• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ሃናን በመድፈር የተጠረጠሩት ክስ ተመሰረተባቸው

December 20, 2014 02:34 am by Editor 4 Comments

በ16 ዓመቷ ታዳጊ ሃና ላላንጎ ላይ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመፈፀም ለሞት አብቅተዋታል በተባሉ አምስት ተጠርጣሪዎች ላይ የፌዴራል ዐቃቤ ሕግ ክስ መሰረተባቸው። ዐቃቤ ሕግ ትናንት ማክሰኞ ታህሳስ 7 ቀን 2007 ዓ.ም በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ ሁለት ሲሆን፤ ለአካለመጠን ያልደረሰችን ሴት በአሰቃቂ ሁኔታ መድፈር እና ከባድ የሰው መግደል ወንጀል የሚሉት ክሶች ተጠቅሶባቸዋል። ከትናንት በስቲያ ሜክሲኮ በሚገኘው በፌዴራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የነበረውን የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ያጠናቀቀው ይህ ጉዳይ ከዚህ በኋላም በልደታ ፍርድ ቤት መታየቱን ይቀጥላል።

በመሆኑም በዐቃቤ ሕግ የክስ መዝገብ ዝርዝር ውስጥ ስማቸው የተጠቀሰው አምስቱ ተጠርጣሪዎች 1ኛ ተከሳሽ ሳምሶን ስለሺ ሙያ ሹፌር፣ 2ኛ ተከሳሽ በዛብህ ገ/ማርያም ሾፌር፣ 3ኛ ተከሳሽ በቃሉ ገ/መድህን የታክሲ ረዳት፣ 4ኛ ተከሳሽ ኤፍሬም አየለ የታክሲ ረዳት እና 5ኛ ተከሳሽ ተመስገን ፀጋዬ ሾፌር ናቸው። ትናንት በችሎት ቀርበው ማንነታቸውን ለፍርድ ቤቱ ያረጋገጡ ሲሆን፤ የተከሰሱበት ወንጀል የዋስትና መብት የማያሰጥ በመሆኑም ጉዳያቸውን በማረሚያ ቤት ሆነው እንዲከታተሉ ሲል ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል።

hana3ዐቃቤ ሕግ በክስ ዝርዝሩ ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ለመፈፀም አስበው መስከረም 20 ቀን 2007 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 11 ሰዓት ሲሆን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ክልል ልዩ ስሙ ጦር ኃይሎች ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የ16 ዓመት ዕድሜ ያላትን ታዳጊ ሟች ሃና ላላንጎን ታክሲ ቆማ በምትጠብቅበት ወቅት 1ኛ ተከሳሽ ከሚያሽከረክረው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-21253 አ.አ. ሚኒባስ ታክሲ ውስጥ ጠርቶ በማስገባት ቀራኒዮ አደባባይ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ አብረው እስከምሽቱ 2፡30 ከቆዩ በኋላ 1ኛ ተከሳሽ 2ኛ ተከሳሽን በስልክ ደውሎ በመጥራት፤ 2ኛ ተከሳሽም በሚያሽከረክረው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-17035 አ.አ. ሚኒባስ ታክሲ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾችን ይዞ በመምጣት ከ1ኛ ተከሳሽ ጋር በመገናኘት ሟችን ወደቤቱ ይዞ እንደወሰዳትና እርሱም የሚያሽከረክረውን ታክሲ አቁሞ ተመልሶ እንደሚያገኛቸው በመናገር 4ኛ ተከሳሽ ደግሞ ሟችን 2ኛ ተከሳሽ በሚያሽከረክረው ታክሲ እንድትገባ በማድረግ 2ኛ፣ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ሟችን ይዘዋት ኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ክልል ልዩ ቦታው አንቺን አሉ ህንፃ አካባቢ ከሚገኘው የ2ኛ እና የ3ኛ ተከሳሾች መኖሪያ ቤት በመውሰድ በግምት ከምሽቱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ ሌሊቱን በሙሉ ሁሉም ተከሳሾች እየተፈራረቁ በአሰቃቂ ሁኔታ የግብረስጋ ግንኙነት ሲፈፅሙባት ያደሩ በመሆኑ ዐቃቤ ሕግ 18 ዓመት ባልሞላቸው ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረስጋ ድፍረት በደል ወንጀል ከስሻቸዋለሁ ይላል።

በሁለተኛው ክስ ስርም ተከሳሾቹ ድርጊታቸው ህገወጥና የሚያስቀጣ ውጤት ሊያስከትል እንደሚችል እያወቁ በግዴለሽነት እየተፈራረቁ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል እንደፈፀሙባት፤ የድረሱልኝ ጥሪ እያሰማች ማህፀኗ እየደማ በተለይ ጨካኝነታቸውን፣ ነውረኝነታቸውን እና አደገኝነታቸውን በሚያሳይ ሁኔታ ለአምስት ቀናት አቆይተዋታል ይላል ዐቃቤ ሕግ በክሱ፤ ከዚያም ከአምስት ቀናት በኋላ 2ኛ ተከሳሽ በ3ኛ ተከሳሽ አማካኝነት ሟችን በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ክልል ልዩ ቦታው ጦር ኃይሎች ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ወስደው ጥለዋታል፡፡ ለመጣል ሟች በደረሰባት ጉዳት የሰውነት ክፍሎቿ ስራ በማቆማቸውና ብዛት ያለው ደም የፈሰሳት በመሆኑ ከቀናት በኋላ ህይወቷ ያለፈ በመሆኑ በፈፀሙት ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ተከሰዋል ይላል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍ/ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎትም በትናንትናው ዕለት የተከሳሾችን ማንነት በማጣራትና ክሱ እንዲደርሳቸው በማድረግ፤ በችሎቱ ፊት ክሱ ከመነበቡ በፊት በማረሚያ ቤት ቆይተው ጉዳያቸውን እንዲከታተሉ እና ተጠርጣሪዎቹ ጠበቃ የማቆም አቅም የለንም በማለታቸውም መንግሥት ጠበቃ እንዲቆምላቸው ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡ ክሱን ለማንበብም ለታህሳስ 30 ቀን 2007 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። (ምንጭ: ሰንደቅ)

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. ስለሺ says

    December 22, 2014 01:04 pm at 1:04 pm

    አስተማሪ የሆነ ቅጣት በአፋጣኝ ልሠጣቸው ይገባል ፡፡ ግቢ ውስጥ ያሉትም ተከራዮችም ሆኑ ነዋሪዎች ልቀጡ ይገባል ፡፡

    Reply
  2. dij mj says

    December 23, 2014 07:30 am at 7:30 am

    ለካ! ሞኞች ናቸዉ የደፈሩ፤ከሞት የምበልጥ ዉሳኔ ካለ ይሰጥ !!!

    Reply
    • Adferes solomon says

      January 10, 2015 11:37 am at 11:37 am

      ቅጣቱ የማያዳግምና ለሌሎች ወጣቶች ከፍተኛ ግንዛቤ የሚሰጥ መሆን አለበት ሌላው በዚህ ወንጀል ላይ ሊጠየቁ የሚችሉ የፖሊሰ አካላቶች ካሉ ሊካተቱ ይገባል

      Reply
  3. Sara says

    January 20, 2015 06:50 pm at 6:50 pm

    Death penalty is a good lesson in future. Right noq.

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule