• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የተቃውሞ ሠልፍ “ሱስ”?!

November 19, 2019 01:24 am by Editor 2 Comments

ሠልፍ፣ ተቃውሞ፣ መፈክር፣ … ያለፉት 50ዓመታት መለያችን ሆኖ ቆይቷል። በተለይ ባለፉት 27ዓመታት ዘመነ ፍዳ ወወያኔ ደግሞ በተለይ በአውሮጳና አሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን “ሼም ኦን ዩ …” ሳይሉ የሚያልፍ ወር አልነበረም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ለዚህም ይመስላል “አሜሪካ አገር ኋይት ሃውስ ደጃፍ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ” ስትል ብትውል ማንም የሚነካህ የለም ሲባል የሰማው ክበበው ገዳ “እኛስ ሃገር ቢሆን አራት ኪሎ ቤተመንግሥት በር ላይ ቆመህ “ኦባማ ይውረድ!” እያልክ ብትጮህ ማን ይነካሃል?” በማለት የቀለደው።

ይህ “ማንም አይነካኝም” የሚለው አስተሳሰብ ሊሆን ይችላል በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያውያን የሰልፍ ሱሰኛ እስኪመስሉ ድረስ ለሁሉም ችግር ሰልፍን ብቸኛ አማራጭ ሲያደርጉ የሚታዩት። ያለፉት 27ዓመታት የተወጣው ሰልፍ ውጤት አላመጣም ለማለት አይቻልም። የተወጡም ሰልፎች አግባብነት ያላቸው ናቸው ለማለት ይቻላል። ምክንያቱም ህወሓት መስማት የተሳነው ስለነበር ለሚሰሙ አገራትና በተለይም ለድርጎ ሰፋሪዎቹ ምዕራባውያን አለቆቹ ድምጽ ማሰማት ተገቢ ነበር።

ሁልጊዜ ግን በሰልፍ ለውጥ አይመጣም። ዲጂታል ሆኖ ከጊዜው ጋር መራመድ የግድ ይላል። ይህ ግን የተስተዋለ አይመስልም። እንዲያውም የሰልፍ ሱስ የተጠናወተን እንመስላለን፤ በተለይ ዳያስፖራው። “የተቃውሞ ሰልፍ ሱሰኛ ያደርጋል” በሚል ዳጎስ ያለ መጣጥፍ ያቀረበች ላራ ቡለንስ የተባለች ጋዜጠኛ በፓሪስ ተቀጣጣይ የተቃውሞ ሰልፍ ይካሄድ በነበረበት ጊዜ አንዱ የተናገረው የሰልፍን ሱስ አሲያዥነት እንድታጤን እንዳደረጋት ትናገራለች፤ “ተቃውሞ ሰልፍ ሲጠራማ ማን ይቀራል?” በማለት አንዱ ተቃዋሚ ሲናገር ነበር የሰማችው።

በአሜሪካ የሚገኙ ዳያስፖራዎች ለወራት ሠልፍ የናፈቃቸውንና የተጨመዳደዱ ባንዲራዎቻቸውን አንግበው ሰልፍ መውጣት ጀምረዋል። ያሁኑ ዘመቻ ጃዋር መሐመድ ላይ ያነጣጠረ ነው። የተለመደው “እናወግዛለን፤ ቁም፤ ያቁም፤ ይብቃ፤ ለፍርድ ይቅረብ፤ …” የሚሉ መፈክሮች እየተሰሙ ነው። አንድ ግልጽ ያልሆነው ነገር ሰልፎቹ የሚወጡት ለማን እንደሆኑ አለመታወቃቸው ነው። ለኢትዮጵያውያን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ከሆነ ሰልፍ ላይ ከወጣውና ከተናገረው በላይ ዝም ብሎ ያደፈጠው ያገሩን ጉዳይ አሳምሮ የሚያውቅ እጅግ ብዙ ሕዝብ አለ። ለአሜሪካውያን ፖሊሲ አውጪዎች፣ ለሕዝብ እንደራሴዎች፣ … ከሆነ ደግሞ ሲፈከር የተዋለው በአማርኛ ስለነበር በሰውም ሆነ በጉግል ቢያስተረጉሙቱም ሊገባቸው አይችልም።

አሳዛኙ ነገር ራሱን ከሚገባው በላይ መካብ የማይበቃው፣ የጫትና የመጠጥ ሱሰኛ ለሆነው ጃዋር መሐመድ ክብር ሰጥቶ እንዲህ ዓይነት ሰልፍ መውጣት እርሱን ከሚገባው በላይ ማግነን እና ራስን ማዋረድ ነው። በምን ስሌት ነው ብረት ይዞ አገር በግፍ ሲገዛ ለነበረው ህወሓትም ለአንድ ዛሬ የተናገረውን ነገ ለሚክድ ወስላታ የሺሻ ተገዢ በእኩል ሰልፍ የሚወጣው? ሰልፍ አዘጋጆቹም ሆነ ሰልፈኞቹ አልገባቸው ይሆናል እንጂ በእነዚህ ሰልፎች ጃዋርን ኃያል፣ ታላቅ፣ ጀግና እያደረጉት ነው ያሉት። የዚያኑ ያህልም በርካታ ዕልኸኛ ደጋፊዎች እንዲነሳሱ የሚደርግ ኃይል እየፈጠሩ መሆኑን የተገነዘቡት አይመስልም።  

ከሁሉ በላይ የሚሳዝነው ደግሞ በአሁኑ ጊዜ የአማራና የኦሮሞ፣ የአማራና የትግራይ ምሁራን በጋራ አብሮ ስለመኖር፣ ስለ መሥራት፣ ስለ ወደፊት፣ ወዘተ ምን ማድረግ አለብን እሉ አደብ ገዝተው እየተወያዩ ባሉበት ወቅት በ“ሰልፍ” እና በ“ተናድጃለሁ” ሰበብ ጸያፍ ስድቦችን በአደባባይ መናገር በቃላት ሊገለጽ የማይችል እጅግ የውርደት ተግባር ነው። በተለይ ለሥልጣኔ ዋንኛ ተጠቃሽ በሆኑ አገራት ተቀምጦ አንድን ግለሰብ በራሱ በተከራየው አዳራሽና ቦታ “አትናገርም”፣ “አትወያይም”፣ “አትሰበሰብም”፤ ወዘተ የሚለው ፈሊጥ ከበርበሬና ሽሮ ጋር ተጭና አሜሪካ የገባች የችግር መፍቻ ስልት ትመስላለች።

በዳያስፖራ ባሉት ዋና የሚባሉት እነ ቪ.ኦ.ኤ. እና መሰል ሚዲያ ከስማቸው በፊትና በኋላ በርካታ ማዕረጎችን አስቀድመውና አስከትለው የሚጠሩት ምሁራኖቻችን ለጃዋር መፍትሔ የሚሆን ስልት አለመቀየሳቸው በታሪክ ተወቃሽ የሚያስደርጋቸው ነው። ለትንታኔውና ለማይጨበጠው ሀተታቸው ጆሮውን ሰጥቶ ሲሰማቸው ለኖረው ህዝብ የሚበጅ ነገር ሳያደርጉ በሚዲያ ላይ ወጥቶ ጆሮ አደንቋሪ አንጀባ መንፋት ከንቱነት ነው። በዳያስፖራው በርካታ የሕግ፣ የግብር (ታክስ) አሰባሰብ፣ የሒሳብ (አካውንቲንግ)፣ ወዘተ ኤክስፐርቶች አሉን። ነገርግን ጃዋር ሕግ በሚከበርበት አገር መጥቶ እንደፈለገ ሲፈነጭ የተቀናጀና የተባበረ ቡድን መሥርቶ እርሱን ለሕግ ማቅረብ አለመቻል የወሬ እንጂ የተግባር ጀግና አያስብልም። አሁንም ግን ቀን ሳያልፍ ዕድሉን ቢጠቀሙበት ለራሳቸውም ለአገርም የሚበጅ ይሆናል።

ሌሎች ደግሞ በሲቪክ ማኅበራት ስም የተመሠረቱና በሁለት የቤተሰብ ስም “ድርጅት” እንደ ሱቅ ከፍተው ከሚነግዱት እስከ ታላላቅ ሥራቸው መለያቸው እስከሆኑነት አኢጋን ድረስ ያሉ የሲቪክ ድርጅቶች ከወደ ሰልፉና አሰላለፉ ጋብ ብለው በኅብረት በመምከር ዘላቂነት ያለው ተግባር ቢጨምሩ ዓቅም አልባ ከሆነው ሕዝብ ጋር አብረው ከሚለቅሱ የተሻለ ነው።

በመጨረሻም የሰልፍ ሱስ የተጠናወተው ዳያስፖራ ቢያንስ የአሰላለፍ ስልት ከሸገር አራዶች ቢማር ጥሩ ሊሆን ይችላል። ለታላቁ ሩጫ የወጡ የአዲሳባ ልጆች ብሶታቸውን በእንዲህ መልኩ ነበር የተወጡት፤

ጃዋር መሐመድ፤ ጃዋር መሐመድ፤ የሺሻ ገመድ።

በቀለ ገርባ፤ በቀለ ገርባ፤ የጫት ገለባ።

ይህ መሰሉ ስላቅ ለፍርድ ባያስቀርብም ቢያንስ ግን ሐቁን በመናገር እውነቱ ፍንትው አድርጎ ከማሳየት ባለፈ አንጀትን ያረካል። (ፎቶ፤ ከፋይል ለማሳያነት የቀረበ)

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ™” አቋም ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Editorial Tagged With: Full Width Top, jawar, Middle Column, protest

Reader Interactions

Comments

  1. Rome says

    November 20, 2019 09:53 am at 9:53 am

    Well stated, hope lesson learned to communicate effectively your causes with appropriate linguistic channels. If you are not involved in your community, not use of voting rights and have no knowledge to use your local and national representative offices become less fruitful. If you are in France and wants the French support, or in Germany, Russia…….. engage with proper language, have knowledge of how to public protest marches, and effectively write on the news media, have your advocacy on interviews and so on to bring awareness to capitalize.

    Reply
  2. tika@yahooo.com says

    November 22, 2019 10:15 pm at 10:15 pm

    100 % agree with author
    I also heard from our diaspora insult directed to young Oromos like calling “Kero Korkoro” Imagine demonizing the entire 6 million so young Oromo generation. Diaspora learn how to be civil. Use proper and respectful manner to communicate your message across. Ethiopia is a divers country, its people have lived and will live for centuries together. Let’s not loose our cool!!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule