳ ይመርጣል። ሃገሪቷን እየጠላ፣ ታሪኳን እያንቋሸሸ፣ ሕዝቧን እየገደለ የሚገዛ ስርዓት። ጭንቅ ሲይዘው፣  የባንዲራ ቀን ማክበር እንደጀመረ ሁሉ፣ አድዋም ዘንድሮ እንዲከበር ፈቅዷል። ይህ ያለምክንያት አልሆነም። ሕዝብ በአደባባይ በነቂስ ወጥቶ በእልህ ስሜት አድዋን ሲያከብር፣ ፓርላማ ውስጥ አንድ ድራማ ይታይ ነበር።

ፓርላማ ውስጥ እያሉ በ346 ድምጽ ጸደቀ አሉን። ከፓርላማ ሲወጡ ደግሞ ድምጹ አድጎ 395  ሆነ! ልብ በሉ ልዩነቱ የ49 ሰው ድምጽ ነው። 49 ድምጽ ከየት መጣ? ሞተዋል የተባሉ አባላትም ቢሆኑ 8 ናቸው። ለመዋሸት እንኳ የማይመች ውሸት ነው ምክንያቱም ቁጥር ነዋ! ቀጥር ደግሞ ከመደመር፣ ከመቀነስ፣ ከማካፈል እና ከማባዛት ውጭ አይደለም። በነሱ አተያይ 90 ሚሊየን ሕዝብ ሂሳብ አይችልም። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ አልተማረም። በዚህ ደረጃ ዘቅጦ ሕዝብን መናቅ እና ሕዝብ ላይ መቀለድ ግን ከምን ሊመጣ ይችላል? ከፍርሃት ወይንስ ከድንቁርና?

አባዱላ የተቀመጠበት ወንበር ራሱ በተሰረቀ ድምጽ የተገኘ ስለሆነ፣ ስርቆቱ ለሱ አዲስ አይሆንበትም። ስለተደጋገመ ለምዶታል። ሰውዬው የፓርላማውን መዶሻ ከመጨበጡ አስቀድሞ መሰረታዊ የሂሳብ ትምህርት እንኳን ቢወስድ፣ ለአሁኑ ውርደት ላይዳረግ ይችል ነበር። የ539 2/3ኛን ለማስላት መሰረተ ትምህርት መማር ብቻ ይበቃል እኮ!

እርግጥ ነው ሂሳብን ለፖለቲካ ስሌት መጠቀም ሽምደዳን ሳይሆን ችሎታን ይጠይቃል። ብስለትን እና ጭንቅላትን ይጠይቃል። 27 አመት ወንበሩ ላይ ተቀምጠው ያልበሰሉ፣ መቼም ሊበስሉ አይችሉም። “ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል” ይላል መጽሃፍ ቅዱስ። የሰው ልጅ ግን ያስመለሰውን መልሶ  አይበላም። አባዱላ ወጥቶ ሲመለስ ከበፊቱ  የከፋ ስራ መስራት መጀመሩን አሁን አሳየ። ወገኔ የሚለው ሕዝብ ላይ የተዶለተውን የእልቂት አዋጅ ለማጽደቅ ተጨነቀ። “ድምጽ ከምንሰጥ በጭብጨባ እናሳልፈው!” እስከማለት እጅግ ሩቅ ተጓዘ።

ደብረጽዮን፣ ሳሞራ የኑስ እና ጌታቸው አሰፋ በሕዝብ ላይ የጫኑትን ሕግ ለማጽደቅ ቢያንስ 539 ድምጽ ያስፈልግ ነበር። አባዱላ ገመዳ በ 346 ድምጽ አጽድቆታል። የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ዘጋቢ ከስፍራው በመቅረጽ-ድምጽ የስተላለፈም መልዕክት፣ ከአፈጉባኤው ድረ-ገጽ ላይ ሰፍሮ ከነበረው ጋር አንድ ነው። እጅግ የሚያሳዝነው፣ አዋጁን በተጭበረበረ መንገድ ማሳለፋቸው ሳይሆን፣ ስህተታቸውን ለመሸፈን የሚፈጥሩት ሌላ ስህተት ነው። እውነታውን ላይለውጠው፣ እንደ ሰነፍ ተማሪ ማህበራዊ ድረ-ገጻቸውን መሰረዝ እና መደለዝ ብዙ ጣሩ።

ወደ ህሊናቸው የተመለሱት አባላት፣ በተገኘችው ትንሽ ቀዳዳ ድምጻቸውን ለማሰማት እጅ ቢያወጡም አልተሳካም። ህሊናቸውን የሸጡ አባላት ይሰሩ የነበረውን ድራማ እየተመለከትን ብዙ ታዘብን። የአንዳንዶቹ መንሰፍሰፍ ጉድ ያስብላል። ሁለት እጁን ያወጣ “የህዝብ ተወካይ” በምስል ይታይ ነበር። ታዛቢዎች እንደሚሉት ሰውየው ምናልባት  እጆቹን ከፍ አድርጎ “እግዚኦ” እያለ ይሆናል። አባ ዱላ ግን አንድ ሳይሆን ሁለት ብሎ ሳይቆጥረው አልቀረም። ጌታቸው ረዳ እና አህመድ ሽዴ፣ አንገታቸው እስኪጣመም እየተጠመዘዙ አባላቱን በአይን ሲያስፈራሩ ይታያል።  ሰዎቹ ምን ያህል ብርክ እንደያዛቸው በግልጽ ይታያል። ግን አዋጁ መሬት ላይ ያለውን ሁነታ አይለውጠውም። 27 ዓመታት በአዋጅ ለምትገዛ ሃገር አስቸኳይ የሚሉት አዋጅ አዲስ ነገር አይደለም። ለሃገሪቱ ችግር መፍትሄው አዋጅ ያለመሆኑን ከቅርቡ ግዜው ትዝታ እንኳን አልተማሩም።

ስርዓቱ በስብሻለሁ ብሏል። ደግመው ደጋግመው ይህንን ብለውታል። እንደ ጫማ ወልቆ ለሚቀየር ለዚህ ስርዓት በዚህ ደረጃ የሚያጎበድዱ ግን በጣም ያስገርማሉ። ከሰው የተፈጠረ፣ እንደሰብአዊ ፍጡር የሚያስብ ይህንን ህገ-ወጥ አዋጅ ለማጽደቅ ህሊናውን አይሸጥም።

አይ አንቺ የጉድ ሃገር። “የሕዝብ ተወካዮች” በሕዝብ ላይ ጦርነት የሚያውጁባት ሃገር!

ክንፉ አሰፋ


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column, state of emergency, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. በለው ! says

    March 3, 2018 10:50 am at 10:50 am

    *ይህ የፈረደበት ዩኒቨርሲቲ እንደ ጎሎ ዛፍ በበዛ ዘመን የፊደል ቆጣሪና ቀመር አዋቂው ቁጥር እንዲህ መላ ቅጡእንዴት ጠፋ!?
    በሕግና ሥርዓት የአንድን ሀገር አስችኳይ አዋጅ ማናናቅ መቃወምም ሆነ ድምፅ አለመስጠት ነገሩ እንዲው በጭብጫቦ እናሳልፈው እንዳሉት ብ/ጄ አባ ዱላ…ማን እጅ አወጥቶ ማን እንደቆጠበ ባይታወቅም አዋጁ ቢወድቅ እንኳ እነአጅሬዎች እራሳቸው ወንጀል አቀናብረው ብጥጥብጥ አስነስተው”የፓርላማ አባላቱ በሀገር መደፈር/ብጥብጥና ውድመት ላይ የተደረገ ትብብር “ብለው ካስቀመጧቸው ጓዳ እየለቀሙ ልዩ ጥቅማጥቀማቸውን ገፈው ላጭተው ያስገቧቸው እዚያው ደርግ የሚያሰቃይበት ህወሓት/ኢህአዴግ ጥፍር እየነቀለ፡ ዘቀዝቆ ከሚያጫውትበት ጥራትና ብቃቱ ዘመናዊ ከሆነው ማዕከላዊ ያጉራቸው ነበር ።
    * እነኝህ ሰዎች እንኳን ሽብር መፍጠር ጦርነት መፍጠር እንችላለን ያሉትን ማመን ነው።
    *ይልቁንም በአዋጁ አፈጻጸም ላይ ተቧድኖ በጋራ የሕዝብ መብት ጥሰት እንዳይኖር በዚያው ፓርላማ ላይ መሞገት ይሻላል።
    ለመሆኑ ህወሓት/ኢህአዴግ ፓርላማወን ያሸነፈው ፻በ ፻ አደለምን!? ያም ማለት…
    (፭፻፵፯) መቀመጫ ከሰው ጋር አለው፡(፺፰ አባላት አውጫጭኝ!?)
    ዛሬ (፰) ሰዎች በሞትና ሀገር በመልቀቅ አልነበሩም።
    (፯) አባላት ድምጽ ባስቸኳይ አዋጁ ላይ ይፅደቅ አይፅደቅ ድምጽ አልሰጡም፡
    (፹፰) የአስቸኳይ አዋጁን ተቃውመዋል፡
    ፫፻፵፮ አዋጁን መውጣትና መተግበር ደግፈው አሳልፈዋል፡ የፓርላማ ፫/፬ኛ = ፫፻፶፱ ቢሆንም ፫፻፵፮ አለፈ!።
    ፹፰ + ፯ + ፰ + ፫፻፵፮ = ፬፻፵፯
    ፭፻፵፯ – ፬፻፵፱ = ፺፰ አባላት የት ሄዱ/ገቡ
    ፹፰ + ፯ + ፰ + ፺፰ = ፪፻፩
    ፪፻፩ + ፫፻፵፮ = ፭፻፵፯
    ********************************!

    Reply
  2. Mulugeta Andargie says

    March 3, 2018 08:29 pm at 8:29 pm

    ሚኖ ባኪህ!! ድምፂ ሳራቃ?? እኔ ሳርቅ ብሎ ኪሲስ ኖ ኢንጂ ፊዲስዲስ!! ቅዲስዲስ ! ያላም!! ነግርቻሎ!! Oromo elite!!

    Reply
  3. በለው! says

    March 7, 2018 04:18 pm at 4:18 pm

    March 2, 2018 at 3:54 PM
    *ይህ የፈረደበት ዩኒቨርሲቲ እንደ ጎሎ ዛፍ በበዛ ዘመን የፊደል ቆጣሪና ቀመር አዋቂው ቁጥር እንዲህ መላ ቅጡእንዴት ጠፋ!?
    በሕግና ሥርዓት የአንድን ሀገር አስችኳይ አዋጅ ማናናቅ መቃወምም ሆነ ድምፅ አለመስጠት ነገሩ እንዲው በጭብጫቦ እናሳልፈው እንዳሉት ብ/ጄ አባ ዱላ…ማን እጅ አወጥቶ ማን እንደቆጠበ ባይታወቅም አዋጁ ቢወድቅ እንኳ እነአጅሬዎች እራሳቸው ወንጀል አቀናብረው ብጥጥብጥ አስነስተው”የፓርላማ አባላቱ በሀገር መደፈር/ብጥብጥና ውድመት ላይ የተደረገ ትብብር “ብለው ካስቀመጧቸው ጓዳ እየለቀሙ ልዩ ጥቅማጥቀማቸውን ገፈው ላጭተው ያስገቧቸው እዚያው ደርግ የሚያሰቃይበት ህወሓት/ኢህአዴግ ጥፍር እየነቀለ፡ ዘቀዝቆ ከሚያጫውትበት ጥራትና ብቃቱ ዘመናዊ ከሆነው ማዕከላዊ ያጉራቸው ነበር ።
    * እነኝህ ሰዎች እንኳን ሽብር መፍጠር ጦርነት መፍጠር እንችላለን ያሉትን ማመን ነው።
    *ይልቁንም በአዋጁ አፈጻጸም ላይ ተቧድኖ በጋራ የሕዝብ መብት ጥሰት እንዳይኖር በዚያው ፓርላማ ላይ መሞገት ይሻላል።
    ለመሆኑ ህወሓት/ኢህአዴግ ፓርላማወን ያሸነፈው ፻በ ፻ አደለምን!? ያም ማለት…
    (፭፻፵፯) መቀመጫ ከሰው ጋር አለው፡(፺፰ አባላት አውጫጭኝ!?)
    ዛሬ (፰) ሰዎች በሞትና ሀገር በመልቀቅ አልነበሩም።
    (፯) አባላት ድምጽ ባስቸኳይ አዋጁ ላይ ይፅደቅ አይፅደቅ ድምጽ አልሰጡም፡
    (፹፰) የአስቸኳይ አዋጁን ተቃውመዋል፡
    ፫፻፵፮ አዋጁን መውጣትና መተግበር ደግፈው አሳልፈዋል፡ የፓርላማ ፫/፬ኛ = ፫፻፶፱ ቢሆንም ፫፻፵፮ አለፈ!።
    ፹፰ + ፯ + ፰ + ፫፻፵፮ = ፬፻፵፱
    ፭፻፵፯ – ፬፻፵፱ = ፺፰ አባላት የት ሄዱ/ገቡ
    ፹፰ + ፯ + ፰ + ፺፰ = ፪፻፩
    ፪፻፩ + ፫፻፵፮ = ፭፻፵፯
    ********************************!

    Reply
  4. ኪሮስ says

    March 10, 2018 05:56 pm at 5:56 pm

    ጎልጉል፣
    የምን “አባዜ”? ሌብነት፣ ውንብድና፣ ወንጀል እንጂ።

    የሙሉጌታ አስተያየት ሥነ ሥርዓት የጎደለውና ጸያፍ ስለሆነ ለመወያያ ምን ጥቅም ስለሚሰጥ ነው ያተማችሁት?

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule