• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የዐማራ ድምፅ ሬድዮን እንርዳ

November 25, 2016 01:58 am by Editor Leave a Comment

በአሁኑ ዘመን በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉ ነገር እያለው ሁሉንም ያጣ ዜጋ ዐማራው ነው ቢባል የተጋነነ ነው ሊባል አይችልም። በግልጽ እንደሚታወቀው፣ ዐማራው ቋንቋው አማርኛ ነው። ይህንን ቋንቋውን ከሌሎች የኢትዮጵያ ጎሣዎች ቋንቋዎች ጋር አጣጥሞ በማሳደግ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ መግባቢያ እንዲሆን አበርክቷል። ይሁን እንጂ፣ በአሁኑ ጊዜ የአማርኛ ቋንቋ ለዐማራው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ተለይቶ መከበሪያው መሆኑ ቀርቶ መጠቂያው ሆኗል። በአማርኛ ቋንቋ የሚጻፉት፣ በሬድዮ እና በቴሌቪዥን የሚቀርቡት ዝግጅቶች በአብዛኛው ማለት ይቻላል፣ ዐማራው የሚወገዝባቸው፣ የሚዋረድባቸው እና የሚኮነንባቸው እየሆኑ ከመጡ ዓመታትን ተሻግረው ዘመናት ተቆጥረዋል። ስለሆነም ዐማራን እና አማርኛን በጠላትነት ፈርጀው የጥፋት ተግባራቸውን ለፈጸሙና ለሚፈጽሙ ኃይሎች አጸፋውን በመስጠት፣ የአማርኛ ቋንቋም ሆነ የዐማራ ነገድ ተገቢ ቦታቸውን እንደያዙ እንዲቀጥሉ ለማስቻል፣ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ተመሥርቶ ሠፊ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል። ከሞረሽ ወገኔ የተግባር እንቅስቃሴዎች ውስጥ የዐማራው ድምፅ የሆነ፣ የዐማራ ድምፅ ሬድዮን  ማቋቋሙ አንዱ ነው።

የዐማራ ድምፅ ሬድዮ ሥራውን በመስከረም 21 ቀን 2009 ዓም (October 1, 2016) በይፋ ሲጀምር ዓላማዬ ብሎ የተነሣው ድምፁ ለታፈነበት ዐማራው ኢትዮጵያዊ ድምፅ ለመሆን ነው። ይህ ሬድዮ በእኒህ ሁለት ወራት ባልሞሉ ጊዜያት ውስጥ ለዓላማው ስኬት ተስፋ ሰጪ የሆነ እንቅስቃሴ አድርጓል። ይህ እንቅስቃሴ ያሰጋቸውና ዐማራው ራሱን የቻለ ኃይል ሆኖ መውጣት እነርሱ ላቀዱት ዐማራን ተዋራጅ እና ተሰዳች፣ ሟች እና አናሳ አድርጎ የመግዛት አባዜ የተጫናቸው ቡድኖች፣ የዕድሜ-ጠገቦቹ የሚዲያ ተቋሞች እንኳን ሊያሟሉት ያልቻሉትን በሁሉም ዘርፍ እንከን የለሽ ዝግጅት እንድናቀርብ ከተለያዩ አቅጣጫዎች አስተያየቶችና ትችቶች ይደርሱናል። አስተያየቶቹም ሆነ፣ ትችቶቹ ለራዲዮው ዕድገት ከፍተኛ  የሆነ አስተዋጽዖ  እንደሚያበረክቱ እናምናለን። ሆኖም ትችቶቹ እና አስተያየቶቹ ለዐማራ ድምፅ ሬዲዮ ዕድገት አስተዋጽዖ የሚኖራቸው ገንቢ እና በሐቅ ላይ የተመሠረቱ ሲሆኑ እንደሆነ ግልፅ ነው።

ይህ ይሻሻል፣ ይህ ይጨመር፣ ይህ ይደረግ፣ እንዲህ አይባል፣ ወዘተርፈ የሚባሉት አስተያየቶች ዋጋ የሚኖራቸው ዝግጅቱን ለማቅረብ ምን ያህል ገንዘብ አለ? ስንት ሙያተኛ ሙሉ ጊዜውን ይሰጣል? ስንቱስ ተገቢ መረጃ ያቀርባል? ለእንከን የለሽ ዝግጅት ምን ምን ነገሮች መሟላት ይኖርበታል? የሚሉትን ጥያቄዎች አንስተን ተገቢ መልስ ስናገኝ ነው። በሌላም በኩል የሚጎድለውን ስንሞላ፣ የራቀውን ስናቀርብ እና ከእኛ የሚጠበቀውን ኃላፊነት ስንወጣ ነው። መሥራት አንድ አስቸጋሪ ነገር ነው። በተሠራ ሥራ ላይ መተቸት ደግሞ በጣም ቀላል ተግባር ነው። ይህም በመሆኑ በቀረቡት ዝግጅቶች ላይ ስሕተቶች እንደሚኖሩ እናምናለን። የማይሳሳት ሬሳ ወይም የማይሠራ እንደሆነ እናምናለንና! ትችቶቹን እና አስተያየቶቹንም በአግባቡ እንቀበላለን፤ እናርማለንም። ከዚያ አልፎ ግን  የሚቀርቡትን ዝግጅቶች በጥቅሉ ማጠልሸት እና ውግዝ ከመ-አርዮስ ማለት ለዐማራው ድምፅ ከማሰብ ሳይሆን፣ የዐማራውን ድምፅ ለማፈን ከሚደረግ ሙከራ ተለይቶ አይታይም።

በመሠረቱ ዐማራው፣ ከውስጥ እና ከውጭ ከምድረ-ገፅ ሊያጠፉ የተነሱ ጠላቶቹን በተቀነባበረ ሁኔታ ለመታገል እና ኅልውናውን ለማስጠበቅ በማንነቱ ዙሪያ መደራጀቱ እና ድምፁን ለማሰማት መትጋቱ፣ ዐማራው፣ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን በተቃራኒ በጠላትነት ቆሟል ማለት እንዳልሆነ ወዳጅም ጠላትም ሊረዳው ይገባል። ዐማራው ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲል፣ ሌሎች ነገዶችን እና ጎሣዎችን በጠላትነት ፈርጆ ሳይሆን፣ ከእርሱ በምንም መልኩ ሊነጠሉ የማይችሉ አካሎቹ መሆናቸውን አምኖ ነው። ይህም በመሆኑ፣ ዐማራው ለማንነቱ በሚያደርገው ትግል የሁሉም ኢትዮጵያውያን ድጋፍ ያስፈልገዋል፣ የእርሱም ድጋፍ ለሌሎቹ አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታ ጭምር እንደሆነ ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ያምናል።

በአሁኑ ጊዜ ዐማራው በማንነቱ ዙሪያ ለመደራጀት የተገደደው ኅልውናውን ለማጥፋት የተነሱበት ታሪካዊ ጠላቶቹ በፈጠሩበት አደጋ ምክንያት ተገዶ እንጂ፣ ወዶ ወይም ፈቅዶ አለመሆኑ ግልጽ ሊሆን ይገባል። ነገር ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ አካል ከመሆን አልፎ፣ በቁጥሩ ብዛት፣ በአገሪቱ አንድነት እና ነፃነት አጠባበቅ ሂደት ከተጫወተው ሚና በላይ ለኢትዮጵያዊነት ዳብሮ መቀጠል ብሎ በጽኑ እምነት የተነሳው ኢትዮጵያዊው ዐማራ ከምድረ-ገጽ እንዲጠፋ ሲፈረድበት፣ የሌሎች ነገዶች እና ጎሣዎች ተወላጆች በዝምታ የመመልከታቸው ሁኔታ፣ በራሱ ማንነት ዙሪያ እንዲደራጅ እንዳስገደደው መረዳት አይከብድም። በዓለም ታሪክ እንደሚታወቀው ኦቶማን ቱርኮች አርመኖችን እና ግሪኮችን፣ ናዚ ጀርመኖች አይሁዶችን፣ ሁቱዎች ቱትሲዎችን በጅምላ ለመጨረስ ተነስተው የብዙ ሕዝብ ሕይዎት ቢቀጥፉም በመጨረሻ ግን በታሪክ የሚያስጠይቃቸውን እጅግ አሣፋሪ ተግባር ፈፀሙ እንጂ፣ አሸናፊዎች አልሆኑም። የማታ ማታ ድሉ የተገፉት ሆነ። በዚህ በያዝነው እና በምንገኝበት ዘመንም ዐማራውን ለማጥፋት የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች ብዙ ርቀት የተጓዘ ጥፋት ፈጽመውበታል። የማታ ማታ ግን ድሉም ሆነ አኩሪ ታሪኩ የዐማራው እንደሚሆን ጥርጥር የለንም። ስለዚህም ዐማራው ለኅልውናው በሚያደርገው ትግል ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከጎኑ ሊቆም ይገባል እንላለን፤ የዐማራው ኅልውና መጠበቅ ለመላ ኢትዮጵያውያን ህልውና መጠበቅ ዋስትና ነውና።

ይህ ሲባል ግን በተለይ የኢትዮጵያን እና የዐማራውን ጠላቶች ሤራ ለማክሸፍ፣ የዐማራ ተወላጆች እጃቸውን አጣጥፈው ይቀመጡ ማለት አይደለም። እንዲያውም ኅልውናችንን ለማስጠበቅ ከፍተኛው ኃላፊነት ያረፈው በእኛው በዐማሮች እጅ ነው። ሞረሽ ወገኔ  የዐማራ ድርጅት ለዐማራው ድምፅ እንዲሆን ያቋቋመው የሬድዮ ጣቢያ ዐማራው በማንነቱ ዙሪያ ተደራጅቶ ኅልውናውን በማስጠበቅ የኢትዮጵያ አንድነት ትንሣኤ አብሳሪ የሆነ ተግባር እንዲሠራ ከእያንዳንዱ የዐማራ ነገድ ተወላጅ እና ኢትዮጵያዊ ነኝ ከሚል ዜጋ ገንቢ ትችት እና አስተያየት የዝግጅት ክፍሉ ይጠብቃል። ዛሬ የዐማራ ድምፅ ራዲዮ በሚያቀርበው ዝግጅት ያልተደሰቱ ግለሰቦች ፣ ዐማራው በሐረርጌ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በሲዳሞ፣ በጋሞጎፋ፣ በከፋ፣ በኢሉባቦር፣ በወለጋ፣ በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎንደር፣ በጎጃም እና በትግራይ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ተለይቶ የዘር ማጥፋት እና የዘር ማጽዳት ሲፈጸምበት ምን ዓይነት ድምፅ አሰምተው እንደነበረ የሚያውቁት ራሳቸው ብቻ ናቸው። ከአራት ዓመታት በፊት ዐማራው ከጉራፈርዳ በገፍ እና በግፍ ሲባረር ምንም አላሉም። በጋምቤላ፣ በአሶሳ እና በመተከል ዐማራው በዘሩ ተለይቶ ሲጨፈጨፍ ድምፃቸው የአሁኑን ያህል አስተጋብቶ ቢሆን ኖሮ፣ የዐማራው ጥፋት በእጅጉ ይቀንስ እንደነበር እናምናለን። ከዓመት በፊት በመተከል ዐማራው እንደከብት ታርዶ ሥጋው ሲበላ፣ ያንን ሃቅ ያልተቀበሉ እንደነበሩ ስናስታውስ የዐማራው ጠላቶች የቱን ያህል ሥር የሰደዱ እንደሆኑ መገንዘብ ይቻላል። ዛሬ እኒህ ዐይናቸውን በጨው የታጠቡ የዐማራው ጠላቶች የዐማራው ድምፅ እንዳይሰማ ዝግጅቱን በተለያዩ መንገዶች ለማጥላላት ሲጥሩ እያስተዋልን ነው። ይህን ድርጊት የዐማራው ልጅ በዝምታ ሊያልፈው የሚገባ አይሆንም። ማለፍም የለበትም። ይህ ሬድዮ ጣቢያ ሥራውን እንዲቀጥል ከተፈለገ በውጪ ያለነው የዐማራ ልጆች ተቀዳሚው ኃላፊነት አለብን። ይህንን ጉዳይ አገር ቤት ያላችሁ ወገኖቻችን በውጭ ላሉት ወገኖቻችን አስገንዝቡልን። ይህ ሬድዮ ጣቢያ ገና በእንጭጩ በዐማራው ጠላቶች የተቀነባበረ ሤራ ቢዘጋ፣ በታሪክ ይቅር ሊባል የማይችል ስህተት የሠራነው በስደት ያለነው የዐማራው ልጆች እንደሆነ ሊታወቅ ይገባል።

[ዕርዳታ ለማድረግ እዚህ ላይ ይጫኑ]

[በየጊዜው የሚተላለፉትን የሬዲዮ ፕሮግራሞች ለመከታተል እዚህ ላይ ይጫኑ]

ዐማራን ከፈጽሞ ጥፋት እንታደጋለን!
ፈለገ-አሥራት የትውልዳችን ቃል-ኪዳን ነው!
ዐማራው ኅልውናውንና መብቱን በትግሉ ያስከብራል!

አርብ ኅዳር ፱ ቀን ፪ሺህ፱  ዓ.ም. ቅፅ ፭ ፣ ቁጥር ፬

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጃዋርና በቀለ መታሠራቸው ተሰማ June 30, 2020 09:17 am
  • አገራዊ መድረክ ውጪ ድብቅ ውይይትን አንቀበልም June 17, 2020 06:57 am
  • ዴክሳሜታሶን! የኮሮና መድሀኒት June 17, 2020 06:49 am
  • የሰኔ 14ቱ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ በኢትዮጵያ! June 17, 2020 06:38 am
  • የግብፅ የአባይን ውሃ ብቻዬን ልጠቀም ግትር አቋም ድርድር እንቅፋት ሆኗል June 10, 2020 07:15 am
  • የቴድሮስ “ሥልጣን” – የመጨረሻው መጀመሪያ!? April 12, 2020 02:48 am
  • በብዛት የትግራይ ተወላጆች የሚጠቀሙበት የኤርትራ ስደተኛ ካምፕ ሊዘጋ ነው March 18, 2020 08:37 pm
  • እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ March 18, 2020 08:09 pm
  • ኮሮና አዲስ ጉድ መዘዘ – ከቻይና በፊት በአሜሪካ ቁጥራቸው የማይታወቅ ሰዎችን ቀጥፏል March 16, 2020 11:41 pm
  • የኮንዶሚኒየም ቤቶች በደላሎችና በመመሪያ ሰጪዎች ኔትዎርክ እየተቸበቸበ ነው! ታከለ የት ናቸው? March 9, 2020 10:18 am
  • ኤርሚያስ ለገሠ ከባለአደራ ተባረረ March 9, 2020 08:09 am
  • ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥ March 7, 2020 11:24 pm
  • ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል? March 7, 2020 10:29 pm
  • WHY I WROTE “MONEY, BLOOD AND CONSCIENCE” March 4, 2020 11:15 pm
  • አድዋ፤ የጥቁር ሕዝብ ድል! March 2, 2020 11:24 am
  • ፊታውራሪ ገበየሁ ገቦ (አባ ጎራው) March 2, 2020 11:12 am
  • የኦነግ ሁለት መልክና ሦስት ግብሮች – ቃርሚያው ኃይል ቅጥር ነፍሰገዳይ ሆኗል February 25, 2020 11:26 pm
  • በቡራዩ “የጃል ማሮ” ፎቶ ጨረታ አፈናከተ፤ “ቡራዩ ሆኖ ከሃዲን ማሞካሸት አይቻልም” ነዋሪዎች February 17, 2020 09:13 pm
  • “ዲቃላ” የፍረጃ ፖለቲካ በኦሮሚያ የኃይል አሰላለፉን እየቀየረ ነው February 13, 2020 11:58 pm
  • “ከዚህ በኋላ ማናቸውንም በወንጀል ድርጊት ውስጥ የሚሳተፉ አካላትን” አንታገስም – ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ February 13, 2020 05:07 pm
  • “እኛ ማንም ተሳዳቢ እንዲመጣብን አንፈልግም” የጅማ ነዋሪ February 13, 2020 09:28 am
  • “ወላጆቻችሁ ሰላማዊ ሰልፍ በሕዝቡ ያስደርጉልን” – አጋቾች February 11, 2020 07:53 pm
  • “ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል፤ ምርመራም ተጀምሯል” February 11, 2020 06:59 pm
  • ጃዋር ወደ መጨረሻው “የትግል” ስልቱ – አማራን ማበጣበጥ! February 10, 2020 11:54 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule