በሌብነት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር የዋሉት በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሣ “በማረፊያ ቤት ቆይታችን ሰብዓዊ መብታችንን እና ክብራችንን የሚነካ ድርጊት ተፈጽሞብናል” በማለት ለፍርድቤት ቅሬታ አቀረቡ። ጉዳያቸው በአዲስ አበባ እንዲታይ ለፍርድቤቱ ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ የአስራ አራት ቀን ቀጠሮ ሰጥቷል። በረከት ስምዖንና ታደሰ ካሳ በተጠረጠሩበት የጥረት ኮርፖሬት የሀብት ብክነት ጉዳይ ዛሬ ጥር 17 ቀን 2011 ዓ.ም. በባሕር ዳርና አካባቢዋ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል። ተጠርጣሪዎቹ ካለባቸው የጤና ችግር አንጻር በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ እንደሚመገቡ ገልጸው፤ ይሁንና በማረፊያ ቤቱ ምግብ በአግባቡ እና በሰዓቱ እንደማይቀርብላቸው ተናግረዋል። ለአብነትም ትናንት ምሳ በ10፡00 እንደቀረበላቸው ለችሎቱ አስረድተዋል። የኢኮኖሚ ችግር እንዳለባቸው እና ጡረታ በአግባቡ … [Read more...] about “በማረፊያ ቤት ሰብዓዊ መብታች ተጥሷል”፤ በጥንቃቄ የተዘጋጀ ምግብ በአግባቡና በሰዓቱ አይቀርብልንም – በረከትና ታደሰ

